የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በስዊዘርላንድ የዙሪክ ማህደረ ስብሃት ቅድስት ልደታ ለማርያም

  • Startseite
  • Schweiz
  • Zürich
  • የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በስዊዘርላንድ የዙሪክ ማህደረ ስብሃት ቅድስት ልደታ ለማርያም

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በስዊዘርላንድ የዙሪክ ማህደረ ስብሃት ቅድስት ልደታ ለማርያም Kontaktinformationen, Karte und Wegbeschreibungen, Kontaktformulare, Öffnungszeiten, Dienstleistungen, Bewertungen, Fotos, Videos und Ankündigungen von የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በስዊዘርላንድ የዙሪክ ማህደረ ስብሃት ቅድስት ልደታ ለማርያም, . Bänlistrasse 15, Zürich.

https://youtu.be/GrhPwY07UfA
27/02/2020

https://youtu.be/GrhPwY07UfA

This video is presented to you by Mahtot Tube and Janderebaw Media. © Mahtot Tube is the sole owner of this video and reproduction of this video to any other...

26/12/2017
05/09/2017

✔ አዲስ ዓመት ➌ ✔��እግዚአብሔር የሚወዳችሁ እናንተም የምትወዱት ልጆቼ! አዲሱ ዓመት የእውነት አዲስ ዓመት እንዲኾንላችሁ ካሻችሁ ነፍሳችሁን ከኀጢአት ቀንበር አላቋት እንጂ ድጋሜ በኀጢአት ሸክም አትጫኗት፡፡ አሮጌው ዓመት እንዳለቀ ስታዩ እግዚአብሔርን አመስግኑት፡፡ ወደሌላ ዘመን አሸጋግሯቸዋልና እግዚአብሔርን አመስግኑት፡፡ ልቡናችሁንም ውቀሱት፡፡ በዕሜአችሁ ስንት ጊዜ እያለፈ እንደ ኾነ እያሰባችሁም ራሳችሁን እንዲህ ብላችሁ ጠይቁት፡- “ቀናት እየሮጡ ነው፡፡ ዓመታቱም እየነጐዱ ነው፡፡ የዕድሜዬ መንገድም እየተጋመሰ ነው፡፡ ታዲያ ምን በጐ ምግባር ያዝኩ? ከዚህ ምድር የማልፍበት ቀን እየቀረበ ነው፡፡ ታዲያ ምን የጽድቅ ሥራ ሠራሁ? በዚህ ዕድሜዬ መሥራት የነበረብኝ ምግባር ትሩፋት ዕድሜዬ ሲገፋ ማድረግ አልችልም፡፡ ታዲያ ዕድሜዬ ሲገፋ ማድረግ የማልችላቸውም የጽድቅ ሥራዎች (ፆም፣ ጸሎት፣ ስግደት፣ አገልግሎት፣… ዕድሜ ሲገፋ ይከብዳሉና) እንዳቅሜ እያደረግኩ ነውን?”��ተወዳጆች ሆይ! አዲስ ዓመት ሲመጣ እነዚህን ነገሮች በጥንቃቄ ልናስብባቸው ይገባናል፡፡ ይህን እያደረግንም ስለ ቀጣዩ ዓመት እናስብ፡፡ ይህን የምናደርግ ከኾነ “ቀኖቻቸውም በከንቱ አለቁ፤ ዓመቶቻቸውም በችኰላ” አይባልብንም (መዝ.78፡3)፡፡ ዕለት ዕለት በዓልን እናድርግ ብዬ የገለጥኩላችሁም ይኸው ነው፡፡ የእኛ በዓል ዘወትር መኾን ይገባዋል፡፡ የክርስቲያኖች በዓል በዓመታትና በቀናት ብቻ መወሰን የለበትም፡፡ ቤተ ክርስቲያንም በሳምንት፣ በወር፣ በዓመት የሚከበሩ በዓላት እንዲኖሩ ማድረጓ ዘወትር ከዚሁ ልንርቅ እንደማይገባ ማሳሰቧ እንጂ ሌላ አይደለምና፡፡ ይህን በዓል በየዕለቱ ማድረግም ለኹሉም ይቻላል፤ ለድኻውም ለባለጸጋውም ይቻላል፡፡ በዓልን ለማድረግ (የጽድቅ ሥራን ሠርቶ ሐሴት ለማድረግ) የሚያስፈልገው ቅን ልቡና እንጂ ገንዘብ አይደለምና፡፡ ��ወዳጄ ሆይ! ገንዘብ የለህምን? ፈሪሐ እግዚአብሔርን ገንዘብ አድርግ፡፡ ፈሪሐ እግዚአብሔርን ገንዘብ የምታደርግ ከኾነ ገንዘብ ካላቸው በላይ ባለጠጋ ነህ፡፡ “እንዴት?” ትለኝ ይኾናል፡፡ እኔም እንዲህ ብዬ እመልስልሃለሁ፡- የእነዚያ (የባለጠጐቹ) ገንዘብ ያልቃል፡፡ ያንተ ግን ብል አይበላውም፡፡ ጊዜ አይለውጠዉም፡፡ አያልቅም፡፡ ወደ ሰማያት፣ ወደ ሰማየ ሰማያት፣ ወደ ምድር፣ ወደ አየራት፣ ወደ እንስሳቱ ዓይነት፣ ብዙ የብዙ ብዙ ወደሚኾኑት ዕፅዋት፣ ወደ ደቂቀ አዳም በጠቅላላው፣ ወደ መላዕክት፣ ወደ መላዕክት አለቆች፣ ወደ ኀይላት ተመልከት፡፡ እነዚህ ኹሉ የአምላክህ ፍጥረቶች ናቸው፡፡ የእነዚህን አምላክና መጋቢ ባሪያ መኾን ድኻ መኾን አይደለምና ድኻ አይደለህም ብዬ እነግርሃለሁ፡፡��ተወዳጆች ሆይ! ቀናትን ቈጥሮ በዓል ማድረግ የክርስቲያን ግብር አይደለም፤ የአሕዛብ ግብር እንጂ፡፡ እንዴት? የክርስቲያኖች ተፈጥሮ በቀንና በወር የተገደበ አይደለምና፡፡ አገራችን ሰማይ ነው፡፡ ግብራችን ሰማያዊ ነው፡፡ ኅብረታችንም ከሰማያውያን መላዕክት ጋር ነው፡፡ በዚያ መዓልት ለሌሊት ስፍራውን አይለቅም፡፡ ሌሊትም በተራው ለመዓልት አይለቅም፡፡ እዚያ ኹሌ መዓልት ነው፡፡ እዚያ ኹል ጊዜ ብርሃን ነው፡፡ ስለዚህ “ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ ያለውን እሹ” እንደተባልን ኹል ጊዜ ማሰብ ያለብን ይህንን ነው (ቈላስ.3፡1)፡፡ ክርስቲያናዊ ተፈጥሮአችን ከዚህ ምድራዊ አቈጣጠር በላይ ነው፡፡ በንጽህና በቅድስና እየኖርን ዘወትር በዓልን የምናከብር ከኾነም የዚሁ ዓለም ሌሊት ለእኛ ሌሊት አይደለም፤ መዓልት ነው እንጂ፡፡ ዘመናችንን በሙሉ በገቢረ ኀጢአት፣ በስካር፣ በዘፈን የምናሳልፈው ከኾነ ግን መዓልቱ ለእኛ መዓልት አይደለም፤ ሌሊት ነው እንጂ፡፡ ፀሐይዋ ብትወጣም ልቡናችን ገና በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ይኖራልና ቀን እንደወጣ አይቈጠርም፡፡��~ ሰማዕትነት አያምለጣችሁ መጽሐፍ

05/09/2017

'ኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊነት በውስጧ ምን ይዛለች?'��፨፨፨��ኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊነት ምን ዓይነት ይዘት እንዳላት ብዙ መጽሐፏ ያልደረሰቻቸው ወዳጆቼ በውስጥ መስመር ጠይቀውኝ በቻልኩት መጠን ስመልስ ቆይቻለሁ። ነገር ግን በግል ለብቻ ከመንገር ለኹሉም እንዲሆን ብዬ እዚሁ እንደሚከተለው በአጭሩ ለመግለጽ ሞክሬአለሁ።��ኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊነት የተተረጎመችው Orthodox Spirituality በሚል ርእስ Bishop Hierotheos of Nafpaktos ካዘጋጁት መጽሐፍ ሲሆን፣ እኔ የተረጎምኹት ግሪኩን ሳይሆን Effie Mavromichali የተባሉ ተርጓሚ ወደ እንግሊዝኛ የመለሱትን ቅጂ ነው።��መጽሐፏ በገጽ አነስተኛ ብትሆንም ይዘቷ ግን ጠጠር ያለ ዶግማ ነው።�በዚህ ምክንያትና በመጽሐፏ ውስጥ የተጠቀሱት ጽንሰ አሳቦች እንግዳ እንደሆኑ በመረዳትም በመጽሐፏ መጀመሪያና መጨረሻ ኹለት ምዕራፍ ጨምሬአለሁ። ከትርጉሙ በፊት የጨመርኩትን ምዕራፍ 'መንደርደሪያ ምዕራፍ' ብዬዋለሁ። በዚህ ክፍል የሚከተሉትን ቃላተ-ምሁር ለማስተዋወቅ ሞክሬአለሁ፦�1.ኑስ-Nous-ልቡና�2. ባሕርይና ግብረ-ባሕርይ (Essence /Ousia/ and Energy of God)�3. ቲኦሲስ-Theosis-ሱታፌ አምላክ�4. ሎጊስሞስ-Logismos-መግፍኤ አሳብ�5. ሄሲካዝም-Hesychasm-አርምሞ��ከዚህ በኋላ በቀጥታ ወደ ትርጉሙ በመግባት የደራሲውንና ወደ እንግሊዝኛ የተረጎሙትን ሰው መግቢያዎች አቅርቤአለሁ። ስምንቱ የመጽሐፏ ምዕራፎችና ማጠቃለያው ከዚህ በኋላ ተካተዋል። ከነዚህም የመጀመሪያዎቹ ዐራት ምዕራፎች ጠጠር ስለሚሉ በአትኩሮት መነበብ እንዳለባቸው መጽሐፏን ያነበቧት ወዳጆቼ ገልጸውልኛል። (ምዕራፎቹ ምን ምን እንደያዙ በፎቶው ላይ ካለው ማውጫ ማየት ይቻላል)��የኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊነት ዋና ጽንሰ አሳብ ከልብ (not biological heart) እና ከልቡና ጋር ተፈጥሯዊ ግንኙነት እንዳለው፤ ስለ መንፈሳዊ ደረጃዎች ማለትም ስለ አንጽሆት (Purification - katharsis) ፣ አብርሆት (Illumination - Theoria) ፣ ሱታፌ አምላክ (divinization - Theosis)፤ ስለ ሄሲካዝምና ስለ በርለዓማዊነት፤ በኦርቶዶክሳዊውና በሌሎች 'መንፈሳዊነቶች' መካከል ስላለው መሠረታዊ የትምህርተ ሃይማኖት ልዩነት፤ ባሕታዊ ሰው በሕዝብ መካከል ከሚኖረው ሰው ይልቅ እጅግ ማኅበራዊ (sociable) ስለተባለበት መንፈሳዊ ምሥጢር፤ እመቤታችን ከሐዋርያት ይልቅ ሐዋርያ ስለ መባሏ ምሥጢር፤ ስለ ጸሎተ ልቡና (Noetic Prayer) እና የአባቶች ብቃት፤ ስለ ጋብቻና ምንኩስና ሕይወቶች ...ወዘተ የምታብራራ መጽሐፍ ናት።��ልክ እንደ መንደርደሪያው ምዕራፍ ኹሉ በመጽሐፏ መጨረሻም፣ በመጽሐፏ ውስጥ የተገለጹትን አባቶችና ሊቃውንት እንዲሁም ቦታዎችና ቡድኖችን ለማስተዋወቅ "ማጣቀሻ ምዕራፍ" የሚል ምዕራፍን ጨምሬአለሁ። በማጣቀሻ ምዕራፍ ውስጥ Gregory Palamasን ከመሳሰሉት አባቶች በተጨማሪ ስለ ቅዱሱ ተራራ - Mount Athos ፣ ማሳሊያኖች ስለ ተባሉት መናፍቃን ፣ ስለ ፍራንኮችና ስለ ሌሎችም አጭር ማስተዋወቂያን ለማድረግ ሞክሬአለሁ።��አስቀድሜ እንደ ገለጽኩት መጽሐፏ ጠንከር ያለ ዶግማን በአጭሩ የምታስተዋውቅና የምታስተምር ናት። የኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊነትን ትምህርት ሃይማኖታዊ መሠረት በአንባቢው ውስጥ የምትገነባ ናት። በብዙ ንባቦች ያልተለመዱ የነገረ ሰብእ (Theological Anthropology) ጭብጦች ያሉባትም ናት። ስለዚህ አንባቢ እጅግ በተረጋጋ ልቡና በግንዛቤ እንዲያነባት በትሕትና እጠይቃለሁ።��አንብባችሁም እንደተለመደው ገንቢ አስተያየታችሁን እንደምትሰጡኝ ተስፋ አደርጋለሁ።��መልካም ንባብ!��©ዘሕሊና

04/09/2017

✔ አዲሱ ዓመት - ➋ ✔��ሰነፍ ሰው “ቀኑ ክፉ ወይም መልካም የሚኾነው በእኔ ምክንያት አይደለም” ብሎ ያምናል፡፡ እንዲህ በማመኑም ክፉ ነው ብሎ በሚያስበው ቀን ገቢረ ጽድቅ መሥራት እንደሚቻል አያስብም፡፡ ቢያደርግም ትርጕም እንደሌለው አድርጐ ይቈጥሯል፡፡ የጽድቅ ሥራ ለመሥራት በተመቻቸለት ቀንም ልል ዘሊል ከመኾኑ የተነሣ ምግባር ትሩፋት ለመሥራት አይሽቀዳደምም፡፡ ስንፍናው ምን ዓይነት ጉዳት እንደሚያመጣበት አይረዳም፡፡ ድኅነቱን ሳይፈጽም ዕድሜውን ኹሉ በከንቱ ይገፋል፡፡ እንዲህ ያለ የሥጋም የነፍስም ጕዳት እንደሚያገኘው ዲያብሎስ ዓይነ ልቡናውን ስለሚያሳውርበት ከአጋንንት ወጥመድ ለመሸሽ ዓቅምን ያጣል፡፡��ዲያብሎስም ዕለት ዕለት ይህን እንዳንገነዘብ በተለያየ ማጥመጃ መንገዶች እኛን ለመጣል ይሯሯጣል፡፡ አንዱ መንገድም ስለ ክርስትና ሕይወታችን ግድ እንዳይኖረን ማድረግ ነው፡፡ በዚህም ክርስቲያናዊ ተፈጥሮአችንን ያሳጣናል፡፡ የእግዚአብሔርን ሥራ በገቢር እንድንሰድብ ያደርገናል፡፡ ነፍሳችንን በቆሸሸ ስፍራ ተወሽቃ እንድትቀር ያደርጋታል፡፡��የምወዳችሁ ልጆቼ! እኛ ግን ይህን ልናውቅ ልንረዳ ይገባናል፡፡ በዓለም ላይ ከኀጢአት በቀር ክፉ ነገር እንደሌለ ልናውቅ ልንረዳ ይገባናል፡፡ ከምግባር ከትሩፋት በቀርም መልካም ነገር እንደሌለ ልናውቅ ልንረዳ ይገባናል፡፡ በዚህም ዘወትር እግዚአብሔርን ደስ አሰኝተን ልንኖር እንዲገባን ማወቅ መረዳት ይገባናል፡፡ ��መጠጥ ደስታን አያመጣም፤ ደስታን የሚያመጣው ጸሎት ነው፡፡ ደስታን የምናገነኘው ቃለ እግዚአብሔርን ከመስማት እንጂ ከስካር አይደለም፡፡ ስካር የነፍስ መታወክን ያመጣል፤ ቃሉን መስማት ግን ተመስጦን ያመጣል፡፡ ስካር ሁካታን ያመጣል፤ ቃሉን መስማት ግን ሁካታን ያርቃል፡፡ ስካር ዓይነ ልቡና እንዲጨልም ያደርጋል፤ ቃለ እግዚአብሔር ግን የጨለመው ዓይነ ልቡናችን ብሩህ እንዲኾን ያደርጋል፡፡ ስካር የኀጢአት ጓዝ ይዞ ይመጣል፤ ቃለ እግዚአብሔር ግን አዲስ የሚመጡትን ብቻ ሳይኾን የነበሩትንም ያስወግዳል፡፡�ልጆቼ! የዚህን ዓለም ደስታ ንቆ ሰማያዊ ደስታን እንደ መሻት ያለ ጥበብ ምንም የለም ብዬ እነግራችኋለሁ፡፡ ይህን ገንዘብ የምናደርግ ከኾነ፣ ለሰማያዊ ሕይታችን ቅድሚያን የምንሰጥ ከኾነ የዚህ ዓለም ዝባዝንኬ ቢቀርም አይከፋንም፡፡ አንድ ሰው ባለጸጋ ስለኾነ ቅናት አይይዘንም፡፡ ምንም ምድራዊ ሀብት ባይኖረንም ድኾች እንደኾንን አናስብም፡፡ ባለ ጸጋውን ክርስቶስ የያዘ ሰውስ እንዴት ድኻ ይባላል? በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ ሳይኾን በየዕለቱ በዓል ማድረግ ማለትም ይኸው ነው፡፡��እግዚአብሔር የሚወዳችሁ አንድም እግዚአብሔርን የምትወዱት ሆይ! አንድ ክርስቲያን በዓልን ሲያከብር ሳምንትን ወይም ወርን ወይም ዓመትን ጠብቆ መኾን የለበትም፡፡ ከክርስቲያናዊ ተፈጥሮው ጋር እንደሚስማማ አድርጐ ዕለት ዕለት በዓል ሊያደርግ ይገቧል እንጂ፡፡ ከክርስቲያናዊ ተፈጥሮው ጋር የሚስማማ በዓል ማለትስ ምን ማለት ነው? ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ምን እንደሚለን አብረን እናድምጠው፡- “በቅንነትና በእውነት ቂጣ በዓልን እናድርግ እንጂ በአሮጌ እርሾ በክፋትና በግፍ እርሾም አይደለም” (1ኛ ቆሮ.5፡8)፡፡ ንጽሐ ልቡናን ገንዘብ ያደረገ ሰው ዕለት ዕለት በዓልን ያከብራል፡፡ ተስፋ መንግሥተ ሰማያት የተጠበቀለት ነው፡፡ ከሰማያዊው ማዕድና መጠጥ ተካፍሎ ሐሴት ያደርጋል፡፡ በዚህ ምድር ላይ የሚደረጉ ጊዜያዊ ክንውኖች ስለቀረበት የኾነ ነገር እንደቀረበት አያስብም፤ እርሱ ያገኘው ከዚህ በእጅጉ የሚልቅ ነውና፡፡ ነፍሱን ከሚያቆሽሹ ገቢረ ኀጢአቶች ራሱን ይጠብቃል፡፡��በገቢረ ኀጢአት ተሰማርተን ሳለ ሺሕ ጊዜ በዓላትን ብናከብር ግን እንዳከበርን ልንቈጥረው አይገባንም፡፡ ያከበርነው የበዓል ቀን (በዓል ማለት ደስታ ማለት ነው) ሳይኾን የኀዘን ቀን ነውና፡፡ ነፍሴ በኀጢአት ቀንበር ተይዛ በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ሳለች የደስታን ቀን ባከብር ለእኔ ምን ጥቅም ያመጣልኛል?�~ ሰማዕትነት አያምልጣችሁ መጽሐፍ

* The Departure of St. Malachi, the Prophet.1. The Departure of St. Malachi, the Prophet.On this day, the great prophet,...
04/09/2017

* The Departure of St. Malachi, the Prophet.

1. The Departure of St. Malachi, the Prophet.

On this day, the great prophet, Malachi, one of the twelve minor prophets, departed. He prophesied about the return of the people from captivity in Babylon to Jerusalem. He rebuked the children of Israel because of their transgression against God and His Law. He also admonished them because of their vile offerings, and prophesied about the acceptance of the Gentiles when he said, "For from the rising of the sun, even to its going down, my name shall be great among the Gentiles; In every place incense shall be offered to My name, and a pure offering; For My name shall be great among the nations." (Malachi 1:11) He pointed out to them that they did not give the tithes nor their first fruits, by saying, "'Bring all the tithes into the storehouse, that there may be food in My house, and prove Me now in this,' says the LORD of hosts, 'If I will not open for you the windows of heaven And pour out for you such blessing That there will not be room enough to receive it. And I will rebuke the devourer for your sakes, so that he will not destroy the fruit of your ground, nor shall the vine fail to bear fruit for you in the field,' says the LORD of hosts." (Malachi 3:10-11)

He prophesied about the coming of St. John the baptizer before the Lord, the Savior of the World, by saying, "'Behold, I send My messenger, and he will prepare the way before Me. And the Lord, whom you seek, will suddenly come to His temple, even the Messenger of the covenant, in whom you delight. Behold, He is coming,' says the LORD of hosts." (Malachi 3:1) He also prophesied about the coming of Elijah before the Lord at His second coming, saying, "Behold, I will send you Elijah the Prophet before the coming of the great and dreadful day of the LORD. And he will turn the hearts of the fathers to the children, and the hearts of the children to their fathers, lest I come and strike the earth with a curse." (Malachi 4:5-6)

Having pleased God by his strife, and having completed his days in peace, he departed to God Whom he loved.

May his prayers be with us and Glory be to our God forever. Amen.

03/09/2017

Ethiopian Orthodox Preaching by Megabe Hadis Rodas Tadese about Ethiopian Calendar. Listen to the sibket and learn about Ethiopian New Year. Please share and...

03/09/2017

Ethiopian Orthodox Preaching by Megabe Hadis Rodas Tadese about Ethiopian Calendar. Listen to the sibket and learn about Ethiopian New Year. Please share and...

03/09/2017

✔ አዲሱ ዓመት ➊ ✔�(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)�ልጆቼ! አዲሱ ዓመት የደስታ የሰላምና የጤና እንዲኾንላችሁ ትሻላችሁን? እንኪያስ ገና ከጅመሩ በስካር፣ በዘፈን፣ በገቢረ ኀጢአት ለማሳለፍ አታቅዱ፡፡ የአዲሱ ዓመት የመጀመሪያውን ዕለት ብቻ ሳይኾን እያንዳንዱን ቀን በገቢረ ኀጢአት አትጀምሩት፡፡ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሥራ፣ ምግባር ትሩፋት በመሥራት አሐዱ በሉ እንጂ፡፡ ዕለታት ክፉዎች ወይም ጥሩዎች የሚኾኑት በተፈጥሮአቸው እንደዚያ ኾነው አይደለም፡፡ ዕለቱን ክፉ ወይም ደግ እንዲኾን የምናደርገው እኛው ነን፡፡ የአምናው ማክሰኞ ከዘንድሮ ማክሰኞ የተለየ አይደለም፡፡ የተለየ የሚያደርገው የእኛ ብርታት ወይም ስንፍና ብቻ ነው፡፡�የጽድቅን ሥራ የምንሠራበት ከኾነ አዲሱ ቀን ብቻ ሳይኾን አዲሱ ዓመት ለእኛ መልካም ነው፡፡ ኀጢአት የምንሠራበት ከኾነ ግን ቀኑ ብቻ ሳይኾን አዲሱ ዓመትም ክፉና መከራ የመላበት ይኾንብናል፡፡ አዲሱን ዓመት በበጐ ሥራ የምንጀምረው ከኾነ በዓመቱ በምናደርገው ማንኛውም ክንውን ላይ በጐ ተጽዕኖ ያሳድርብናል፡፡ በትግሃ ሌሊት፣ በቀዊም፣ በጾም በጸሎት እንድንበረታ ስንቅ ይኾነናል፡፡ በስካር፣ በዘፈን፣ በኀዘን የምንጀምረው ከኾነ ግን ዓመቱ ሙሉ እንዲህ የተጐሳቈለ ዓመትን እናሳልፋለን፡፡ ሕይወታችንን በከንቱ እንገፋለን፡፡ ዲያብሎስም ይህን ጥንቅቅ አድረጐ ስለሚያውቅ ዓመቱን በገቢረ ኀጢአት እንድንጀምረው እየቀሰቀሰ ነው፡፡ ፈቃዳችንን አጥፍቶ፣ ዓይነ ልቡናችንን አሳውሮ በዘፈን፣ በስካር፣ በዋይታ እንድንጀምረው በተለያየ መንገድ እየለፈፈ ነው፡፡
ገብረ እግዚአብሔር ኪደ

በሰላም ንጊሣ ለቤተ ክርስቲያን ፤ ወበሰላም ንቁም ቅድሜሃ ፤ ነአምኀ ንበላ በሀ ፤ ምስትሥራየ ኃጥያት የዕቲ ፤ ቅድስት ደብተራ ፡ -     “ ወደ ቤተ ክርስቲያን በሰላም እንገስግስ ፤ በጸ...
03/09/2017

በሰላም ንጊሣ ለቤተ ክርስቲያን ፤ ወበሰላም ንቁም ቅድሜሃ ፤ ነአምኀ ንበላ በሀ ፤ ምስትሥራየ ኃጥያት የዕቲ ፤ ቅድስት ደብተራ ፡ -
“ ወደ ቤተ ክርስቲያን በሰላም እንገስግስ ፤ በጸጥታ ከደጇ እንቁም ፤ እጅ እንንሳት ፤ ሰላም ለኪ እንበል ፤ የኃጢያት ማስተሥረይ ፤ ቅድስት ደብተራ ድንኳን ናት።” (ጾመ ድጓ ዘገብር ኂአር)

Adresse

. Bänlistrasse 15
Zürich
8460

Webseite

Benachrichtigungen

Lassen Sie sich von uns eine E-Mail senden und seien Sie der erste der Neuigkeiten und Aktionen von የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በስዊዘርላንድ የዙሪክ ማህደረ ስብሃት ቅድስት ልደታ ለማርያም erfährt. Ihre E-Mail-Adresse wird nicht für andere Zwecke verwendet und Sie können sich jederzeit abmelden.

Die Kultstätte Kontaktieren

Nachricht an የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በስዊዘርላንድ የዙሪክ ማህደረ ስብሃት ቅድስት ልደታ ለማርያም senden:

Teilen