Debre Gennet Qiddist Maryam Ethiopian Orthodox Tewahedo Church

Debre Gennet Qiddist Maryam Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Ethiopian Orthodox Tewahedo Church in Opfikon (Zurich) Switzerland

04/06/2026
ቤተ ክርስቲያን ልጆቿን አከበረች፣በዙሪክ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን እንደተለመደው የዘንድሮው ግንቦት ልደታን እጅግ ደማቅ በሆነ ሁኔታ አክብራለች፤ ብዙ ምእመናን ከመላው ስዊ...
19/05/2026

ቤተ ክርስቲያን ልጆቿን አከበረች፣
በዙሪክ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን እንደተለመደው የዘንድሮው ግንቦት ልደታን እጅግ ደማቅ በሆነ ሁኔታ አክብራለች፤ ብዙ ምእመናን ከመላው ስዊዘርላንድና አካባቢዋ ተገኝተው ማክበራቸው የተለመደ ዓመታዉ ኩነት ቢሆንም የዘንድሮውን ለየት ያደረገው አዲስ የተመረጠው ሰበካ ጉባኤ የሥራ መጀመርያው ያደረገውን እስከ አሁን ለአገለገሉ የሰበካ ጉባዔ አባላት ያዘጋጀው የምስጋና ሰርተፊኬትና ልዩ ልዩ ሽልማቶች በስዊዘርላንድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪ በቆሞስ አባ ኃይለ ጊዮርጊስ አማካይነት እንዲበረከትላቸው በማድረግ ነው።
የዙሪክ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ከተመሠረተች ሃያ ስድስት (26) ዓመታት ተቆጥረዋል፣ በወቅቱ አቶ ምሥጢረ ና ቤተሰባቸው የተዋሕዶ እምነት አገልግሎት ቢጀመር ይደሰታሉ ብለው ያሰቧቸውን ጓደኞቻቸውንና በቅርብ የሚያውቋቸውን ሁሉ አገልግሎት የሚጀመርበትን ቀንና ቦታ አሳውቀው በአስራ አራት አዋቂዎችና ሕፃናት የተጀመረው ቤተ ክርስቲያን ብዙ ውጣ ውረዶችን አልፎ በእግዚአብሔር ረድኤትና ፈቃድ፣ በእመቤታችን ድንግል ማርያም እገዛ በቀጥተኛዋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ የሚያምኑ ሁሉ የሚገለገሉባት ማድረግ ተችሎ እዛሬ ላይ ተደርሷል።
አዲስ በተመረጠው ሰበካ ጉባኤ ለአገልግሎታቸው እውቅና ሰጥቶ በእለቱ ልዩ ልዩ ሽልማቶችንና ሰርተፊኬት ያገኙት፣
1. አቶ ምሥጢረ ኃይለ ሥላሴ ከምስረታው ጀምሮ በተከታታይ እየተመረጡ በተለያዩ የሰበካ ጉባኤው እርከን፣ በዙሪክ የኦርየንታልና ምሥራቅ ኦርቶዶክሳውናን ሕብረት ከመሥራቹቹ አንዱ የሆኑና፣ የዙሪክ አብያተ ክርሲያናት ሕብረት በአባልነት ያገለገሉ፤
2. አቶ ጌታቸው ግርማ ለረጂም ዓመታት በሰበካ ጉባኤና በአብይ ኮሚቴ የዙሪክ ደብረ ገነትን በመወከል የሥራ አስፈጻሚ የሆኑ፤
3. አቶ ፒተር አረጋይ የሰበካ ጉባኤ ሰብሳቢም በመሆን አባል ሆነው ያገለገሉ፤
4. ዶክተር ወንድወሰን አይሸሽም ለረጂም ዓመታት የሰበካ ጉባኤ ሥራ አስፈጻሚ አባልና በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያናት ሕብረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስን በመወከል የሥራ አስፈጻሚ የሆኑና ለአዲሱም የሰበካ ጉባኤ ተመርጠው በማገልገል ላይ ያሉ፤
5. በኩረ መዘምራን ጥላሁን አብሽር በድጋሚ የተመረጡ፤
6. አቶ አንዱ ዓለም በቀለ ለአዲሱም ሰበካ ጉባኤ ተመርጠው በማገልገል ላይ ያሉ
7. ወ/ሮ የቺመቤት ደጄኔ ከመስራች አባላት አንዷና የሰበካ ጉባኤ አባል የነበሩ፤
8. ወ/ሮ ሂሩት ልዬው በድጋሚ የተመረጡ፣
9. አቶ ተክሉ ደበበ፣ ሰበካ ጉባኤ አባል
10. . አቶ ንጉሤ በቀለ ሰበካ ጉባኤ አባል ናቸው።
ተሸላሚዎቹም ለአዲሱ የሰበካ ጉባኤ መልካም ያገልግሎት ዘመን በመመኘት ከሰበካ ጉባኤ ባሻገር በሚያስፈልጉ ቦታዎች ሁሉ ድጋፋቸውን እንደሚያደርጉ፣ ለቤተ ክርስቲያኒቱ እድገት የተቻላቸውን ከማድረግ እንደማይቆጠቡ ቃል በመግባት ሥነ ስርዓቱ ባማረ መልኩ ተደምድሟል።

12/05/2026
የጌታችንና የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ እናት የእኛም እናት የቅድስት ድንግል ማርያም በዙሪክ ልደት እንዲህ ከብሮ ውሏል።
12/05/2026

የጌታችንና የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ እናት የእኛም እናት የቅድስት ድንግል ማርያም በዙሪክ ልደት እንዲህ ከብሮ ውሏል።

ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን፤ በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤ አሰሮ ለሰይጣን፤ አግዐዞ ለአዳም፤ ሠላም እምይዕዜሰ፤ ኮነ፤ ፍስሐ ወሠላም፡፡አንኳን አደረሳችሁ፤ እንኳን አደረሰን።በስዊዘርላንድ የኢትዮጵያ...
13/04/2026

ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን፤ በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤ አሰሮ ለሰይጣን፤ አግዐዞ ለአዳም፤ ሠላም እምይዕዜሰ፤ ኮነ፤ ፍስሐ ወሠላም፡፡
አንኳን አደረሳችሁ፤ እንኳን አደረሰን።
በስዊዘርላንድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ የዙሪክ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ሰሞነ ሕማማት ከ"ህጽበተ እግር ጸሎተ ሐሙስ " ጀምሮ የስግደትና የትንሣኤ በኣል እጅግ በደመቀ እና ባማረ ሁኔታ ተከብሮ አልፏል። በስዊዘርላንድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ዋና አስተዳዳሪ በቆሞስ አባ ኃይለ ጊዮርጊስ የተመራው ተዋህዷዊ ስነ ሥነ ስርአት በከፊልም ቢሆን በምስልና በተንቀሳቃሽ ምስል እንደሚከተለው ተከታተሉ።

25/02/2026

#ምኩራብ :- የአብይ ፆም ሶስተኛው ሳምንት ምኩራብ | ምኩራብ ምንድን ነው? | mikurab mindin new? | ዮናስ ቲዩብ | yonas tubeእንኳን ወደ ዮና...

Adresse

Milchbuchstrasse 57
Zürich
8057

Öffnungszeiten

Donnerstag 10:00 - 17:00
Freitag 10:00 - 17:00
Samstag 18:00 - 19:00
21:00 - 05:00
Sonntag 08:00 - 17:00

Benachrichtigungen

Lassen Sie sich von uns eine E-Mail senden und seien Sie der erste der Neuigkeiten und Aktionen von Debre Gennet Qiddist Maryam Ethiopian Orthodox Tewahedo Church erfährt. Ihre E-Mail-Adresse wird nicht für andere Zwecke verwendet und Sie können sich jederzeit abmelden.

Die Kultstätte Kontaktieren

Nachricht an Debre Gennet Qiddist Maryam Ethiopian Orthodox Tewahedo Church senden:

Teilen