15/09/2026
2019 አዲስ ዓመት ዝግጅታችን በፍራንክፈርት በድምቀት ተከበረ!
በ13.09.2026 የተካሄደው የአዲስ ዓመት ዝግጅታችን፣ ከቅርብም ከሩቅም፣ በተለይም ከባቫሪያ የመጡ በርካታ አባላት በተገኙበት በታላቅ ደስታና ድምቀት ተከብሮ ውሏል።
ክቡር አባ ግርማቸው ከእህታችን ሊዲያ የተበረከተውን የመዘምራን ልብስ በመባረክ አስጀምረው፣ የአዲስ ዓመት ቡራኬ ፀበል ከረጩን በኋላ መሰዋዕተ ቅዳሴውን መርተዋል።
በአዳራሽ ውስጥ እህቶቻችን “አበባየሁ ሆይ ለምለም” በማዜም የቆየውን ውድ ባህላችንን እንድናስታውስና እንድንወያይበት አድርገውናል። በማዜም ያገኙትን ገንዘብ ለማህበራች ህፃን አባላት አገልግሎት እንዲውል ለግሠውታል።
ከዚያም የምሳና የቡና ጊዜ ከተለያዩ አዝናኝ ጨዋታዎች ጋር በደስታ አሳልፈናል። በመጨረሻም አባ ግርማቸው በመዝጊያ ፀሎት የዕለቱን መርሃ ግብር አሳርገዋል።
ይህ የአብሮነት፣ የፍቅርና የደስታ ቀን በሁላችንም ልብ ውስጥ የማይረሳ ትዝታን ጥሎ አልፋል።
አዲሱ ዓመት የፍቅር፣ የሰላም፣ የጤናና የበረከት ዓመት ይሁንልን!