ሐመረ ተዋሕዶ ሚዲያ /Hamere Tewahedo Media

ሐመረ ተዋሕዶ ሚዲያ /Hamere Tewahedo Media ይህ በኢ.ኦ.ተ.ቤ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ይፋዊ የፌስቡክ ገጽ ነው።
This is the official page of the Eastern Showa Diocese of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church.
(1)

23/08/2026
Eebbifamoo Abuna Gorgooriyoos Baazaarii Hafuurawaa Galii Walitti Qabiinsa Ijaarsa Mana Kiristaanaa Kawaala Baatuu Hamara...
23/08/2026

Eebbifamoo Abuna Gorgooriyoos Baazaarii Hafuurawaa Galii Walitti Qabiinsa Ijaarsa Mana Kiristaanaa Kawaala Baatuu Hamara Nooh Qulqulleetti Kidaana Mihireet Haaromsisuuf Qophaa'e Eebbisuun bananiiru.

Hagayya 17 bara 2018 A.L.I. [ ]

— Biyya Lallabaa Shawaa Bahaatti Mana Lubummaa Aanaa Adaamii Tulluu Jiiddoo Kombolchaa jalatti kan argamtu kawaala seenaa qabeessaa fi durii Baatuu Hamara Nooh Qulqulluu Kidaana Mihireet ijaarsa mana kiristaanaa ishee haaromsisuuf baazaarii hafuurawaa galii walitti qabiinsa qophaa'e;

Eebbifamoo Abbaa Keenya Abuna Gorgooriyoos፦ Angafa Phaaphaasii Biyya Lallabaa Shawaa Ba'aa, Hooganaa Kawaala Baatuu Ziwaay Hamara Birhaan Qulqulluu Gabri'eelii fi Koolleejii Bulchiinsa Hafuurawaa, Miseensa Dhaabbataa Qulqulluu Sinoodosii akkasumas Walitti-qabaa Boordii Hojii Raawwachiiftu Dhaabbilee Amantaa Itiyoophiyaa eebbisuudhaan ifatti bananiiru.

Ijaarsi mana kiristaanaa kawaalichaa sadarkaa ijaarsa ol-aanaa irra kan argamu yoo ta'u; hojiin ijaarsaa yeroo kaa'ameef fi qulqullina akka xumuramuuf baazaariin hafuurawaa galii walitti qabiinsa hagayya 18 hanga 19 bara 2018 A.L.I.tti turu qophaa'eera.

Eebbifamoo Abbaa keenya Abuna Gorgooriyoos kadhannaadhaan fi eebbaan bifa seeraatiin kan banan yoo ta'u; amantoonni ijaarsa mana kiristaanaa kawaalichaa xumursiisuuf hojii gaarii taasifamu kana irratti dammaqinaan fi jaalala amantaatiin akka hirmaatan waamicha dhiheessaniiru.

Sirna kana irratti Magaabaa Hadiis Qoomos Abba Hayila Gabri'eel Tasfaa (Hoogganaa Kutaa Lallabaa Wangeelaa Biyya Lallabaa Keenyaa), Malaaka Birhaanat Qoomos Abba Gabra Hiywot (Hoogganaa Kutaa Bulchiinsa Luboota Biyya Lallabaa Keenyaa), Magaabii Haymaanoot Luba Taaffasa Waggaayyehuu (Diinii Koolleejii Bulchiinsa Hafuurawaa Kawaala Baatuu Ziwaay Hamara Birhaan Qulqulluu Gabri'eel), bulchitoonni, luboonni, diyaaqonoonni fi amantoonni hedduun kan argaman yoo ta'u; baazaarichi hanga boruu hagayya 19 bara 2018 A.L.I.tti banaa ta'ee akka turu beekameera.

Biyya Lallabaa Shawaa Bahaa

Gabaasaafi suura D/N Ayyalaa










ለባቱ ሐመረ ኖኅ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ገዳም ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን እድሳት ማስፈጸሚያ የተዘጋጀውን የገቢ ማሰባሰቢያ መንፈሳዊ ባዛር ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ባርከው በይፋ ከፈቱ።ነሐሴ ፲፯ ቀ...
23/08/2026

ለባቱ ሐመረ ኖኅ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ገዳም ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን እድሳት ማስፈጸሚያ የተዘጋጀውን የገቢ ማሰባሰቢያ መንፈሳዊ ባዛር ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ባርከው በይፋ ከፈቱ።

ነሐሴ ፲፯ ቀን ፪ሺ፲፰ ዓ.ም

#ባቱ — በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በአዳሚ ቱሉ ጂዶ ኮምቦልቻ ወረዳ ቤተ ክህነት ሥር የምትገኘው የጥንታዊቷና ታሪካዊቷ የባቱ ሐመረ ኖኅ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ገዳም ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን እድሳት ማስፈጸሚያ የተዘጋጀውን መንፈሳዊ የገቢ ማሰባሰቢያ ባዛር ፤

ብፁዕ አባታችን አቡነ ጎርጎርዮስ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳምና ሥራ አመራር መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ኃላፊ የቅዱስ ሲኖዶስ ቋሚ አባል እንዲሁም የኢትዮጵያ ሃይማኖቶች ተቋማት የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ሰብሳቢ ፤ ባርከው በይፋ ከፍተዋል።

የገዳሙ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን በከፍተኛ የግንባታ ሂደት ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ የግንባታ ሥራው በተቀመጠለት ጊዜና ጥራት እንዲጠናቀቅ ለማድረግ ከነሐሴ ፲፰ እስከ ፲፱ ቀን ፪ሺ፲፰ ዓ.ም የሚቆይ መንፈሳዊ የገቢ ማሰባሰቢያ ባዛር ተዘጋጅቷል።

ብፁዕ አባታችን አቡነ ጎርጎርዮስ በጸሎትና በቡራኬ በይፋ የከፈቱት ሲሆን፤ ምዕመናን የገዳሙን ሕንጻ ለማጠናቀቅ በሚደረገው በዚህ በጎ ሥራ ላይ በንቃትና በሃይማኖታዊ ፍቅር እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።

በሥነ ሥርዐቱ ላይሜ መጋቤ ሐዲስ ቆሞስ አባ ኃይለ ገብርኤል ተስፋ ሀገረ ስብከታችን የስብከተ ወንጌል ክፍል ኃላፊ ፣ መልአከ ብርሃናት ቆሞስ አባ ገብረ ሕይወት የሀገረ ስብከታችን የካህናት አስተዳደር ክፍል ኃላፊ፣ መጋቤ ሃይማኖት ቀሲስ ታፈሰ ወጋየሁ የባቱ ዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የሥራ አመራር ኮሌጁ ዋና ዲ/ን፣

አስተዳዳሪዎች፣ ካህናት፣ ዲያቆናትና በርካታ ምዕመናን የተገኙ ሲሆን፤ ባዛሩ እስከ ነገ ነሐሴ ፲፱ ቀን ፪ሺ፲፰ ዓ.ም ድረስ ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ ታውቋል።

የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት
ሐመረ ተዋሕዶ ሚዲያ

#ባቱ #ኦርቶዶክስ #ተዋሕዶ

Ayyaanni Waggaa Ol-ba'iinsa (Tinsa'ee) Giiftii Keenya Qulqulleetti Kidaana Mihiret Kawaala Seenaa qeessaa fi Durii Baatu...
23/08/2026

Ayyaanni Waggaa Ol-ba'iinsa (Tinsa'ee) Giiftii Keenya Qulqulleetti Kidaana Mihiret Kawaala Seenaa qeessaa fi Durii Baatuu Ziwaay Hamara Noohitti Eebbifamoo Abuna Gorgooriyoos Bakka Argamanitti Haala Ho'aadhaan Kabajame

[ ]

— Ayyaanni ol-ba'iinsa (Tinsa'ee) waggaa giiftii keenya qulqulleetti Durboo Maariyaam Kawaala Baatuu Ziwaay Hamara Nooh Qulqulleetti Kidaana Mihiretitti;

Eebbifamoo Abbaa Keenya Abuna Gorgooriyoos፦ Angafa Phaaphaasii Biyya Lallabaa Shawaa Bahaa, Hooganaa Kawaala Baatuu Ziwaay Hamara Birhaan Qulqulluu Gabri'eelii fi Koolleejii Bulchiinsa Hafuurawaa, Miseensa Dhaabbataa Qulqulluu Sinoodosii akkasumas Walitti-qabaa Boordii Hojii Raawwachiiftu Dhaabbilee Amantaa Itiyoophiyaa bakka argamanitti gammachuu hafuurawaa fi haala ho'aa ta'een kabajamee ooleera.

Sirna kabaja ayyaana kana irratti Eebbifamummaa isaanii dabalatee; Magaabii Haymaanoot Qoomos Abba Abrahaam Garamawuu (Itti-aanaa Barreessaa Ol'aanaa Qulqulluu Sinoodosii), Magaabi Hadiis Qoomos Abba Hayila Gabri'eel Tasfaa (Hoogganaa Kutaa Lallabaa Wangeelaa Biyya Lallabaa Keenyaa), Malaaka Birhaanat Qoomos Abba Gabra Hiywot (Hoogganaa Kutaa Bulchiinsa Luboota Biyya Lallabaa Keenyaa), Liqa Liqawwint Qoomos Abba Atnaatewoos Wolda Gorgooriyoos (Abamineetii Kawaala Hamara Birhaan Qulqulluu Gabri'eel), Magaabii Haymaanoot Luba Taaffasa Waggaayyehuu (Diinii Koolleejii Bulchiinsa Hafuurawaa), bulchitoonni kawaalotaa fi manneen amntaa, abbootii monoksoota kawaalotaa, liqaawwintoota Mana Kiristaanaa, luboonni fi diyaaqonootni, faarfattoonni mana barumsa dilbataa akkasumas amantoonni Ortodoksii hedduun dhiyoo fi fagoodhaa walitti qabaman argamaniiru.

Jecha isheetiin kan amanamte, hojii isheetiinis kan jaallatamte Qulqulleetti Durboo Maariyaam ergamoonni osoo ishee galateeffatanii fi gammachuu hafuurawaadhaan osoo ishee geessanii gara samiitti ol-ba'uun ishee kan itti yaadatamu guyyaan kun; zeemaa Yaareediin, faarfannaan fi sirna hafuurawaatiin kabajamee ooleera.

Araarsummaan giiftii keenyaa, arjummaan Waaqa keenya Iyyesuus Kiristoos kan duu'a ka'uumsa keenya hangafa ta'ee nu hunda wajjin haa ta'u; Ameen!

Biyya Lallabaa Shawaa Bahaa

Gabaasaafi Suura፦ D/n Ayyalaa




በዓለ ዕርገቷ ለማርያም (ትንሣኤዋ) ዓመታዊ የንግሥ በዓል በአዳማ ደብረ ገነት ቅድስት ኪዳነ ምህረት ካቴድራል በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ውሏል። ነሐሴ ፲፮ ቀን ፪ሺ፲፰ ዓ.ም   የእመቤታችን የ...
22/08/2026

በዓለ ዕርገቷ ለማርያም (ትንሣኤዋ) ዓመታዊ የንግሥ በዓል በአዳማ ደብረ ገነት ቅድስት ኪዳነ ምህረት ካቴድራል በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ውሏል።

ነሐሴ ፲፮ ቀን ፪ሺ፲፰ ዓ.ም

የእመቤታችን የቅድስት ኪዳነ ምህረት በዓለ ዕርገቷ (ትንሣኤዋ) ዓመታዊ የንግሥ በአዳማ ደብረ ገነት ቅድስት ኪዳነ ምህረት ካቴድራል በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ውሏል።

በክብረ በዓሉም ላይም ላይም መልአከ ሣህል ቀሲስ ነጋሽ ሀብተ ወልድ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣ መጋቤ ጥበባት ቀሲስ ጌቱ ሞቲ የሀገረ ስብከቱ ም/ሥራ አስኪያጅ ፣የሀገረ ስብከቱ የየመምሪያው ክፍል ኃላፊዎች ፣ የገዳማት አድባራት አስተዳደሪዎች ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ካህናት ወዲያቆናት መምህራነ ወንጌል ፣ የሰንበት ት/ቤት ዘማርያን ማኅበራት: በርካታ ኦርቶዶክሳውያን ተገኝተዋል።

ፎቶ:- የአዳማ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም

22/08/2026

በዓለ ዕርገታ ለማርያም በባቱ ሐመረ ኖኅ ቅድስተ ኪዳነ ምህረት ገዳም

የእመቤታችን የቅድስት ኪዳነ ምህረት ዓመታዊ የዕርገት በዓል በጥንታዊቷና ታሪካዊቷ የባቱ ዝዋይ ሐመረ ኖኅ ገዳም ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከበረ::ነሐሴ ፲፮ ቀን ፪...
22/08/2026

የእመቤታችን የቅድስት ኪዳነ ምህረት ዓመታዊ የዕርገት በዓል በጥንታዊቷና ታሪካዊቷ የባቱ ዝዋይ ሐመረ ኖኅ ገዳም ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከበረ::

ነሐሴ ፲፮ ቀን ፪ሺ፲፰ ዓ.ም

#ባቱ — የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የዕርገቷ (የትንሣኤዋ) ዓመታዊ የንግሥ በዓል በባቱ ዝዋይ ሐመረ ኖኅ ቅድስት ኪዳነ ምህረት ገዳም በብፁዕ አባታችን አቡነ ጎርጎርዮስ (የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳምና ሥራ አመራር መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ኃላፊ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ቋሚ አባልና የኢትዮጵያ ሃይማኖቶች ተቋማት የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ሰብሳቢ በታላቅ መንፈሳዊ ፍሥሐና ድምቀት ተከብሯል።

በዕለቱ በበዓሉ አከባበር ላይ ብፁዕ አባታችን አቡነ ጎርጎርዮስ ለምዕመናን አባታዊ ትምህርትና ቃለ ምዕዳን አስተላልፈዋል።

ብፁዕነታቸው በቃለ ምዕዳናቸው ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የዕርገትና የትንሣኤ ምሥጢር ሲያስረዱ፦ «አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ፣ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ ሰው ሆኖ አድኖናል» በማለት የድኅነት ምሥጢርን አብራርተዋል።

ብፁዕ አባታችን፦ «ኢትዮጵያ ቅድስተ ሀገር፣ የቅዳሴ ሀገር፣ የባሕታውያንና የመናንያን ሀገር ናት» በማለት የሀገራችንን መንፈሳዊ ክብር ያወሱ ሲሆን፤ ምዕመናን ስለ ቅድስት ሀገራችን፣ ስለ ሰላምና ስለ ፍቅር በጸሎት ሊተጉ እንደሚገባ አባታዊ አደራ ብለዋል።

በበዓሉ መርሓ ግብር ላይ በሦስት ክፍሎች የተከፈለ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት የቀረበ ሲሆን፤ በመጀመሪያው ክፍለ ጊዜ በሸገር ሀገረ ስብከት የኮዬ ፈጬ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን መምህር የሆኑት መጋቤ ሐዲስ ብርሃኑ ተስፋዬ በአፋን ኦሮምኛ ትምህርተ ወንጌል ሰጥተዋል። በመቀጠል በሁለተኛው ክፍለ ጊዜ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሲኤምሲ ደብረ ጽባሕ ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል መምህር መጋቤ ሐዲስ መምህር አድህነው በአማርኛ ቋንቋ ሰፊ አስተምህሮ አቅርበዋል።

በሦስተኛው ክፍለ ጊዜ «ከድካማቸው ያርፉ ዘንድ ሥራቸውም ይከተላቸዋል» (ከመ ያዕርፉ እምነ ጻማሆሙ ወይተልዎሙ ግብሮሙ) በሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ላይ ተመስርተው በመጋቤ ሃይማኖት ቆሞስ አባ አብርሃም ገረመው፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ምክትል ዋና ጸሐፊ የቀረበው ትምህርት ሲሆን፤ ከእመቤታችን መወለዱን፣ መስቀሉን፣ በሦስተኛው ቀን ከሙታን መነሣቱንና ዳግመኛም ለፍርድ እንደሚመጣ የሚያምን ሁሉ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሥራ ሊኖረው እንደሚገባ በትምህርታቸው አስገንዝበዋል።

አያይዘውም የቅዱሳን ሞት የሕይወት እንጂ የሐዘን ሳይሆን የዕረፍት መሆኑን አስረድተዋል። «ሥራቸው ይከተላቸዋል» የተባለው በጎ ተግባራችን፣ የታመሙትን መጠየቅ፣ ያዘኑትን ማረጋጋትና የተከዙትን ማጽናት እንደሆነ አብራርተው አስተምረዋል::

በበዓሉ አከባበር ሥነ ሥርዓት ላይ ብፁዕነታቸውን ጨምሮ የቅዱስ ሲኖዶስ ምክትል ዋና ጸሐፊ መጋቤ ሃይማኖት ቆሞስ አባ አብርሃም ገረመው፣ የሀገረ ስብከታችን የስብከተ ወንጌል ክፍል ኃላፊ መጋቤ ሐዲስ ቆሞስ አባ ኃይለ ገብርኤል ተስፋ፣ የሀገረ ስብከታችን የካህናት አስተዳደር ክፍል ኃላፊ መልአከ ብርሃናት ቆሞስ አባ ገብረ ሕይወት፣ የሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም አበምኔት ሊቀ ሊቃውንት ቆሞስ አባ አትናቴዎስ ወልደ ጎርጎርዮስ፣ የሥራ አመራር ኮሌጁ ዋና ዲያቆን መጋቤ ሃይማኖት ቀሲስ ታፈሰ ወጋየሁ፣ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ገዳማውያን አበው መነኮሳት፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ ካህናትና ዲያቆናት፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ዘማሪያን እንዲሁም ከሩቅና ከቅርብ የተሰበሰቡ በርካታ ኦርቶዶክሳውያን ምዕመናን ተገኝተዋል።

የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት
ሐመረ ተዋሕዶ ሚዲያ
ዘገባና ፎቶ፦ ዲ/ን አየለ

#ኦርቶዶክስ #ተዋሕዶ

የእመቤታችን የቅድስት ኪዳነ ምህረት በዓለ ዕርገቷ (ትንሣኤዋ) ዓመታዊ የንግሥ በዓል በጥንታዊቷና ታሪካዊቷ የባቱ ዝዋይ ሐመረ ኖኅ ገዳም ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ በተገኙበት በታላቅ ድምቀት እ...
22/08/2026

የእመቤታችን የቅድስት ኪዳነ ምህረት በዓለ ዕርገቷ (ትንሣኤዋ) ዓመታዊ የንግሥ በዓል በጥንታዊቷና ታሪካዊቷ የባቱ ዝዋይ ሐመረ ኖኅ ገዳም ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ በተገኙበት በታላቅ ድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

ነሐሴ ፲፮ ቀን ፪ሺ፲፰ ዓ.ም

#ባቱ — የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የዕርገቷ (የትንሣኤዋ) ዓመታዊ የንግሥ በዓል በባቱ ዝዋይ ሐመረ ኖኅ ቅድስት ኪዳነ ምህረት ገዳም፤
ብፁዕ አባታችን አቡነ ጎርጎርዮስ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳምና ሥራ አመራር መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ኃላፊ የቅዱስ ሲኖዶስ ቋሚ አባል እንዲሁም የኢትዮጵያ ሃይማኖቶች ተቋማት የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ሰብሳቢ በተገኙበት በታላቅ መንፈሳዊ ፍሥሐና ድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

በበዓሉ አከባበር ሥነ ሥርዓቱ ላይ ብፁዕነታቸውን ጨምሮ፤ መጋቤ ሃይማኖት ቆሞስ አባ አብርሃም ገረመው
የቅዱስ ሲኖዶስ ምክትል ዋና ጸሐፊ ፣መጋቤ ሐዲስ ቆሞስ አባ ኃይለ ገብርኤል ተስፋ ሀገረ ስብከታችን የስብከተ ወንጌል ክፍል ኃላፊ ፣ መልአከ ብርሃናት ቆሞስ አባ ገብረ ሕይወት የሀገረ ስብከታችን የካህናት አስተዳደር ክፍል ኃላፊ፣ ሊቀ ሊቃውንት ቆሞስ አባ አትናቴዎስ ወልደ ጎርጎርዮስ የሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም አበምኔት፣ መጋቤ ሃይማኖት ቀሲስ ታፈሰ ወጋየሁ የሥራ አመራር ኮሌጁ ዋና ዲ/ን፣ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ገዳማውያን አበው መነኮሳት፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ ካህናትና ዲያቆናት፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ዘማሪያን እንዲሁም ከሩቅና ከቅርብ የተሰበሰቡ በርካታ ኦርቶዶክሳውያን ምዕመናን ተገኝተዋል።

በቃሏ የታመነች በሥራዋም የተወደደች ቅድስት ድንግል ማርያምን መላእክት እያመሰገኗትና በመንፈሳዊ ደስታ እያጀቧት ወደ ሰማይ ማረጓ የሚታሰብበት ይህ ዕለት፤ በያሬዳዊ ዜማ፣ በቅኔና በመንፈሳዊ ሥርዓት እየተከበረ ይገኛል።

የእመቤታችን አማላጅነት፣ የትንሣኤያችን በኵር የሆነው የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቸርነት ከሁላችን ጋር ይሁን፤ አሜን!

(የንግሥ በዓሉን ሙሉ ዘገባ ይዘን እንመለሳለን!)
የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ዘገባና ፎቶ፦ ዲ/ን አየለ

#ኦርቶዶክስ #ተዋሕዶ

እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ዕርገቷ(ትንሣኤዋ) በሰላም በጤና አደረሳችሁ ! አደረሰን ! ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የዐጽብ ለኲሉ» በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ...
22/08/2026

እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ዕርገቷ(ትንሣኤዋ) በሰላም በጤና አደረሳችሁ ! አደረሰን !

ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የዐጽብ ለኲሉ»

በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ፣ በነገረ ማርያም፣ በስንክሳርና በተአምረ ማርያም እንደተገለጸው፤ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጥር ፳፩ ቀን አርፋለች። ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ «ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የሐጽብ ለኲሉ፤ ሞት ለማናቸውም ሰው ሁሉ የተገባ ነው የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል» በማለት እንደተናገረው የእመቤታችን ዕረፍት እጅግ ድንቅና ልዩ ነው።

ቅዱሳን ሐዋርያት የእመቤታችንን የከበረ ሥጋን ወደ ጌቴሴማኒ ሊቀብሩ ይዘው ሲሄዱ፣ አይሁድ በቅንአት ተነሣሥተው ሥጋዋን በእሳት ለማቃጠል ተነሱ። ታውፋንያ የሚባል አይሁዳዊ የአልጋውን ሸንኮር (ቃሬዛ) በድፍረት በያዘ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ በእሳት ሰይፍ ሁለት እጆቹን ቆረጣቸው፤ በኋላ ግን አምኖ ስለተማጸነ እጆቹ ተመልሰውለታል። ከዚህ በኋላ መልአከ እግዚአብሔር የእመቤታችንን የከበረ ሥጋ ከሐዋርያው ዮሐንስ ጋር ነጥቆ ወስዶ በገነት ከዕፀ ሕይወት ሥር አስቀመጠው።
ሐዋርያት የእመቤታችንን ሥጋ አግኝተው ለመቅበር ከነሐሴ ፩ ቀን ጀምረው በጾምና በጸሎት ሱባኤ ያዙ። በ፲፬ኛው ቀን (በሁለተኛው ሱባኤ መጨረሻ) ጌታችን የእመቤታችንን የከበረ ሥጋ ስለሰጣቸው በጌቴሴማኒ ቀበሯት። በዕለቱ ያልነበረው ቅዱስ ቶማስ በደመና ተጭኖ ሲመጣ እመቤታችን በተቀበረች በሦስተኛው ቀን ተነሥታ ስታርግ አገኛት፤ እርሷም ለምልክት የሚሆነውን ሰበኗን ሰጥታው አጽናናችው። ሐዋርያት መቃብሯን ቢከፍቱ ሥጋዋን በማጣታቸው ሲደነግጡ፣ ቅዱስ ቶማስ ትንሣኤዋንና ዕርገቷን መስክሮ ሰበኗን አሳያቸው።

በዓመቱ ሐዋርያት ትንሣኤዋን ለማየት ነሐሴ ፩ ቀን ሱባኤ ገቡ። ነሐሴ ፲፮ ቀን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ ቀዳሲ፣ ቅዱስ ጴጥሮስ ንፍቅ ቄስ፣ ቅዱስ እስጢፋኖስ ገባሬ ሰናይ ዲያቆን ሆነው ቀድሰው ካቆረቧቸው በኋላ፣ እመቤታችን በታላቅ ክብርና በይባቤ በሐዋርያት ፊት ወደ ሰማይ ዐርጋለች። ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት «ተንሥእ እግዚኦ ውስተ ዕረፍትከ አንተ ወታቦተ መቅድስከ፤ አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ አንተና የመቅደስህ ታቦት» (መዝ. ፻፴፩፥፰) ብሎ የተናገረው ትንቢት በእርሷ ፈጸመ።
የእመቤታችን ትንሣኤና ዕርገት ልዩ የሚያደርገው፡-
እንደ አልዓዛር፣ እንደ ጣቢታና እንደ ኤልያስ ያስነሣው ብላቴና ዳግም ሞትን የሚያስከትል ሳይሆን፤ እንደ ልጇ ትንሣኤ በሦስተኛው ቀን የተፈጸመና ዳግም ሞት የሌለበት የዘለዓለም ሕይወት ትንሣኤ ነው።
እንደ ሄኖክና ኤልያስ ወደፊት ሞትንና ትንሣኤ ዘጉባኤን የሚጠብቅ ሳይሆን፣ ከሞት በኋላ ተነሥታ ትንሣኤ ዘጉባኤን ሳትጠብቅ በክብር ያረገችበት በኩር ትንሣኤ ነው።
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነትና የልጇ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቸርነትና በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን። አሜን!

የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት

በዲ/ን አየለ

#እመቤታችን #ዕርገት #ትንሣኤ #ነሐሴ16 #ኦርቶዶክስ #ተዋሕዶ #እምነት

21/08/2026

ጎርጎርዮስ ባርክ ጉባዔነ በመስቀልከ (2) ከመ ነቢያት ወሐርያት አበው እለ ቀደሙነ

እንደ ቀደሙ አባቶች ነቢያትና ሐዋርያነት ጎርጎርዮስ ጉባዔያችንን በመስቀልክ ባርክ

Address

Eastern Shoa Diocese Office
Adama
271

Telephone

+251941372168

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሐመረ ተዋሕዶ ሚዲያ /Hamere Tewahedo Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to ሐመረ ተዋሕዶ ሚዲያ /Hamere Tewahedo Media:

Shortcuts

Share