Youth for Christ#ወጣት ለክርስቶስ

07/06/2024
07/06/2024
11/04/2024

አንድ ቀን ናይት ክለብ ደጃፍ ቆሙኩና እግዚአብሔርን እንዲህ
አልኩት፦
"...ቄስ ልታደርገኝ እንደፈለክ አውቃለው።አሁን ግን እኔ ድሃ ነኝ።ቤተሰቦቼም ይናፍቁኛል።ታዋቂ ዘፋኝ አርገኝና።ከታወቅኩ በኋላ...ዝነኛ ከሆንኩ በኋላ...ገንዘብ ካገኝው በኋላ ቄስ እሆንልሃለው። አሁን ግን በርኖስ አልለብስልህም።" አልኩት።
ጌታም የሰማኝ መሰለኝ። እኔም ታዋቂ ዘፋኝ ሆንኩ።
(ሙሉቀን መለሰ በአንድ ቃለ መጠይቅ ላይ ስለ ህይወቱ የተናገረው ነበር።)

ከብዙ ዘመን በኋላ ግን በጌታ ቀን በርኖስ ለበሰ።ቄስ ሆነ።ልክ እንደሳምራዊቷ ሴት መሲሁን (ክርስቶስን) ካገኝ በኋላ እንስራውን ጥሎ መነነ።ለመካድ የሚያስቸግር ዝና ካደ። " ምን ቢያገኝ ነው? ምን ቢታየው ነው?" ሁሉንም አስባለ።

" ከበረት ወይፈኑን ከአዝርትም ምርጡን
ከሃብት ከበረከት ከአስራት ምፅዋቱን
ነፍሴንም ጨምሬ ሚዛን ላይ ብሰፍረው
ጌታ ለውለታህ እጅግ ያነሰ ነው...ስለምህረትህ " ብሎ ተቀኝ።

'ህይወት' ከገንዘብ...ከዝና...ከጥበብ እጅግ እንደሚልቅ፣ እንደሚያልፍ አሳይቶ አለምን ኮነነ!።
(ናትናኤል ገብረወልድ)

29/08/2023
28/02/2023
በ1970 ዓ.ም በዚሁ ከተማ Wilmore - Asbury university ታላቅ መነቃቃት ሆኖ ነበር ይላሉ ታሪኩን የሚያውቁ ሰዎች። በወቅቱ ለ144 ሠዓታት የጸሎት፣ የዝማሬ፣ የቃል ትምህርትና...
16/02/2023

በ1970 ዓ.ም በዚሁ ከተማ Wilmore - Asbury university ታላቅ መነቃቃት ሆኖ ነበር ይላሉ ታሪኩን የሚያውቁ ሰዎች። በወቅቱ ለ144 ሠዓታት የጸሎት፣ የዝማሬ፣ የቃል ትምህርትና የንስሓ ጊዜ እንደነበር ያስታውሳሉ። ከዚያም በኋላ ታላቅ የወንጌል ሥርጭት ተካሂዶ በርካታዎች ወደ ጌታ የመጡበት ጊዜ ነበር ይላሉ።

ባለፈው ረቡዕ ዕለት ጠዋት Feb. 8, 2023 በተለመደው የዩኒቨርሲቲ ክርስቲያን ተማሪዎች ጸሎት ወቅት (regular chapel) በHughes መታሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ነበር የመንፈስ ቅዱስ እሳት በወጣት ተማሪዎች ውስጥ የተቀጣጠለው። ከጠዋቱ 10:00AM በተለመደው ሁኔታ አምልኮውን የሚመሩ ወጣቶች ለአገልግሎት ቆሙ። ማቆም ተሳናቸው። ሰዎች ያለቅሳሉ፣ ንስሓ ይገባሉ፣ አንዱ ሌላው ላይ እጁን እያኖረ ይጸልያል በቃ ቀጠለ። ዘመሩ፣ በየመሐሉ ጸለዩ፣ ቀጠሉ ቀጠሉ። ያልተገኙ ተማሪዎችና ፕሮፌሰሮች ተጨመሩ፣ የቤተ ክርስቲያን መጋቢዎች የሌላ ከተሞች አገልጋዮች ወደ አዳራሹ መግባት ጀመሩ። የሚገባ እንጂ የሚወጣ ሳይኖር መሸ። ነጋ፣ መሸ፣ ሌላም ቀን ነጋ ይኼው ዛሬ ሳምንት ሆኖታል። ❤️

ሰዎች ከተለያዩ ከተሞች ከተለያዩ ግዛቶች ይመጣሉ። ይቀጣጠላሉ። አንዱ ይሄዳል ሌላው ይመጣል… አንዱ ያለቅሳል፣ ሌላው ይደሰታል፣ … ሌላው ይመሰክራል፣ ሌላው ይንበረከካል፣ ሌላው ይያያዛል፣ ሌላው ይዘምራል፣ ሌላው እጁን ወደ ላይ ያነሳል፣ ሌላው ዝም ብሎ ይቀመጣል፣ ሌላው ይነሳና መድረክ ላይ ወጥቶ መልዕክት ያስደምጣል። የጊዜ ጉዳይ የሥራ ጉዳይ የሌክቸር ጉዳይ የሪሰርች ጉዳይ ማን ያስባል? “Lord I need you every hour I need you” ይላሉ። “Way maker, miracle worker, promise keeper” ይላሉ። የክፍል ጓደኞቼ ሲነግሩኝ ከአቅም በላይ የሆነ ነገር ነው። ነገ ሄጄ እስክሳተፍ ልቤ ቸኩሏል። 😲😲🔥🔥

Workneh D. Koyra እንደፃፈው

Adresse

Frankfurt

Öffnungszeiten

09:00 - 17:00

Webseite

Benachrichtigungen

Lassen Sie sich von uns eine E-Mail senden und seien Sie der erste der Neuigkeiten und Aktionen von Youth for Christ#ወጣት ለክርስቶስ erfährt. Ihre E-Mail-Adresse wird nicht für andere Zwecke verwendet und Sie können sich jederzeit abmelden.

Die Kultstätte Kontaktieren

Nachricht an Youth for Christ#ወጣት ለክርስቶስ senden:

Teilen