EOTC Germany Archdiocese ፤ የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት

EOTC Germany Archdiocese ፤ የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት Verband der Äthiopisch-Orthodoxen Tewahedo Kirchen Erzdiözese von Deutschland und Umgebung e. V., Frankfurt a.

Main
Amtsgericht Frankfurt am Main VR 16730
Ethiopian Orthodox Tewahedo Church (EOTC) Germany Archdiocese
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሚድያ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የጀርመንና አካባቢ ሀገረ ስብከት የፌስቡክ ገጽ።
Official page of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church in Germany and surroundings Archdiocese

የባንክ ስም መረጃ

Bank Account: Volksbank, Frankfurt
IBAN : DE62 5019 0000 6201 1255 94
BIC: FFVBDEFF # # #

🔔   የመስከረም (ብዙኀን) ማርያም ክብረ_በዓል ጥሪበጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት ለምትገኙ ምእመናን እና ምእመናት ኦርቶዶክሳውያን በሙሉ በመጀመሪያ እንኳን ለአዲሱ ዘመን 2019 ዓ.ም ...
14/09/2026

🔔 የመስከረም (ብዙኀን) ማርያም ክብረ_በዓል ጥሪ

በጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት ለምትገኙ ምእመናን እና ምእመናት ኦርቶዶክሳውያን በሙሉ በመጀመሪያ እንኳን ለአዲሱ ዘመን 2019 ዓ.ም እና ለበዓለ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ እያልን የመስከረም ማርያምን በዓለ ንግሥ በደብራችን ፍራንክፈርት ጽርሐ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በታላቅ ድምቀትና ሥነ ሥርዓት ለማክበር የአጥቢያው ሰበካ ጉባኤ ኑ አብረን እናክብር በማለት መንፈሳዊ ጥሪውን ያቀርባል።
በበዓሉ ላይም ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ፣ የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪዎች፣ ሊቃውንት ፣ ካህናት፣ የሰንበት ት/ቤት መዘምራን፣ በዛ ያሉ ምዕመናንና ምዕመናት ይገኛሉ።
🗓
ዓርብ እና ቀዳሚት መስከረም ፳፪ እና ፳፫ ቀን 2019
Freitag & Samstag, October 2 & 3 2026
በደመቀ ሁኔታ ይከበራል፡፡

መርሐ ግብር
• በዋዜማው ዓርብ ከ16:00 ሠዓት ጀምሮ ዋዜማ ይቆማል
• ዓርብ ከምሽቱ 23:00 - 05:30 ሠዓት ሥርዓተ ማኅሌት
• ቅዳሜ ከጠዋቱ 05:30 - 09:00 በጸሎተ ኪዳን እና በሥርዓተ ቅዳሴ አገልግሎቱ ከተከናወነ በኋላ
በስብከተ ወንጌል ፣ በመዝሙር እና የተለያዩ መርሐ ግብሮች ተከብሮ፤
ታቦተ ሕጉ ወጥቶ ዑደት ይደረግና
በብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ ሊቀ ጳጳስ
ቃለ ምዕዳን እና ቡራኬ የበዓሉ ፍጻሜ ይሆናል።
🚩
በዓሉ የሚከበርበት አድራሻ ፤
Matthäuskirche
Friedrich-Ebert-Anlage 33,
60327 Frankfurt am Main

ወደ ቦታው ለመምጣት ከውናው ባቡር ጣቢያ Hauptbahnhof straßebahn 16 &17 በመያዝ ወደ Festhalle/Messe እቅጣጫ 2 Station ወይም ከ Hauptbahnhof በእግር ከ3-5 ደቂቃ ሄደው ቤተ ክርስቲያኑን ያገኙታል

🔔 ❖በጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት⛪የኮሎኝ ርእሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት⏰መስከረም ፱ እና ፲ ፳...
14/09/2026

🔔
❖በጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት
⛪የኮሎኝ ርእሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን
ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት
⏰መስከረም ፱ እና ፲ ፳፻፲፱ ዓ.ም. (19.-20.09.2026)
🚩የአዲሱ ቤተ ክርስቲያን አድራሻ:
Salvatorkirche
Schlesischer Platz 2a, 50737 Köln

ለበለጠ መረጃ ታች ይመልከቱ።

እንኳን ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ በሰላም አሸጋገረን። የጀርመንና ኡካባቢው ሀገረ ስብከት ሚዲያ
12/09/2026

እንኳን ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ በሰላም አሸጋገረን።

የጀርመንና ኡካባቢው ሀገረ ስብከት ሚዲያ

እንኳን ለ፳፻፲፱ ዓ.ም. ዐዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችኹ። "...እርስ በእርሳችኹ በሰላም ኑሩ።..." ፩ኛ ተሰ. ፭÷፲፫እግዚአብሔር ሀገራችና ቤተ ክርስቲያናችንን በሰላም ይጠብቅልን። በዓሉ ...
10/09/2026

እንኳን ለ፳፻፲፱ ዓ.ም. ዐዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችኹ።

"...እርስ በእርሳችኹ በሰላም ኑሩ።..." ፩ኛ ተሰ. ፭÷፲፫

እግዚአብሔር ሀገራችና ቤተ ክርስቲያናችንን በሰላም ይጠብቅልን።
በዓሉ የተቀደሰ፣ የሰላም፣ የደስታና የጤና እንዲኾንላችኹ እመኛለሁ።
ልዑል እግዚአብሔር የተቀደሰ ዐዲስ ዓመት ያድርግልን።

አባ ዲዮናስዮስ
የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

 በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ ለ፰ ደቀ መዛሙርት የዲቁና መዐርግ ሰጡ። በሀገረ ስብከቱ ከተለያዩ አጥቢያ...
06/09/2026



በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ ለ፰ ደቀ መዛሙርት የዲቁና መዐርግ ሰጡ። በሀገረ ስብከቱ ከተለያዩ አጥቢያዎች የመጡት ደቀ መዛሙርት የተሾሙት ነሐሴ ፴ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም ቀን በፍራንክፈርት ምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ነው።

በዓለ ሢመቱን ከፈፀሙ በኋላ ብፁዕነታቸው ለደቀ መዛሙርቱ ምክርን ሰጥተዋል። "በውጭው ዓለም ተወልዳችኹ አድጋችኹና ለክህነት የሚያስፈልገውን የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ተምራችሁ ለዚህ በመብቃታችኹ ቤተ ክርስቲያን ተደስታለች" ያሉት ብፁዕነታቸው፤ "ምንም እንኳን ለዚህ ክብር ትበቁ ዘንድ ፈቃዱ የእግዚአብሔር ቢኾንም፤ ወላጆቻችኹ ከመደበኛ ትምህርታችኹ ጎን የቤተ ክርስቲያንን ትምህር እንድትማሩ ስላበረቷችኹ ምስጋና ይገባቸዋልና የካህናቱ ወላጆች እንኳን ደስ አላችኹ። ይልቁንም በሀገራቸው በብዙ ድካም በተማሩት ትምህርት በስደት ልጆቻቸውን ተከትለው በማስተማር ለዚህ ያበቁ የሀገረ ስብከታችን ሊቃውንት ምስጋና ይገባቸዋል። እናንተንም እንኳን ደስ አላችኹ" ብለዋል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጀርመንና አካባቢው መንበረ ጵጵስና ሀገረ ስብከት የ፳፻፲፰ ዓ.ም አገልግሎት ዘመን ጠቅላላ ጉባኤ ተሳታፊዎች በሀገረ ስብከቱ ሥር የሚገኙ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪዎች፣ የምእመናንና የሰንበት ት/ቤት ተወካዮች በበዓለ ሢመቱ ላይ ተገኝተዋል።

(ዜና ሀገረ ስብከት ፤ ነሐሴ ፴ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም ፤ ፍራንክፈርት ጀርመን ፤ Sept. 5th 2026 Frankfurt Germany)

የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሚድያ

🟩 የ፳፻፲፱ ዓ/ም  ቀን መቁጠሪያ 🌼🟨 በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት 🌼🟥 የ፳፻፲፱ ዓ/ም ቀን መቁጠሪያ አዘጋጅቶ አሳትሞ አቀረበ። 🌼✥ በዚህ ቀን መቁጠሪያ ውስጥ የኢት...
05/09/2026

🟩 የ፳፻፲፱ ዓ/ም ቀን መቁጠሪያ 🌼
🟨 በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት 🌼
🟥 የ፳፻፲፱ ዓ/ም ቀን መቁጠሪያ አዘጋጅቶ አሳትሞ አቀረበ። 🌼
✥ በዚህ ቀን መቁጠሪያ ውስጥ የኢትዮጵያውያንና የአውሮጳውያን ቀን አቆጣጠር እንዲሁም የበዓላትና የአጽዋማት ማውጫ ተዘጋጅቷል።
ቀን መቁጠሪያውን በሀገረ ስብከቱ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ከእሑድ ሰንበት ጳጉሜን ፩ / Sept 6 ቀን ጀምሮ ያገኙታል።
📱 ለበለጠ መረጃ +49 162 9825646
ቅድስት ቤተክርስቲያናችን በቀመረችው ቀን መቁጠሪያ እየተጠቀሙ ሀገረ ስብከትዎን ያጠናክሩ!
የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሚድያ

 በኢ.ኦ.ተ.ቤ. የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት የ፳፻፲፯ እና ፳፻፲፰ ዓ.ም የመንበረ ጵጵስና ሀገረ ስብከት ጠቅላላ መንፈሳዊ ጉባኤ ተጠናቀቀ። ነሐሴ ፳፱ እና ፴ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም. በፍ...
05/09/2026



በኢ.ኦ.ተ.ቤ. የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት የ፳፻፲፯ እና ፳፻፲፰ ዓ.ም የመንበረ ጵጵስና ሀገረ ስብከት ጠቅላላ መንፈሳዊ ጉባኤ ተጠናቀቀ።

ነሐሴ ፳፱ እና ፴ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም. በፍራንክፈርት ምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን በተከናወነውና በሀገረ ስብከቱ ሥር ከሚገኙ አጥብያ አብያተ ክርስቲያናት ማኅበረ ካህናትና ምእመናን የተወከሉበት ጠቅላላ ጉባኤው በሁለት ቀናት ጉባኤው የህገረ ስብከቱንና የአጥቢያዎችን የኹለት ዓመታት የተግባርና የሒሳብ ዘገባ ሰምቶ በመወያየትና የማሻሻያ ሐሳቦችን በመስጠት አጽድቋቸዋል። የተሰሙት የሥራ እንቅስቃሴዎች ሀገረ ስብከቱ የደረሰበትን ደረጃ ያመላከቱ፤ ይሁንና ከዚህም በላይ መሥራት እንደሚቻል በአጽንዖት አንሥቷል፤ ይህ ይኾን ዘንድም አጥቢያዎች ሀገረ ስብከቱን በሚችሉት መንገድ ሁሉ ማገዝ እንዳለባቸው አሳስቧል።

ጉባኤው በየደረጃው የቀረቡ ዘገባዎችን ከሰመና በውይይት ካጸደቀ በኋላ የቀረበለት ቃለ ዐዋዲው በሚያዝዘው መሠረት የአገልግሎቱ ዘመኑ የተጠናቀቀውን የሀገረ ስብከቱን አስተዳደር ጉባኤ በዐዲስ የመተካት አጀንዳ ነበር። ይሁንና ጉባኤው ወቅቱ በተለይ አሁን ያለንበት ጊዜ በብዙ ድካም የተገኘውን የገዳም ቦታ የምንገዛበት፣ ገዝተንም ወደ ሥራ የምናስገባበት በመኾኑ ጉዳዩን ሲከታተል የነበረውን አስተዳደር ጉባኤ አንሥቶ በዐዲስ መተካት በእንቅስቃሴው ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ሊያመጣ የሚችል በመኾኑ የአገልግሎት ዘመኑ በአንድ ዓመት እንዲራዘም ወስኗል።

ቀጥሎ ለጉባኤው የቀረበለት አጀንዳ “ዘገባ በእንተ ገዳም በሀገረ ጌርመን” የሚል ነበር። በዚህ አጀንዳ ሀገረ ስብከቱ በአውሮጳ የመጀመሪያውን ገዳም ለማቋቋም ሲያደርግ የቆየውን እንቅስቃሴ፣ የተገኘውን ውጤትና የግዢው ሒደት አሁን ያለበትን ደረጃ አስመልክቶ ፕሮጄክቱን በሚያስተባብረው ዐቢይ ኮሚቴ ዘገባ ቀርቦለታል። ጉባኤውም በዘገባው የተሰማውን ውጤት አድንቆ፤ ገዳሙን ገዝቶ ለመረከብ የቀረው ሒደት በፍጥነት ተጠናቅቆ ቦታውን እንረከብ ዘንድ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።

ጉባኤውን በር እሰ መንበርነት የመሩት ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የሀገረ ስብከቱን አጠቃላይ እንቅስቃሴ አስመልክቶ አስተያየትና የሥራ መመሪያ ከሰጡ በኋላ ጉባኤው ወደ መጨረሻው የመወያያ አጀንዳ አምርቷል።
ለጉባኤው የቀረበለት የመጨረሻ አጀንዳ “የቤተ ክርስቲያናችን አጠቃላይ ወቅታዊ ሁኔታና ሀገረ ስብከታችን” የሚል ሲኾን በርእሰ ጉዳዩ ላይ የጉባኤው አባላት ሐሳብ ተለዋውጠዋል። እንደ ሀገረ ስብከት ብንሠራቸው የተባሉ ተግባራትን በይሁንታነት ዘርዝሯል።

በመጨረሻም በመስመር ላይ የሚከናወነው የመንፈቀ ዓመት የሀገረ ስብከቱ ጠቅላላ ጉባኤ ጊዜውን ጠብቆ እንዲከናወን፤ ነገር ግን ከዚሁ ጋር የገጽ ለገጽ ጉባኤ የሀገረ ስብከቱ የሰንበት ት/ቤቶች ማስተባበሪያ ክፍል ከሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጋር በመተባበር ከሚያከናውነው ዝማሬ ተዋሕዶ ጋር ተያይዞ እንዲከናወን በመወሰን ተጠናቋል።

(ዜና ሀገረ ስብከት ፤ ነሐሴ ፴ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም ፤ ፍራንክፈርት ጀርመን ፤ Sept. 5th 2026 Frankfurt Germany)

የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሚድያ

  በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጀርመንና አካባቢው መንበረ ጵጵስና ሀገረ ስብከት የ፳፻፲፰ ዓ.ም አገልግሎት ዘመን ጠቅላላ ጉባኤ ሁለተኛ ቀን በፍራንክፈርት ምስካየ ኅዙናን ...
05/09/2026



በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጀርመንና አካባቢው መንበረ ጵጵስና ሀገረ ስብከት የ፳፻፲፰ ዓ.ም አገልግሎት ዘመን ጠቅላላ ጉባኤ ሁለተኛ ቀን በፍራንክፈርት ምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ መሪነት እየተካሔደ ይገኛል።

በዛሬው ጉባኤም በሀገረ ስብከቱ ሥር የሚገኙ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪዎች፣ የምእመናንና የሰንበት ት/ቤት ተወካዮች ተገኝተዋል።

ጉባኤው በብፁዕነታቸው ጸሎት ከተከፈተ በኋላ የአጥቢያዎች የሥራና የሒሳብ ዘገባ እየቀረበ ነው።

ጉባኤው ትናንት ተጀምሮ ዛሬ የሚጠናቀቅ ሲኾን በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መሠረት በልዩ ልዩ መወያያ አጀንዳዎች በመወያየት ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል።

(ዜና ሀገረ ስብከት ፤ ነሐሴ ፴ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም ፤ ፍራንክፈርት ጀርመን ፤ Sept. 5th 2026 Frankfurt Germany)

የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሚድያ

  በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጀርመንና አካባቢው መንበረ ጵጵስና ሀገረ ስብከት የ፳፻፲፰ ዓ.ም አገልግሎት ዘመን ጠቅላላ ጉባኤ በፍራንክፈርት ምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ...
04/09/2026



በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጀርመንና አካባቢው መንበረ ጵጵስና ሀገረ ስብከት የ፳፻፲፰ ዓ.ም አገልግሎት ዘመን ጠቅላላ ጉባኤ በፍራንክፈርት ምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ተጀመረ።

በጉባኤው በሀገረ ስብከቱ ሥር የሚገኙ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪዎች፣ የምእመናንና የሰንበት ት/ቤት ተወካዮች ተገኝተዋል።

ጉባኤው በጸሎት ከተከፈተ በኋላ የሀገረ ስብከቱ የሥራና የሒሳብ ዘገባ ቀርቦ ጉባኤው ውይይት ካደረገበት በኋላ ጸድቋል። በመቀጠልም የአጥቢያዎች የሥራና የሒሳብ ዘገባ እየቀረበ ነው።

ጉባኤው እስከ ነገ ቅዳሜ ነሐሴ ፴ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም የሚቀጥል ሲኾን በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መሠረት በልዩ ልዩ መወያያ አጀንዳዎች በመወያየት ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል።

(ዜና ሀገረ ስብከት ፤ ነሐሴ ፳፱ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም ፤ ፍራንክፈርት ጀርመን ፤ Sept. 4th 2026 Frankfurt Germany)

የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሚድያ

🔔"ቅዱስ ዮሐንስን" በቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን በሩስልስሀይም ጥሪ፤ 🗓 መስከረም ፪ እና ፫ ቀን (September 12 - 13, 2026) ⏰ ቅዳሜ  ከዋዜማው 16 ሰዓት ጀምሮ💠በጀርመንና ...
04/09/2026

🔔"ቅዱስ ዮሐንስን" በቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን በሩስልስሀይም ጥሪ፤
🗓 መስከረም ፪ እና ፫ ቀን (September 12 - 13, 2026)
⏰ ቅዳሜ ከዋዜማው 16 ሰዓት ጀምሮ
💠በጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት በደብረ ምጥማቅ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቤ/ክ፤
እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪዎች፣ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፣ ተጋባዥ መምህራን፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣት መዘምራን እንዲሁም ምዕመናንና ምዕመናት በተገኙበት ቅዳሜ ከ 16 ሰዓት አንስቶ በዋዜማ፣ በማኅሌት፣ በቅዳሴ፣ በመዝሙር፣ በወንጌል ትምህርት በድምቀት ይከበራል።

እናንተም የደብራችሁን አገልጋይ ካህናት፣ ዲያቆናት፣ መዘምራን እና ምዕመናን በማስተባበር እንድትገኙልን እና የበዓለ ረድኤቱ ተካፋዮች ይሆኑ ዘንድ የአክብሮት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
የደብሩ ሰበካ ጉባኤ አስተዳደር ጽ/ቤት
ዝርዝር መረጃውን ከታች ይመልከቱ።

የአጥቢያውን ሚድያ ገጽ እናስተዋውቅዎ ይከታተሉት፦
ደብረ ምጥማቅ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስትያን
ሀገረ ስብከት ሚድያ

Adresse

E. O. T. C./Germany And Surroundings Archdiocese Abune Dionasiyos C/o Street Immanuel Aethiopisch-Orthodoxe Kirchengemeinde
Frankfurt

Webseite

Benachrichtigungen

Lassen Sie sich von uns eine E-Mail senden und seien Sie der erste der Neuigkeiten und Aktionen von EOTC Germany Archdiocese ፤ የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት erfährt. Ihre E-Mail-Adresse wird nicht für andere Zwecke verwendet und Sie können sich jederzeit abmelden.

Die Kultstätte Kontaktieren

Nachricht an EOTC Germany Archdiocese ፤ የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት senden:

Verknüpfungen

Teilen