ዓ/ገ/ደ/ሲ/ቅ/ኪዳነ ምሕረት ቤ/ክ ፍኖተ ሎዛ ሰ/ት/ቤት fenote loza16

  • Home
  • Ethiopia
  • `Alem Gena
  • ዓ/ገ/ደ/ሲ/ቅ/ኪዳነ ምሕረት ቤ/ክ ፍኖተ ሎዛ ሰ/ት/ቤት fenote loza16

ዓ/ገ/ደ/ሲ/ቅ/ኪዳነ ምሕረት ቤ/ክ ፍኖተ ሎዛ ሰ/ት/ቤት fenote loza16 Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ዓ/ገ/ደ/ሲ/ቅ/ኪዳነ ምሕረት ቤ/ክ ፍኖተ ሎዛ ሰ/ት/ቤት fenote loza16, Religious organisation, `Alem Gena.

22/02/2024
አለም ገና ኪዳነ ምህረት😍😍
21/08/2023

አለም ገና ኪዳነ ምህረት😍😍

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜንእንኳን ለእናታችን ለእመቤታችን ለቅድስት ኪዳነ ምሕረት አመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሰንየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ...
22/02/2023

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

እንኳን ለእናታችን ለእመቤታችን ለቅድስት ኪዳነ ምሕረት አመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሰን

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በየዓመቱ የካቲት ፲ ፮ (16) እመቤታችን ድንግል ማርያም ከልጇ ከወዳጇ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ የምህረት ውል ስምምነት የተቀበለችበት ቀን በታላቅ መንፈሳዊ በረከት ታከብራለች፡፡ ኪዳነ ምህረት ማለት የምህረት ቃል ኪዳን ማለት ነው፡፡ ይህም ፍጹም ከከበሩ የእመቤታችን በዓላት አንዱ ሲሆን ከልጇ ከወዳጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ የማይጠፋ የዘላለም ኪዳን የተቀበለችበት ዕለት መታሰቢያ ነው፡፡
እግዚአብሔር ከፍጥረቱ ጋር ካለው ግንኙነት አንዱ ቃል ኪዳን ነው፡፡ ˝ኪዳነ ተካየድኩ ምስለ ኅሩያን፡- ከመረጥኳቸው ጋር ቃል ኪዳን አደረግሁ˝ ብሎ እንደተናገረ ከብዙዎቹ ጋር ቃል ኪዳን አለው፡፡ መዝ 89 ፥3 ምድርን ዳግመኛ በንፍር ውኃ ላይመታ ሥጋ ለባሽንም አንድ ጊዜ ፈጽሞ ላያጠፋ ለኖኅ ቃል ኪዳን ገብቶለታል፡፡ ዘፍ 9፥1-17 የምድር አሕዛብ በዘሩ እንዲባረኩ ለአብርሃም ቃል ኪዳን ገብቷል፡፡ ዘፍ 22፥18፡፡ ለይስሐቅና ለያእቆብም ተስፋቸውን ነግሯዋል፡፡ ለቅዱስ ዳዊትም ምሎለታል፡፡ መዝ 89፥3 ቃል ኪዳን እግዚአብሔር በወዳጆቹ አድሮ ለሕዝቡ የሚያደርሰው የምሕረቱ መገለጫ በመሆኑ በቅዱሳኑ በዓላት ይነገራል፣ ትምህርት ይሰጥበታል፣ አማኞችም አምነው በቃል ኪዳናቸው እግዚአብሔርን በመማጸን ይጠቀሙበታል፡፡

የእመቤታችን ቃል ኪዳን ግን ለየት ያለ ነው፡፡ ለየት የሚለው በሁለት ዐበይት ምክንያቶች ነው፡፡ የመጀመሪያው እርሷ ምልዕተ ጸጋ በመሆኗና ፍጽምት ርኅርኂተ ኅሊና ከመሆኗ የተነሣ ስለ ሰው ልጆች አብዝታ የማለደች እና ክርስቲያኖች ሁሉ ይድኑ ዘንድ ከሌሎቹ በተለየ የለመነች በመሆኗ ነው፡፡ ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ወላዲተ አምላክ ለመባል የበቃች ከእርሷ በቀር ሌላ የሌለ፣ በዚህም መልዕልተ ፍጡራን ትሆን ዘንድ የተገባት ናት፡፡ ለአምላክ እናትነት (ልዩ) ሆና መመረጧን ለሚያምን ሁሉ ልዩ ቃል ኪዳን መቀበሏ ጥያቄ አይሆንበትም፡፡ ስለዚህም ልዩ ቃል ኪዳንተ ገብቶላታል። ይህ ኪዳን ልዩ የሆነበት ነገሩ አንዱ የራሱ መታሰቢያ ዕለት ያለው መሆኑ ነው፡፡
ዕለቱም ጌታችን በጌቴ ሴማኒ ተገልጾ ኪዳኑን የገባበት ዕለት ነው፡፡ ይኸውም የካቲት ዐስራ ስድስት ቀን ነው፡፡ እመቤታችን ወደ ጎልጎታ ወደ ጌታ መቃብር እየሔደች አብዝታ ትለምን ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት መላእክት ወደ ሰማያት አሳርገው ገነትንና ሲኦልን አስጎብኝተዋታል፡፡ እርሷም በሲዖል ያሉ ነፍሳትን አይታ በእጅግ አዝናላቸዋለች ከዚህም በኋላ ስለ ኃጢአን አብዝታ ስትለምን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህች ዕለት ተገልጾ ልዩ የምሕረት ቃል ኪዳን ስለገባላት ኪዳነ ምሕረት እየተባለች ትከበራለች፡፡
ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንኀለሁ˝ የሚለውን ለአዳም የገባውን ኪዳን የፈጸመው በእመቤታችን ስለሆነ እርሷ ራሷም ኪዳነ ምሕረት እየተባለች ትጠራለች፡፡ ማዳኑን የፈጸመባት በኋላም ተነሳሕያን ኃጥአን ይቅርታን ያገኙ ዘንድ ኪዳን የገባላት ናትና፡፡ ስንክሳሩም በመግቢያው ላይ ˝በዚያችም ዕለት የክርስቲያን ወገኖች ሁሉም አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዓልን ያደርጋሉ በዚች ዕለት መታሰቢያዋን ለሚያደርግ ስሟን ለሚጠራ ለድሆችና ለችግረኞች እስከ ቀዝቃዛ ውኃ ለሚሠጥ የክብር ባለቤት ከሆነ ከተወደደ ልጅዋ ከጌታችንና ከመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የምሕረት ቃል ኪዳንን (ኪዳነ ምሕረት) ተቀብላለች˝ ይላል፡፡ጌታም ይህን ቃል ኪዳን በነሐሴ ዐስራ ስድስት ቀን ደግሞታል፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

የመንፈሳዊ ትምህርት ለመማር አስበዋል! 📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖      የፍኖተ-ሎዛ ሰንበት ት/ቤት የበጋ  ተከታታይ መንፈሳዊ ትምህርት አዘጋጅቶ ይጠብቆታል።👉📝 በአካል በመገኘት በሰንበት ...
30/09/2022

የመንፈሳዊ ትምህርት ለመማር አስበዋል!
📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖
የፍኖተ-ሎዛ ሰንበት ት/ቤት የበጋ ተከታታይ መንፈሳዊ ትምህርት አዘጋጅቶ ይጠብቆታል።

👉📝 በአካል በመገኘት በሰንበት ት/ቤቱ ጽ/ቤት ዘወትር እሑድ መመዝገብ ይችላሉ።

👉 📅 ትምህርቱ የሚጀምረው መስከረም 29 ቀን 2015 ዓ.ም

👉 🕰 ትምህርቱ የሚሰጥበት ቀን እሑድ ከጠዋቱ 3:30-6:30 ሰዓት ድረስ

⚡️ ትምህርቱ የሚሰጠው በነጻ ነው!!
⚡️ በአካል ተገኝተው መማር ለማይችሉ የተልዕኮ/የርቀት ትምህርት ተዘጋጅቷል

"አንተ ግን በተማርክበት እና በተረዳህበት ነገር ጸንተህ ኑር" 2ጢሞ 3÷14

22/08/2022

ነሐሴ 16🙏🙏

13/07/2022

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።የእናታችንን የቅድስት ድንግል ማርያምን እርገት አስመልክቶ በአለም ገና ቅድስት ኪዳነምህረት ቤት ክርስትያን በፍኖተ ሎዛ ሰንበ...

11/06/2022

በዓለ መንፈስ ቅዱስ / ጰራቅሊጦስ /ጰንጠ ቆስጤ

ይህች ታላቅ ዕለት ከቅድስት ሥላሴ አንዱ አካል የሆነው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ለቅዱሳን ሐዋርያት፣ ለቅዱሳን አርድእትና ለቅዱሳት አንስት የተገለጠባት ዕለት ናት፡፡ እነዚህ ሁሉ በጸሎት ተግተው በሚጸልዩበት ወራት መንፈስ ቅዱስ በተከፋፈሉ የእሳት ልሳን አምሳል የወረደበት ቅዱስ ቀን ነው፡፡ አስቀድሞ ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱሳን ሐዋርያት ደብረ ዘይት በተባለ ታላቅ ተራራ ላይ ሳሉ እንዲህ ብሎ አስተምሯቸው ነበር “ኃይልን ከአርያም እስክልክላችሁ ድረስ በኢየሩሳሌም በጸሎት ቆዩ፡፡”/ሉቃ 24፡36/ መቶ ሃያው ቤተሰብም በኢየሩሳሌም ሀገር በምትገኝ በቤተ መቅደስ በአንድነት ሆነው በጸሎት በመትጋት ቆዩ፡፡ 120ው ቤተሰብ የሚባሉት 12ቱ ሐዋርያት፣ 72ቱ አርድእት/አገልጋዮች/ እና 36ቱ ቅዱሳን አንስት/ሴቶች/ ናቸው፡፡

ከዕርገት በኋላ በአሥረኛው ቀን እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ሐዋርያት ወዳሉበት፣ በጸሎትና በምሥጋና ወደ ሚተጉበት ሥፍራ በእሳት አምሳል /ምሳሌ/ ወርዶ በእያንዳንዳቸው ላይ ተቀመጠባቸው፡፡ ይሄንንም ሁኔታ ተከትሎ ምስጢር ተገለጠላቸው፣ ይፈሩ የነበሩት ሐዋርያትም ወንጌልን ለማስተማር ደፋሮች ሆኑ፣ በተለያየ ቋንቋዎች እንዲናገሩ እውቀት ተሰጣቸው፤ የእግዚአብሔርንም ጸጋ ተቀበሉ፡፡

በዚያም ዕለት በዓለ ሃምሳ የሚባለውን የአይሁድን በዓል ለማክበር ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ቁጥራቸው በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የሐዋርያቱን ታላቅ የዝማሬና የእልልታ ድምፅ ሰሙ፡፡ ከመቶ ሃያው ቤተሰብ መካከል አንዱ የሆነው ቅዱስ ጴጥሮስ የተሰበሰቡት ሁሉም እንዲሰሙት ድምፁን ከፍ አድርጎ ቃለ እግዚአብሔርን እንዲህ ብሎ አስተማራቸው፡፡ “እናንተ የእስራኤል ሰዎች ሆይ እኛን የሰው ልጆችን ለማዳን እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ሆኖ ወደ ምድር መጥቶ ከክፉ ሥራ ተመለሱ፣ ኀጢአትን አታድርጉ፣ በቅድስና ኑሩ፣ ወደ እኔም ተመለሱ ቢላችሁ፤ እናንተ ግን ምንም በደል ሳይኖርበት ገረፋችሁት፣ አንገላታችሁት፣ በመስቀል ላይም ሰቀላችሁት፡፡ እርሱ ግን እግዚአብሔር ነውና ሞትን ድል አድርጎ ተነሣ፡፡ እርሱ ግን አሁንም ይቅር ባይ ነውና ከኀጢአታችሁ ተመለሱ ንስሐም ግቡ፡፡” በማለት አስተማራቸው፡፡ የተሰበሰቡት ሰዎች ሁሉ ተገረሙ፡፡ ምክንያቱም ሐዋርያት በፊት የሚያውቁት አንድ ቋንቋ ብቻ ነበረ፡፡ በዚህ ሰዓት ግን ሰባ ሁለት ቋንቋን እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ገልጦላቸው ለሁሉም በየቋንቋቸው አስተማሯቸው፡፡ ይህንንም ድንቅ ተአምር ከተመለከቱት ብዙዎች እግዚአብሔርን አመሰገኑት፡፡ ወደ ሐዋርያትም ቀርበው “አባቶቻችን እናንተ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ናችሁና ምከሩን፡፡ እንደ እናንተ የእግዚአብሔር ልጆች እንድንሆንና በቅድስና እንድንኖር ምን እናድርግ?” በማለት ጠየቁ፡ በዚያች ቀን ቁጥራቸው ሦስት ሺ ያህል ሰዎች በቅዱስ ጴጥሮስ ትምህርት አምነው ክርስቲያን ለመሆን ቀረቡ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም እንዲህ አላቸው፡፡ “እነሆ ሁላችሁም ንስሐ ግቡ፡፡ በአምላካችን በኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት አምናችሁ ተጠመቁ፡፡” አላቸው በዚያው ዕለትም ሦስት ሺ ሰዎች ወደ ሐዋርያት በመቅረብ ኀጢአታቸውን ተናገሩ፤ ሐዋርያትም እግዚአብሔር ይፍታችሁ እያሉ ልጅነትን የሚያሰጣቸውን ጥምቀት አጠመቁዋቸው፡፡
ከዚያ ቀን ጀምሮም በየዓመቱ ይህችን ታላቅ የቤተ ክርስቲያን የልደት ቀን የምትባለውን በዓለ ጰራቅሊጦስን ክርስቲያኖች በታላቅ ደስታና ምሥጋና እናከብራታለን፡፡

በጽርሐ ፅዮን የወረደው የአብ በረከት፣ የወልድ ፍቅር ፣ የመንፈስ ቅዱስ አንድነት ከሁላችንም ጋር ይሁን

Address

`Alem Gena

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ዓ/ገ/ደ/ሲ/ቅ/ኪዳነ ምሕረት ቤ/ክ ፍኖተ ሎዛ ሰ/ት/ቤት fenote loza16 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share