Ahaw Church Of Christ Toronto Local Congregation

Ahaw Church Of Christ Toronto Local Congregation Orthodoox Reformed Church

11/03/2023

"መዳናችሁን ፈጽሙ"
ፊልጵስዩስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹² ስለዚህ፥ ወዳጆቼ ሆይ፥ ሁልጊዜ እንደ ታዘዛችሁ፥ በእናንተ ዘንድ በመኖሬ ብቻ ሳይሆን ይልቁን አሁን ስርቅ፥ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ፤
¹³ ስለ በጎ ፈቃዱ መፈለግንም ማድረግንም በእናንተ የሚሠራ እግዚአብሔር ነውና።

08/03/2023

መዝሙር 119
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁹⁷ አቤቱ፥ ሕግህን እንደ ምን እጅግ ወደድሁ! ቀኑን ሁሉ እርሱ ትዝታዬ ነው።
⁹⁸ ለዘላለም ለእኔ ነውና ትእዛዝህ ከጠላቶቼ ይልቅ አስተዋይ አደረገኝ።
⁹⁹ ምስክርህ ትዝታዬ ነውና ካስተማሩኝ ሁሉ ይልቅ አስተዋልሁ።
¹⁰⁰ ትእዛዝህን ፈልጌአለሁና ከሽማግሌዎች ይልቅ አስተዋልሁ።
¹⁰¹ ቃልህን እጠብቅ ዘንድ ከክፉ መንገድ ሁሉ እግሬን ከለከልሁ።
¹⁰² አስተምረኸኛልና ከፍርድህ አልራቅሁም።
¹⁰³ ቃልህ ለጕሮሮዬ ጣፋጭ ነው፤ ከማርና ከወለላ ይልቅ ለአፌ ጣፈጠኝ።
¹⁰⁴ ከትእዛዝህ የተነሣ አስተዋልሁ፤ ስለዚህ የሐሰትን መንገድ ጠላሁ።
¹⁰⁵ ሕግህ ለእግሬ መብራት፥ ለመንገዴ ብርሃን ነው።

አልተዋችሁም.  . . . . .
07/25/2023

አልተዋችሁም. . . . . .

07/24/2023

ጨለማን አስወግዶ በዓለም ላይ ብርሃኑን ያበራ ደግሞም የዓለም ብርሃን እንድንሆን በውስጣችን የበራ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ በስጋ የተገለጠበት ዓላማ በዓለሙ ላይ ነግሶ የነበረውን ኃጢአት ለማስገውገድ መሆኑን መጽሐፍ እንዲህ ይላል፡- " እርሱም ኃጢአትን ሊያስወግድ እንደ ተገለጠ ታውቃላችሁ፥ በእርሱም ኃጢአት የለም።" (1ኛዮሐ3፥5) መጽሐፍ ቅዱስ የኅጢአትን ምንነት ሲገልጥ፡- "ኅጢአት ዓመጽ ነው"(1ዮሐ3፥4) ይላል። ዓመጽ ደግሞ አልታዘዝ ባይነት፡ እንቢታን በተጻራሪነት መቆምን ... ወዘተ የሚያመለክት ቃል ነው ። ሰለዚህ ኅጢአት በዋናነት በእግዚኣብሔር፡ እንዲሁም እርሱ በሰጠው ሕግና ትእዛዝ ላይ የሚደረገውን ዓመጽ ያሳያል። "ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ" እንደሚባለው ሰው እግዚአብሔር በሰጠው ሕግና ትእዛዝ ላይ የሚያምጸው አስቀድሞ በእግዚአብሔር ላይ ስላመጸ ነው ብሎ መደምደም ይቻላል። እግዚኣብሔር ኅጢአትን በመስራት ከመንግስቱ የኮበለለውን ዓለም በክርስቶስ ወደ መንግስቱ ለመጠቅለል ፡ በኅጢአት ለተያዘው መዳንን ለማወጅ ልጁን ወደ ዓለም ላከ ፡ በልጁ ስራ ሁላችንም፡ መዳንን አገኘን ፡ መጽሐፍም ፡- "እኛም አይተናል አባትም ልጁን የዓለም መድኃኒት ሊሆን እንደ ላከው እንመሰክራለን።" (1ኛ ዮሐ4፥14) ይላል። ከኃጢአታችን ስርየት ከበደላችንም ይቅርታንን እና ምሕረትን ያገኘውን በራሳችን ስራ ሳይሆን እግዚኣብሔር እኛን ለማዳን በገለጠው ጸጋ ነው ። የዳነው በጸጋው ነው "ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤ በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ።"(ሮሜ3፥23-24) እግዚኣብሔር የገለጠው ጸጋ ለሰው ሁሉ መዳንን የሚሰጥ ነው ፡ መጽሓፍም እንድህ ይላል ፡- " ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤" (ቲቶ2፥11)። እንግዲህ እግዚአብሔር ሰዎችን ለማዳን የገለጠው ጸጋ ምንድን ነው? በእቅፉ የሚኖረውን አንድያ ልጁን ለሞት አሳልፎ ቤዛ ኃጢአት በመስጠት ነው። እንግድያስ መዳናችን ለኛ እንዲሁ በጻጋው ቢሆንም፡ ያስከፈለው ዋጋ ግን እጅግ ታላቅ ነው። ኃጢአት ያስከፈለው ዋጋ ካወቅን ክርስቶስም ስለኃጢኣት መሞቱን ከተረዳን፡ እግዚአብሔር በኃጢኣት ላይ ያለውን የጸና አቅዋም ለመረዳት አይዳግተንም ። ደግሞም የተገለጠው የእግዚኣብሔር ጸጋ መዳናችንን ለመፈጸም ራሱን ቤዛ አድርጎ ሰጥቷል እንዲሁም ራሳችንን እንዴት ለእሱ መቀደስ እንዳለብን ደግሞ እንዲህ ሲል ያስተምረናል፡- "ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊ ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፤"(ቲቶ2፥12-13) ስለዚህ እኛ በታላቅ ዋጋ የተገዛን የክርስቶስ ነን ፡ ደግሞ ራሳችን ለእግዚአብሔር መቀደስ እናም ለእግዚአብሔርር የተለየን ከዓለሙ ሃሳብ እና ስራ ከመተባበር የጸዳን መሆን እንዳለብን የእግዚአብሔር ቃል አበክሮ የሚያስተምረን እውነት ነው። ጌታ መንፈስ ቅዱስ ይርዳን።

07/24/2023

"እግዚአብሔር ብርሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም"(1ኛዮሐ1፥5)
ብርሃን ፡- ቅድስናን እና ጽድቅን
ጨለማ ፡- ኃጢአትን እና ዓመጽን ይወክላል። በክርስቶስ ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ የብርሃን ልጅ ተብሎ ይጠራል። መጽሐፍም እንዲህ ይላል፡- "ሁላችሁ የብርሃን ልጆች የቀንም ልጆች ናችሁና። እኛ ከሌሊት ወይም ከጨለማ አይደለንም" (1ኛተሰ5፥5)። የእግዚኣብሔር ልጅ ወደ ዓለም የመጣው በጨለማ ላይ የሚያበራ እውነተኛ ብርሃን ሆኖ ነው ፡ "ደግሞም ኢየሱስ እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም ብሎ ተናገራቸው" (ዮሐ 8:12) ተብሎ እንደተጻፈ። ስለዚህ ከብርሃን የተወለድነው እኛ የብርሃን ልጆች ከሆንን እኛም ደግሞ ብርሃን ነን ፡ ብርሃናችን ግን የራሳችን ሳይሆን በህይወታችን ውስጥ የሚበራ የክርስቶስ ብርሃን ነው። መጽሐፍም "እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ"(ማቴ5፥14) ይላል። ደግሞም " መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።"(ማቴ5፥16) ፡ ሲል በብርሃን የሚወከለውን መልካሙን ሥራ በመስራት ራሳችንን ለእግዚአብሔር በቅድስና በመለየት እንደ ብርሃን ልጆች እየተመላለስን ብርሃናችንን በሰው ሁሉ እንድናበራ መጽሐፍ ያስተምረናል።
- ኢሄውላቹህ ወገኖቼ ዛሬ የጌታ መምጫ በእጅጉ የተቃረበበት ዘመን ላይ እንዳለን ከማንም የተሰወረ አይደለም፡ አሁን ራሳችንን የምንመለከትበት ህይወታችንን የምንፈትሽበት ግዜ ነው፡ በክርስቶስ ያገኘነው አርነት ከክብር ወደክብር የምንሸጋገርበት ፡ የጌታን መምጣት እየተጠባበቅን ራሳችንን ለእግዚኣብሔር የምናስገዛበት ጸጋ ነው፡- "እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም። በክርስቶስ ኢየሱስ ያለው የሕይወት መንፈስ ሕግ ከኃጢአትና ከሞት ሕግ አርነት አውጥቶኛልና። "(ሮሜ8፥1-2) ነገር ግን ኋጢአት በባህርያችን ስፍራ አግኝቶ ከሆነ ምልልሳችን አምልኮታችን ከንቱ ይሆንብናል፡ ስለዚህ መጽሐፍ እንዳለ፡-" አርነት ወጥታችሁ እንደ እግዚአብሔር ባሪያዎች ሁኑ እንጂ ያ አርነት ለክፋት መሸፈኛ እንዲሆን አታድርጉ።" (1ኛጴጥ2፥16) በጸጋው ላዳነን ጌታ ራሳችንን እንድናስገዛ፡ መንፈስ ቅዱስ ይርዳን ።

07/24/2023

Our vision is to see the Orthodox Church, which serves God's ideas revealed in the Bible, renewed by His word and spirit, fulfilling its mission throughout the world.

ራእያችን ፦ በመጽሐፍ ቅዱስ የተገለጠውን የእግዚአብሔር ሃሳብ የምታገለግል በቃሉና በመንፈሱ የታደሰች ኦርቶዶክሳዊት ቤተ-ክርስቲያን በመላው ዓለም ተልዕኮዋን ስትፈጽም ማየት ነው።
07/23/2023

ራእያችን ፦
በመጽሐፍ ቅዱስ የተገለጠውን የእግዚአብሔር ሃሳብ የምታገለግል በቃሉና በመንፈሱ የታደሰች ኦርቶዶክሳዊት ቤተ-ክርስቲያን በመላው ዓለም ተልዕኮዋን ስትፈጽም ማየት ነው።

Address

Toronto, ON

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ahaw Church Of Christ Toronto Local Congregation posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Ahaw Church Of Christ Toronto Local Congregation:

Share