Sea-Eye Ministry

Sea-Eye  Ministry � "የባሕር አይን" (Sea-eye) ከመንፈስ ቅዱስ የመጣ ድምጽ ሲሆን የ? � “እግዚአብሔር ልጁን ወደ ዓለም የላከው በዓለም ለመፍረድ ሳይሆን፣ ዓለምን በእርሱ ለማዳን ነው።”
— ዮሐንስ 3፥17 (አዲሱ መ.ት)

12/08/2023

“ለእግዚአብሔር ተገዛ ተስፋም አድርገው። #መንገድም በቀናችለትና #ጥመትን በሚያደርግ ሰው አትቅና።”መዝሙር 37፥7

ኢየሱስ ያድናል።
19/08/2022

ኢየሱስ ያድናል።

29/03/2022

Jesus

የኔ ውድ
29/03/2022

የኔ ውድ

እግዚአብሔር  ሲሸሽ..!      📖 ጠቢባኑ ከሄዱ በኋላ የጌታ መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ተገልጦ፣ “ተነሥ! የምትመለስበትን ጊዜ እስካስታውቅህ ድረስ ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብፅ በመሸሽ ...
08/01/2022

እግዚአብሔር ሲሸሽ..!

📖 ጠቢባኑ ከሄዱ በኋላ የጌታ መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ተገልጦ፣ “ተነሥ! የምትመለስበትን ጊዜ እስካስታውቅህ ድረስ ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብፅ በመሸሽ በዚያ ቈይ፤ ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይሻልና” አለው።
ስለዚህም ዮሴፍ ተነሣ፤ ሕፃኑንና እናቱን ይዞ በሌሊት ወደ ግብፅ ሄደ፤ ማቴዎስ 2:13-14 (አዲሱ መ.ት)
➢ እግዚአብሔር እርሱ ማንን ፈርቶ ሸሸ???? ኢየሱስ በአንድ ደቂቃ ብቅል ያለ ምትሃት አይደለም አስተዳደጉ እንደሰው በሰው መካከል በሞገስ በጥበብ በቁመት በሰውና በእግዚአብሔር ፊት እያዩት አድጓል። ከንጉስ ሄሮድስ ቤት ለተነሳበት ቁጣ እግዚአብሔር በህልም ለዮሴፍ ተገልጦ ህጻኑን ይዘህ ወደ ግብጽ #ሽሽ አለው። እንግዲህ እናስተውል ሽሽ ባዩ እግዚአብሔር ሲሆን ..! እርሱ ማንን ፈርቶ ሸሸ???????? “በዚያም ሄሮድስ እስከ ሞተበት ጊዜ ድረስ ኖረ። በዚህም፣ “ልጄን ከግብፅ ምድር ጠራሁት” በማለት እግዚአብሔር በነቢዩ አንደበት የተናገረው ቃል ተፈጸመ። ማቴዎስ 2፥15 (አዲሱ መ.ት)
🖊 ዮሴፍና ማርያም ልጁን ይዘው ሸሹ ወደ ግብጽ የሸሹት ልጁን ከግብጽ ሊጠራው የተነገረው ትንቢታዊ ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው። .....! እግዚአብሔር ነገርን በጊዜ ለክቶታል ጊዜው እስኪደርስ ባስቀመጠህ ስፍራ ተቀመጥ አለጊዜው ሊገሉህ ከሚነሱ ጋር አትታገል ከእነርሱ ሽሽ..! ከከክፉ ሀሳባቸውና ስራቸው ሽሽ ለመንፈሳዊ ሰው መሸሽ ፈሪነት አይደለም ነገን ለመድረስ በመሸነፍ ማሸነፍ እንጂ..!

✍️...... ከማን እንሽሽ ..?

1ኛ- #ከነፍሰ ገዳይ ሽሹ ...! 1ኛ ሳሙ 23:14
➢ #ዳዊት ከተቀባ በኃላ ሳኦል ሁልጊዜም ሊገለው ይፈልግ ነበር። ዳዊት ከሳኦል በመሸሽ የኖረ ሰው ነው። አንድ ቀን አጠገቡ ያሉ ሰዎች የዳዊት አምላክ ሳኦልን አሳልፎ እንደሰጠው ነግረውት በዋሻ ውስጥ ተኝቶ ባገኘው ቀን ግደለው ሲሉት አልገልም ብሎ ከነፍሰ ገዳይነት #ሸሸ...! ዳዊትን እግዚአብሔር ቀብቶታል ነገር ግን ይሸሻል ምክንያቱም እግዚአብሔር በቀን የወሰነው ነገር እንዳለ ስለተረዳ በጉልበት ገልብጦ የሚይዘው ስልጣን ስለሌለ እግዚአብሔር ትነግሳለህ እንዳለው በቀኑ ሁሉን አሸንፎለት ስልጣንን ሰጠው ስልጣን በግፊያ ሳይሆን ከሿሚው የሚገኝ ሹመት ነው። ዳዊትን ሰማይ የሾመው የቀባው ቀን ቢሆንም በመሸሽ የኖረው ግን ቀኑ እስኪደርስ ነበር።
➢ #ዮሴፍ እንደሚነግስ መላው ቤተሰቡ ሁሉ ገብቶታል ከዚህም የተነሳ ወንድሞቹ ጠሉት ሊገሉት በተማከሩበት ስብሰባቸው ላይ የተቃውሞ ድምጽ ባሰማው ይሁዳ በኩል ለመሸጥ ተስማሙ ከዚህም የተነሳ አሳልፈው በ20 ብር ሸጡት ........ ዘፍ 37:26-28..... በግብጽ በንጉስ ቤት ባሪያ ሆኖ ገባ በመልካም ሕይወት በዚያ ሲኖር ሳለ አንድ ቀን ንግስቲቱ አይኗን ጥላበት አብረን እንተኛ ስትለው አሻፈረኝ አለ በፍቅር ያልጣለችውን በትግል ለመጣል ስትታገለው ልብሱን ጥሎላት #ሸሸ። እውነትን በልቡ አንግሶ በሀሰት ክስ ከስር ቤት ቢጣልም ጻድቅን የሚዳኝ እስኪመጣለት ድረስ ታግሶ ኖረ...! እርሱን በሀሰት ያሳሰረችውም ሴት እንደማይፈታ እርግጠኛ በሆነችበት በዚያን ዘመን በእግዚአብሔር ታስቦ በአደባባይ በቀኑ ወደ ክብር መጣ ህልሙም እውን ሆነ! ከጨለማ ወደ ብርሃን ወጣ።
➢ #ሙሴ በግብጽ ሳለ የገዛ ወንድሞቹን ለማግባባት በተማረው ጥበብ ወድማማቾቹን ለመዳኘት ወንበር ሲሻ አንተን በእኛ ላይ ሹምና ፈራጅ ማን አደረገህ ባሉት ቀን ተቀባይነት የሚያገኝ የመሰለው የገዛ መንገዱ ስላላዋጣው በገደለው ሰው ምክንያት የገዛ ወንድሞቹ ስላጋለጡት የንጉሥን አዋጅ ፈርቶ #ሸሽቶ ከሞቀ ቤት በመውጣት በምድረ በዳ የበግ እረኛ ሆኖ ተቀመጠ
ሐዋ 7:20-35 .... ቀኑ ሲደርስ በጡንቻና በጥበብ ሞክሮ ያልተሳካለት ቤት ላይ እግዚአብሔር በትር አስይዞ ሂድ አለው እግዚአብሔር ሹምና ፈራጅ አድርጎ በእነርሱ መካከል ዳግመኛ ላከው።

🖊 #መሸሽ መሸነፍ ለመሰላቸው ሰዎች ተሸነፍላቸው! ኢየሱስ በመስቀል ላይ ተሽንፎ ስላሸነፈ.... ዳዊት ተቀብቶ ከሳኦል እንደሸሸ አንተም/ቺም ከክፉ ሰዎች #ሽሹ ....! ዮሴፍ ለሕልሙ በተሰደደበት ከዝሙት እንደሸሸ አንተም/ቺም ከዝሙት ከንዋይ ፍቅር #ሽሹ ....! ሙሴ ከድሎት ቤት ወጥቶ #ሸሽቶ በምድበረዳ እንደኖረ ለብድራቱ በሰጠው ትኩረት የድሎትን ቤት ጥሎ ወጥቶ በእረኝነት መንደር ከእግዚአብሔር ጋር ሆኖ እንደተመቸው እናተም የሚመቸውን እንቢ ብላቹ በማይመች ቦታ ብትሆኑም ቀን እስኪመጣ በታማኝነት ጠብቁ...!!!!!!
📖 “ስለዚህ እናንተ ሰዎች ሆይ፥ አይዞአችሁ፤ እንደ ተናገረኝ እንዲሁ እንዲሆን እግዚአብሔርን አምናለሁና።”
— ሐዋርያት 27፥25

ኢየሱስ ሊመጣ ነው።
05/01/2022

ኢየሱስ ሊመጣ ነው።

“ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ።”  — ኤፌሶን 5፥16“Redeeming the time, because the days are evil.” — Eph 5፥16 (AKJV)
01/01/2022

“ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ።”
— ኤፌሶን 5፥16
“Redeeming the time, because the days are evil.” — Eph 5፥16 (AKJV)

ፊልጵስዩስ 2¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯⁶ እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፥⁷ ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ...
01/12/2021

ፊልጵስዩስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁶ እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፥
⁷ ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፥
⁸ በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ።
⁹ በዚህ ምክንያት ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው፥ ከስምም ሁሉ በላይ ያለውን ስም ሰጠው፤
¹⁰ ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ፥
¹¹ መላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው።

“እንዲህም አሏቸው፤ “እናንት የገሊላ ሰዎች ሆይ፤ ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ እዚህ የቆማችሁት ለምንድን ነው? ይህ ከእናንተ ዘንድ ወደ ሰማይ ሲያርግ ያያችሁት ኢየሱስ፣ ልክ ወደ ሰማይ ሲወጣ...
17/11/2021

“እንዲህም አሏቸው፤ “እናንት የገሊላ ሰዎች ሆይ፤ ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ እዚህ የቆማችሁት ለምንድን ነው? ይህ ከእናንተ ዘንድ ወደ ሰማይ ሲያርግ ያያችሁት ኢየሱስ፣ ልክ ወደ ሰማይ ሲወጣ እንዳያችሁት በዚሁ ሁኔታ ይመለሳል።”” — ሐዋርያት 1፥11 (አዲሱ መ.ት)

08/11/2021

ወንጌል የምስራች ነው።

አቤቱ ማረን ይቅር በለንም!
08/11/2021

አቤቱ ማረን ይቅር በለንም!

በጨለማው ላይ ብርሃን ይብራ አለ።
17/10/2021

በጨለማው ላይ ብርሃን ይብራ አለ።

Address

Adama
SEER.COM

Telephone

+251912188920

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Sea-Eye Ministry posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Sea-Eye Ministry:

Share