Aba Gebrehiwot

Aba Gebrehiwot Addis Abeba

17/07/2017
06/04/2017

ማቴዎስ 7 እንዳይፈረድባችሁ አትፍረዱ፤ በምትፈርዱበት ፍርድ ይፈረድባችኋልና፥ በምትሰፍሩበትም መስፈሪያ ይሰፈርባችኋል።በወንድምህም ዓይን ያለውን ጉድፍ ስለምን ታያለህ፥ በዓይንህ ግን ያለውን ምሰሶ ስለ ምን አትመለከትም? ወይም ወንድምህን፦ ከዓይንህ ...

ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር እንኳን ለጾመ ፍልሰታ ለማርያም በሰላምና በጤና አደረሳችሁ።ጾመ ፍልሰታ ከልሂቅ እስከ ደቂቅ ኦርቶዶክሳውያን የእመቤታችን ወዳጆች ሁሉ የእመቤታችን የድንግል ማርያምን...
21/08/2016

ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር
እንኳን ለጾመ ፍልሰታ ለማርያም በሰላምና በጤና አደረሳችሁ።
ጾመ ፍልሰታ ከልሂቅ እስከ ደቂቅ ኦርቶዶክሳውያን የእመቤታችን ወዳጆች ሁሉ የእመቤታችን የድንግል ማርያምን በረከት ለማግኘት በጉጉት የሚጠብቋት፣ሕጻናት ሳይቀሩ ወደ ቤተክርስቲያን ለመሄድ የሚቸኩሉባት፣ገዳማውያን አበው በዓታቸውን ዘግተው ከሰው ተለይተው ከእግዚአብሔር ጋር ብቻ በጸሎት የሚነጋገሩባት፣ ካህናቱ ቀን ከሌሊት በጸሎት የሚተጉባት፣ ብዙ ሰዎች በዓለም ያለውን ነገር ሁሉ እርግፍ አድርገው ትተው ወደ ገዳማት በመሄድ ከእግዚአብሔር ጋር የሚገናኙባት የተመረጠችና ፍጹም በረከት የምታስገኝ የጾም ጊዜ ናት። ምድራዊ ያይደለ ሰማያዊ ፣ሥጋዊ ያይደለ መንፈሳዊ፣ አፍአዊ ያይደለ ውሳጣዊ የሆነ እውነተኛውን ምግብ እውነተኛውን መጠጥ ያስገኘችልን እመቤታችንን በፍጹም መንፈሳዊ ፍቅር የምናስብባት፣ሐዋርያት ለእመቤታችን ያላቸውን ፍጹም ፍቅር በጾም የገልጹባት ናት። / ኦ ማዕዶት ዘበኃቤኪ ዐደዉ አበው ቀደምት እሞት ውስተ ሕይወት/ የቀደሙት አበው ከሞት ወደ ሕይወት የተሸጋገሩብሽ መሸጋገሪያ ድልድይ ተብላ የተመሰገንች ምልዕተ ጸጋ ምልዕተ ክብር፣ ነቢያት ትንቢት የተናገሩላት፣ ምሳሌ የመሰሉላት፣ የነቢያት ትንቢታቸው፣ ሐዋርያት ወንጌልን የሰበኩለትን ጌታ የወለደችላቸው የሐዋርያት ሞገሳቸው፣ ስደትን ለሰማዕታት ያስተማረች የሰማዕታት እናታቸው፣ መላእክትን በንጽሕና በቅድስና የምትመስላቸው የመላእክት እኅታቸው፣ ተብላ በቅዱሳን አንደበት የተመሰገነች እመቤታችን በድንግልና በቅድስና የወለደችው የልጅዋን ፍጹም በረከት ይዛ የተገለጸችበት ጊዜ ነው። ጌታም የሐዋርያትን ጾምና ጸሎት ተቀብሎ ለደቀ መዛሙርቱ እመቤታችንን በክብር የገለጸበት ናት። ጌታ እነኋት እናትህ ብሎ በቀራንዮ በመስቀሉ ስር ለዮሐንስ ካስረከበ ጊዜ ጀምሮ አብረው ሲኖሩ በጥር ፳፩ እሑድ ቀን በ፷፬ ዓመቷ አረፈች። ደቀ መዛሙርቱም ጌታ ካረገ በኋላ በምድር ላይ በሥጋ ከነሱ ጋር የቀረች እናት ሆና የተሰጠቻቸው ናትና ስትለያቸው አዝነው አልቅሰው ሊቀብሩ ወደ ጌቴሴማኒ ይዘው ሲሄዱ ልጅዋን በግፍ የገደሉት አይሁድ ዛሬም ከምቀኝነት አያርፉምና ነገ እንደ ልጅዋ ተነሳች አረገች እያሉ ያውኩናል ብለው ደቀ መዛሙርቱን አሳደዷቸው ። በዚህ ጊዜ በሐዘን ልባቸው ተነካ ሳያስቡት በክብር ሳይቀብሯት ተበታተኑ። የደርሰችበትን ሳያውቁ ቀሩ ከዮሐንስ በስተቀር። ከዚህ የተነሳ በነሐሴ ፩ ቀን ሱባኤ ጀመሩ ጌታም በ፲፬ኛው ቀን አምጥቶ ሰጣቸው በክብር ቀበሯት ። በሶስተኛው ቀን ተነስታ አርጋለች። የአይሁድ ጫጫታ ጩኸትና ምቀኝነት እመቤታችንን በመቃብር ሊያስቀር አልቻለም በ፩ኛ ቆሮ ፲፭፥፶፭ ላይ ሞት ሆይ መውጊያህ የት አለ እንዲል ሞትን የገደለው ልጅዋ እርሷንም በክብር አስነስቷል። ዛሬም ይህንን ፍጹም የበረከት ጾም እንድናጣ በረከታችንን በመቃብር ሊያስቀሩ የሚፈልጉ ብዙ የተረፈ አይሁድ ጫጫታዎች በበዙበት ዓለም የምንኖር ክርስቲያኖች ከእግዚአብሔር ጋር ፍጹም ኅብረት እንዲኖረን፣ የእመቤታችንን በረከት እንድንቀበል፣ በመብል ሳይሆን በጾም በጸሎት፣ በምሥጋና በውዳሴ በቅዳሴ የእግዚአብሔርን ይቅርታና ምሕረት እያሰብን በአግባቡ ጾመን የበረከቱ ተከፋዮች ልንሆን ይገባል። ጾማችንን የበረከት፣ የሰላም፣ የይቅርታ፣ የምሕረት ጾም ያድርግልን። በሰላም አስጀምሮ በሰላም ያስፈጽመን። እመቤታችን ድንግል ማርያም በምልጃዋ አትለየን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር።
በአባ ገ/ሕይወት

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ዱ አምላክ አሜን።[♦] [♦]ድንግል [፪] ወላዲተ ቃል [፪]አሟሟትሽ በጥር ነሀሴ መቃብር ---------ድንግል ያንቺስ ለብቻ ነው ትንሳኤሽ ሲነገር ----...
21/08/2016

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ዱ አምላክ አሜን።

[♦] [♦]

ድንግል [፪] ወላዲተ ቃል [፪]

አሟሟትሽ በጥር ነሀሴ መቃብር ---------ድንግል
ያንቺስ ለብቻ ነው ትንሳኤሽ ሲነገር ------ድንግል
ስጋሽ በምድር ላይ የታል እንደፍጡር ----ድንግል
አርጓል ወደ ሰማይ ከክርስቶስ መንበር-- ድንግል

ስጋሽን ሲያሳርጉ መላዕክት ከሰማይ --- ድንግል
ቶማስ በደመና ሲመጣ መንገድ ላይ --- ድንግል
መግነዝ ተረከበ ከሀዋርያት ሊያሳይ ---- ድንግል

ትንሣኤን ሽተው ግራ ሲገባቸው------ ድንግል
ሀዋርያት ጾመው ተገለጥሽላቸው -----ድንግል
ተቀብራ አልቀረችም በምድር ከደጇ --ድንግል
ወደላ አረገች እርሷም እንደ ልጇ-------ድንግል

ለማየት ሲጓጉ የድንግልን ትንሣኤ---- ድንግል
እርገቷን አወቁ በብዙ ሱባዔ ---------- ድንግል
እኛም እንፀልይ ደጃችንን እንዝጋ ----- ድንግል
ከወላዲት አምላክ እንድናገኝ ዋጋ -----ድንግል

ብሒለ አበው ክፍል ፬§  ‹‹እግዚአብሔር ሆይ አፈርና ትቢያ ሆኜ ሳለ ጻድቅ አድርገው ከሚቆጥሩኝ ሰዎች አድነኝ››     አባ እንጦንስ§  ‹‹ፍጡራንን መርምሮ ማወቅ ካልተቻልን ሁሉን የፈጠረ ...
21/08/2016

ብሒለ አበው ክፍል ፬

§ ‹‹እግዚአብሔር ሆይ አፈርና ትቢያ ሆኜ ሳለ ጻድቅ አድርገው ከሚቆጥሩኝ ሰዎች አድነኝ››
አባ እንጦንስ

§ ‹‹ፍጡራንን መርምሮ ማወቅ ካልተቻልን ሁሉን የፈጠረ እርሱን መርምሮ ማወቅ እንደምን ይቻልናል››
ቅዱስ አትናቴዎስ

§ ‹‹ወርቅ በእሳት እንደሚፈተን ሁሉ የክርስቶስንም ፀጋና ክብር ሳይፈተኑ ማግኘት አይቻልም የዚህ ዓለም ፈተናና እሳት ቶሎ ያልፋል ይጠፋል ኃጢያተኞች የሚገቡበት የገሀነም እሳት ግን ለዘላለም እንደ ነደደ ይኖራል››
ቅዱስ ሚናስ

§ ‹‹በማንም ላይ ክፈትን አትስሩ አትፍርዱ ይህንን ከጠበቃችሁ ርስቱን ትወርሳላችሁና››
ታላቁ አባ መቃርስ

§ ‹‹ብዙ ጊዜ ብዙ እናገራለሁ በመናገሬም አዝናልሁ በዝምታዬ ግን ያዘንኩበት ጊዜ የለም››
ቅዱስ አርሳንዮስ

§ ‹‹ቤተክርስትያን መጠጊያችን ነች ቤተክርስትያን የኖኅ መርክብ ነች በውስጧ እንጠለላልን ከውጭዋ ግን ማዕበልና ቀላያት ተከፍተዋል››

ቅዱስ እንድርያስ

§ ‹‹ልባችንን ጠፊና በስባሽ ከኾነው ከምድራዊው ምኞት አርቀን ከበደል በንስሐ ነጹሕ ካደረግነው በጸጋ መንፈስቅዱስ የተሞላን እንሆናለን››
አባ አብርሃም መፍቀሬ ነዳያን

§ ‹‹ስጋዊ ፍላጎቶችን ማሸነፍ ለአክሊለ ህይወት የሚያበቃ ሰማዕትነት ነው››
ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ

§ ‹‹የቤተክርስቲያን ህይወት በመስቀል ላይ ስለሆነ ፈተና ይበዛበታል ስለዚህ ከግል ህይወታችሁ ይልቅ የቤተክርስቲያናችሁን አቋም አጠንክሩ››
ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ

§ ‹‹ከመኝታህ በፊት የምታደርገውን ፀሎት ትተህ እንድትተኛ መንፈስህ ሲገፋፋህ እሺ ብለህ አትቀበለው፡፡ እንዲያውም መዝሙረ ዳዊትን ጨምርና ሌሊቱን በሙሉ ስትፀልይ እደር››
ቅዱስ ይስሐቅ ሶርያዊ

§ ‹‹ኃጥያታችንን እኛ እያሰብን የምንፀፀት ከሆነ እግዚአብሔር ይረሳልናል ኃጥያታችንን እኛ እረስትን የምንፅናና ከሆነ እግዚአብሔር ያስብብናል››

«መልካም እውቀት ሞገስን ይሰጣል።»ምሳ፡13፥15(የእውነት ምስክርነት) ሊቀ ልሳናትአብርሀም ዲበኩሉ ።ሊ/ብ አባ ገ/ሕይወት ፍሥሐበኦሮሚያ ክልል በጀልዱ ወረዳ ልዩ ስሙ ቢቾ ተብሎ በሚጠራው አ...
21/08/2016

«መልካም እውቀት ሞገስን ይሰጣል።»
ምሳ፡13፥15
(የእውነት ምስክርነት) ሊቀ ልሳናትአብርሀም ዲበኩሉ ።
ሊ/ብ አባ ገ/ሕይወት ፍሥሐ
በኦሮሚያ ክልል በጀልዱ ወረዳ ልዩ ስሙ ቢቾ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የተወለዱ ሲሆን በአሁን ሰአት «በመልካም ዕውቀታቸው» በእግዚአብሔርና በብፁአን አባቶች ዘንድ ለኤጲስ ቆጶስነት ምርጫ ሞገስን ካገኙ ዕጩ አባቶች መካከል አንዱ ናቸው።
ሊ/ብ አባ ገ/ሕይወት ፍሥሐ በጀልዱ ወረዳ ቢቾ ተብሎ በሚጠራው መንደር ተወልደው የአባታቸው የመምሬ ፍሥሐን የክህነት አገልግሎት ፈለግ በመከተል እግዚአብሔርን እንደ አባታቸው በክህነት ተለይተው ለማገልገል ካላቸው ጽኑ ፍላጎት የተነሳ የእናት አባታቸውን ፍቅር እንኳን ሳያጣጥሙ ገና በለጋነት የልጅነት እድሜአቸው ነበር ወደ ገዳም ምናኔን የጀመሩት።
አባ ገ/ሕይወት በኢትዮጵያ ውስጥ አሉ በሚባሉ ታላላቅ ገዳማት በመዘዋወር ከታላላቅ መምህራን እግር ስር ቁጭ ብለው አቋቋምን፣ቅኔን፣ቅዳሴን፣ሌሎችንም በብቃት አስመስክረው የተማሩ ከመሆኑም ሌላ በሰዋስወ ብርሐን ቅ/ጳውሎስ መ/ኮሌጅ ለ5 አመት የመጻሕፍትን ትርጓሜ ከዚያም በቅ/ሥላሴ መ/ኮሌጅ በቲዎሎጂ ዲግሪአቸውን በመያዝ በአለማዊውም በብቃት ደረጃ እውቀት ያላቸው ሲሆን ጀርመንኛ እና ሌሎችንም የውጪ ሀገር ቋንቋ በመማር ከራስ ፀጉር እስከ እግር ጥፍራቸው በእውቀት የተሞሉ ታላቅ የቤተ ክርስቲያናችን ብርቅዪ አባት ሲሆኑ በስራ ካሳለፏቸው ዘመናት ይልቅ አብዛኞቹን ዘመናት ያሳለፉት በትምህርት ነው ቢባል በማስረጃ የተደገፈ ስለሆነ ምስክርነቱ እውነት ነው።
አባ ገ/ሕይወት በአዲስ አበባ በብዙ አድባራት በአስተዳዳሪነት ያገለገሉ ሲሆን በአገልግሎት ዘመናቸው ምንም አይነት የዘረኝነት መንፈስ የሌለባቸው ቅ/ጴጥሮስ «ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባናል» ባለው ቃል መሰረት ወገናዊነታቸውን ለቤ/ክ ብቻ በማድረግ በዚህም አገልግሎታቸው ከአንዱ ደብር ወደ ሌላ ደብር ሲዛወሩ ለምን ይሔዱብናል በማለት በየጊዜው ካህናት፣ዲያቆናት፣የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች፣ምዕመናን በጋራ በመሆን የሚያቀርቡት አቤቱታ በቂ ምስክር ነው።
አባ ገ/ሕይወት በቤ/ክ ሌሊት የደወል ድምጽ ሲሰማ ተነስተው በመግባት በስመአብ ብለው ጀምረው የማህሌቱ መሪ በመሆን ማህሌት ቆመው፣ቅዳሴ ቀድሰው፣በአውደመህረት ትምህርተ ወንጌል ሰጥተው፣ልብን በሚመስጠው ድምጻቸው ዘምረው ደከመኝ ሰለቸኝ የማይሉ ሲሆን ይሔ አገልግሎታቸው ከሀገር አልፎ በውጪውም አለም በመታወቁ በውጪ ያሉ ምዕመናንም ወደ እኛም ይምጡልን የሚል አቤቱታ ለቤተክህነት በማቅረባቸው ምክንያት በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ መልካም ፈቃድ በአሁን ሰአት በጀርመን የሙኒክ ደ/ብ/ት ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ አስተዳዳሪ ሆነው በሀገር ውስጥ የነበረውን አገልግሎት በምድረ አውሮፓም በብቃት እያከናወኑ ይገኛሉ።በጽሑፌ መግቢያ ላይ ያነሳሁት ርዕስ«መልካም ዕውቀት ሞገስን ይሰጣል።»እንዲል አባ ገ/ሕይወትም በመልካም ዕውቀታቸው በእግዚአብሔር ዘንድ አንደ አብርሐም፣ሙሴ፣ዮሴፍ…ግርማ ሞገስን ስላገኙ በአሁን ሰዓት ደግሞ ቅዱስ ሲኖዶስ ኤጲስቆጶሳትን ለመሾም ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት በአስመራጭ ኮሚቴው በአበው አባቶች ዘንድ ግርማ ሞገስን በማግኘት ለእጩነት ቀርበዋል።
በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው ቀዱስ ሲኖዶስ እንዲሁም አበው አባቶች ሊ/ብ አባ ገ/ሕይወት ፍሥሐ ኤጲስ ቆጶስ ሆነው ቢሾሙ እኔ በትንሽ አንደበቴ ከገለጽኩት በላይ ለቤተክርስቲያናችን ለሃይማኖታችን ከፍተኛ ጥቅም የሚሰጡ አባት መሆናቸውን እመሰክራለሁ።
«መልካም ዕውቀት ሞገስን ይሰጣል።»

Adresse

Munich
80992

Telefon

+49152137065500

Webseite

Benachrichtigungen

Lassen Sie sich von uns eine E-Mail senden und seien Sie der erste der Neuigkeiten und Aktionen von Aba Gebrehiwot erfährt. Ihre E-Mail-Adresse wird nicht für andere Zwecke verwendet und Sie können sich jederzeit abmelden.

Teilen