Ortodoksi Tawaahidoo Page

Ortodoksi Tawaahidoo Page This page works on the way to strengthen ETHIOPIAN ORTHODOX CHURCH followers

Enkwn aderesachu/Baga itti geessani
14/07/2026

Enkwn aderesachu/Baga itti geessani

28/06/2026
02/03/2026

Zone Admnistrative
What is your opinion on genocides in Shirka ?

Qaamni aangoo daweefatee irra deddeebiin cunqursaa fi duguuggaa Kiristaanota Arsii bahaa irratti raawwatu qoratamee seer...
02/03/2026

Qaamni aangoo daweefatee irra deddeebiin cunqursaa fi duguuggaa Kiristaanota Arsii bahaa irratti raawwatu qoratamee seeraaf haa dhiyaatu. Tiruun tuni bullaan lafee taati yaa sabaa.

"ድርጊቱ በሃይማኖቶች መካከል ግጭት ለመፍጠር የታለመ ነው!" ቋሚ ሲኖዶስ​በምሥራቅ አርሲ የተፈጸመው የንጹሐን ግድያ ለዘመናት የዘለቀውን የሃይማኖቶች ተከባብሮ የመኖር እሴት ለመናድ የታለመ ...
02/03/2026

"ድርጊቱ በሃይማኖቶች መካከል ግጭት ለመፍጠር የታለመ ነው!" ቋሚ ሲኖዶስ

በምሥራቅ አርሲ የተፈጸመው የንጹሐን ግድያ ለዘመናት የዘለቀውን የሃይማኖቶች ተከባብሮ የመኖር እሴት ለመናድ የታለመ ነው ሲል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ ድርጊቱን በጽኑ አወገዘ።

በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በተለያዩ ወረዳዎች በኦርቶዶክሳውያን ላይ እየተፈጸመ ያለው ጥቃት በአዲስ መልክ ቀጥሎ የ21 ንጹሐን ወገኖች ሕይወት በግፍ ማለፉን ቋሚ ሲኖዶስ በመሪር ኃዘን ገልጿል።

ኦርቶዶክሳውያን በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል በነፃነት የመኖርና ሥርዓተ አምልኮ የመፈጸም ሕገ-መንግሥታዊ መብታቸው ሊከበር ይገባል ያለው ቋሚ ሲኖዶሱ፤ የፌዴራልና የክልሉ መንግሥት እርምጃዎች በአፋጣኝ እንዲወስዱ አሳስቧል።

በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በተደጋጋሚ እየተፈጸመ ያለው ሞትና መፈናቀልም ኦርቶዶክሳውያን ልጆቻችን በየትኛውም የሀገራችን ክፍል በነጻነት ሠርተው የመኖርና ሥርዓተ አምልኮ የመፈጸም ሕገ መንግሥታዊ መብታቸውን የሚጋፋ በመሆኑ የክልሉና የፌዴራል መንግሥት ጉዳዩን በልዩ ሁኔታ ተከታትለው አፋጣኝ መፍትሔ እንዲሰጡበት ቋሚ ሲኖዶስ በጥብቅ ያሳስባል፣
እንዲሁም ለተፈጸመው ግፍ አፋጣኝ ፍትሕ እንዲሰጥና ገዳዮች በሕግ እንዲጠየቁ እና የዜጎችን ደኅንነትና ንብረት የማስጠበቅ የመንግሥት ተግባር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ፤የሀገር ሰላምና የቤተ ክርስቲያን አንድነት ዐቢይ ኮሚቴ ከመንግሥት ጋር በመነጋገር ዘላቂ መፍትሔ እንዲያመጣ ቋሚ ሲኖዶስ አሳስቧል ።

​በመጨረሻም ቋሚ ሲኖዶስ ስለስሙ መከራን ለተቀበሉ" ንጹሐን ዕረፍተ ነፍስን፣ ለቤተሰቦቻቸውም መጽናናትን ተመኝቷል።
( )

  Gadda Teessoo Paatriyaarkii Mana Lubummaa Waliigalaa irraa------------------------------------------------------------...
02/03/2026

Gadda Teessoo Paatriyaarkii Mana Lubummaa Waliigalaa irraa
-----------------------------------------------------------------------

Biyya Lallaba Arsii Bahaa, Mana Lubummaa Aanaa Shiraakaa, Ganda Jaawwii keessatti, hordoftoonni amantaa Ortodoksii 21 ta'an hidhattootaan ajjeefamuu isaanii hordofuun gadda nutti dhaga’ame ibsina.

xalayaa Phaaphaasiin Biyya lallabichaa, Eebbifamoo Abuna Elsaa’i, gara wajjira keenyaatti nuuf barreessanirraa akka hubannetti, Gurraandhala 19 gara 20 bari’u Biyya Lallaba Arsii Bahaa, Mana Lubummaa Aanaa Shiraakaa, Ganda Jaawwii keessatti:

Lubni tokko,

Dubartoonni lama, fi

Dhiironni hordoftoota Ortodoksii 18,

Gocha gara jabinaan raawwatameen ajjeefamuu isaanii yommuu dhageenyu gaddi guddaan nutti dhaga’ameera.

Kanaafuu, biyya lallaba kana keessatti yeroo adda addaatti ijoollee keenya Ortodoksii irratti ajjeechi raawwatamaa jiru kun, ijoolleen keenya Ortodoksii kutaa biyyattii kamiyyuu keessatti bilisaan jiraachuu fi sirna amantaa isaanii raawwachuuf mirga qaban kan sarbudha. Kanaaf, mootummaan naannichaa fi mootummaan Federaalaa dhimma kana xiyyeeffannoo addaan hordofuun furmaata dhumaa akka itti fidan cimsinee hubachiifna.

Wajjirri Teessoo Paatriyaarkii Mana Lubummaa waliigalaas rakkoon naannichaa bu’uuraan amma furmaata argatutti carraaqqii taasisu kan itti fufu ta’uu carraa kanaan ibsuu barbaadna.

Dhumarrattis, ijoollee keenya gocha suukanneessaa kanaan lubbuu isaanii darbeef Waaqayyo mootummaa bara baraa akka isaaniif laatu, maatii fi firoottan isaaniif immoo jajjabina akka kennuuf Qulqulleettiin Manni Kiristaanaa keenyaa kadhannaa hojii ishee guyyaa hundaa ta'uu isaa ibsina.

Abba Saawiroos
Hoji-Gaggeessaa Teessoo Paatriyaarkii Mana Lubummaa Waliigalaa Mana Kiristaana Ortodoksii Tawaahidoo Itoophiyaa, akkasumas Qondaala Phaaphaasii Biyyaalee lallaba Shawaa Kibba Lixaa fi Magaalaa Shaggar.

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን  ቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ የኃዘን መግለጫ‹‹እለ ሐሙ በእንተ ስሙ፤ ምድር ሠናይት ርስቶሙስለስሙ መከራን የተቀበሉት፤ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናት›...
02/03/2026

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ የኃዘን መግለጫ

‹‹እለ ሐሙ በእንተ ስሙ፤ ምድር ሠናይት ርስቶሙ
ስለስሙ መከራን የተቀበሉት፤ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናት››
(ማቴ 5÷51 ፤ ቅዱስ ያሬድ)

ከዚህ በፊት በአርሲ ሀገረ ስብከት በተለያዩ ወረዳዎች የበርካታ ኦርቶዶክሳውያን ወገኖቻችን ሕይወት በመጥፋቱና ከሞት የተረፉትም ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ወደ አጎራባች ከተሞች ተሰደው ለረሀብና ለእርዛት ተጋልጠው እየኖሩ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ቀደም ሲል በተለያዩ ጊዜያት፣ በደረሰው ሞትና ስደት ምእመናን እያዘነ ባሉበት፣ እኛም ከኃዘናችን ባልተጽናናንበት ሁኔታ ጥቃቱ በአዲስ መልኩ ቀጥሎ የ21 ንጹሐን ወገኖቻችን ሕይወት በግፍ ማለፉን፣ በሕይወት የተረፉትም በታጣቂዎቹ መታገታቸውንና የደረሱበት አለመታወቁን፣ h10 የሚበልጡ አባውራዎች ቤትና ንብረት እንደተቃጠለ በመግለጽ ከሀገረ ስብከቱ የቀረበውን ሪፖርት የተመለከትነው ጥልቅ በሆነ ኃዘን ነው፡፡

አገር ሰላም ብለው በሚኖሩት ከምንም ጉዳይ ጋር ንክኪ በሌላቸው ኦርቶዶክሳውያን ልጆቻችን ላይ ይህን አስነዋሪ ድርጊት የፈጸሙት አካላትም ግድያውን በሃይማኖት ስም ይፈጽሙት እንጂ የሃይማኖት ስዎች ግን አይደሉም፡፡ ዓላማቸውም በሀገራችን ለረዥም ዘመናት ተከባብረው አብረው በኖሩት የሃይማኖት ተቋማት መካከል ግጭትን መፍጠር ነውና የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮችና ሕዝበ ክርስቲያኑ በጋራ ልናወግዛቸው ይገባል፡፡

በመሆኑም በወገኖቻችን ላይ የተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ በሕዝበ ክርስቲያኑ ዕለታዊ ኑሮ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚፈጥር፣ በቅዱሳት መጻሕፍትም ሆነ በሰው ልጅ ሰብአዊ አኗኗር ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው አጸያፊ ድርጊት በመሆኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ በጽኑ አውግዞታል፡፡

በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በተደጋጋሚ እየተፈጸመ ያለው ሞትና መፈናቀልም ኦርቶዶክሳውያን ልጆቻችን በየትኛውም የሀገራችን ክፍል በነጻነት ሠርተው የመኖርና ሥርዓተ አምልኮ የመፈጸም ሕገ መንግሥታዊ መብታቸውን የሚጋፋ በመሆኑ የክልሉና የፌዴራል መንግሥት ጉዳዩን በልዩ ሁኔታ ተከታትለው አፋጣኝ መፍትሔ እንዲሰጡበት ቋሚ ሲኖዶስ በጥብቅ ያሳስባል፣

ፍርድን በመሻት የሚጮኸው ስለስሙ መከራን የተቀበሉት የንጹሐን ደም ተገቢውን ፍትሕ ይፈልጋልና ይህን አስነዋሪ ድርጊት የፈጸሙት አካላት በሕግ እንዲጠየቁ፣ ወደፊትም ክቡር የሆነው የሰው ልጅ ሕይወት እንዳይጠፋ፣ የዜጐች ሀብትና ንብረት እንዳይወድም መንግሥት የዜጎችን ደኅንነት የማስጠበቅ ተግባሩን እንዲያከናውን ቋሚ ሲኖዶስ ጥሪውን በአጽንኦት ያስተላልፋል፤

በደረሰው አደጋ ዙሪያ ተነጋግሮ ተገቢውን ውሳኔ ለማስተላለፍ የተሰበሰበው ቋሚ ሲኖዶስም የአካባቢው ችግር አስተማማኝ በሆነ መንገድ ተፈትቶ ዘላቂ ስላም እስኪገኝ ድረስ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ የተሰየመው የሀገር ሰላምና የቤተ ክርስቲያን አንድነት ዐቢይ ኮሚቴ ከፌደራልና ከክልሉ መንግሥት ጋር በመነጋገር ሥራውን አጠናክሮ እንዲቀጥልና የሚመለከታቸውም አካላት በየድርሻቸው አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ቋሚ ሲኖዶስ በክብር ያሳስባል፡፡

የክልሉ መንግሥትና የአካባቢው መስተዳድርም ችግሩን ለመፍታት እያደረገ ያለው ጥረት አጠናክሮ እንዲቀጥልና ወደፊትም ችግሩ እንዳይደገም ከመሠረቱ መፍታት የሚያስችል እርምጃ እንዲወስድ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ትጠይቃለች፡፡

በመጨረሻም ስለስሙ በሥጋቸው መከራን በመቀበል ሕይወታቸውን በአጡት ኦርቶዶክሳውያን ልጆቻችን የተሰማንን መሪር ኃዘን እየገለጽን ልዑል እግዚአብሔር ዕረፍተ ነፍስን እንዲሰጥልን፣ ቤተሰቦቻቸውንም እንዲያጽናናልን እንጸል

 #የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በአርሲ የደረሰውን ጥቃት አወገዘ​የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ሺርካ ወረዳ በንፁሐን የኦርቶዶክ...
02/03/2026

#የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በአርሲ የደረሰውን ጥቃት አወገዘ

​የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ሺርካ ወረዳ በንፁሐን የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮች ላይ የደረሰውን አሰቃቂ ጥቃት በፅኑ ማውገዙን ገለጸ።

​ምክር ቤቱ ባወጣው መግለጫ፣ በደረሰው አሰቃቂ አደጋ ማዘኑን ገልጾ፣ ድርጊቱ ማንኛውንም ሃይማኖት የማይወክልና እኩይ ዓላማ ያለው መሆኑን አመልክቷል። ድርጊቱ በሃይማኖቶች መካከል ለዘመናት የቆየውን የመከባበር እሴት በመናድ፣ በአማኞች መካከል ጥርጣሬና ግጭት ለመፍጠር የታለመ "እኩይ ሴራ" ነው ብሎ እንደሚያምን ገልጿል።

መንግስት ድርጊቱን የፈጸሙ አጥፊዎችን በአፋጣኝ ለይቶ ተገቢውን ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድ ጥሪ አቅርቧል። በሃይማኖቶች መካከል ያለውን ሰላምና መከባበር ለማፍረስ የሚሰሩ አካላትን ህዝቡ በንቃት ሊከላከል እንደሚገባ ተመልክቷል።

​ምክር ቤቱ ለሟች ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች "አላህ መፅናናቱን ይስጣቸው" በማለት ፀሎቱንና መልካም ምኞቱን አስተላልፏል።

Address

Adama

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ortodoksi Tawaahidoo Page posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Ortodoksi Tawaahidoo Page:

Shortcuts

Share