28/05/2019
"ሞትም ለካ ይሰረቃል"
ይህን ተአምር ሳታነቡ እንዳታልፉት "
በአንድ ወቅት አንድ አገልጋይ ወንጌል ለመመስከር እሩቅ አገር ለመሔድ ከተሳፋሪዎች ጋር በአውቶብስ ጉዞ ይጀምራል። ጉዞ ከተጀመረ በኋላ ግን መንገድ ላይ አንዱ ከተማ ተሳፋሪው በሙሉ ምሳ ለመብላት ይወርዳል። ከተሳፋሪዎቹ መሐከልም አንዱ ወደ አንድ ምግብ ቤት ይሔድና ምሳውን ከበላ በኋላ ለመክፈል ቦርሳውን ሲፈልግ ያጣዋል። መሰረቁንም ከተረዳ በኋላ ለምግብ ቤት ባለቤቱ የደረሰበትን አስረድቶ በነበረበት ከተማ የሚያውቀው ዘመድ ስለነበር ገንዘብ አምጥቶ እንደሚከፍል ተናግሮ ገንዘብ ይዞ መጥቶ ይከፍልና ወደ አውቶብሱ ሲሔድ አውቶብሱ ለካ ጠብቆ ጠብቆ የደረሰበትን ነገር ስላላወቀ ትቶት ሔዷል። ሠውየውም ገንዘቡም ተዘርፎ አውቶብሱም ጥሎት መሔዱ እየገረመው "ይሄ ፈተና ነው ሰይጣ...ን እፈር እኔ እንደሆነ ከአገልግሎት አልቀርም ብሎ ብዙ ከተንከራተተ በኋላ በሌላ አውቶብስ ተሳፍሮ ጉዞ ይጀምራል። በመንገድ ላይም ተገልብጦ አንድ ትልቅ ገደል ላይ የገባ አውቶብስ ያያል። ከተሳፋሪዎቹም የተረፈ ሰው አለመኖሩ ያያል። በጣም አዝኖ እያለም ወርዶ አውቶብሱን በደንብ ሲያየው እርሱ ተሳፍሮባት የነበረችውና ጥላው የሔደችው አውቶብስ መሆንዋን ይረዳል። በጣም ገርሞት ለካ አውቶብሱ ጥሎኝ የሔደው ለበጎ ነው በሚል እግዚአብሔርን እያመሠገነ ጉዞ ይጀምራል የሚያገለግልበት ቦታ ደርሶም ስለተደረገለት ነገር ለአንድ ሣምንት እዛው እግዚአብሔርን ሲያመሰግን እና ወንጌል ሲመሰክር ሰንብቶ ወደ ቤቱ ሲመለስ መኖሪያ ቤቱ ድንኳን ተተክሎ ያያል። ምን ተፈጥሮ ይሆን? በሚል ጠጋ ብሎ ሲያይ ለቅሶ ነው ጎረቤቶቹ በሙሉ ደንግጠው እርሱን ሲያዩት ያያል። ሠውየውም "ማን ነው የሞተው?" ብሎ ይጠይቃል። እነርሱም "አንተ" ይሉታል። አርሱም እንዴት እኔማ ይሄው አለሁ። ይላል። የእርሱን በሕይወት መምጣት የሰሙ ቤተሰቦቹም ማመን አቅቷቸው እየመጡ ይጠመጠሙበታል። ሐዘኑም ወደ ደስታ ይለወጣል። ሰውየውም ቤተሰቡም ጎረቤቱም ረጋ ብለው ስለተፈጠረው ሁኔታ ያወራሉ። ለካ አውቶብሱ ሲገለበጥ አደጋው የከፋ ስለነበር የሰዎቹ ማንነት በመልክ መለየት ስላልተቻለ የሟቾች ኪስ ፓሊስ እየበረበረ ማንነታቸውን መለየት ሲጀምር የሰውየውም የጠፋው ቦርሳ አንዱ የሰረቀውና አንዱ ሟች ኪስ ውስጥ ይገኛል። ፓሊስም በመታወቂያው መሠረት ለሰውየው ቤተሰቦች መርዶ ይነገራል። ለቤተሰቡም በቤ/ክን በተዘጋጀ አዲስ የመቃብር ቦታ ይቀብሩታል። ለካ ሠውየው ነው ተብሎ የተቀበረው ሌባው ነው። ሁሉም ሠው ይህን ሲሰማ ይገረማል። ከሰውየውም መካከል አንዷ ልጁ "የአንተ አዲሱ መቃብር የተቀበረው ሌባው ነው። አንተ መቃብር ላይ ሌባ አይቀበርም። ይውጣ።" ስትል ሠውየው አንድ አስገራሚ ነገርተናገረ " አይሆንም ሌባውን እወደዋለሁ ሞቴን የወሰደልኝ ሞቴን የሰረቀኝ ባለውለታየ ነው። እርሱ ቦርሳየን ሰርቆኝ ለምሳ መክፈያ ብር ፍለጋ ባልሔድ ኖሮ አውቶብሱ አያመልጠኝም ነበር። እኔም ሟች ነበርኩ። አትንኩት።" ነበር ያለው
እናንተየ እስኪ ልጠይቃችሁ እግዚአብሔር ሲፈቅድ ለካ ሞትም ይሰረቃል አይገርምም የሰውየው ንግግር በጣም ይገርማል። መጽሐፍ ቅዱስም ይላል "ነገር ሁሉ ለበጎ ነው።"
ሁሌም በመንገዱ ጌታን ያስቀደመ አያፍርም!
አስተማሪ ሆኖ ካገኙት ለወዳጅዎ share ሼር ያድርጉት