St. Urael Eotc Switzerland

St. Urael Eotc Switzerland We learn to love and to be loved. We gain in confidence and self esteem. We pray, work and enjoy life together. We are learning to be self-reliant.!!! St.

Who We Are
ተራዳዩ መልዓክ ቅዱስ ዑራኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሉዘርን ስዊዘርላንድ

St. Urael Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Lucerne, Switzerland

በየወሩ የወንጌል ትምህርት: በመላከ ገነት ቆሞስ አባ ኃይለ ጊዮርጊስ Melake Gennet Qomos Aba Haile Georgis በመ/ር ህሩይ እስጢፋኖስ Memhir Hiruy Estifanos

What is the community like? Urael Ethiopian Orthodox Tewahedo Church is open to one & all Ethiopians and non Ethiopians who follow the beliefs of the The Ethiopian Orthodox Tewahedo Church, without any consideration to their political, ethnic or racial affiliations. All are welcome as long as they are coming to worship and not disrupt. It is a place where the word of God is spoken and the congregation comes to worship. What if I'm not a Christian? We all are the children of God.

ተዋሕዶ ሀይማኖታችን ለዘለአለም አለም ፀንታ ትኑርልን!!! ጸልዩ በእንተ ሰላመ ቤተክርስትያን!!! ይህ ቤት (Page) ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተከታይ ወገኖቻችን የመማማርያ መድረክ ይሆን ዘንድ ተከፈተ!

28/09/2025
06/01/2024

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በዓለ ልደትን አስመልክቶ ያስተላለፉት ቃለ በረከት ሙሉ ቃል!!!
++++
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !

- በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣
- ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፣
- የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፣
- በሕመም ምክንያት በየፀበሉና በየሆስፒታሉ ያላችሁ፤
- እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ሁሉ:-

በፍጹም ፍቅሩ እኛን ወደ ሰላም ለማምጣት በእኛ ሰውነት በዚህ ዓለም የተወለደው ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በደኅና አደረሳችሁ!

“ትእምርተ ሰላምነ ወልድ ተወልደ ለነ፤ የሰላማችን ሰንደቅ ዓላማ የሆነው ወልድ ወይም ወልደ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ለኛ ተወለደልን''
(ድጓ ዘቅዱስ ያሬድ)
++++

ዓለም ሁሉ በተለይም የክርስቲያኑ ዓለም በትክክል እንደሚያውቀው ቅዱስ መጽሐፍ በሰዎች የቋንቋ ዘይቤ የተጻፈ የእግዚአብሔር ቃል ነው። በመንፈሳዊም ሆነ በዓለማዊ ርእዮት ቋንቋ የመልእክት ማስተላለፊያና መግባቢ መሳሪያ እንደሆነ ይታወቃል። እግዚአብሔርም ከጥንት ጀምሮ መልእክቱን በዚህ መንገድ ለሰዎች ሲያስተላል ኖሮአል። የሚያስተላልፈውም መልእክት እንዲሁ ተሰምቶ እንዲቀር ሳይሆን እንዲታወቅ፣ እንዲታመን እንዲተገበርና ሰዎች እንዲጠቀሙበት ነው። ከሚፈለገው ጥቅም ለመድረስም ሰዎች መልእክቱን በሚገባ መረዳት የግድ ይሆናል። ሰዎች እንዲረዱት ደግሞ በቋንቋቸውና በባህላቸው ዘይቤ ሊነገራቸው ይገባል።

በመሆኑም እግዚአብሔር ቃሉን በሰዎች ቋንቋ ባህላዊ ዘይቤ መልእክቱን ለዓለም ሲያስተላልፍ ኖሮአል። ቤተ ክርስቲያንም ይህንን መሠረት አድርጋ የእግዚአብሔርን ቃል በሰው ቋንቋ ዘይቤ ታስተምራለች። ከዚህ አንጻር በሰው ልማዳዊ የዘይቤ ቋንቋ ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም "የሰላም ሰንደቅ ዓላማ" የሚል ቅፅል ተሰጥቶታል። ምክንያቱም ንጉሥም ወታደርም ተራው ሕዝብም የሀገሩ ነጻነትና ክብር፤ አንድነትና ሉዓላዊነት ምልክት የሆነውን ሰንደቅ ዓላማ ተከትሎ ሥራ ይሠራል፣ ክብሩንም ይገልፃልና ነው። ተከተል አለቃህን ተመልከት ዓላማህን የሚለው ብሂልም ይህንን ያንፀባርቃል።

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን! ምእመናንና ምእመናት!

ጌታችን በመድኅንነቱ የሁላችን የሰላም ሰንደቅ ዓላማ በመሆኑ መምህራችን ቅዱስ ያሬድ "የሰላማችን ሰንደቅ ዓላማ የሆነ ልጅ ተወለደልን" ብሎ ይገልፀዋል። ጌታችን በዛሬው ዕለት በቤተልሔም ሰውነታችንን ሰውነት አድርጎ መወለዱ ራሱ የሰላም ማሳያ ምልክት ነው። ምክንያቱም ሳይወደን አይቀርበንም፤ አይዋሐደንምና ነው። በልደቱ ዕለት "ለዕጓለ እመሕያው ሠምሮ፤ የሰው ልጅን ወደደው" ተብሎ በቅዱሳን መላእክት የተዘመረበትም ምክንያት ይኸው ነው።

እንደ እውነቱ ከሆነ ጌታችን የተዋሐደው ሰውነት የወዳጁ አልነበረም። የጠላቱ እንጂ። ቅዱስ መጽሐፍ ይህንን ሲገልፅ "ጠላቶቹ ሳለን እግዚአብሔር በልጁ ሞት ታረቀን" ይላልና ነው። በዚህ ዓለም የኖረውም ከሚያሳድዱት፣ ከሚከሱት፤ ስሙን ከሚያጠፉና ሊገድሉት ከሚከጅሉ ጋር እንጂ ከወዳጆቹ ጋር ብቻ አልነበረም። እሱ ግን ሁሉንም በፍቅር ይቀበል ነበረ። ይፈውስና ያድን ነበረ። ያስተምርም ነበረ። ለሁሉም ሥርየተ ኃጢአትን ሰጠ። ለጠላቶቹም ጸለየ። ጌታችን በዚህ ሁሉ ለኛ አርእያና የተግባር መምህር በመሆኑ የሰላም ሰንደቅ ዓላማችን ነው።

ምእመናንና ምእመናት!

ዓለም በጌታችን ዕለተ ልደት የተዘመረውን ሰማያዊውን የሰላም መዝሙር መዘመር ከጀመረች እነሆ ዛሬ ድፍን ሁለት ሺሕ ዐሥራ ስድስት ዓመት ሆነ። የሰላሙ መዝሙር ዛሬም በመላው ዓለም በሚገኙ ክርስቲያኖች ይዘመራል። ይሁን እንጂ በዚህ ዓለም ሰላም ሰፍኖ እየታየ አይደለም። ይህ ለምን ሆነ ቢባል ደምበኛ መልስ ሊሆን የሚችለው እግዚአብሔርን አለማመንና አለመፍራት ያመጣው ችግር ነው የሚል ነው። ምክንያቱም ሃይማኖትና ፈሪሐ እግዚአብሔር ከሌለ ፍትሕ ይጎድላል፣ ፍትሕ ከጎደለ ብሶት ይፈጠራል። ብሶት ካለ ሰላም ሊኖር አይችልም።

በሁሉም የዓለማችን ክፍል ሃይማኖትና ፈሪሐ እግዚብሔር እየተዘነጋ በመሄዱ ቀውሱ ተባብሶ ይታያል። የሰው ልጅ ኑሮ በየትም ይሁን በየት በስጋት የተሞላ ሆኖአል። የሚወራው ሁሉ ስለ ግጭት፣ ስለ አየር ብክለት፣ ስለ ረኃብና እልቂት ሆኖአል። ዓለም የጉልበተኞችና የባለ ሀብቶች ብቻ እንድትሆን የተፈጠረች እስክትመስል ድረስ ከባድ የፍትሕ መዛባት አጋጥሞአታል። የዝቅተኛው ማኅበረሰብ ሰብአዊ መብት ተዘንግቶአል። ከዚህ አኳያ ዓለም በዚህ እስከ ቀጠለች ድረስ ሰላም የማግኘቷ ዕድል በጣም አጠራጣሪ ነው። የክርስቶስ ልደት ያስተማረን ግን እንደዚህ አልነበረም።

ጌታችን የተወለደው በተዋበና ምቹ በሆነ የሀብታም ቤት ሳይሆን በከብቶች በረት ነበረ። የተገለጠውም ለባለሥልጣኖች ሳይሆን ዝቅተኞች ለሚባሉ እረኞች ነበረ። ልዑላኑ ሰማያውያንና ትሑታኑ ምድራውያንን በአንድነት አገናኝቶ ስለ ሰላም በጋራ እንዲዘምሩ አደረገ። አሳዳጅ ሳይሆን ተሳዳጅ ሆኖ በግብጽ አገር በመንከራተት አደገ። ይህን ሁሉ ያደረገው እኛ እሱን እያየን እንደ ሰንደቅ ዓላማ እንድንከተለው ነበር። ጌታችን ከባለሥልጣናቱና ከባለሀብቶቹ ይልቅ በድሆቹ ደረጃ የተወለደው ለድሆቹና ለዝቅተኞቹ ትኩረት እንድንሰጥ ለማስተማር ነው። የእኛ ድርጊት ግን ግልባጩ ሆኖ እየተስተዋለ ነው፡፡

እጅግ የሚያሳዝነው ደግሞ ክርስቲያን ነኝ ብሎ፤ በስመ እግዚአብሔር ተሰይሞ፤ መስቀልን በአንገቱ ተሸክሞ የእሱ መሰል በሆነው ወይም መስቀል በተሸከመው ወንድሙ እና እኅቱ እንዲሁም በመሰል ፍጡር ላይ ያለ ርኅራኄ ሲጨክን መታየቱ ነው። እንዲህ እየሆነ እንዴት ሰላም ይምጣ? እግዚአብሔርስ እንዴት በረከቱን ይሰጣል? ይህ እጅግ በጣም ሊታሰብበት የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!

እኛ ኢትዮጵያውያን ከእንዲህ ዓይነቱ የሃይማኖትና የሞራል ዝቅጠት በአስቸኳይ መውጣት አለብን። ጠቡ፤ መለያየቱ፣ መጨካከኑ፤ ለኔ ለኔ መባባሉን ከረምንበት። ሆኖም ያመጣልን ነገር ቢኖር ሁለንተናዊ ውድመት ብቻ ነው። ያስገኘልን ትርፍ ይህ መሆኑን እያወቅን በዚሁ ልንቀጥል አይገባም። ሰው ችግሩን በልቡ እያወቀ፣ በዓይኑ እያየ እንዴት ገደል ውስጥ ይገባል? ዕርቅና ይቅርታ ማንን ጎዳ? ሰላምና አንድነት ማንን አከሰረ? ሰበብ አስባብ እየተፈለገ በሆነውም ባልሆነውም ከመተላለቅ ለምን ኢትዮጵያ የሁላችን ናት ብለን በእኩልነትና በስምምነት መኖር አቃተን?

ሦስት ሺሕ ዘመናት አብረው የኖሩ ሕዝቦች እንዴት ችግራቸውን በጠባይና በብልሐት ማስወገድ አቃታቸው? ይህ ከቶ ሊሆን አይገባ። ሁላችንም ሰከን ብለን እናስብ። ለሁሉም የማሰቢያና የመመካከሪያ ጊዜ ፈጥረን ችግሩን በስፍሐ አእምሮ እንፍታው። ችግርን በምክክርና በይቅርታ መፍታት አማራጭ የሌለው ጥበብ ነው። የሃይማኖት መሪዎች፤ የሀገር ሽማግሌዎች፤ ምሁራንና ልኂቃን በዚህ ተግተን ልንሠራ ይገባል። መንግሥትና የፓለቲካ ፓርቲዎችም ለዚህ የበኩላቸውን ድጋፍ ያድርጉ። በዚህም ሰላማችንን እንመልስ፡፡

በመጨረሻም፡-

በአሁኑ ጊዜ በሀገራችን በተከሠተው የድርቅና የሰው ሰራሽ ምክንያት በችግር ላይ የወደቁ ወገኖች በርካታ ናቸው። በመሆኑም የወገን ደራሽ ወገን ነውና ሁሉም ካለው ብቻ ሳይሆን የቀን ቍርሱን ለተቸገሩ ወገኖች እንዲለግስና በመተጋገዝ ረኃቡን እንድንከላከለው ጥሪያችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፡፡

መልካም የልደት በዓል ያድርግልን። እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!! ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!! አሜን።
+++

አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ

Adresse

Moosmattsrasse 13
Lucerne
6000

Benachrichtigungen

Lassen Sie sich von uns eine E-Mail senden und seien Sie der erste der Neuigkeiten und Aktionen von St. Urael Eotc Switzerland erfährt. Ihre E-Mail-Adresse wird nicht für andere Zwecke verwendet und Sie können sich jederzeit abmelden.

Die Kultstätte Kontaktieren

Nachricht an St. Urael Eotc Switzerland senden:

Teilen