Kassel Debre Qeraneyo Medhane-Alem EOTC

Kassel Debre Qeraneyo Medhane-Alem EOTC Kontaktinformationen, Karte und Wegbeschreibungen, Kontaktformulare, Öffnungszeiten, Dienstleistungen, Bewertungen, Fotos, Videos und Ankündigungen von Kassel Debre Qeraneyo Medhane-Alem EOTC, Religiöse Gemeinschaft, Kassel.

17/07/2015
17/07/2015

ቀን/Dat._ ፳፱ /፲/ ፳፻፯ ዓ/ም
“ንሥኡ ትምህርተ እምብሩር ወአእምሮ እምወርቅ እስመ ትኄይስ ጥበብ እምዕንቊ ክቡር ዘብዙኅ ሤጡ“
“ከብር ይልቅ ትምህርትን ከወርቅም ይልቅ ዕውቀትን ያዙ
ጥበብ ዋጋው ብዙ ከሆነ ዕንቊ ትበልጣለችና“
ምሳ ፰፥፲
የትምህርተ ወንጌል ልዩ ጉባዔ
የካስል ደብረ ቀራንዮ መድኃኔዓለም ቤ/ክ ከወርኃዊ እና ዓመታዊ በዓላት መደበኛ አገልግሎት በተጨማሪ ልዩ የትምህርተ ወንጌል መርሐ ግብር ለሁለተኛ ጊዜ አዘጋጅቷል።
ጉባዔው ቅዳሜ ሐምሌ ፳፭ ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ከቀኑ 3፡00 /15፡00/ ጀምሮ በደብሩ የሚካሄድ ሲሆን ከዓመት በፊት በተሳካ ሁኔታ እንደተካሄደው የመጀመሪያው ዓመታዊ ልዩ የትምህርተ ወንጌል ጉባዔ ከተጋባዥ መምህራን፣ ከዘማርያንና ከሰ/ት/ቤት መዘምራን ዐቢይ ተሳትፎ ጋር ትምህርተ ወንጌል፣ መዝሙርና የጥያቄ መልስ መርሐ ግብሮች ያለው ሁኖ ተዘጋጅቷል።
በማግሥቱ እሑድ ሐምሌ ፳፮ ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ከሰንበተ ክርስቲያንነቱ በተጨማሪ የመድኃኔዓለም ወርኃዊ እንዲሁም የጻድቁ የቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በመሆኑ መደበኛው መንፈሳዊ አገልግሎት በአግባቡ ከተከነዋወነ በኋላ ጉባዔው እስከ ቀኑ 8፡00 /14፡00/ ድረስ የሚቀጥል ሲሆን ከቀኑ 8፡00 /14፡00/ ሰዓት ላይ የጉባዔው ፍጻሜ ይሆናል።
በመሆኑም በየትኛውም አካባቢ የምትኖሩ የቤተ ክርስቲያን ልጆች በሙሉ በደብራችን ተገኝታችሁ ጉባዔውን በመሳተፍ በረከትም መንፈሳዊ ዕውቀትና የመንፈስ ስንቅም ትካፈሉ ዘንድ መንፈሳዊ ጥሪያችንን በፍቅርና በአክብሮት እናስተላልፋለን።
ከመንፈሳዊ ሰላምታ ጋር
የደብሩ ሰ/ጉ ጽ/ቤት
የቤ/ክኑ አድራሻ ፡ -
Schwanenweg 15
34117 Kassel

01/06/2015
በደብራችን በደብረ ቀራንዮ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ከ6፡30 እስከ 10፡00 ሰዓት ድረስ የጸሎተ ፍትሐት እና የምሕላ ጸሎት ስነ ሥርዓት ተከናውኗል። በጸሎት መርሐ ግብሩ ላይ ትምህርት እ...
25/04/2015

በደብራችን በደብረ ቀራንዮ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ከ6፡30 እስከ 10፡00 ሰዓት ድረስ የጸሎተ ፍትሐት እና የምሕላ ጸሎት ስነ ሥርዓት ተከናውኗል። በጸሎት መርሐ ግብሩ ላይ ትምህርት እና መዝሙር ቀርቧል። ከአኅት ቤተ ክርስቲያን መካከል ከኤርትራ ቤተ ክርስቲያን ተወካይም የኀዘን መልእክት ተላልፏል። አምላከ ሰማዕታት በሞተ ሥጋ ከተለዩን ወንድሞቻችን በረከት ይክፈለን።

22/04/2015

በሊብያ ሰማዕትነትን ለተቀበሉት ወገኖቻችን ቅዳሜ ሚያዚያ 17 ቀን 2007 ዓ/ም ነግህ ከጠዋቱ 6፡30 ጀምሮ የጸሎተ ፍትሐት ስነ ሥርዓት በደብራችን በካስል ደብረ ቀራንዮ መድኃኔዓለም ቤ/ክ ስለሚካሄድ ሕይወታቸው አደጋ ላይ የሆኑትን እግዚአብሔር አምላክ ይታደግ ዘንድ ከተሰውትም ወንድሞቻችን በረከትን ያድለን ዘንድ በኅብረት ጸሎት እንድናደረስ በካስልና በአካባቢው ለምትገኙ ምእመናን ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። የደ/ሰ/ጉ/ጽ/ቤት

መልካም ዜና ከበርሊን ደብረ ገነት ቅዱስ አማኑኤል ቤ/ክበቅድሚያ ሰላመ እግዚአብሔር እንዲበዛላችሁ እየተመኘሁ ፈቃደ ቅዱስ አማኑኤል ሆነና ብዙዎቻችሁ በገንዘባችሁና በሐሰባችሁ ከፍተኛ አስተዋጽ...
25/01/2015

መልካም ዜና ከበርሊን ደብረ ገነት ቅዱስ አማኑኤል ቤ/ክ

በቅድሚያ ሰላመ እግዚአብሔር እንዲበዛላችሁ እየተመኘሁ ፈቃደ ቅዱስ አማኑኤል ሆነና ብዙዎቻችሁ በገንዘባችሁና በሐሰባችሁ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያደረጋችሁበትና እያደረጋችሁ የላችሁለት የሕንፃ ቤተ ግርስቲያን ግዥ ጉዳይ ዳር መድረሱን አመልካች የሆነው የግዥ ውል ትናንት ጥር 14ቀን 2007 ዓ.ም /22.01.2015/ በሕጋዊ ጠበቃ ፊት መፈረሙን ሳበስር ከፍተኛ ደስታ እየተሰማኝ ነው።

የሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑ ርክክብም በመጭዎቹ ሳምንታት ውስጥ ይከናወናል ።
ለዚህ ላበቃን ለልዑለ ባህርይ አምላክ ምስጋና ይድረሰው።
ይህ የሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ግዥ ከዚህ ደረጃ እንዲደርስ ድጋፍ ላደረጋችሁና እያደረጋችሁ ላላችሁ ሁሉ ቅዱስ አማኑኤል በረከቱን አብዝቶ እንዲሰጣችሁ ከልብ እመኛለሁ።

ማሳሰቢያ
ምንም እንኳን የጥሪው ደብዳቤ ወደፊት የሚላክ ቢሆንም ባለፈው የቅዱስ አማኑኤል በዓል ላይ እንደተገለጠው ቅዳሴ ቤተ ክርስቲያኑ የሚከበረው ግንቦት 22እና 23 2007 ዓ.ም /30-31.05.2015/ ስለሆነ ከአሁኑ ቀናቱን ለዚሁ በዓል እንድትይዙልን ለማሳስብ እወዳለሁ።

መልአከ ገነት አባ ብርሃነ መስቀል ተድላ
https://www.youtube.com/watch?v=Fptouv4EI4c

የቅዱስ፡አማኑኤል፡ቤተ-ክርስቲያን፡ልዑካን፡ጉ ብ ኝ ት የላንክቪትዙን፡ካቶሊካዊት፡ቤ/ክ በጎበኙበት፡ወቅት

25/01/2015

Kassel Debre Qeranyo Medhane-Alem Ethiopian Orthodox Tewahedo Church in Germany

የከተራና የጥምቀት በዓል ዘንድሮ ለሦስተኛ ጊዜ በደብራችን በካስል ደብረ ቀራንዮ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ቅዳሜ ጥር 9 እና 10 ቀን 2007 ዓ/ም (17- 18/2015) ይከበራል።
14/01/2015

የከተራና የጥምቀት በዓል ዘንድሮ ለሦስተኛ ጊዜ በደብራችን በካስል ደብረ ቀራንዮ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ቅዳሜ ጥር 9 እና 10 ቀን 2007 ዓ/ም (17- 18/2015) ይከበራል።

Adresse

Kassel

Benachrichtigungen

Lassen Sie sich von uns eine E-Mail senden und seien Sie der erste der Neuigkeiten und Aktionen von Kassel Debre Qeraneyo Medhane-Alem EOTC erfährt. Ihre E-Mail-Adresse wird nicht für andere Zwecke verwendet und Sie können sich jederzeit abmelden.

Die Kultstätte Kontaktieren

Nachricht an Kassel Debre Qeraneyo Medhane-Alem EOTC senden:

Teilen