Äthiopisch-orthodox Tewahdo Kirche Tserha Tsion Kidist Mariam Frankfurt

Äthiopisch-orthodox Tewahdo Kirche Tserha Tsion Kidist Mariam Frankfurt Kontaktinformationen, Karte und Wegbeschreibungen, Kontaktformulare, Öffnungszeiten, Dienstleistungen, Bewertungen, Fotos, Videos und Ankündigungen von Äthiopisch-orthodox Tewahdo Kirche Tserha Tsion Kidist Mariam Frankfurt, Kirche, Sebastian-Rinz-Straße 19 and 22, Frankfurt am Main, Frankfurt.

ደብረ ምጥማቅ እንኳን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በደብረ ምጥማቅ ለተገለጸችበት ክብረ በዓል መታሰቢያ በሰላም አደረሰን❤ ግብጽ በምትገኘው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም በተ...
29/05/2026

ደብረ ምጥማቅ

እንኳን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በደብረ ምጥማቅ ለተገለጸችበት ክብረ በዓል መታሰቢያ በሰላም አደረሰን

❤ ግብጽ በምትገኘው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም በተሰራችው ደብረ ምጥማቅ ቤተክርስቲያን ጉልሃት ላይ የታየችበት መታሰቢያ

❤ ከግንቦት ፳፩ እስከ ፳፭ ቀናት በተከታታይ በመገለጧ ሕዝበ ክርስቲያን በዓሉን ያከብራል

❤ በእነዚህ ቀናት በርፍራው የተገኙ ምዕመናን የድንግል ማርያም ን በረከት ተካፋይ ሆነዋል

በእኛም ላይ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃና በረከት ይደርብን።

የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ፥ እንደ ሰዶም በሆንነ እንደ ገሞራም በመሰልነ ነበር።              ትንቢተ.ኢሳይያስ 1:9እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያ...
05/05/2026

የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ፥ እንደ ሰዶም በሆንነ እንደ ገሞራም በመሰልነ ነበር።
ትንቢተ.ኢሳይያስ 1:9

እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የልደቷ ቀን በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን

ግንቦት 1 ልደታ 2018 ዓ.ም

የተከበራችሁና የተወደዳችሁ የልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦች የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የቃል ኪዳን ልጆች እንደምን ሰነበታችሁ
ቅዳሜ በ09.05.2026 (ግንቦት 1ቀን2018 ) የእናታችን የእመቤታችንን የቅድስት ድንግል ማርያምን የልደት በዓል በእለተ ቀኗ በሥርአተ ቅዳሴና በዝማሬ ከ06:00 ሰዓት ጀምሮ የምናከብር ስለሆነ በእለቱ በሰዓቱ በቤተ ክርስቲያናችን በመገኘት የበረከቱ ተሳታፊ ይሆኑ ዘንድ መንፈሳዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ።
*አድራሻ*
Sebastian-Rinz Strasse 19&22
60323 Frankfurt am main

ውዳሴ ማርያም ዘ ረቡዕ : አምላክን የወለድሽ እመቤታችን ሆይ ትውልድ ሁሉ አንቺን ብቻ ያመሰግኑሻል። የእግዚአብሔር ሀገር(ከተማ) ሆይ ነቢያት ድንቅ ድንቅ የሆነ ነገርን ተናገሩልሽ። ደስ የተ...
29/04/2026

ውዳሴ ማርያም ዘ ረቡዕ :

አምላክን የወለድሽ እመቤታችን ሆይ ትውልድ ሁሉ አንቺን ብቻ ያመሰግኑሻል። የእግዚአብሔር ሀገር(ከተማ) ሆይ ነቢያት ድንቅ ድንቅ የሆነ ነገርን ተናገሩልሽ። ደስ የተሰኙ የጻድቃን ማደሪያ ሆነሻልና የምድር ነገሥታት ሁሉ በብርሃንሽ ይሄዳሉ ሕዝቡም ሠራዊቶቻቸውም በብርሃንሽ ይሄዳሉ ማርያም ሆይ ትውልድ ሁሉ ያመሰግኑሻል ● ካንቺ ለተወለደውም ይሰግዱለታል ያገኑታልም ቅድስት ሆይ ለምኝልን

ሚያዚያ 21
እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ወርሀዊ መታሰቢያ ቀን በሰላም አደረሰን አሜን።

እንደተናገረ ተነሥቷል (ማቴ28፥5)እንኳን ለጌታችን፣ ለአምላካችንና ለመድኃኔታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ትንሣኤ በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን።
11/04/2026

እንደተናገረ ተነሥቷል (ማቴ28፥5)

እንኳን ለጌታችን፣ ለአምላካችንና ለመድኃኔታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ትንሣኤ በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን።

ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም።ዐማኑኤል አምላኪየ ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም።ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ  ...
10/04/2026

ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም።

ዐማኑኤል አምላኪየ ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም።

ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም

ለከ ይደሉ ኃይል ወለከ ይደሉ ስብሐት ወለከ ይደሉ አኮቴት ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ ለዓለመ ዓለም።

ለአምላክ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም።
ለሥሉስ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም።
ለማኅየዊ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም።
ለዕበዩ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም።
ለእዘዙ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም።
ለመንግስቱ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም።
ለሕማሙ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም።
ለመስቀሉ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም።

ሆሣዕና
05/04/2026

ሆሣዕና

እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት፤ ሐሤትን እናድርግ፥ በእርስዋም ደስ ይበለን።አቤቱ፥ እባክህ፥ አሁን አድን፤ አቤቱ፥ እባክህ፥ አሁን አቅና።መዝሙረ  ዳዊት 118:25
04/04/2026

እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት፤ ሐሤትን እናድርግ፥ በእርስዋም ደስ ይበለን።

አቤቱ፥ እባክህ፥ አሁን አድን፤ አቤቱ፥ እባክህ፥ አሁን አቅና።
መዝሙረ ዳዊት 118:25

እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ወርሀዊ የመታሰቢያዋ ቀን በሰላም አደረሳችሁ !!!ማርያምም እንዲህ አለች፦"ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፥ መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋ...
30/03/2026

እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ወርሀዊ የመታሰቢያዋ ቀን በሰላም አደረሳችሁ !!!

ማርያምም እንዲህ አለች፦

"ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፥ መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች፤ የባሪያይቱን ውርደት ተመልክቶአልና። እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤ ብርቱ የሆነ እርሱ በእኔ ታላቅ ሥራ አድርጎአልና፤ ስሙም ቅዱስ ነው። ምሕረቱም ለሚፈሩት እስከ ትውልድና ትውልድ ይኖራል። በክንዱ ኃይል አድርጎአል፤ ትዕቢተኞችን በልባቸው አሳብ በትኖአል፤ ገዥዎችን ከዙፋናቸው አዋርዶአል፤ ትሑታንንም ከፍ አድርጎአል፤ የተራቡትን በበጎ ነገር አጥግቦአል፤ ባለ ጠጎችንም ባዶአቸውን ሰዶአቸዋል። ለአባቶቻችን እንደ ተናገረ፥ ለአብርሃምና ለዘሩ ለዘላለም ምሕረቱ ትዝ እያለው እስራኤልን ብላቴናውን ረድቶአል።"
ሉቃ. 1፥46-55

አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም ያድርሰን
የእመቤታችን በረከቷ ረድኤቷ አይለየን!!

14/03/2026
እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ወርሀዊ የመታሰቢያዋ ቀን በሰላም አደረሳችሁየቅዳሜ ውዳሴ ማርያም ንጽሕት ነሽ ብርህትም ነሽ። ጌታን በመካከል እጅ የያዝሽው ሆይ በሁሉ የተቀደሽ ...
27/02/2026

እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ወርሀዊ የመታሰቢያዋ ቀን በሰላም አደረሳችሁ

የቅዳሜ ውዳሴ ማርያም
ንጽሕት ነሽ ብርህትም ነሽ። ጌታን በመካከል እጅ የያዝሽው ሆይ በሁሉ የተቀደሽ ነሽ። ፍጥረት ሁሉ ቅድስት ሆይ ለምኝልም ብለው እየጮኹ ካንቺ ጋር ደስ ይላቸዋል።

ጸጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ። ባለሟነትን አግኝተሻልና ደስ ይበልሽ። እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነውና ደስ ይበልሽ። ግርማ ያለሽ ድንግል ሆይ ገናነትሽን እናመሰግናለን እናደንቃለን። እንደ መልአኩ ገብርኤልም ምስጋና እናቀርብልሻለን የባሕርያችን መዳን በማህጽንሽ ፍሬ ተገኝቷልና። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

እንደ ሠርግ ቤት ጉድፍ የሌለብሽ ነሽ መንፈስ ቅዱስ አድሮብሻልና። የልዑል ሃይልም ጸልዮብሻልና። ማርያም ሆይ ለዘለዓለም የሚኖር መጥቶ ከኃጢአት ያዳነን የአብ ልጅ ቃል በእውነት ወለድሽ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

ከዳዊት ሥር የተገ
ኘሽ ባሕርይ (ዘር) አንቺ ነሽ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በሥጋ ወልደሽልናልና። ከአብ የተወለደ ከዓልም በፊት የነበረ አንዱ ቃል ራሱን (ባሕርዩን) ሰወረ ካንቺም የተገዥን (ሰውን) አርአያ ነሣ።ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

አምላክን ያለርኩስት የወለድሽው ሆይ የምድር ሁለተኛ ፀሐይ ካንቺ ወጥቶልናልና። እንደነቢያት ትንቢትም ያለዘርና ያለመለወጥ ወደልሽው።ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

ከተለዩ የተለየች የተባልሽ የኪዳን ጽላት ያለብሽ የተሰወረ መና ያለበት የወርቅ መሶብ ያለብሽ ደብተራ ድንኳን አንቺ ነሽ። ይኸውም መና የተባለው መጥቶ በድንግል ማርያም ያደረው የእግዚአብሔር ልጅ ነው። የአብ ቃል በርስዋ ሰው ሆነ መጥቶ ያዳነን የባሕርይ ንጉሥን በዓለም ውስጥ የወደችው የሚናገር በግ የክርስቶስ እናቱ ገነት ደስ ይላታል ለዘላለም የሚኖር የአብ ልጅ እርሱ መጥቶከኃጢአት አድኖልና።ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

የንጉስ ክርስቶስ እናትን ተባልሽ እርሱን ከወለድሽ በኋላም በድንግልና ኖርሽ። ድንቅ በሆነ ምሥጢርም (ተዋህዶ) አማኑኤልን ወለድሽው ስለዚህም ባለመለወጥ አጸናሽ።ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

እግዚአብሔር በላይዋ ተቀምጦባት ያዕቆብ ያያት መሰላል አንቺ ነሽ በሁሉ በኩል የማይመረመር እርሱን ተፈትሖ በሌለበት ምህፅንሽ ተሸክመሽዋልና። እኛን ስለማዳን ካንቺ ሰው በሆነ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ አማላጅ ሆንሽን።ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

የተባረክሽ ንጽህት የሆንሽ አዳራሽ ሆይ እንሆ ጌታ የፈጠረውን ዓለም ሁሉ በይቅርታው ብዛት ያድን ዘንድ ካንቺ ወጣ (ተወለደ) ፈጽመን እናመስግነው። ቸርና ሰውን ወዳጅ ነውና።ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

ያለርኩሰት ድንግል የሆንሽ ጸጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ የዓለም ሁሉ ምክበርያ ጽዋ ነሽ። የማትጠፊ ፋና ነሽ የማትፈርሽ መቅደስ ነሽ የቅዱሳን መደገፊያቸው (መጠጊያቸው) የማትለወጪ የሃይማኖት በትር ነሽ ቸር አዳኛችን ወደ ሆነ ልጅሽ ለምኝልን ፈጽሞ ይቅር ይለን ይምረን ዘንድ ኃጢአታችንንም ያስተሠርይልን ዘንድ።ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

Adresse

Sebastian-Rinz-Straße 19 And 22, Frankfurt Am Main
Frankfurt
60323

Webseite

Benachrichtigungen

Lassen Sie sich von uns eine E-Mail senden und seien Sie der erste der Neuigkeiten und Aktionen von Äthiopisch-orthodox Tewahdo Kirche Tserha Tsion Kidist Mariam Frankfurt erfährt. Ihre E-Mail-Adresse wird nicht für andere Zwecke verwendet und Sie können sich jederzeit abmelden.

Teilen

Kategorie