Ethiopian Orthodox Tewahedo Kidus Amanuel GermanyMunich

Ethiopian Orthodox Tewahedo  Kidus Amanuel GermanyMunich "ወደ ተራራው ውጡ፥ እንጨትንም አምጡ፥ ቤቱንም ሥሩ፤ እኔም በ?

23/08/2016
ታቦር ተራራ የመንግሥተ ሰማያት ምሳሌ ነው!1.     ተራራ በብዙ ችግር እንዲወጡት ወደ እግዚአብሔር መንግሥትም በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናልና /ሐዋ 14፡22/፡፡2.    በታቦር ...
19/08/2016

ታቦር ተራራ የመንግሥተ ሰማያት ምሳሌ ነው!

1. ተራራ በብዙ ችግር እንዲወጡት ወደ እግዚአብሔር መንግሥትም በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናልና /ሐዋ 14፡22/፡፡
2. በታቦር ተራራ የብሉይ ኪዳን ነቢያት ከሐዲስ ኪዳንም ሐዋርያት እንደተገኙ መንግሥተ ሰማያትን ነቢያትም፣ ሐዋርያትም አንድ ሆነው ይወርሷታልና፡፡
3. በታቦር ተራራ ከመዓስባን ሙሴ ከደናግል ደግሞ ኤልያስ እንደተገኙ መንግሥተ ሰማያትንም ደናግልም መዓስባንም በአንድ ላይ ይወርሷታልና፡፡
4. በታቦር ተራራ ሞተው ከተቀበሩት መካከል ሙሴን በብሔረ ሕያዋን ካሉት ደግሞ ኤልያስን እንደመጡ መንግሥተ ሰማያትንም ሞተው የተቀበሩትም በብሔረ ሕያዋን ያሉትም በአንድነት ይወርሷታልና፡፡

በአጠቃላይ ታቦር ተራራ የክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት የተመሠከረበት፣ የምሥጢረ ሥላሴ ትምህርት የተሰጠበት፤ ፈጣሪ ከቅዱሳን ሰዎቹ ጋር የተገኘበት፤ በልበ ሐዋርያት የነበረ ሰይጣን ድል የተደረገበት፤ የሐዋርያት በተለይም የሦስቱ ባለሟልነት የተገለጠበት፤ አሉባልታና ተራ ወሬ የከሸፈበት፤ የቅዱሳንን ክብር ለሚያናንቁ ተራራም እንኳን “ቅዱስ” እንደሚባል የተማርንበት፤ የብሔረ ሕያዋን መኖር የተመሰከበረበት፤ የትንሣኤ ሙታን ዋስትና የተገለጠበት የክብር ሰገነት፣ የምሥጢር መቅደስ፣ ታላቅ ትምህርት ቤትም ጭምር ነው፡፡
ፈጣሪያችን እግዚአብሔር እስከ መጨረሻዋ ሕቅታ ድረስ በታቦር ተራራ በተመሰለች ቤተክርስቲያን በሃይማኖታችን ጸንተን የመንግሥተ ሰማያት ወራሾች የስሙ ቀዳሾች እንድንሆን የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን፡፡ አሜን!!

አንድ አምላክ በሚሆን በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።ነሐሴ 12-ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ንጉሥ ቆስጠንጢኖስን ረድቶ በድል ያነገሠበት ዕለት ነው፡፡ ንጉሥ ቆስጠንጢ...
17/08/2016

አንድ አምላክ በሚሆን በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
ነሐሴ 12-ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ንጉሥ ቆስጠንጢኖስን ረድቶ በድል ያነገሠበት ዕለት ነው፡፡ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ገና በወጣትነቱ አባቱ ስለሞተ የአባቱ ባለሟሎችና ህዝቡ ተስማምተው በ18 ዓመቱ ቆስጠንጢኖስን በአባቱ ቦታ ሐምሌ 25 ቀን 300 ዓ.ም በሮም ምዕራብ ክፍል በገላትያ አነገሡት፡፡ እርሱም በጦር ሜዳዎች ብዙ የጀግንነት ሥራዎች ስለሠራ በሠራዊቱ ዘንድ ይወደድ ነበር፡፡
ንግሥት ዕሌኒ ልጅዋን ቆስጠንጢኖስን ከልጅነቱ ጀምሮ ስለክርስትና ሃይማኖትና ስለክርስቲያኖች መከራ ታስተምረው ስለነበር በክርስቲያኖች ላይ የነበረው አመለካከት በሮም ከነገሡት ቄሣሮች ሁሉ የተሻለ ነበር፡፡ በተለይም በ312 ዓ.ም ከጠላቱ ከመክስምያኖስ ጋር ለመዋጋት እንደተነሣ በራእይ በሰማይ ላይ ‹‹በዚህ የመስቀል ምልክት ጠላትህን ድል ታደርጋለህ›› የሚል መስቀልና ጽሑፍ ስላየ ለሠራዊቱ ሁሉ የመስቀል ምልክት በመሣሪያቸውና በሰንደቅ ዓላማው ላይ እንዲያደርጉ አዘዘ፡፡ ወደያው ጦርነት ቢገጥም በቲቤር ወንዝ ድልድይ ላይ ጠላቱን ድል ነሥቶ በጠቅላላው የሮም መንግስት ግዛቶች ሁሉ ገዥ ሆነ፡፡ ይኸውም የሆነው በመላእክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል ረዳትነት ነው፡፡ ‹‹ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ›› (ዳን 10፡13፡፡)
ታላቁ ቆስጠንጢኖስ በመላእክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል ረዳትነት ጠላቶቹን ሁሉ ድል ነሥቶ በጠቅላላው የሮም መንግሥት ግዛቶች ሁሉ ገዥ ከሆነ በኋላ በ300 ዓመታት ውስጥ ለመጀመርያ ጊዜ ለክርስቲያኖች የነፃነት ዐዋጅ ዐወጀ፡፡ ክርስትናም ብሔራዊ ሃይማኖት ተባለች፡፡ ንግሥት እሌኒም ይህን ጊዜ የጌታችንን ቅዱስ መስቀል ከተቀበረበት ለማውጣት በ327 ዓ.ም ወደ ኢየሩሳሌም ሄደች፡፡ እርሷም ልጇ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ አምኖ ክርስቲያን ከሆነላት ወደ ኢየሩሳሌም ሄዳ መስቀሉን ለመፈለግ እንዲሁም በኢየሩሳሌም ያሉ ቅዱሳት መካናትንና አብያተ ክርስቲያናትን ለማነጽ ለእግዚአብሔር ተሳለች፡፡ ከዚህም በኋላ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ አምኖ በ337 ዓ.ም ተጠመቀ፡፡
ጻድቁ ንጉሥ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ አስቀድሞ ገና ሳይጠመቅ በቅዱስ መስቀል ምልክት ድል ማድረግ የጀመረ ነው፡፡ በእናቱ በቅድስት ዕሌኒ ስዕለት ካመነ በኋላ በ325 ዓ.ም ጉባዔ ኒቂያን የጠራና ጸሎተ ሃይማኖት እንዲደነገግ ያደረገ ነው፡፡ በዓለም ላይ አብያተ ጣኦታትን አጥፍቶ አብያተ ክርስቲያናትን ያሠራና በከሃዲው ዲዮቅልጥያኖስ የተዘጉትን ያስከፈተ ታላቅ የቤተ ክርስቲያን ባለውለታ ነው፡፡ በነገሥታት ታሪክ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በዓለም አቀፍ ደረጃ እንደ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ያከበራት የለም፡፡ የዚህ ጻድቅ ንጉሥ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን፡፡ የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሚካኤል ጥበቃው ተራዳኢነቱ አይለየን፡፡

“በመከራዬ ጊዜ በአፌ የተናገርሁትን፥ ከንፈሮቼምያሉትን ስእለቴን                       ለአንተ እፈጽማለሁ፤ ”መዝ፡፷፭፥፲፬።                                  ...
09/08/2016

“በመከራዬ ጊዜ በአፌ የተናገርሁትን፥ ከንፈሮቼምያሉትን ስእለቴን
ለአንተ እፈጽማለሁ፤ ”መዝ፡፷፭፥፲፬።
በአምላክ ኅሊና ተቀርፃ የኖረች ጽላት፥ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፡- የብጽዓት ልጅ ናት። ቅዱስ ኢያቄምና ቅድስት ሐና፡- “ወንድ ልጅ ብንወልድ፡- ወጥቶ ወርዶ፥ አርሶ ቆፍሮ ይርዳን አንልም፤ ለቤተ እግዚአብሔር እንሰጠዋለን። ሴት ልጅም ብንወልድ፡- እንጨት ሰብራ ውኃ ቀድታ፥ ፈጭታ ጋግራ ታገልግለን አንልም፤ ለቤተ እግዚአብሔር እንሰጣታለን።” ብለው ተስለው ነበር። በመሆኑም፡- ገና በሦስት ዓመቷ ለቤተ እግዚአብሔር ሊሰጧት ተስማሙ። ይህም፡- ሕልቃና እና ሐና፥ ነቢዩ ሳሙኤልን፡- ለቤተ እግዚአብሔር ለመስጠት እንደተስማሙት አይነት ነው። ሐና ሕልቃናን፡- “ሕፃኑ ጡት እስኪተው ድረስ እቀመጣለሁ፤ ከዚያም በኋላ በእግዚአብሔር ፊት ይታይ ዘንድ፥ በዚያም ለዘለዓለም ይሆን ዘንድ አመጣዋለሁ።” እንደ አለችው፥ ቅድስት ሐናም ቅዱስ ኢያቄምን፡- “ይህች ብላቴና ሆዷ ዘመድ ሳይወድ፥ አፏ እህል ሳይለምድ ወስደን አንሰጥምን? «የሰጠ ቢነሳ የለበትም አበሳ፤» እንደሚባለው፥ አንድ ነገር ብትሆንብን ከልጃችንም ከእግዚአብሔርም ሳንሆን እንቀራለን፤” ብለዋለች። በኦሪቱ ዘመን ሕልቃና ለሐና፡- “በዓይንሽ ደስ ያሰኘሽን አድርጊ፥ ጡትም እስኪተው ድረስ ተቀመጪ፤ ብቻ እግዚአብሔር ቃሉን ያጽና፤” እንደ አላት፥ ቅዱስ ኢያቄምም ቅድስት ሐናን፡- “ፍቅርሽ ያልቅልሽ እንደሆነ ብዬ ነው እንጂ፥ እኔማ ፈቃደኛ ነኝ፤” ብሎአታል። ምክንያቱም ከፍቅሯ ጽናት የተነሣ አንድም ቀን ከእቅፏ አውጥታት፥ ከጭኗ አውርዳት አታው ቅም። እንዲህም ማድረግዋ፡- አንድ ቀን ለብቻዋ ትታት ከደጅ ወጥታ ስትመለስ፥ መልአከ እግዚአብሔር ሰውሮባት በመከራ አግኝታት ስለነበረ ነው፤ ሁሌም እንደዚያ እየመሰላት ከላይዋ አታወርዳትም ነበር። ቅዱስ ኢያቄምና ቅድስት ሐና፡- ሕፃኗን ማርያምን ይዘው ከቤተ እግዚአብሔር ሲደርሱ፥ ሊቀ ካህናቱ ዘካርያስ፡- ሕዝቡን ሰብስቦ እያስተማረ ነበር። እነርሱም “እነሆ ስእለት ተቀበሉን፤” አሉአቸው። “እንቀበላለን፤” ብለው ቢቀርቡ፥ ከፀሐይ ሰባት እጅ አብርታ፥ ከመብረቅ ሰባት እጅ አስፈርታ፥ የምታበራ ዕንቈ ባሕርይ መስላ ታየቻቸው። እንዲህ አይነቱ ድንቅ ተአምራት፥ እግዚአብሔር ለመረጣቸው እንደሚደረግ መጽሐፍ ቅዱስ ቋሚ ምስክር ነው። “ሙሴም ከተራራው በወረደ ጊዜ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ስለ ተነጋገረ የፊቱ ቍርበት አንጸባረቀ፤ (እንደ ፀሐይ አበራ)፤ . . . ጥበበኞቹም እንደ ሰማይ ፀዳል፥ ብዙ ሰዎችንም ወደ ጽድቅ የሚመልሱ እንደ ከዋክብት ለዘላለም ይደምቃሉ። . . . ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ይበራሉ።. . . እስጢፋኖስም ጸጋንና ኃይልን ተሞልቶ በሕዝቡ መካከል ድንቅንና ታላቅ ምልክትን ያደርግ ነበር።. . . በሸንጎም የተቀመጡት ትኵር ብለው ሲመለከቱት እንደ መልአክ ፊት ሆኖ አዩት።” ይላል፤ ዘጸ፡፴፬፥፳፱፣ ዳን፡፲፪፥፫፣ ማቴ፡፲፫፥፵፫፣ የሐዋ፡፮፥፯፤፲፭። የመልአክ ፊቱ ምን እንደሚመስል መጽሐፍ ቅዱስ ሲነግረን፡- “አካሉም እንደ ቢረሌ ይመስል (እንደ ብርሃን ያብለጨ ልጭ) ነበር፥ ፊቱም እንደ መብረቅ ምስያ ነበረ፥ ዓይኖቹም እንደሚንበለበል ፋና (መብራት)፥ ክንዶቹና እግሮቹም እንደ ጋለ ናስ፥ የቃሉም ድምፅ እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ ነበረ። . . . የጌታ መልአክ ከሰ ማይ ስለ ወረደ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ቀርቦም ድንጋዩን አንከባሎ በላዩ ተቀመጠ። መልኩም እንደ መብረቅ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ነበረ፤” ብሎናል። ዳን፡፲፥፮፣ ማቴ፡፳፰፥፪።
ሊቀ ካህናቱ ዘካርያስ እና ካህናቱ፡- የተሰጣትን ጸጋ አይተው፥ “ይህችን የመሰለች ልጅ ተቀብለን ምን እናደርጋታለን? ምን እናበላታለን? ምን እናጠጣታለን? ምን እናለብሳታለን? ምን እናነጥፍላታለን? ምን እንጋርድላታለን?” በማለት እንደ ሰው ተጨነቁ። በዚህ መካከል ሕፃኗ ማርያም ረኀብ ተሰምቷት አለቀሰች። በዚህን ጊዜ መልአኩ ቅዱስ ፋኑኤል፡- ሰማያዊ እንጀራን በመሶበ ወርቅ፥ ሰማያዊ መጠጥን ደግሞ በብርሃን ጽዋ ይዞ፥ ወደ ታች ሳይወርድ ረቦ ታያቸው። ሕዝቡም ለአባታቸው ለካህኑ ለዘካርያስ የመጣ ጸጋ በረከት መስሎአቸው፡- “እጅ ነስተህ፥ ሰግደህ ተቀበል፤” ብለውት፥ እጅ ነስቼ ሰግጄ እቀበላለሁ ብሎ ቢቀርብ፡- ወደ ሰማይ ራቀው። ከሕዝቡም እያንዳንዳቸው እጅ ነስተን፥ ሰግደን እንቀበላለን ብለው ቢቀርቡ፡- እነርሱንም ወደ ሰማይ ራቃቸው። ከዚህ ሁሉ በኋላ ዘካርያስ ሐናን ጠርቶ፡- “ለእናንተ ለእንግዶቹ የወረደ ጸጋ በረከት ሊሆን ስለሚችል ሕፃኒቱን ይዘሽ ወደዚያ ፈቀቅ ብለሽ ተቀመጪ፤” አላት። ቅድስት ሐናም ካህኑ እንደ ነገራት ብታደርግ፥ ቀረብ ብሎ ከራሳቸው ላይ ረቦ አልወርድም አለ። ሁለተኛም ዘካርያስ ሐናን ጠርቶ፡- “አምላከ እስራኤል የሚያደርገው ነገር ስለማይታወቅ (ስለማይመረመር)፥ ሕፃኒቱን እዚያው ትተሽ አንቺ ወዲህ ነዪ፤” አላት። ቅድስት ሐና ገና ዘወር ከማለቷ፥ ቅዱስ ፋኑኤል ወርዶ፥ አንደኛውን ክንፉን አንጥፎላት፥ ሁለተኛውን ክንፉን ደግሞ ጋርዶላት እመቤታችንን መገቦአታል፥ ሰግዶላታልም። በእግዚአብሔር የታዘዙ ቅዱሳን መላእክት፡- የእግዚአብሔርን ቅዱሳን እንዲህ እንደሚመግቡ በመጽሐፍ ቅዱስ የታወቀ ነው። እመቤታችን ደግሞ ቅድስት ቅዱሳን በመሆኗ ከእነዚህ ሁሉ ትበልጣለች። “ነቢዩ ኤልያስ ከኤልዛቤል ፊት ሸሽቶ የአንድ ቀን መንገድ ተጓዘ፤ መጥቶም ከክትክታ ዛፍ በታች ተቀመጠና፡- ይበቃኛል፤ አሁንም፥ አቤቱ፥ እኔ ከአባቶቼ (ከአብርሃም ከሙሴ) አልበልጥምና ነፍሴን ውሰድ ብሎ እንዲሞት ለመነ። በክትክታውም ዛፍ በታች ተጋ ደመ፥ እንቅልፍም አንቀላፋ፤ እነሆም መልአክ ዳሰሰውና፡-ተነሥተህ ብላ አለው።ሲመለከትም፥ እነሆ፥ በራሱ አጠገብ የተጋገረ እንጐቻና በማሰሮ ውኃ አገኘ።በላም ጠጣም፥ ተመልሶም ተኛ። የእግዚአብሔር መልአክ ደግሞ ሁለተኛ ጊዜ መጥቶ ዳሰሰውና፡- የምትሄድበት መንገድ ሩቅ ነውና ተነ ሥተህ ብላ አለው። ተነሥቶም በላ ጠጣም፤ በዚያም ምግብ ኃይል እስከ እግዚአብሔር ተራራ እስከ ኮሬብ ድረስ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ሄደ፤” ይላል። ፩ኛ፡ነገ፡፲፱፥፩-፰።
ካህናቱና ሕዝቡም፡- “የምግቧ ነገር በቅዱሳን መላእክት እጅ ከተያዘማ ከተርታው ሰው ጋር ምን ያጋፋታል፤” ብለው፥ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን አስገብተው፥ መኖሪያዋን በቤተ መቅደስ አደረጉላት። ይኸውም ነቢዩ ሳሙኤል ገና በሦስት ዓመቱ ለቤተ መቅደስ ተሰጥቶ በዚያ እንደኖረው ማለት ነው። ፩ኛ፡ሳሙ፡፩፥፳፪-፳፱። የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሕንፃው ብቻ አይደለም፥ የሰው ሰውነቱም የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነው። “የእግዚአ ብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ፥ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን?. . . ወይስ ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን? በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ።” ይላል። ፩ኛ፡ቆሮ፡፫፥፲፮፤፮፥፲፱። ከዚህ የምንማረው ትልቅ ትምህርት አለ፤ ይኸውም፡- ሰውነታችን በእውነት የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ከሆነ፥ እመቤታችን በልባችን ውስጥ እንድትኖር፡- የተሰጠችን የእግዚአብሔር ጸጋ እንደሆነች እናምናለን። የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሆኖ ካልተገኘ ደግሞ ፈጽሞ በውስጣችን ልትኖር አትችልም። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ የገባችው ታኅሣሥ ሦስት ቀን ነው። በዚህም፡- አባቷ ቅዱስ ዳዊት ተናግሮት የነበረው ቃለ ትንቢት ፍጻሜውን አግኝቶአል። ከእናት ከአባቷ ቤት ወጥታ፥ ለቤተ መቅደስ ተሰጥታ፥ በዚያው እንደምትኖር አስቀድሞ ስለ ተገለጠለት፡- “ልጄ ሆይ፥ ስሚ እዪ፥ ጆሮሽንም አዘንብዪ፤ ወገንሽንም የአባትሽንም ቤት እርሺ፤ ንጉሥ (ንጉሠ ሰማይ ወምድር እግዚአብሔር) ውበትሽን (የአዳም ኃጢአት ያልወደቀበትን ንጽሕናሽን) ወድዶአልና፤” ብሎአል። መዝ፡፵፬፥፲። ከጥንት ጀምሮ የነበሩ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፡- ከቅዱስ ያሬድ ድርሰቶች በተቀመመ ምስጋናቸው፡- “አንቲ ውእቱ ንጽሕተ ንጹሐን፥ ዘነበርኪ ውስተ ቤተ መቅደስ ከመ ታቦት፥ ወመላእክት ያመጽኡ ወትረ ሲሳየኪ፥ ስቴኪኒ ስቴ ሕይወት ውእቱ፥ ወመብልዕኪኒ ኅብስት ሰማያዊ። እንደ ታቦተ እግዚአብሔር በቤተ መቅደስ ውስጥ የኖ ርሽ አንቺ፥ ከንጹሐን ይልቅ ንጽሕት ነሽ፤ ቅዱሳን መላእክት ዘወትር ምግብሽን ያመጡልሽ ነበር፥ ትጠጪው የነበረውም መጠጥ የሕይወት መጠጥ ነው፥ መብልሽም በሰው እጅ ያልተሠራ ሰማያዊ እንጀራ ነው፤” ብለዋታል።

ጾመ ፍልሰታ የሚለው ቃል የሚገልጸው ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለቆ መሔድን መሰደድን መፍለስን ያመለክታል። ይህም የእመቤታችንን ሥጋ ከጌቴሴማኒ ወደ ገነት መፍለሱን በኋላም በገነት በዕፀ ሕይ...
05/08/2016

ጾመ ፍልሰታ
የሚለው ቃል የሚገልጸው ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለቆ መሔድን መሰደድን መፍለስን ያመለክታል። ይህም የእመቤታችንን ሥጋ ከጌቴሴማኒ ወደ ገነት መፍለሱን በኋላም በገነት በዕፀ ሕይወት ስር ከነበረበት መነሳቱን ለማመልከት ይነገራል።
ጾመ ፍልሰታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፷፬ ዓመት በዚች ምድር ኖራ እንደ አንድ ልጇ መሞቷን መነሳቷንና ማረጓን ያዩ ዘንድ ሐዋርያት የጾሙት ጾም ነው። ጾሙ ከነሐሴ ፩ ቀን እስከ ነሐሴ ፲፮ ቀን ሲጾም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአዋጅ ከደነገገቻቸው ሰባቱ አጽዋማትም አንዱ ነው።
ኃይማኖታዊ መሠረት
እመቤታችን ከአባቷ ከኢያቄም እና ከናቷ ከሐና ነሐሴ ፯ ቀን ተጸንሳ ግንቦት ፩ ቀን በሊባኖስ ተወልዳለች። እንደተባለ ። እምቤታችን በእናት አባቷ ቤት ሦስት ዓመት፤ በቤተ መቅደስ አሥራ ሁለት ዓመት፤ ከልጇ ከወዳጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ሠላሳ ሦስት ዓመት ከሦስት ወር ፡ ከዮሐንስ ወልደዘብዴዎስ ዘንድ አሥራ አራት ዓመት ከዘጠኝ ወር ቆይታ በ ፷፬ ዓመት ዕድሜዋ በ፵፱ ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች። የእመቤታችንን ስም የሚገልጹ የውዳሴ ጽሑፎችም በእድሜዋ ልክ ተደርሰዋል። ለምሳሌ የውዳሴ ማርያም ቁጥር ፷፬ ነው፤ የመልክአ ማርያም ቁጥርም ፷፬ ነው።[1]
ባረፈች ጊዜ ቅዱሳን ሐዋርያት ተሰባስበው አስከሬኗን ይዘው ወደ ጌቴሴማኒ መቃብር ለማሳረፍ ሲሄዱ አይሁድ ለተንኮል አያርፉምና ተተናኮሏቸው። ቀድሞ ልጇ ሞቶ ተነሳ፣ አረገ እያሉ ሲያስቸግሩን ይኖራሉ: ደግሞ አሁን እሷም ተነሳች፣ አረገች ሊሉ አይደል በማለት አይሁድ ተሰባስበው አስከሬኗን ለማቃጠል ሲተናኮሉ እግዚአብሔር በተአምር ከነዚያ አይሁዶች አድኗቸዋል ። የእመቤታችንንም አስከሬን ነጥቆ ከሐዋርያው ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር በገነት በዕፀ ህይወት ስር አኑሯቸዋል ። ከዚያ በኋላ ሐዋርያት ሥጋዋን አግኝተው ይቀብሩት ዘንድ በአረፈች በስምንተኛው ወር ከነሐሴ ፩ ጀምሮ እስከ ነሐሴ ፲፬ ቀን ድረስ ሁለት ሱባዔ ይዘው በአሥራ አራተኛው ቀን ሥጋዋን ከጌታ ተቀብለው በጸሎትና በምህላ በፍጹም ደስታ በጌቴሰማኔ አሳረፉት ። በ ሦስተኛውም ቀን ተነስታ ስታርግ ከሰኡቃዊያን ወገን የሆነው ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ አያት። እርሱም በቀብር ስርዓቱ ጊዜም አልነበረም። ሀገረ ስብከቱ ህንድ ስለነበር ሊያስተምር ወደዛው ሂዶ ነበርና። በዚያም ሲያስተምር ሰንብቶ በደመና ተጭኖ ሲመጣ ያገኛታል። ትንሳኤዋን ከርሱ ሰውራ ያደረገች መስሎት አዝኖ «ቀድሞ የልጅሽን ትንሳኤ ሳላይ ቀረሁ አሁን ደግሞ ያንቺን ትንሳኤ ሳላይ ቀርቼ ነውን ?» ብሎ ቢያዝንባት እመቤታችንም ከርሱ በቀር ማንንም ትንሳኤዋን እንዳላየ ነግራ አጽናናችው። ለሌሎቹ ሐዋርያትም እንዲነግራቸው ለምልክትም /ለምስክርም እንዲሆነው ሰበኗን /መግነዟን ሰጥታው አረገች። ቶማስም ኢየሩሳሌም ደርሶ ሐዋርያትን «የእመቤታችን ነገርስ እንደምን ሆነ?» ሲል ቢጠይቅ «አግኝተን ቀበርናት እኮ» አሉት። እርሱ ምስጢሩን አዉቆ ደብቆ «ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር» እንዴት ይሆናል ? አይደረግም ይላቸዋል። ሊያሳያቸውም መቃብሩ ዘንድ ሂደው ቢከፍቱት አጧት። እርሱም «አታምኑኝም ብዬ እንጂ እርሷስ ተነስታ አርጋልች» በማለት ሁኔታውን ተረከላቸውና ለምስክር ይሁንህ ብላ የሰጠችውን ሰበኗን አሳያቸው። ከዚህ በኋላ ለበረከት ይሆናቸው ዘንድ ሰበኑን ተካፍለው ወደየአህገረ ስብከታቸው ሄዱ። ዛሬ በቅዳሴ ጊዜ ዲያቆኑ በሚይዘው የመጾር መስቀል ላይ በሁለት ቀዳዳዎች አልፎ ተጠምጥሞ የምናየው መቀነት መሰል ጨርቅ የዚያ ሰበን ምሳሌ ነው።
በዓመቱ ሐዋርያት ከያሉበት ተሰባስበው ቶማስ ትንሳኤሽን አይቶ እኛስ እንዴት ይቀርብናል ብለው ከነሐሴ ፩ ቀን ጀምርው ሱባዔ ቢይዙ ከሁለት ሱባዔ በኋላ እንደገና ትንሳኤዋንና እርገቷን ለማየት በቅተዋል። ሐዋርያዊት የሆነች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናም ምእመኖቿ ከእመቤታችን በረከትን እንዲያገኙ ይጾሙ ዘንድ ይህን ሐዋርያት የጾሙትን ጾም እንዲጾሙ አዉጃለች። ምእመናንም በተለየ መልኩ በጾም በጸሎት በሱባዔ ጽሙድ ሆነው ይህን ወቅት ያሳልፋሉ።
የእመቤታችን ትንሳኤ ድንገት እንደእንግዳ ደራሽ እንደ ዉሀ ፈሳሽ የተደረገ ሳይሆን በቅዱሳት መጻሕፍት በትንቢተ ነቢያት የተገለጸ ነው። ነቢዩ ዳዊት በመዝሙር ፻፴፩ ቁጥር ፲ ላይ «አቤቱ ወደ እረፍትህ ተነስ አንተና የመቅደስህ ታቦትም» ይላል። በዚህም ምዕመናንን ወደ ምታሳርፍበት ወደ መንግሥተ ሰማያት የመቅደስህ ታቦት ድንግል ማርያምን ይዘህ ተነስ አለ። ታቦት የጽላት ማደርያ እንደሆነ ሁሉ እምቤታችንም ለክርስቶስ ማደርያ በመሆኗ አማናዊት ታቦት ትባላለች።
ንጉስ ሰሎሞንም በመኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን ምዕራፍ ፪ ቁጥር ፲ ላይ «ውዴ እንዲህ ብሎ ተናገረኝ፤ ወዳጄ ሆይ ተነሽ፡ ውበቴ ሆይ ነይ» ብሏል። እዚህ ላይ «ወዳጄ ...ዉበቴ»" የተባለች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት ። ክቡር ዳዊት መዝሙር ፵፬ ቁጥር ፱ ላይ «በወርቅ ልብስ ተጎናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች» እንደሚል ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ ለዓለም ቤዛነቱን ከፈጸመ በኋላ ወደ ቀደመ ክብሩ እንዳረገ እመቤታችን ቅድስት ድንገል ማርያምም በቀኙ ትቀመጥ ዘንድ «ተነሽ ነይ» አላት ። እንግዲህ ይህንና የመሰለዉን ሁሉ ይዘን የእናታችንን እረፍቷን ትንሳኤዋን እንዘክራለን እንመሰክራለንም።

“ወብዙኀን ይትፌሥሑ በልደቱ በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል” ሉቃ.1፥14በዘመነ ብሉይ የእግዚአብሔር ድምፅና የመልአክ ብሥራት ብርቅ በነበረበት ወቅት ካህኑ ዘካርያስና ቅድስት ኤልሳቤጥ ልጅ...
31/07/2016

“ወብዙኀን ይትፌሥሑ በልደቱ በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል” ሉቃ.1፥14

በዘመነ ብሉይ የእግዚአብሔር ድምፅና የመልአክ ብሥራት ብርቅ በነበረበት ወቅት ካህኑ ዘካርያስና ቅድስት ኤልሳቤጥ ልጅ መውለድ አጥተው ባረጁበት ዘመን የእግዚአብሔር መልአክ ካህኑ ዘካርያስን እንዲህ አለው፡፡

መልአኩም እንዲህ አለው “ዘካርያስ ሆይ፥ አትፍራ፤ ጸሎትህ በእግዚአብሔር ፊት ተሰምቶአልና፤ ሚስትህ ኤልሣቤጥም ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅንም ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ፡፡ ደስታና ሐሤትም ይሆንልሃል፤ በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል፡፡ እርሱ በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ ይሆናልና የወይን ጠጅና የሚያሰክርም መጠጥ ሁሉ አይጠጣም፤ ከእናቱ ማሕፀን ጀምሮም መንፈስ ቅዱስ ይመላበታል፡፡ ከእስራኤልም ልጆች ብዙዎችን ወደ አምላካቸው ወደ እግዚአብሔር ይመልሳቸዋል፡፡ እርሱም የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች፥ የከሓድያንንም ዐሳብ ወደ ጻድቃን ዕውቀት ይመልስ ዘንድ፥ ሕዝብንም ለእግዚአብሔር የተዘጋጀ ያደርግ ዘንድ በኤልያስ መንፈስና ኀይል በፊቱ ይሄዳል፡፡”ሉቃ1፥13-18 ይህ ለመጥምቁ ዮሐንስ የተነገረ ቃል ቢሆንም ወላጆቹ (ካህኑ ዘካርያስና ቅድስት ኤልሳቤጥ) በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን እንደነበሩ በቅዱስ ወንጌል ተገልጿል /ሉቃ.1፥6-7/ እንደዚሁ ሁሉ ካህኑ ጸጋዘአብና ሚስቱ እግዚእ ሐረያ በእግዚአብሔር ሕግና ሥርዓት ይመሩ የነበሩ ደጋግ ክርስቲያኖች ነበሩ፡፡ ይህም ሊታወቅ በትሩፋት ሥራ፣ በጾም፣ በጸሎት፣ በምጽዋት የታወቁ ነበር፡፡ በተለይም የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሚካኤል በዓልን ምክንያት በማድረግ ይመጸውቱ ነበር፡፡ የመልአኩም ጥበቃ ባለ ዘመናቸው ሁሉ አልተለያቸውም ነበር፡፡ ጌታችን በቅዱስ ወንጌል ላይ “መልካም ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬን ያፈራል፣” /ማቴ.7፥17/ እንዳለ፣ ለዓለም ሁሉ የወንጌልን ብርሃን የሚያበስር ሐዲስ ሐዋርያ በቅድስናና በክብሩ ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ሃያ አምስተኛ ሆኖ ያመሰገነውን ጻድቅ ወለዱ፡፡ በሰሜን ሸዋ ጽላልሽ ልዩ ስሙ ኢቲሳ በተባለ ቦታ የተወለዱት ጻድቁ ተክለ ሃይማኖት በ12ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተነሡና የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ትምህርት ከየመን እስከ ኬንያ ከሶማሌ እስከ ሱዳን ድረስ የተስፋፋበትን ወርቃማ ዘመንን ያስገኙ ጻድቅ አባት ናቸው፡፡

“ነገርን ከሥሩ ውኃን ከጥሩ” እንዲሉ የጻድቁን ታሪክ በአጭሩ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡

ቅዱሳኑ በትሩፋት ሥራ የተጠመዱ ነበሩ

ልጅ አጥተው ሲያዝኑ ይኖሩ የነበሩት ካህኑ ፀጋ ዘአብና ቅድስት እግዚእ ሐረያ፣ በየወሩ የቅዱስ ሚካኤልን በዓል ያከብሩ ነበርና መጋቢት 12 ቀን የተራበን ሲያበሉ ሞቶሎሚ ንጉሠ ዳሞት ሀገራቸውን ወርሮ ከእነርሱ ደረሰ፡፡ ጸጋ ዘአብም እንደማይምራቸው አውቀው አንከርት ወደሚባለው ባሕር ሮጡ፡፡ ከሞተሎሚ ጭፍሮች አንዱ ተከተላቸው፣ የማይደርስባቸው ሲሆን ሰይፉን ሊወረውርባቸው ቃጣ፡፡ ሰይፉ ከእጁ ተጠቅልላ ቀረች፡፡ በሌላ እጁ ሁለተኛ ሊወረውር ቢቃጣ አሁንም ተጠቅልላ ቀረች፡፡ እሳቸውም እንዳልተዋቸው አይተው ዘለው ከባሕር ገቡ፡፡ ከባሕር ውስጥ ሆነው እንዲህ አያሉ ይጮሁ ጀመረ…” ኀይል የምትሆነኝ ቅዱስ ሚካኤል፣ አምባ መጠጊያ የምትሆነኝ ቅዱስ ሚካኤል፣ ኀይልህ ወዴት ነው? ከኃሊነትህ ወዴት ነው? ተአምራት ማድረግህ ወዴት ነው? እንሆ መሞቻዬ ደረሰ፡፡ ዛሬ የሽብር ቀን ነው፡፡ ዛሬ የመከራ ቀን ነው፡፡ ዛሬ ጥፋት ተፈርዶብኝ፡፡ በበዓልህ ደስ ሳታሰኘኝ ታሳዝነኛለህን? እያሉ ያለቅሱ ጀመረ፡፡ እስመ ለመላእክቲሁ ይኤዝዞሙ በእንቲአከ ከመ ኢትትዐቀፍ በዕብን፤ እግርከ በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዛቸዋልና፣ እግርህ በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸውም ያነሡሃል፡፡ እንዲል /መዝ.90፥11/ ቅዱስ ሚካኤል በውስጥ ሆኖ ተቀብሏቸዋል፡፡ “ወባሕርኒ ኮነቶ ከመ ደብተራ ዘድለት ለማኅደር” ይላል ባሕርም እንደ ድንኳን ሆነላቸው “ኦ ፍቁርየ ጸጋ ዘአብ አስመ አነ አዐቅበከ በይነ ዘይወጽእ እምሐቁከ፤ ወዳጄ ጸጋ ዘአብ ሆይ፥ ከአብራክህ ስለሚከፈለው ቅዱስ እጠብቅሃለሁና አትፍራ” አላቸው፡፡ ከዚህ በኋላ በሦስተኛው ቀን አውጥቶ ቤተ ክርስቲያን አድርሷቸዋል፡፡

በሌላ በኩል በሞቶሎሚ ወታደሮች የተማረኩት እግዚእ ሐረያ ለንጉሡ ሚስት ሊያደርጓቸው፣ ከቤተ መንግሥቱ አገቧቸው፡፡ ቅድስት እግዚእ ሐረያ ግን “ጌታዬ ፈጣሪዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ስንፍናዬን ለምን ተመለከትክ፡፡ በንጹሕ ሆኖ የሚያገለግል ባሪያህ ጸጋ ዘአብን ለምን አላሰብከውም አንተን ለሚክዱ ኃጥአን ለሚሆኑ ጠላቶች አሳልፈህ ለምን ሰጠኸኝ ሕግህን ሥርዓትህን ከማያውቅ ከሚያጸይፍ ባሪያ ልጅ ትሰጠኝ ዘንድ ወደድክን? ከዚያም ከንጹሕ አገልጋይህም ቢሆን አንተን ደስ የማያሰኝ ልጅ ካለሆነ ማኅፀኔን ዝጋው እልሃለሁ፡፡ አቤቱ የትድግና ባለቤት ዛሬ በእኔ ላይ ትድግናህን ግለጽ” በማለት ያመለክቱ ነበር፡፡ ጠባቂ መልአካቸው፡- ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ተገልጦ ከሠራዊት ሞቶሎሚ በመንጠቅ በክንፉ ታቅፎ ከዳሞት ዞረሬ በሦስት ሰዓት አደረሳቸው፡፡ በመጋቢት ሃያ ሁለት ቀን ጸጋ ዘአብ ከቤተ መቅደስ ገብተው ሲያጥኑና ስለ እግዚእ ሐረያ ሲለምኑ፣ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ከቤተ መቅደስ አግብቶ ከዚያ ትቷቸው ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ ገድለ ተክለሃይማኖት ምዕ.12

በዚህ ሁኔታ በእግዚአብሔር ቸርነት፣ በመልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነት ደግም የተገናኙት ሁለቱ ቅዱሳን /ጸጋ ዘአብና እግዚእ ሐረያ/ መጋቢት ሃያ አራት ቀን ከአብራካቸው የሚከፈለውን ጻድቁ ተክለሃይማኖትን ፀነሱ፡፡ እነሆም ታኅሣሥ 24 ቀን ቅዱስ አባታችን ተወለዱ፡፡

“ገድለ ተክለሃይማኖት” የተባለው መጽሐፍ አባታችን ተክለሃይማኖት በተፀነሱበት መጋቢት 24 ቀን ለእናትና አባታቸው እግዚአብሔር ራእይ እንዳሳያቸው ይገልፃል፡፡ ቅድስት እግዚእ ሐረያ ያዩት ራእይ “የብርሃን ምሰሶ ከቤታቸው ውስጥ ቁሞ የሞሶሶው ራስ ከሰማይ ደርሶ በዓለም ያሉ ሕዝብ ሁሉ ነገሥታቱም ጳጳሳቱም በዙሪያው ቁመው እኩሌቶቹም ይሰግዱለታል፤ እኩሌቱቹም እሱን ጥግ አድርገው ይቀመጣሉ፡፡ በሱም ላይ ብዙ አዕዋፍ ተቀምጠውበታል፡፡እኩሌቶቹ ነጫጮች፣ እኩሌቶቹም ቀያዮች፣ እኩሌቶቹ አመድ አመድ ይመስላሉ፡፡ ዝጉርጉርም ናቸው፡፡ በሌላ በኩል ካህኑ ጸጋ ዘአብ ደግሞ በዚሁ ሌሊት ስላዩት ሕልም ለእግዚእ ሐረያ ሲነግሩ እንዲህ ብለዋል፡- “ከምንተኛበት አጎበር ሥር ፀሐይ ሲወጣ፥ስፍር ቁጥር የሌላቸው ብሩሃን ከዋክብት በክንፉ ላይ ተቀምጠው ለዓለሙ ሁሉ ሲያበሩ፣ ከብርሃኑም ብዛት የተነሣ ሀገሩ ሁሉ አበራ፡፡ ይህን ራእይ ዐይቼ ደንግጬ አለቀስኩ”

ከዚህ በኋላ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል የሁለቱንም ህልም ይተረጉሙላቸው ዘንድ ከእግዚአብሔር ተልኳል፡፡ በትርጓሜውም፡- “ከጸጋ ዘአብ ቤት ሲወጣ የታየው ፀሐይ ከአብራኩ የሚከፈለው ልጁ ተክለ ሃይማኖት ነው፡፡ በብርሃኑ ከምእመናን ላይ የኃጢአትን ጨለማ የሚያርቅ ይሆናል፤ በክንፉም ላይ ታዝለው፥የታዩት ከዋክብት በመንፈስ ቅዱስ በእርሱ ትምህርት ይወለዱ ዘንድ ያላቸው ልጆቹ ናቸው፡፡ የእግዚእ ሐረያ ሕልም ትርጉሙ እንዲህ ነው በቤታቸው የብርሃን ምሶሶ ቁሞ ራሱ ከሰማይ ደርሶ ያያቸው ልጅህ ነው፡፡ ነገሥታቱ ጳጳሳቱ ሲገዙለት ያየችውም በእውነት ነገሥታቱ ይሰግዱለታል፡፡ አሕዛብም ይገዙለታል፡፡ ለሁሉም መጠጊያ ይሆናል፡፡ ከነገሥታቱ በላይ ሆኖ ይኖራል፡፡ ተአምራቱ ከዛፍ ፍሬ ይበዛል ሥፍር ቁጥር የለውም፡፡ እንደሣዕረ ምድር ጸንቶ ይኖራል፡፡ ስሙም ለዘለዓለም ሲመሰገን ይኖራል፡፡ ሰማይ ከምድር በላይ እንደሆነ የሱም ስም አጠራሩ እንደሱ ካሉ ከቅዱሳን ምእመናን በላይ ሆኖ ይኖራል፡፡ የሕልማችሁ ትርጓሜ ይህ ነው፡፡” በማለት የሕልሙን ፍች አስታውቋቸዋል፡፡

በሚያስደንቅ ልዩ ልዩ ተአምራት በቅዱስ ሚካኤል ጥበቃና በእግዚአብሔር ቸርነት ከብዙ መከራ ተጠብቀው የኖሩት ሁለቱ ቅዱሳን ባልና ሚስት /ካህኑ ጸጋ ዘአብና ቅድስት እግዚእ ሐረያ/ ታኅሣሥ 24 ቀን ፃድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን ወለዱ፡፡

ከሠተ አፉሁ

ታኅሣሥ 26 ቀን /በተወለዱ ሦስተኛው ቀን/ በዕለተ ሰንበት ከጧቱ ሦስት ሰዓት ላይ እጆቻቸውን አንሥተው ወደ ሰማይ እየተመለከከቱ “አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ፤ ማለትም፦ ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ በባሕርይ በሕልውና አንድ የሚሆን አብ በአካል በስም ልዩ ነው፣ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ በባሕርይ በህልውና አንድ የሚሆን ወልድ በአካል በስም ልዩ ነው፣ በህልውና አንድ የሚሆን መንፈስ ቅዱስ በአካል በስም ልዩ ነው” በማለት ሰማያዊያን መላእክት ምድራውያን ጻድቃን ፈጣሪን በሚያመሰግኑበት ሥርዓት ሆነው አመሰገኑ፡፡ እናትየው እግዚእ ሐረያ ግን ይህንን በልባቸው እያደነቁ “ልጄ ፍሥሐ ጽዮን ምን ትላለህ ይህ ቃል የአባትህ ሥራ ነው፡፡ ላንተ ግን የሚገባህ ጡት መጥባት ነው” በማለት ተናገሩ፡፡ ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ግን ክቡር ዳዊት “እም አፈ ደቂቅ ወሕፃናት አስትዳሎከ ስብሐት፡፡ በእንተ ጸላዒ ከመ ትንሥቶ ለጸላኢ ወለገፋዒ፤ ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ ስለ ጠላትህ ጠላትንና ቂመኛን ለማጥፋት” በማለት የተናገረው ቃል ተፈጽሞላቸዋል፡፡ መዝ.8፥2

“በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል” ተብሎ በመጋቢ ሐዲስ በቅዱስ ገብርኤል የተነገረለት ዮሐንስ መጥምቅ /ሉቃ.1፥14/ ከእናት አባቱ አልፎ ብዙዎችን ከመድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያገናኘ የደስታ ምንጭ የሆነ ነቢይም ሐዋርያም ነው፡፡ በጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት መወለድም፣ ለጊዜው ልጅ ባለማግኘት ለብዙ ዓመታት ሲያዝኑ ለነበሩ ወላጆቻቸው ታላቅ የምሥራችና ደስታ ሆኗል፡፡በፍጻሜው ግን ፈጣሪያቸውን ባለማወቅ በአጋንንት አገዛዝ ሥር ወድቀው የነበሩ በብዙ መቶ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች በጸሎታቸው ኀይልና ግሩም በሆነው ትምህርታቸው ብርሃን ኢየሱስ ክርስቶስን ከባሕርይ አባቱ ከእግዚአብሔር አብና፣ ከባሕርይ ሕይወቱ መንፈስ ቅዱስ ጋር በአንድነት አውቀው ተረድተው ለስሙ እንዲገዙ አድርገዋል፡፡

ነቢዩ ኤርሚያስን ፈጣሪያችን ልዑል እግዚአብሔር ከእናቱ ሆድ ጀምሮ ለቅድስና ለክብር በነቢይነት እንደጠራው በመጻሕፋችን ተገልጦአል፡፡ /ኤር.1፥5/ ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖትም ለኢትዮጵያ ሰዎች ሐዋርያ ሆነው ያገለግሉ ዘንድ በባለቤቱ በመድኀኔዓለም በኢየሱስ ክርስቶስ አንደበት “እስመ ረሰይኩከ ሐዲስ ሐዋርያ፤ አዲስ ሐዋርያ አድርጌ ሾሜሃለሁ” ተብሎ የተነገረላቸው ናቸው፡፡ በዚህም በጌታችን ቃል “በእኔ የሚያምን እኔ የምሠራውን ሥራ እርሱም ይሠራል ከዚያም የሚበልጥ ይሠራል” /ዮሐ.14፥12/ ተብሎ በተነገረው ቃል መሠረት፤ በሰው ሰውኛ ሊደረጉ የማይችሉ ታላላቅ ተአምራትን በመፈጸም ኢ-አማንያንን ወደ ሃይማኖት መልሰዋል፡፡ ተጋድሏቸውን የመዘገበው መጽሐፍ /ገድለ ተክለ ሃይማኖት/ እንደተመዘገበው በዛፍ ላይ አድሮ ሲያሰግዳቸውና ሲያስመልካቸው የነበረ ጋኔኑን አዋርደው እርሱን ከኢትዮጵያ ምድር አርቀው በአምልኮተ ባዕድ የነበሩ ሰዎችን ወደ ቤተ ክርስቲያን ኅብረት ቀላቅለዋል፡፡

ባለብዙ ገድል ጻድቁ ተክለ ሃይማኖት “ዳግማዊ ዮሐንስ” የሚል ስያሜ የተሰጣቸው ሐዋርያ ናቸው፡፡ ዮሐንስ መጥምቁ በተፀነሰ ጊዜ የአባቱን አንደበት የዘጋ፣ ሲወለድ ደግሞ የአባቱን አንደበት ዳግመኛ የከፈተ ነው፡፡ (ሉቃ.1፥62-66) መምህር ወመገስጽ ዘኢያደሉ ለገድ የተባለለት፥ ዮሐንስ መጥምቁ ንጉሥ ሔሮድስን ሳይፈራና ሳያፍር የገሰጸ እንደሆነ ሁሉ፤ አባታችን ተክለ ሃይማኖትም እንደ ሞቶሎሚ ያሉ ጣዖት አምላኪና አስመላኪ ነገሥታትና ኀያላንን ሳይፈራ የተጠራለትን አገልግሎት በጽኑ መታመን የፈጸመ ነው፡፡

ፈጣሪያችን ከጻድቁ አባታችን ከተክለሃይማኖት በረከት ረድኤት ያሳትፈን፡፡ አሜ

ቅዱስ ጊዮርጊስየቅዱስ ጊዮርጊስ አባቱ መስፍን ሲሆን ሲሙም አንስጣስዮስ ይባላል አገሩም ቀጰዶቅያ ሲሆን እናቱም ቴዎብስታ ትባላለች እሱአም ከፍልስጤም አገር ናት ከዛም ትንሽ ሆኖ ሳለ አባቱ አ...
30/07/2016

ቅዱስ ጊዮርጊስ
የቅዱስ ጊዮርጊስ አባቱ መስፍን ሲሆን ሲሙም አንስጣስዮስ ይባላል አገሩም ቀጰዶቅያ ሲሆን እናቱም ቴዎብስታ ትባላለች እሱአም ከፍልስጤም አገር ናት ከዛም ትንሽ ሆኖ ሳለ አባቱ አረፈ: 20 አመትም በሆነው ግዜ የአባቱን ሹመት ሊቀበል ወደ ንጉስ ዱድያኖስ ዘንድ ሄደ:ንጉሱም ጣዖት አቁሞ ጣዖትን እንዲያመልኩ ሰዎችን ሲያስገድዳችው አገኘው:ይህንን አይቶ ቅዱስ ጊዮርጊስ አዘነ በርሱ ዘንድ ያለውን ገንዘቡን ሁሉ ለድሆች ለምስኪኖች ሰጠ ባሮቹንም ነጻ አወጣቸው:ከዛም በንጉስ ፊት ቆሞ በክብር ባለቤት በጌታችን በመድሃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ:ንጉሱም አባበለው ብዙ ቃል ኪዳንም ገባለት እርሱ ግን አልተቀበለውም:ለመስማት እንኩአን የሚያስጨንቅ ስቃይን አሰቃየው ጌታችን ግን ሁሌም ያጸናዋል ቁስሉንም ያድነዋል:3 ግዜ እንደሚሞት እሱም እንደሚያስነሳው በአራተኛውም የምስክርነት አክሊልን እንደሚቀበል ነገረው:ቃል ኪዳንም ሰጠው ስሙ በአለም ሁሉ የተገለጠ ይሆን ዘንድ:በተጋድሎ እና መከራ በመቀበል ሰባት አመት እንደሚኖር መላእክትም እንደሚአገለግሉት ነገረው: ንጉሱም ባለመታዘዙ እና ባለመመለሱ እጅግ አዘነ ስለዚህም አትናስዮስ የሚባል ስራየኛ አመጣና እርሱም መርዝን ቀምሞ በጽዋ ሞልቶ አስማቱን ደግሞ እንዲጠጣ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ሰጠው:ወዲያውኑ የሚሞት መስሎት ነበር ቅዱሱም ያንን ጽዋ በጌታችን ስም አማትቦ ጠጣው ምንም ጉዳት አልደረሰበትም:ያ መሰርይም በክብር ባለቤት በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ ወዲያው ሰማእት ሆኖ አረፈ:ያንንም ተአምር አይተው ብዙዎች ሰዎች በሰማእትነት ሞተው የህይወት አክሊል ተቀበሉ ቁጥራቸውም 30,700 ነፍሳት ናቸው:ቅዱስ ጊዮርጊስም በዱድያኖስና በሰባው ነገስታት ፊት በቆመ ግዜ በዚያም የተቀመጡባቸው ወንበሮች ነበሩ ቅዱሱንም እሊህን የተቀመጥንባቸው ወንበሮች እንዲበቅሉና እንዲያብቡ እንዲያፈሩም ታደርጋቸው ዘንድ ካንተ እንሻለን አሉት:በዚአን ግዜም ጸልዮ እንዳሉት አለመለመው ይህንን ድንቅ ስራ አይተው ቁጥር የሌላቸው ብዙ አህዛብ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ:ከዛም ቅዱሱን ወስደው በጎድጉአዳ ምጣድ ውስጥ አበሰሉት:አቃጥለው አሳርረውም ስጋውንንና አጥንቱን ፈጭተው አመድ አድርገው ከረጅም ተራራ ላይ በተኑት:ጌታችንም ነፍሱን ወደ ስጋው መልሱአት ደግሞ አስነሳው:ወደ ነገስታቱም ተመልሶ በክብር ባለቤት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አስተማረ ቁትር የሌላቸው አህዛብ አደነቁ በጌታችንም አምነው በሰማእትነት ሞቱ:ነገስታቱም ደግመው ሙታኖችን ብታስነሳ አምላክህ እውነተኛ አምላክ እንደሆነ እናምናለን በርሱም እናምናለን አሉት ቅዱሱም ጸለየ ከጉድጉአድም ውስጥ ወንዶችና ሴቶችን ጎልማሶችንም አስነሳላቸው እነዛም በክብር ባለቤት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አስተማሩ የገሃነምንም ወሬ ተናገሩ ጥምቀትንም ተቀብለው ተመልሰው አረፉ: ከሃድያን ነገስታቱ ግን ሙታንን ያስነሳህ አይደለም የረቀቁ ሰይጣናትን አሳየህ እንጂ ብለው ተከራከሩ ከዚአም ከጭንቀታቸው ብዛት የተነሳ ከአንዲት ደሃ ሴት ዘንድ አስጠበቁት እሱአም እንጀራ ልትለምንለት ወጣች የእግዚአብሄርም መልኣክ በላዩ ከበጎ ነገር ሁሉ የተመላ መኣድ አቀረበለት የዚያች መበለትም የቤቱአ ምሰሶ ቅርንጫፍን አበቀለ ታላቅ ዛፍም ሆነ ያችም መበለት በተመለሰች ግዜ የቤቱአ ምሰሶ ቅርንጫፍ አብቅሎ ታላቅ ዛፍ እንደሆነ ሲለማእዱም ይህን ታላቅ ምልክት አይታ የክርስቲያኖች አምላክ ሰው ተመስሎ ወደ እኔ መጣ አለች ቅዱሱም እኔ አምላክ አይደለውም የአምላክ ባርያ ነኝ እንጂ አላት እሱአም እንዲ ብላ ለመነችው የአምላክ አገልጋይ ከሆንክ ችርነትህ እንድትደርሰኝ እለምንሃለው እውር ደንቆሮ ድዳ ጎባጣ የሆነ ልጅ አለኝ እና ታድንልኝ ዘንድ እለምንሃለው ስለጌታችን እምነትም አስተማራትና መበስቀል ምልክት አማተበው ያን ግዜም ልጁ አየ ቅዱሱም በሌላ ግዜ እንዲሰማ እንዲናገር እና እንዲሄድ እንዲያገለግለኝም እኔ እሻለው አልት በዚአን ግዜ ንጉሱ በአገሩ መዳ ውስጥ ሲዘዋወር ያችን ዛፍ አይቶ አደነቀ ስለሱአም ጠየቀ ቅዱስ ጊዮርጊስ በሱአ ዘንድ የተቀመጠባት የዚያች መበለት የቤቱአ ምሰሶ እንደሆነ ነገሩት ንጉሱም ተቆጣ ቅዱሱንም ከዚያ ወስዶ አስገረፈው በመንኮራኩርም አበራዩት ሞቶም ከከተማ ውጩ ጣሉት ጌታም ከሞት አስነሳው ወደ ነገስታቱም ተመለሰ ንጉሱም አይቶ ደነገጠ ስለህይወቱም አደነቀ ከዚያም በሁአላ ይሸነግለው ዘንድ ጀመረ በመንግስቱ ላይም ሁለተኛ ያደርገው ዘንድ ቃል ገባለት ቅዱስ ጊዮርጊሲም እየዘበተበት ነገ በጠዋት ለአምልክቶችህ መስዋትን አቀርባለው አንተም ህዝብ እንዲሰበሰቡ እዘዝ እኔ ስሰዋ እንዲያዩ አለው:ንጉሱም እውነት የሚሰዋ መስሎት ደስ አለው ወደ ቤተ መንግስቱም እልፊኝ አስገብቶ አሳደረው ለጸሎትም ተነሳ የዳዊትንም መዝሙር አነበበ የዱድያኖስ ሚስቱ እለእስክንድርያ ንግስት ሰምታ ቃሉ ደስ አሰኛት የሚያነበውንም ይተረጉምላት ዘንድ ለመነችው እርሱም እግዚአብሄር አለምን ከፈጠረበት ሰው እስከሆነበት ግዜ የሆነውን ሁሉ ያስረዳት ጀመር ትምህርቱም በልቡአ ተቀርጾ በክብር ባለቤት በጌታችን አመነች በማግስቱም ቅዱስ ጊዮርጊስ ለአማልክት ሲሰዋ ለማየት ሰው ሁሉ እንዲሰበሰብ አዋጅ ነጋሪ ዞረ የበቱአን ሚሰሶ ያበቀለላት ያቺ መበለት ሰምታ እውነት መስሉአት እጅግ እያዘነች ልጁአን ተሸክማ እያለቀሰችም ወጣች ቅዱስ ጊዮርጊስም ባያት ግዜ ፈገግ አለ ልጅሽን በምድር ላይ አኑሪው አላት ከዛም ልጁአን ጠርቶ ወደ አጵሎን ሂድ ወደ እኔም ይመጣ ዘንድ በክብር ባለቤት በጌታዬ ኢየሱስ ስም እዘዘው አለው ያን ግዜ ያ ልጅ ድኖ ቅዱስ ጊዮርጊስ እንደ አዘዘው ወደ ጣዎቱ ቦታ ሄዶ አዛዘው በጣዖቱ ያደረ እርኩስ መንፈስም ከማደሪአው ወቶ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወዳለበት መቶ እኔ ሰውን ሁሉ የማስት እንጂ አምላክ አይደለውም ብሎ በህዝብ ሁሉ ፊት አመነ ቅዱሱም ትውጠው ዘንድ ምድርን አዘዛትና ወዲያውኑ ዋጠችው ጣዖታቱንም ከአገልጋዮቻቸው ጋር አጠፋቸው ንጉሱም ከወገኖቹ ጋር አፈረ:ብስጭት እና ቁታንም እንደተመላ ወደ ንግስት ምስቱ ዘንድ ገባ እሱአም አምላካቸው ጽኑ እና ሃያል ነውና ክርስቲያኖችን አትጥላቸው አላልኩህምን አለችው ይህንንም ከሱአ ሰምቶ በርሱአ ላይ እጂግ ተቆጣ ወደ ክብር ባለበት ክርስቶስ እምነት የከበረ ጊዮርጊስ እንደአስገባት አወቀ ከዚም በሁአላ ከከተማ ውጪ እንዲጎትቱአት እና በመጋዝም እንዲሰነጥኩአት አዘዘ የሰማእትነትንም አክሊልንም በመንግስተ ሰማያት ተቀበለች በዚያን ግዜ ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ስራ ነገስታቱ ሁሉም ደነገጡ ሃፍረት ደግሞ እንዳይጨምርባቸው ከርሱም እንድያርፍ ራሱን በስይፍ ይቆረጥ ዘንድ እንዲጽፍ ንጉስ ዱድያኖስን መከሩት ያን ግዜም የክብር ጊዮርጊስን ራስ በሰይፍ ይቆርጡ ሰንድ አዘዘ ድል አድራጊ ጊዮርጊሲም እጂግ ደስ አለው እሳት ከሰማይ አውርዶ ሰባውን ነገስታት ያቃጥላቸው ዘንድ መከራውም ከክርስቲያን ወገን ጸጥ ይል ዘንድ ጌታችንን ለመነው ወዲያው እሳት ከሰማይ ወርዶ ከነሰራዊታቸው ጋር ሰባውን ነገስታት አቃጠላቸው ከዚም በሁአል የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ተገልጾ ብዙ ቃል ኪዳን ሰጠው በምድር መታሰቢያህን የሚያደርጉ ሁሉ እኔ ሃጥያቱን ሁሉ ደመሣለው በመከራም ውስጥ ሆኖ በባህርም ሆነ በየብስ,ወይም በደዌ በስምህ የሚለምነኝን እኔ ፈጥኜ ከመከራው አድነዋለው ይህንንም ጌታችን ተናግሮ በክብር ወደ ሰማይ ወጣ ከዚ በሁአላ ከ7አመት ተጋድሎ በሁአላ ሚያዚያ 23 ቀን ራሱን ዘንበል አድሪጎ በሰይፍ ቆረጡት በመንግስተ ሰማያት አክሊላትን ተቀበለ ከአገልጋዮቹም የቀሩት ሲጋውን ወስደው በልብስ ጠቀለሉት ወደ ሃገሩም ልዳም ወሰዱት ቤተ ክርስቲያንም ሰርተው በውስጡአ አኖሩት ከርሱም ቁጥር የሌላቸው ብዙዎች ድንቆች ተአምራቶች ተገለጠ ለእግዚአብሄርም ምስጋና ይሁን የቅዱስ ጊዮርጊሲም በረከቱ ረድኤቱ ሃገራችን ኢትዮጵያን እና ህዝቦቹአን ከስጋና ከነፍስ መከራ ይጠብቅልን!!!!!..................

ቅዱስ ሩፋኤል ጦቢት እና ጦቢያስለዚህ እንግዶችን መቀበል አንርሳ፡፡ በዚህም ምክንያት አንዳንዶች ሳያውቁ የመላእክትን እንግድነት ተቀብለዋልና፡፡ ዕብ. 13.1-2 ፡፡በየዓመቱ ጳጉሜ 3 የቅዱስ...
20/07/2016

ቅዱስ ሩፋኤል ጦቢት እና ጦቢያ

ስለዚህ እንግዶችን መቀበል አንርሳ፡፡ በዚህም ምክንያት አንዳንዶች ሳያውቁ የመላእክትን እንግድነት ተቀብለዋልና፡፡ ዕብ. 13.1-2 ፡፡

በየዓመቱ ጳጉሜ 3 የቅዱስ ሩፋኤል መልአክ መታሰቢያ ነው ፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል የጦቢትን ዓይን ያበራና ወለተ ራጉኤልን ተቆራኝቷት ከነበረው ጋኔን ያላቀቃት መሆኑ በመጽሐፈ ጦቢት በስፋት ተገልጿል፡፡

ጦቢት በፋርስ ንጉሥ በስልምናሶር ዘመን የተማረከ ከነገደ ንፍታሌም የተወለደ ጽኑዕ እሥራኤላዊ ነው፡፡ እግዚአብሔር በስልምናሶር ፊት የመወደድን ግርማና ባለሟልነትን ስለ ሰጠው አለቃ አድርጎ ሾሞት ነበር፡፡ ለወገኖቹ ምጽዋት በመስጠት ሕገ ርትዕን በመሥራት የተጋ ሰው ነበር፡፡ ሐና የምትባል ሚስት አግብቶ አንድ ልጅ ወልዷል፡፡ ስልምናሶር ሞቶ ሰናክሬም በነገሠ ጊዜ ከሹመቱ ስለሻረው ደግሞ ወደ ምድያም መሔድ አልቻለም፡፡

ሣራ ወለተ ራጉኤል ከፍተኛ ችግር ደርሶባት ነበር፡፡ ችግሯም ሕፃናት ወልጄ ቤት ንብረት ይዤ እኖራለሁ በማለት ባል አገባች ነገር ግን በዚች ሴት አስማንድዮስ የሚባል ጋኔን አድሮ ያገባችውን ሰው ገደለባት ሌላም ባል ብታገባ ሞተባት እንደዚህ እየሆነ በጠቅላላ ሰባት ድረስ ያሉትን ባሎችን ገደለባት፡፡

የራጉኤል ልጅ ሣራ በዚህ ሁኔታ በኀዘን ተውጣ ስትኖር በነበረበት ጊዜ ጦቢት ሸምግሎ ስለ ነበር ልጁ ጦብያን ጠርቶ በዚህ ዓለም እስካለ ድረስ ሊሠራው የሚገባውን መንፈሳዊ ሥራ እንዲሠራ በጥብቅ ከመከረው በኋላ በመጨረሻ ልጄ እኔ ሳልሞት የኑሮ ጓደኛህን ፈልግ፣ ስትፈልግም ዕወቅበት፣ እኛ የአብርሃም የይስሐቅና የያዕቆብ ዘሮች ነን ስለዚህ ከእነርሱ ወገን የሆነችውን እንድታገባ ከዚህም ሌላ ከገባኤል ዘንድ በአደራ ያስቀመጥኩት ገንዘብ አለና እኔ በሕይወት እያለሁ ብታመጣው የተሻለ ነው አለው፡፡

ጦብያም ያባቱን ምክር ሁሉ በጽሞና ካዳመጠ በኋላ ‹አባባ የነገርከኝን ነገር ሁሉ በተቻለኝ መጠን እፈጽማለሁ ግን ከገባኤል ጋር ስላለው ገንዘብ እንዴት ለማምጣት እችላለሁ? ሀገሩን አላውቀውም› አለው፡፡ በዚህ ጊዜ ነገሩ አሳሳቢ ሆኖ ስላገኘው ጦቢት ልጁ ጦብያን ‹አብሮህ የሚሄድ ሰው እስቲ ፈልግ ምናልባት አብሮ የሚሄድ ጓደኛ ታገኝ ይሆናል ደመወዝም ሰጥተን ቢሆን ካንተ ጋር የሚሄድ አንድ ሰው ግድ ያስፈልግሃልና ሂድ ሰው ፈልግ› አለው፡፡

ጦቢት ስንቃቸውን አስይዞ ጦብያንና ቅዱስ ሩፋኤልን ሸኛቸው

አብሮት የሚሄደው ሰው ለመፈለግም ቢሄድ አንድ መልካም ጐበዝ አገኘ ይኸውም መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡ጦብያ ግን መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል መሆኑን ፈጽሞ አላወቀም ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ጦብያ መልአኩን ሰው መስሎ እንዳገኘው ‹የሜዶን ክፍል ወደ ምትሆነውና ራጌስ ወደ ምትባለው ሀገር ከእኔ ጋር ለመሄድ ትችላለህን የድካምህን ዋጋ የጠየቅኸውን ያህል እሰጥሃለሁ› ሲል ጠየቀው ቅዱስ ሩፋኤልም ‹እሺ ካንተ ጋር ለመሄድ ፈቃኛ ነኝ መንገዱንም ሆነ ሀገሩን በሚገባ አውቀዋለሁ ከገባኤል ቤት ብዙ ጊዜ ኑሬአለሁና› አለው፡፡

ከዚህ በኋላ ጦብያ በል ከአባቴ ጋር ላስተዋውቅህ ብሎ ወደ አባቱ ወስዶ አስተዋወቀው ከእኔ ጋር የሚሄደው ሰው ይህ ነው በማለት ካስተዋወቀው በኋላ ጦቢትም ከወዴት እንደ መጣ ማን ተብሎ እንደሚጠራ ጠየቀው፡፡ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤልም የታላቅ ወንድምህ ወገን ከመሆንም ሌላ ስሜም አዛርያስ ይባላል አለው፡፡ ጦቢ. 5.12 ፡፡ ጦቢትም የወንድሙ ዘመድ መሆኑን ከሰማ በኋላ ‹አንተስ ወንድሜ ነህ በል የልጄ የጦብያን ነገር አደራ ከሀገር ወጥቶ አያውቅምና እንዳይደነግጥ ደኅና አድርገህ እንድትይዝልኝ› ብሎ ስንቃቸውን አስይዞ ሸኛቸው፡፡

አዛርያስ /ቅዱስ ሩፋኤል/ በመንገድ ይመራው ነበር፡፡ በዚህም ቅዱስ ሩፋኤል ‹መራኄ ፍኖት› /መንገድ መሪ/ ይባላል፡፡ እነርሱ ሲሄዱ ውለው ማታ ጤግሮስ ከተባለው ታላቅ ወንዝ ደረሱና ከዚያም ለማደር ወሰኑ፡፡ በዚህ ጊዜ ከድካሙ ጽናት የተነሣ ጦብያ ሊታጠብ ወደ ወንዙ ወረደና ልብሱን አውልቆ መታጠብ ሲጀምር አንድ ዓሣ ሊውጠው ከባሕር ወጣ፡፡ ወዲያውም መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል ጦብያን ያዘው ፤ ዓሣውን እንዳትለቀው አለው ፤ ጦቢያም ከዓሳው ጋር ግብ ግብ ገጥሞ እየጐተተ ወደ የብስ አወጣው ፡፡ከዚህ በኋላ ቅዱስ ሩፋኤል ጦብያን እንዲህ ሲል አዘዘው፡፡ ዓሣውን እረደው ጉበቱንና ሐሞቱን ተጠንቅቀህ ያዘው ሌላውን ግን ጠብሰን እንበላዋለን አለው፡፡

ጦብያም መልአኩ እንዳዘዘው ዓሣውን አርዶ ሐሞቱንና ጉበቱን ያዘ

ጦብያም መልአኩ እንዳዘዘው ዓሣውን አርዶ ሐሞቱንና ጉበቱን ያዘ፣ ሌላውን ሥጋውን ግን ጠብሰው ራታቸው አደረጉት፡፡ ጦብያም ያንን የዓሣውን ጉበትና ሐሞት ለምን እንደሚያገለግል ለመረዳት ‹ይህን ያዘው ያልከኝ ለምንድን ነው?› ሲል ጠየቀው ቅዱስ ሩፋኤልም ጋኔን ያደረበት ሰው ሲገኝ ይህንን ከዕጣን ጋር ቢያጤሱበት ጋኔኑ ይለቃል ሲል መለሰለት፣፡

በዚህ ሁኔታ አንድ ባንድ ሲነጋገሩ ከቆዩ በኋላ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል ጦብያን ‹ዛሬ ከራጉኤል ቤት እናድራለን፡፡ እርሱ ዘመድህ ነው፡፡ የእርሱም ልጅ ሣራ የምትባል ቆንጆ ልጅ አለችው፡፡ እሷን ለሚስትነት ይሰጥህ ዘንድ ለራጉኤል እነግርልሃለሁ› አለው፡፡

ጦብያም ‹ያች ልጅ ከዚህ በፊት ሰባት ሰዎች እንዳገቧትና ሰባቱም ባገቧት ሌሊት ደርቀው /ሞተው/ እንደሚያድሩ ሰምቻለሁ፡፡ ስለዚህ እኔ ላባቴና ለእናቴ አንድ ልጅ ነኝ እርስዋን አግብቼ ከዚህ በፊት እንዳገቧት ሰዎች እኔም የሞትኩ እንደሆነ አባቴንና እናቴን የሚረዳቸው የለም ቢሞቱም የሚቀብራቸው አያገኙምና እፈራለሁ› አለው፡፡ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል ግን ‹አባትህ ከዘመዶችህ ወገን ካልሆኑ በስተቀር ሌላ ሴት እንዳታገባ ሲል የነገረህን ረሳኸውን? በል ሰባት ባሎቿ ሙተውባታል ስለምትለው እኔ መድኃኒቱን አሳይሃለሁ ፤ አይዞህ አትፍራ አትሞትም የዓሣውን ሐሞትና ጉበቱን ለምን መሰለህ ያዘው ያልኩህ ? እንግዲህ ሐሞቱንና ጉበቱን ከዕጣን ጋር ጨምረህ ስታጤስበት በሣራ አድሮ የነበረው አስማንድዮስ የተባለው ጋኔን ወጥቶ ይሄዳል ፈጽሞም ወደ እርሷ በገባህም ጊዜ ሁለታችሁ ይቅር ባይ ወደ ሆነው እግዚአብሔር ጸልዩ እርሷም የተዘጋጀች ናት፡፡ ከእኛ ጋርም ወደ ሀገርህ ይዘናት እንሄዳለን› አለው፡፡ ጦብያምይህንን ቃል በሰማ ጊዜ ደስ አለውና ከእርሷ በስተቀር ሌላ እንዳያገባ በሙሉ አሳቡ ወሰነ፡፡

ከዚህ በኋላ ወደ ራጉኤል ቤት እንደ ደረሱ ሣራ በደስታ ተቀበለቻቸው የሣራ አባትም ጦብያን ገና እንዳለው ሚስቱ አድናን ‹ይህ ልጅ የእኔ ዘመድ ጦቢትን ይመስላል› አላት ከዚያም ጋር አያይዞ ‹ልጆች ከየት ሀገር መጣችሁ?› አላቸው፡፡ እነሱም ‹ከነነዌ ሀገር ነው የመጣን› አሉት፡፡ ‹ከዚያም ሀገር ጦቢት የሚባል ወንድም ነበረኝ ታውቁት ይሆን?› ሲል ጠየቃቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ጦቢያ አባቱን ሲጠራለት ‹እናውቀዋለን፡፡ እኔም ራሴ የጦቢት ልጅ ነኝ› አለው፡፡ ከዚያ በኋላ ራጉኤል ‹የወንድሜ ልጅ ነህን?› ብለ እቅፍ አድርጐ ሳመው፡፡ አድናም ሳመችውና ሁሉም ተያይዘው የናፍቆት ልቅሶ ተላቀሱ፡፡ ከወንድሙ እንደ መጡም ሲገነዘብ በግ አርዶ በጥሩ ሁኔታ ጋበዛቸው፡፡

ራትም ከበሉ በኋላ ጦብያ ቅዱስ ሩፋኤል በመንገድ የነገረውን በልቡ ሲያወጣ ሲያወርድ ስለ ዋለ ቅዱስ ሩፋኤልን ያንን በመንገድ የነገርከኝን አሁን ፈጽምልኝ ሲለው ሰምቶ ስለ ልጅቷ መሆኑን ስለ ገባው ራጉኤል ጦብያን ‹ልጄ ይህች ልጅ ላንተ የምትገባ ናት ሰጥቸሃለሁ አይዞህ አትጠራጠር አሁንም ብላ ጠጣ ለዛሬም ደስ ይበልህ አለውና ሣራ ካለችበት የጫጉላ ቤት አግብተው ዘጉት፡፡ ጦብያም ሣራን በይ እኅቴ ኑሮዋችን እንዲቃናልንና ጋብቻችን እንዲባረክልን አስቀድመን ወደ ፈጣሪያችን ጸሎት እናድርግ› አላትና አብረው ጸሎት ካደረጉ በኋላ ያንን የያዘውንና የዓሣ ጉበትና ሐሞት ከዕጣን ጋር ጨምሮ ቢያጤስበት በሣራ አድሮ ባሎችዋን ይገድልባት የነበረው አስማንድዮስ የተባለው ጋኔን ከሣራ ለቆ ወጥቶ ሄደ ሁለተኛም ሊመለስ አልቻለም፡፡ እነርሱም በሰላምና በጤና አደሩ፡፡ የጦብያንና የሣራን ጋብቻ የባረከ ቅዱስ ሩፋኤል ስለሆነ ‹መልአከ ከብካብ› ይባላል፡፡

ከዚያ በኋላ የጤንነታቸውን ነገር ሲረዱ የሰርጉ ቀን የሚሆን የ14 ቀን በዓል እስኪፈጸም ድረስ ጦብያ ወደ ሀገሬ እሄዳለሁ ብሎ እንዳያውከው በማለት አማለው፡፡

ጦብያ የዓሣውን ሐሞትና ጉበቱን ይዞ ስለ ነበር የአባቱን ዓይን ቀባው ወዲያውም ዓይኖቹ ተከፈቱ

የ14 ቀን በዓለ መርዓ ከተፈጸመ በኋላ ግን ጥሬ ገንዘብና የከብት ስጦታ አድርጐ መርቆ ወደ ሀገሩ ሰደደው፡፡ ወላጆቹ ጦቢትና አድና ግን በመዘግየቱ ልጃችን ምን አግኝቶት ይሆን? እያሉ ለጊዜው ሳያዝኑ አልቀሩም፡፡ ከጥቂት ቀናት በኋላ ሚስቱንና ግመሎቹን ይዞ ሲመጣ በክብርና በደስታ ተቀበሉት፡፡ የጦብያ አባት ጦቢትም ልጅህ መጣ ሲሉት ዓይነ ሥውር ስለ ነበር እርሱን እቀበላለሁ ሲል ስለ ወደቀ ወዲያው ጦብያ የዓሣውን ሐሞትና ጉበቱን ይዞ ስለ ነበር የአባቱን ዓይን ቀባው ወዲያውም ዓይኖቹ ተከፈቱ፡፡

የቅዱሳንን ጸሎት ከሚያሳርጉ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ እኔ ሩፋኤል
ነኝ› ሲል ገለጠላቸው፡፡ እነርሱም ወድቀው የአክብሮት ስግደት ሰገዱለት

በመጨረሻም ከጦብያ ጋር ሄዶ የነበረው መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤልን የድካሙን ዋጋ ገንዘብ ለመስጠት ጠሩት እርሱ

፩፥፫፦ ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውንተዋጉት፤ ራእ ፲፪፥፯ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ በደሴተፍጥሞ በግዞት ሳለ በተመለከተው ራእይሃላፊያትና መጻእያት ተገልጠውለትስለነበረ፥ «በሰማይም ሰልፍ (ጦርነት...
19/07/2016

፩፥፫፦ ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውንተዋጉት፤ ራእ ፲፪፥፯

ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ በደሴተፍጥሞ በግዞት ሳለ በተመለከተው ራእይሃላፊያትና መጻእያት ተገልጠውለትስለነበረ፥ «በሰማይም ሰልፍ (ጦርነት)ሆነ፤» ካለ በኋላ «ሚካኤልና መላእክቱምዘንዶውን ተዋጉት፥ ዘንዶውም ከነሠራዊቱተዋጋቸው። አልቻላቸውምም፥ ከዚያምበኋላ በሰማይ ቦታ አልተገኘላቸውም።ዓለሙን ሁሉ የሚያስተው ዲያቢሎስናሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱምየቀደመው እባብ ተጣለ፥ ወደ ምድርምተጣለ፥ መላእክቱም (የዘንዶው ሠራዊት)ከእርሱ ጋር ተጣሉ፤» ብሏል። ራእ ፲፪፥፯-፱።

ታሪክ፦ ሰይጣን በክህደቱ አጥቶትእንጂ ክብርም ፥ ኃይልም፥ሥልጣንምነበረው። በአሥሩ የመላእክት ከተሞችበተሾሙ አሥርየመላእክት አለቆች ላይየአለቃ አለቃ ነበረ። የተፈጠረውየመላእክትአለቃ ሆኖ ነው። ይኽንንምቀሌምንጦስ ተናግሮታል።እግዚአብሔርመላእክትን በነገድ መቶ ፥በከተማ አሥር አድርጐፈጥሮተሰወራቸው። ይህም ካልፈለጉኝአልገኝም ፥ ባሕርዬምአይመረመርምሲላቸው ነው። ወዲያው፦ «እኛ ምንድርነን? ከየትመጣን ? ማንስ ፈጠረን? በራስበራሳችን ተፈጠርን ? ወይስ ከሌላነው?»አሉ። ሳጥናኤል ከበታቹ እንዲህ ሲሉሰማ። ከበላዩ ደግሞ«ፈጠርኳችሁ፤»የሚል አጣ። በቦታው ከሁሉ በላይ አድርጎፈጥሮትነበርና «እኔ ፈጠርሁ፤» ብሎ አሰበ፥ አስቦም አልቀረ «እኔፈጠርኋችሁ፤» አለ።ይኽን ሰምተው «ሰጊድ ይገባዋል፤» ያሉአሉ።«እኛም እንደ እርሱ ነን፤» ያሉም አሉ።« አምላክ ነኝ ያለስ ከእርሱበቀር ሌላየለምና ፥ ይሆንን?» ብለው የተጠራጠሩአሉ። ሀልዎተእግዚአብሔርን ሳይመረምሩየቀሩም አሉ። እኲሌቶቹ ግን ፦«በምንፈጠርኋችሁ ይለናል፥ በቦታ ከበላይበመሆን ፈጠርኋችሁ እንዳይለን፥ እኛየበታቾቻችንን መቼ ፈጠርናቸውና ነው?።በዚያውስ ላይምቀኞቹ አይደለንም፤በእውነት ፈጣሪ ከሆነ ፈጥሮ ያሳየን ።»ብለው፦«ፈጥረህ አሳየን፤» አሉት።እርሱም እፈጥራለሁ ብሎ ፥ እጁንወደእሳት ቢጨምር ፈጀውና « ዋይ» አለ።በዚህን ጊዜ «በአፍአያለውን(የሚነገረውንና እና የሚሠራውንብቻ የሚያውቅ) አምላክ ቢሆን ነውእንጂውሳጣዊውን (ልብ ያሰበውን የሚያውቅ)አምላክ ቢሆን ኖሮ ገናሳስበው ለምንአሰብከው ፥ ባለኝ ነበር ፤» አለ። ወዲያውልቡንተሰማውና «ዋይ» አለ።እግዚአብሔር ግን ፈወሰው።ይህንንምማድረጉ ንስሐ ቢገባእንደሚምረው ሲነግረው ነበር።

ከዚህ በኋላ በመላእክት ሽብርቢጸናባቸው፦ መልአከ ሰላምቅዱስገብርኤል፦ «ንቁም በበህላዌነ እስከንረክቦ ለአምላክነ ፤አምላካችንንእስክናገኘው ድረስ በየህልውናችን ጸንተንእንቁም ፤»በማለት አጽንቷቸዋል። ይህምበጎ አርበኛ ጦር በተፈታ ጊዜ«አይዞህባለህበት ጽና፤» ብሎእንደሚያጸናው ማለት ነው።« ወበእንተዝደለዎይፁር ዜናሃ ለማርያም ፤ በዚህምክንያት የድንግል ማርያምን ዜናያደርስ ፥ብሥራቷን ይናገር ዘንድ ተገባው ፤ »እንዲል ፥ ብሥራትተሰጥቶታል።«በስድስተኛው ወር (አምስት ሺህ አምስትመቶ ዘመንሲፈጸም ፥ ስድስተኛው ሺህደግሞ ሲጀምር) መልአኩ ገብርኤል . . . ወደ አንዲት ድንግል ተላከ» ይላል። ሉቃ፩፥፳፮።

እግዚአብሔርም ጨርሶ ሳያስታቸው ብሎእርሱ (ሳጥናኤል)በሌለበት በኲልበምሥራቅ ባሕረ ብርሃንን አፍስሶላቸዋል።ከዚህምጋር ስሙ የተጻፈበት መጽሔተብርሃን ቢሰጣቸውአንድነቱሦስትነቱ(ምሥጢረ ሥላሴ)ተገልጦላቸው « አሐዱ አብ ቅዱስ ፥አሐዱወልድ ቅዱስ ፥ አሐዱ ውእቱ መንፈስቅዱስ፤» ብለውአመስግነውታል። እርሱንግን ባደረው ጨለማ ጠቅልሎበዕለተእሑድ ከኢየሩሳሌም ሰማያዊትወደ ኢዮር አውርዶታል። ከሰባቱሰማያትሦስቱ ፦ ኢዮር ፥ራማ፥ ኤረር የመላእክትናቸው።በውስጣቸውም አስር የመላእክትከተሞች አሉ። በእነርሱም ላይአስርአለቆች ተሹመዋል። እግዚአብሔርሳጥናኤል በሌለበት በኲል ባሕረብርሃንንያፈሰሰላቸው «እኔ ፈጠርኩ » እንዳይልነው።

14/07/2016

Zemari Mindaye Berhanu, Selassen Amesginu

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ።እንኳን ለዓመታዊው የቅድስት ሥላሤ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን
14/07/2016

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ።

እንኳን ለዓመታዊው የቅድስት ሥላሤ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን

Adresse

Wendel Dietrich Str 74
Munich
80634

Telefon

+4915213270076

Webseite

Benachrichtigungen

Lassen Sie sich von uns eine E-Mail senden und seien Sie der erste der Neuigkeiten und Aktionen von Ethiopian Orthodox Tewahedo Kidus Amanuel GermanyMunich erfährt. Ihre E-Mail-Adresse wird nicht für andere Zwecke verwendet und Sie können sich jederzeit abmelden.

Teilen