Cairo Prayer and Worship Church

Cairo Prayer and Worship Church this page is promote about God give us free Salvation in Christ Jesus and anybody who believe Jesus it works on us.

our face book page promotes the amazing work of the Holy Spirit through the Name of our Lord Jesus Christ giving to human being Salvation and healing.

04/06/2018

አስደናቂ የጸሎት ጥቅሞች
ሳታቋርጡ ጸልዩ፤
(1ኛ ተሰሎንቄ 5:17)
የጸሎትን ጥቅምና ከፍ ያሉ ዓላማዎቹን ስትረዱ፣ ሁልጊዜም ለመጸለይ በተለይም በልሳን ለመጸለይ ፈቃደኛና ደስተኛ ትሆናላችሁ። እንደ እግዚአብሔር ልጆች መንፈስ ቅዱስ በህይወታችን ካደረገልን ነገሮች መካከል አንዱ፣ በልሳን የመናገር ችሎታ ነው። በልሳን ስንናገር የምናወጣቸውና የምንናገራቸው ቃላት በሰው የተፈጠሩ ሳይሆኑ ከጌታ ናቸው።
በተጨማሪም የምንናገረው ለሰው ሳይሆን ለእግዚአብሔር ነው፡- “በልሳን የሚናገርስ ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው አይናገርም፤ የሚያስተውለው የለምና፥ በመንፈስ ግን ምሥጢርን ይናገራል፤” (1ኛ ቆሮ 14:2)፡፡ በልሳን ስትጸልዩ ከአብ ጋር ህብረት እያደረጋችሁ ነው። በሰማያዊ ቋንቋ ከእግዚአብሄር ጋር በመንፈስ ጋር እየተነጋገራችሁ ነው፣ ይሄ እንዴት ድንቅ በረከት ነው!
ከዚህም በተጨማሪ በልሳን መጸለይ በመንፈሳችሁ ውስጥ ያለውን የእግዚአብሔርን ሀይል ለማንቀሳቀስ ይረዳል። ምንም እንኳን ያ ሀይል መንፈስ ቅዱስን ወደ ህይወታችሁ በተቀበላችሁ ጊዜ ወደ እናንተ የመጣ ቢሆንም (ሐዋርያት ሥራ 1፡8) ሁልጊዜም ልታነቃቁትና ለእግዚአብሔር ክብር ልትጠቀሙበት ይገባል።
በልሳን መጸለይ ሁልጊዜም የበለጠ መንፈሳዊ ብቃት እንዲኖራችሁ ያደርጋል፣ ለመንፈስ ቅዱስ ምሪት፣ የተቃኛችሁና ምላሽ የምትሰጡ ያደርጋችኋል። በመንፈስ ቅዱስ በመጸለይ ከጌታ ጋር ህብረት ለማድረግ የበለጠ ጊዜ ባሳለፋችሁ ቁጥር፣ የእርሱ ባህሪይና ስብእና በይበልጥ በእናንተ ውስጥና በእናንተ በኩል ይገለጣል።
አንዳንድ ሰዎች ለመጸለይ የሚገደዱት በህይወት አስቸጋሪ ሁኔታ ሲገጥማቸው ብቻ ነው፣ ይሄ ደግሞ ትክክል አይደለም። በሰማይ ካለው አባታችን ጋር ህብረት እንድናደርግ ተጠርተናል፣ የጸሎትና የመጸለይ ዋነኛው ዓላማ ህብረት ለማድረግ ነው።
በግልና በጋራ ለሚኖራችሁ የጸሎት ጊዜ ትኩረት ስጡ። በጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት ልታደርጉ የምትችሉባቸውን አጋጣሚዎች ፍጠሩ፤ ህይወታችሁም ከክብር ወደ ክብር እያደገ ይመጣል።

27/10/2017

በክርስቶስ ኢየሱስ የድል ነሺ ህይወት ተሰጥቶናል
ነገር ግን በክርስቶስ ሁልጊዜ ድል በመንሣቱ ለሚያዞረን በእኛም በየስፍራው ሁሉ የእውቀቱን ሽታ ለሚገልጥ ለአምላክ ምስጋና ይሁን፤ (2 ቆሮንቶስ 2:14)
በታሪክ እንድንመለከተው አሁን እንዳለው ዓይነት የከፋ ችግር ከዚህም በፊት በምድር ላይ እንደነበረ መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል። በአለም ዛሬ እንዳለው እንዲሁ ክፉ እና ጨለማ ነበር:: በአለም ዙሪያ እየሆኑ ያሉት ነገሮች በሚዲያዎች የሚሰሙትና የሚታዩት ነገሮች የከፉ እና እጅግ የሚያሳዝኑ ሊሆኑ ይችላሉ። ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ እነዚህ ነገሮች አዲስ እንዳልሆኑ በግልጥ ያሳየናል: "የሆነው ነገር እርሱ የሚሆን ነው፥ የተደረገውም ነገር እርሱ የሚደረግ ነው ከፀሐይም በታች አዲስ ነገር የለም።" (መክብብ 1:9)::
ያን ጊዜም ቢሆን እንደዛሬው የኢኮኖሚ አስቸጋሪነቶች ነበሩ፤ የገንዘብ መውረድ እና መውደቅ ነበሩ:: ሰዎች ከዚህ የተነሳ በፍርሀት ይኖሩ ነበር:: እነዚህን ሁኔታዎች ጠላት (ሰይጣን) ሰዎችን ለመጨቆን እና ለማስጨነቅ የሚጠቀምባቸው ስልቶች ነበሩ አሁንም ናቸው:: በእርግጥ ጠላት አዲስ ማታለያ ስልት የለውም ሁልጊዜም የሚታወቁትና ያው ያረጁት ናቸው ያሉት::
አምላካችን እግዚአብሔር ግን በትውልዶች መካከል ታማኝ ስለነበር፤ በጨለማ ውስጥ ህዝቡን ቀጣይ በሆነ ድል መንሳት መርቷል ፤ ቃሉንም ጠብቋል:: ለዚህ ነው ዘማሪው እንዲህ ያወጀው "አቤቱ፥ ምሕረትህን ለዘላለም እዘምራለሁ፥ ታማኝነትህንም በአፌ ለልጅ ልጅ እናገራለሁ።" (መዝሙር 89:1)::
ምንም ያህል የጥፋት እና የፍርድ ዜናዎች በሚዲያዎች ቢሰራጭ ግድ አይበላችሁ፤ ነገር ግን አልፈራም በሉ:: አትደንግጡ! እንዲህ ተብሎ ተጽፏል፦ " አምላካችን መጠጊያችንና ኃይላችን ፤ ባገኘን በታላቅ መከራም ረዳታችን ነው። ስለዚህ ምድር ብትነዋወጥ፤ ተራሮችም ወደ ባህር ልብ ቢወሰዱ አንፈራም።" መዝ(46) : 1-2 እንደገና በ1ኛ ዮሐንስ 4:4 እንዲህ ይላል, "ልጆች ሆይ፥ እናንተ ከእግዚአብሔር ናችሁ አሸንፋችኋቸውማል፥ በዓለም ካለው ይልቅ በእናንተ ያለው ታላቅ ነውና።" ሰማያዊ አባታችሁ ክፋትን፤ ከባድ ሁኔታዎችን፤ አስከፊ የኢኮኖሚ ሁኔታዎችን እና ሽብርን በአለም እያስተካከለ ብዙ ቆይቷል:: እናንተን እንዴት መንከባከብ እንዳለበት እና ህይወታችሁን እንዴት ውብ ማድረግ እንዳለበት ግራ አይገባውም በሚገባ ያውቃል።
በ2 ቆሮንቶስ 2:14 ላይ ያለውን የሚያነቃቃ የሐዋሪያውን የጳውሎስን ቃሎች አስታውሱ በመግቢያ ጥቅሳችን ላይ ያለውን ቃል፦ "በመሲሁ፤ በክርስቶስ, ከስፍራ ወደ ስፍራ እግዚአብሔር ሁልጊዜ በሚጨምር የድል ሰልፍ ይመራናል::" እግዚአብሔር በውድቀት ውስጥ፤ በኢኮኖሚ መውረድ ውስጥ፤ በግሽበት እና በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ድላችሁን፤ እድገታችሁን እና ብልጥግናችሁን ወስኗል:: በዙሪያችሁና በአለም ምንም ነገር ቢሆን በእናንተ ህይወት ግን ስኬት፤ ድል፤ መከናወን፤ብልጽግና፤ስላም እና መለኮታዊ ጤንነት በኢየሱስ ስም ይሆናል::
ስለዚህ እንዲህ ብላችሁ አውጁ፦ በዚህ አለም ያሉ ክፋቶች እና ስቃዮች ምንም ቢሆኑ የተከለልኩ እና የተጠበኩ ነኝ፤ በውሀ ዳር እንደተተከለ በወንዝ ውስጥም ስሩን እንደሚሰድድ ዛፍ ነኝ:: ሙቀት ሲመጣ አላውቅም:: በክርስቶስ ኢየሱስ ሁልጊዜ ድል ነሺ ነኝ! አለምን እና ስርዓቱን ድል አድርጌአለሁ! ጌታ ኢየሱስ ሆይ አመሰግንሃለሁ! ኤር 17:7-8

26/09/2017

የቅዱሳን ጸሎት እጅግ ሃይልን ያደርጋል!!
ሐዋ 12:1-24 ያለውን ክፍል ስንመለከት ሄሮድስ የተባለው የሮም መንግስት የሾመው ንጉስ ሀዋርያው ያቆብን ካስገደለ በሃላ ሃይማኖተኛ የሆኑትን አይሁዳውያንን ደስ ያሰኛቸው ዘንድ አስቦ ሃዋርያው ጴጥሮስን ለማስገደል ወህኒ ቤት አስገባው። ነገር ግን ካላይ ባለው የመጽሐፍ ቅዱስ ቁጥር 5 ላይ ሰለ ጴጥሮስ መታሰርን በተመለከተ በቤተ ክርስቲያን ያሉ ቅዱሳን መታሰሩን የሰሙ ተሰብስበው በአንድ ቤት ውስጥ ብርቱና ጥብቅ የሆነ ጸሎት ወደ እግዚአብሔር ይጸልዩ ነበር።ጴጥሮስ እንዳይሞት ከእስር እንዲፈታ።እግዚአብሔርም እንደ ቃሉ የቅዱሳንን ጸሎት ሰምቶ ጴጥሮስ ወደ ታሰረበት ወህኒ ቤት ማንም ሊደርስበትና ሊያገኘው ከማይችልበት ቦታ ድረስ መላእኩን ልኮ ጠባቂዎቹ አይናቸው እያየ ጴጥሮስን ከታሰረበት በማስወጣት፤ የሞት ፍርድ እንዲፈጸምበት የወሰነውን ንጉስ ሄሮድስን ግን በቤተመንግስት አልጋው ላይ እያለ በትል ተበልቶ እንዲሞት ተፈረደበት። እግዚአብሔር ጴጥሮስን ያስፈታው በእርሱ የተጀመርው የእግዚአብሔር ስራ ገና ስላላለቀ እግዚአብሔር እርሱን በማስፈታት ክብሩን በዚያ ስፍራ ላይ ገለጠ።ብዙዎችም እንዲህ አሉ ይሄ ከግዚአብሔር እንጂ ከሰው ስለአይደለ ጴጥሮስን ማንም ሰው እንዳይነካው ተከለከለ።ዛሬም ለወንጌል አገልግሎት ሲሉ በግብጽ ካይሮ በእስር ላይ የሚገኙትን የእግዚአብሔር ወንጌል አገልጋዮች ለሆኑት ወንድሞቻችን በእነርሱ የተጀመረው የወንጌል ስራ ስለሚቀጥልና በወንጌል ምክንያት መታሰር እጅግ የማይገኝ ክብር እንደሆነና ትልቅም እድል እንደሆነ በማወቅና በማሰብ በካይሮ የምትገኙ የግዚአብሔር ወገኞችና ቅዱሳን አማኞች ዛሬም የጴጥሮስ አምላክ የሆነውና የኛም አምላክ የሆነው እግዚአብሔር እነዚህን ወገኖች ከእስራታቸው መላእኩን ልኮ እንዲያስፈታቸው ብርቱና ጥብቅ ጸሎት እንዲደረግ አሳስባለሁ።

ፓስተር ኤልያስ ደሳለኝ ከሳውዝ አፍሪካ

01/09/2017
13/08/2017

የዘመኑ ክርሰትና ወደ ድራማነት እየተቀየረ ይመሰለኛል ፣ ሰው ሁሉ ሐይማኖቱን እንጂ ሰለ ሕይወት ቃል በእርሱ ያለውን ሊያውቅ አይፈቅድም መጽሐፉን ሰንመለከት ግን እንዲህ ይላል ፦ በክርስቶስ ኢየሱስ ባለ እምነትና ፍቅር አድርገህ፥ ከእኔ የሰማኸውን ጤናማ ቃል ምሳሌ ያዝ፤"
በክርሰቶሰ ''ባለ እምነት '' እንጂ ባለኝ አይልም በእርሱ ላይ ባለ እንጂ ባለኝ ኖሬ አላውቅም ። እምነት ባለ የምንኖረው እንጂ ባለን ምንኖረው አይደለም ። ሌላው ፦ ከእኔ የሰማኸውን ጤናማ ቃል ምሳሌ ያዝ ይለዋል ። እናም ጤናማ ያልሆነ ቃልም አለ ማለት ነው ። ጤናማ ባልሆነ ትምህርት ያለው ደግሞ ይህ ነው ፦እግዚአብሔርን እንዲያውቁ በግልጥ ይናገራሉ፥ ዳሩ ግን የሚያስጸይፉና የማይታዘዙ ለበጎ ሥራም ሁሉ የማይበቁ ስለ ሆኑ፥ በሥራቸው ይክዱታል። አንድ ነገር ልብ አድርግ እግዚአብሔርን እንዲያውቁ በግልጥ ይናገራሉ አጸያፊና መታዘዝ የሌላቸው ከሀዲ ናቸው ። ክህደት አለመታዘዝ እንጂ እግዚአብሔር የለም ማለት አይደለም ። በክርሰቶሰ ባለ እምነትና ፍቅር ለበጎ ሥራ የሚበቁ አይደሉም ፡ አፋቸውን ከመጠን ይልቅ ምላሳቸውም ከቅቤ ይልቅ ልዝብ ነው ግን ጨካኞችና ከሀዲ ናቸው ።በክርሰቶሰ የተሰጠን ትልቁ ሰጦታ ግን ከአገልግሎት ይልቅ እግዚአብሔርን መምሰል ነው ። ሰይጣን መልክህን እንጂ አፍህን አይፈራም ፣ ልብህ እንጂ ልብሰህንም አያይምና የተደበቅንበት ልብሰና የተካንንበት ምላሰ ያረጃል ፣ ሰለዚህ የሚበልጠውን መከተል ፈትኖም መቀበል ጥሪን ይጠይቃልና በአገልግሎት ሰም እረፍት ያጣንለትን እንመሰለዋለን? መቼም ዛሬ ዛሬ እንዲህ መጠየቅ ፈሪሳዊ እንዲያሰብል ባውቅም እውነቱ የተሰጠኝ ኑሮ ሳይሆን ሕይወት ሰለሆነ በሕይወት እና በኑሮ መካከል ያለን እውነት ለተረዳ ሕይወት እንጀራና ውሃ አይደለም ። እንጀራና ውሃ ኑሮ ነው ። እናም በተከፈለው ዋጋ ውስጥ በክርሰቶሰ እግዚአብሔርን መምሰል ግድ ይላል፣ በመጨረሻም የተቀበልነውን የእውነት ቃል በተፈተነ ሰው እንጂ በሰለጠነ ዘንድ እንደሌለ አያለሁ እንዲህ እንደተባለ ፦ የእውነትን ቃል በቅንነት የሚናገር የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነህ፥ የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ትጋ።" በቅንነት የማያሳፍር ሰራተኛ ሆኖ የተፈተነውን ራሰህን ለማቅረብ መትጋት በዚህ ዘመን እድል ነው ። ሁሉ የሚፈልገውን ፣ እና የመረጠውን በሚፈልገው አሰተማሪው በሚማርበት ዘመን ይህንን ማገኘት ጭንቅ ይመሰለኛል ። ለሁሉም የተባረከው አባት የሚበልጠውንና የሚረባንን በክርሰቶሰ በኩል በእኛ ያድርግ ።
(2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2:15፤)

19/07/2017

የእግዚአብሔር ቃል ፊደል አይደለም ፣ የእግዚአብሄር ቃል ጥቅሰም አይደለም ፣ የእግዚአብሄር ቃል በእግዚአብሄር ዘንድ ያለ እግዚአብሔር ነው ፦እርሱም ከሁሉ በፊት ነው ሁሉም በእርሱ ተጋጥሞአል።ቆላ 1:17

29/06/2017

አንድ እውነት ልንገራችሁ ፦ ከተከበባችሁበት ፥ ነብሳችሁም ከተያዘችበት ብዙ ነገር ይልቅ ዓለም ሳይፈጠር የታሰባችሁለት ነገር ይገዛችኋል ። የተያዛችሁበትና የታገላችሁ ሁሉ ሐሰት ነው፤ አንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም ከወዳጅ ይልቅ አብልጦ የተጠጋህ ፣ በጎነትህ ያልጠራው ፣ አለመቻልህና ድካምህ ፊቱን የማይቀይርብህ ፥ በዘመናት መካከል ያው የሆነው እርሱ እውነት እላችኋለሁ እንደ ሰው አይደም ። ይምራል ፤ ይራራል ፤ ይታደግማል ። እርሱ ያሰበልን ይበልጣል ። ውድድድድድ አድርግሃለሁ አባቴ!!
ዮሐ 14፡18

ካይሮ የጸሎትና የአምልኮ ቤተ ክርስቲያን አካላት ከጁን 14 - 17, 2017 ዓመታዊ የመዝናናኛ ፕሮግራም በስኬትና በበረከት ተጠናቀቀ። ፕሮግራሙ የእግዚአብሔር ክብር የታየበት የቅዱሳን ውበት...
22/06/2017

ካይሮ የጸሎትና የአምልኮ ቤተ ክርስቲያን አካላት ከጁን 14 - 17, 2017 ዓመታዊ የመዝናናኛ ፕሮግራም በስኬትና በበረከት ተጠናቀቀ። ፕሮግራሙ የእግዚአብሔር ክብር የታየበት የቅዱሳን ውበትና ሞገሳቸው እግዚአብሔር እነደሆነ የተመሰከረበት እጅግ አስደሳች ጊዜ እንደነበር ከስፍራው የዘገበው ዘጋቢያችን በፎቶ በማስደገፍ መረጃውን አድርሶናል ቅዱሳንም በእግዚአብሔር ጥበቃ በሰላም ወደ ካይሮ ተመልሰዋል ። ክብር ለእግዚአብሔር ለአምላካችን ይሁን!!!!!አሜን

16/06/2017
08/06/2017

በትር ስልጣን ፤ገዢነትን፤ንግስናንና የበላይነትን አቅምን ያሳያል።ዛሬ እናንተ የእግዚአብሄር ልጆች ስለሆናችሁ ይህ ስልጣን አላችሁ።ስለዚህ በሁሉ ላይ እንዲህ ታደርጋላችሁ፥ ትውጣላችሁ እንጂ በምንም ሆነ በማንም አትዋጡም።ይህ በክርስቶስ ኢየሱስ የእናንተ የድልና የገዢነት ስፍራችሁ ነው።አሜን ሃሌሉያ!!

Address

Port Said Street 17 Maadi
Cairo
654EL-MAADI11765

Opening Hours

Saturday 6pm - 9pm
Sunday 9am - 11am

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Cairo Prayer and Worship Church posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Cairo Prayer and Worship Church:

Share