Citizens Of God Kingdom

Citizens Of God Kingdom Citizens Of Gods Kingdom Church

13/02/2024
የመንግስት አካል ሕዝብን ሆን ብሎ በጅምላ ሲበድል እጥፍ በደል ይሆናል። በአዲሱ የማዕካላዊ ኢትዮጵያ ክልል መዋቅር ለሰፊው የከምባታ ጠምባሮ ዞን ሕዝብ አንድ መሥሪያ ቤት ብቻ ተሰጥቶ ለተቀሩ...
04/08/2023

የመንግስት አካል ሕዝብን ሆን ብሎ በጅምላ ሲበድል እጥፍ በደል ይሆናል።

በአዲሱ የማዕካላዊ ኢትዮጵያ ክልል መዋቅር ለሰፊው የከምባታ ጠምባሮ ዞን ሕዝብ አንድ መሥሪያ ቤት ብቻ ተሰጥቶ ለተቀሩት ሁሉም ከ3 እስከ 12 እና ከዚያም በላይ መ/ቤቶች የተመደቡበት አሰራር ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየር "Injustice anywhere is a threat to justice everywhere" ያለውን ወርቃማ አባባል እንዳስታውስ አድርጎኛል።

ይህ አድሎአዊ ውሳኔ በከምባታ ጠምባሮ ዞን ተወላጆችና ሕዝብ ላይ ከፍተኛ ድንጋጤ ፈጥሯል። ሁሉንም ነገር ለመገኖ (ለእግዚአብሄር) እና ለመንግሥት (ለሕግ) ትቶ በተሰማራበት መስክ ሁሉ ተግቶ መሥራትን ብቻ ሕይወቱ ያደረገው ሕዝብ እንዲህ አይነቱን ግልፅ ንቀትና ያገጠጠ ኢፍትሃዊነት ከመንግሥት ከቶውኑም ስለማይጠብቅ፤ አሁን የሰማዉ ወሬ ዱብእዳ ሆኖበታል።

በመረበሽ ስሜት በዞኑ ተወላጆች የሚጻፉ ሃሳቦች በሶሻል ሚዲያ ሲዘዋወሩ ስለተመለከትኩ የተበታተነውን ሃሳብ ለመሰብሰብ ቢረዳ በማለት ጥቂት ነጥቦችን በግሌ ለመሰንዘር ወደድኩ።

1ኛ። ለከምባታ ጠምባሮ ዞን አንድ መ/ቤት ብቻ ከመመደቡ ጋር የሆሣዕና ማእከል መሆን ምንም ግንኙነት የለውም። ብዙ የሃዲያ ልጆች የከምባታ ጠምባሮ ሕዝብን መበደል እንደማይደግፉና ድምጽ ሊሆኑለት እንደሚችሉ አምናለሁ። እየሆኑም ያሉ አሉ። የሆሳዕና ማዕከልነት በደምና በባህል የተጋመዱትን የከምባታ ጠምባሮና የሃዲያ ሕዝቦችን ይበልጥ የሚያቀራርብ እና በአካባቢው ኢኮኖሚያዊ ትስስር የሚያጠናክር ነው። የከምባታ ጠምባሮ ተወካዮች ለሆሳዕና ማእከልነት ድምጻቸውን አሰምተዋል። ይህም ተገቢ ነው። ስለዚህ በዚህ ዙሪያ አላስፈላጊ ሃሳቦችንና አስተያየቶችን ከመስጠት መቆጠብና በችግሩ ትክክለኛ ምንጭ ላይ ማተኮሩ ፍሬያማ ይሆናል።

2ኛ። ለከምባታ ጠምባሮ ዞን አንድ ቢሮ ብቻ ስለተመደበ የዞኑን አመራሮችና ተወካዮች መሳደቡና ማውገዙ ችግሩን አይፈታውም። ሐዋሳ በተደረገው ስብሰባ ላይ ቀደም ተብሎ በእነርስቱ የተወሰነው 'የክላስተር' ውሳኔ ነዉ የተነበበው። እንዲህ አይነቱን ግልጽ መድሎአዊ ውሳኔ ያሳለፉ ወገኖች የሚፈለጉት የዞኑ ሕዝብ እርስ በርስ እየተወጋገዘ ድምጽ አልባ እንዲሆንና ለበለጠ ውርዳት ተጋላጭ እንዲሆን ስለሆነ የሁሉም (የዞኑ አመራሮችና ተወካዮች ጭምር) ትኩረት የዚህ ውሳኔ ባለቤት በሆነው አካል ላይ መሆን ይኖርበታል።

3ኛ። የከምባታ ጠምባሮ ሕዝብና ፍትሃዊ አስተሳሰብ ያላቸው ዜጎች ሁሉ አምርረው መቃወም ያለባቸው አቶ ርስቱ ይርዳው ያደረገውን ሕገወጥ ድርጊት ነው።

ሀ/ በአዲሱ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን ልክ እንደ ሃዲያ፤ ስልጤ፤ ሃላባ፤ ከምባታ ጠምባሮ 1 (አንድ) ዞን ነው። አቶ ርስቱ ግን "ወልቂጤ ክላስተር" እና "ቡታጂራ ክላስተር" በማለት በግልጽ 2 ዞን አድርጎታል። ይህ በማንኛውም መስፈርት ተቀባይነት የሌለዉ ሕገወጥ ድርጊት ነው። ይህን አሰራር መንግስት እንኳን ጆሮ ዳባ ብል በፍርድ ቤትም በሕግም challenge ማድረግ የሚቻል ነው። አንድን ዞን ክላስተር ብሎ 2 ቦታ መክፈል ቢያስፈልግ ኖሮ ከኩታ ገጠሙ የጉራጌ ዞን ይልቅ የሃዲያ ዞንን "የሆሳዕና ክላስተር" "የሾኔ (ባዳዋቾ) ክላስተር"፤ የከምባታ ጠምባሮ ዞንን "የዱራሜ ክላስተር" "የሙድላ ክላስተር" ማለቱ ከመልክዓ ምድር ርቀት አኳያ ትርጉም ሊሰጥ ይችላል።

ለ/ የፈራሹ ደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት አንድን ዞን "የወልቂጤ ክላስተር" "የቡታጅራ ክላስተር" በማለት ለ2 ከመክፈሉም ባሻገር በእነዚህ 2 ክላስተሮች ብቻ ከ12 በላይ ትላልቅ መ/ቤቶች እንዲታጨቁ አድርጓል። በአንጻሩ ለሰፊውና ሰላማዊው የከምባታ ጠምባሮ ዞን አንድ ብቻ ወርውሯል።
እጅግ የገረመኝ ይህንን ግልጽ ፍርደ ገምድልነት እያዩ ምንም ሳይቆራቁራቸው ያጸደቁ የደቡብ ክልል፤ የብልጽግና ፓርቲና የፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ አካላት ናቸው። ሕልናቸው ባይቆረቁር እንኳ ዘወትር ከአፋቸው የማይለዩት 'ፍትህ' 'እኩልነት' 'ህብረብሄራዊነት' የሚሉ ጽንሰ ሃሳቦች እንዴት ትዝ አላላቸውም? ይህ አሳዛኝ ክስተት የሚያሳየው ጽንሰ ሃሳቦቹ የማይተገበሩ ተራ ቃላቶች መሆናቸውን ነዉ።

ሐ/ ከሁሉም በላይ 12ቱም የጉራጌ ዞን መ/ቤቶች "ሥራ ፈጣሪና ተጽዕኖ ፈጣሪ" የመሰረተ ልማትና የኢኮኖሚ አንቀንቀሳቃሾች ናቸው። በአንጻሩ የክልሉ መቀመጫ የሆነው "የሆሳዕና ክላስተር" ቢሮዎች ብዛት በፖለቲካ ካልሆነ በስተቀር በሥራና ልማት ረገድ የሚያመጡት ፈይዳ እስከዚህም ነው።

4ኛ። የከምባታ ጠምባሮ ዞን በኢህአዴግ ዘመን እንደ ተቃዋሚ ተቆጥሮ ምንም አይነት ልማትና ኢንቨስትመንት እንዳይኖረውና ለሌሎች መቀጣጫ ሆኖ እንዲታይ የተደረገ፤ አንድ የኤሌክትሪክ ሰብስቴሽን እንኳ የሌለው፤ ሁሉም ነገር በደርግ ዘመነ መንግሥት በነበረበት የሚገኝ በኢትዮጵያ ማእከላዊ መንግሥት ከተበደሉት ሕዝቦች መካካል በግንባር ቀደምትነት የሚሰለፍ አካባቢ ነው።

በመሆኑም ለውጡ እንደመጣ ከሁሉም ቀድሞ ለለውጡና ለዶ/ር አቢይ ያለውን ድጋፍ በአደባባይ የገለጸ ሕዝብ ነው። ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም. በአዲስ አባባ ለዶ/ር አቢይ ድጋፍ ሰልፍ በተደረገበት እለት የከምባታ ጠምባሮ ሕዝብ ግልብጥ ብሎ በመውጣት በዱራሜ ከተማ ደማቅ ሰልፍ አድርጓል። በታሪክ አጋጣሚ በዚያች እለት እኔም ዱራሜ ስለነበርኩ ከማለዳዉ 6 ሰአት ጀምሮ የሚተምመውን ሕዝብና ሰልፍ በአይኔ አይቻለሁ። ኮርቻለሁ። የለውጡ መንግሥት ሕልውና ገና ባልጸናበትና የደቡብ ክልል አመራር ሁኔታዉን አድፍጦ ማየትን በመረጠበት በዚያች ሰዓት የወቅቱ የከምባታ ጠምባሮ ዞን አስተዳዳሪ ቆራጥ ውሳኔ አድርጎ (risk ወስዶ) ለለውጥ የተጠማውን ሕዝብ አደባባይ ይዞ መውጣቱ ራሱን የቻለ ታሪክ ነው። በዚያች እለት ኢትዮጵያ ውስጥ ከአዲስ አበባና ከዱራሜ ውጭ ሌላ ቦታ የድጋፍ ሰልፍ ለመደረጉ እርግጠኛ አይደለሁም።

ይህ ታሪክ ታዲያ በትናንትናው እለት የብልጽግና ፓርቲ ም/ ፕሬዚዳንት የተገኙበት የሐዋሳ ስብሰባ ካሳለፈው የከምባታ ጠምባሮ ሕዝብን የመናቅ ውሳኔ ጋር ሊጣጣምልኝ አልቻለም። አንድን ሕዝብ በጅምላ ለመቅጣት መንቀሳቀሱ በግሌ ወንጀል መስሎ ብሰማኝ አትፍረዱብኝ። ይህን ውሳኔ ያሳለፉ ወገኖች እንደገና ያጤኑታል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።

5ኛ። የከምባታ ጠምባሮ ሕዝብ እንደማንኛውም የክልሉ ሕዝብ ግብር የሚከፍል፣ ሕግና ሥርዓትን የሚያከብር፤ አካባቢውን ሊያለማ ደፋ ቀና የሚል፤ ተመጽዋችነትን በታሪኩ የማያውቅና የሚጸየፍ ሕዝብ ነው። ስለዚህም ለክልሉ የሀብት ተጠቃሚነት ከሁሉም ዞኖችና ሕዝቦች ጋር እኩል መብት ያለው ሕዝብ ነው። አቶ ርስቱም ሆነ ሌላ ሰው ሲፈልግ የመስጠት፤ ሲያሻው ደግሞ የመንሳት ምንም አይነት ልዩ መብት ወይም ሥልጣን የላቸዉም። የከምባታ ጠምባሮ ሕዝብ ሲጠይቅ የኖረውም፤ አሁን የሚጠይቀውም የድርሻዉን ዉ። ድርሻው ደግሞ የችሮታ ሳይሆን የዜግነት መብት ነው። የግብር ከፋይነት መብት ነው። በሕግ ፊት እኩል የመታየት መብት ነው። አድሎአዊነትንና ኢፍትሃዊነትን የመቃወምና እኩልነትን የመጠየቅ መብት ነው።

6ኛ። አቶ ርስቱ የሚመራዉ የደቡብ ክልል ፈርሶ ሁለት ክልሎች ስለተመሰረቱ የአቶ ርስቱ ፕሬዚደንትነትም አብቅቷል። ወላይታ ሶዶን ያማከለዉ “የደቡብ ክልል” እና ሆሳዕና ን ያማከለዉ “የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል” በቅርቡ አዳዲስ ፕሬዚደንቶች ይኖሩአቸዋል። አቶ ርስቱ ከመሰናበቱ በፊት ግን በሕገወጥ መንገድ 2 ዞን አድርጎ ካግበሰበሳቸዉ መ/ቤቶች መካከል ጥቂቶቹን ለከምባታ ጠምባሮ ዞን
መመለስ ይኖርበታል። ለዚህም ሁሉም ድምፅና ድጋፍ ሊሰጥ ይገባል እላለሁ።

ሰላምና እድገት ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል!

26/06/2023

Singer Amen!!
# be blessed #

Adresse

123 Christoffile Pretoria West
Democratic Republic Of The
18836

Téléphone

+27736181977

Site Web

Notifications

Soyez le premier à savoir et laissez-nous vous envoyer un courriel lorsque Citizens Of God Kingdom publie des nouvelles et des promotions. Votre adresse e-mail ne sera pas utilisée à d'autres fins, et vous pouvez vous désabonner à tout moment.

Contacter Le Lieu De Culte

Envoyer un message à Citizens Of God Kingdom:

Partager