Aba Yonas word of God Preaching Page

Aba Yonas word of God Preaching Page To preach and teach the word of God for the people

የአዲስ ዓመት መልዕክትአስብያለሁ አደርግማለሁ ( ትንቢተ ኢሳይያስ 46 : 11 )
01/01/2024

የአዲስ ዓመት መልዕክት

አስብያለሁ አደርግማለሁ ( ትንቢተ ኢሳይያስ 46 : 11 )

Check out Apostle Aba Yonas Getaneh's video.

01/01/2024

የአዲስ ዓመት መልዕክት
አስቤያለሁ አደርግማለሁ ( ትንቢተ ኢሳይያስ 46 : 11 )

12/08/2023

ኮመድያን እሼ ምሳና እራት መሆን ይችላልን

ይህንን መልዕክት በጽሑፍ የማስተላልፈው በጣም ለተናደዳችሁና ለተቆጣችሁ ኦርቶዶክሳውያን ነው ::

በእርግጥም አንዳንድ ኦርቶዶክሳውያን ኮመድያን እሼ ይሄም ሲያንስበት ነው ገና እንዘምርለታለን ስትሉ በቁጣ ቃል ብትናገሩም ፣ ሌሎች ኦርቶዶክሳውያን ግን በጣም ነው የተሳሳትነው ደግሞም ያፈርነው በፍጹም እንዲህ አይደረግም ነበር ፣ እነዘማሪ ቴዲም መዝሙር የመቀበያ ጊዜው ስለሌላቸውና ጤናማ መዝሙሮችንም መቀበል ስላቆሙ ነው በወረደና በደከመ መንፈስ ለእሼ እንዲህ የዘመሩለት ስለዚህ አሁን ለእኛ ትክክል ነን ስንል መከራከር ሳይሆን ንስሐ ነው የሚያሻንም ሆነ የሚያስፈልገን ሲሉ መጸጸታቸውን በውስጥ መስመር ገልጸውልኛል ::

ሌላው የምላችሁ እስቲ ራሱ ከመዲያን እሼ ቀርቦ ይጠየቅ ፤ እኔ ምሳና እራት ልሆናችሁ እችላለሁ ማለት ይችላል ? እንደ እኔ እንደ እኔ የኔማ እሽዬ ምሳዬ እራቴ ነህ ወላዲተ አምላክ እቅፍ ድግፍ ታርግህ ስትሉ ስለዘመራችሁለት እርሱም በደስታ ውስጥ ሆኖ አሜን ይሁን ይሁን ሲል ተስማምቶ ይሆናል እንጂ በትክክል ቀርቦ ቢጠየቅ ግን ምሳና እራት መሆን እንደማይችል ካልታመመ በቀር በሙሉ አንደበቱ አረ እኔ አልችልም ሲል ግጥም አድርጎ እንደሚናገር አልጠራጠርም ::

በብዙ ሞቅታና እናንተም በምትሠጡት መገፋፋት ውስጥ ሆኖ ልሁን ፣ እሺ ላድርግም ቢል እንኳ ከአንድና ከሁለት ቀን ምሳና እራት እንደማያልፍ በጣም እርግጠኛ ነኝ :: በሦስተኛው ቀን ግን ለምሳና እራቱ እንደለመድክ ብትመጣ እሽዬ ያራዳው ልጅ እኔስ ምኔ ሞኝ ነው ብሎና የለም በሉት አስብሎ ይደበቅብሃል ፤ አለበለዚያ እየከፋ ከመጣም ተናካሽ ውሻ አለ ብሎና አስብሎ ያስልክብሃል ፤ ካልሆነ ደግሞ ሀገር ለቆ ወይንም ለውጦ ይሄዳል እንጂ ይህቺን ጉዳይ በፍጹም አያደርጋትም ፤ የማድረግ አቅሙም ጉልበቱም የለውም ::

ነገርን ነገር ያነሳዋልና እዚህ ላይ አንድ ታሪክ ላንሳ :: በየዓመቱ ታቦት ሲወጣ ላካህናቱ በሬ አርዶ የሚያበላ አንድ ባለ ሀብት ነበር :: ታድያ እንዳስለመደው በየዓመቱ ታቦት በወጣ ቁጥር ቅልብ ሰንጋ እየገዛ በማረድ ካህናቱን ያበላ ነበር :: ከዕለታት አንድ ቀንም ካህናቱ እንደለመዱት ታቦቱን አውጥተው እርሱ ሠፈር ጋር ሲደርሱ ታቦቱ አልሄድ አለን ስለዚህ ይሄ ወንድም ተጠርቶ ያስለመደውን በሬ ይረድልንና ደም ያፍስስ ብለው ሰው ይልኩበታል :: እርሱም ጉዳዩ ትክት አድርጎትና ሀብቱንም ሙጥጥ አድርጎ ጨርሶበት ስለነበረ ለሚስቱ መልዕክተኞች ወደ እኔ ይልካሉ ሲባል ሰምቻለሁና መልዕክተኞቹ ከመጡ የለም በይና መልሻቸው ብሎ ተደበቀ :: ታድያ መልዕክተኞቹም ቤቱ ድረስ ከመጡ በኋላ ባለቤቱን በብዙ ፈተናና መስቀልያ ጥያቄ ውስጥ አስገብተው ይጠይቋት ጀመር :: እርሷም ታድያ ሳትበገርላቸው በአቋሟ ጸንታ የለም ብላ መለሰችላቸው ፤ ነገር ግን በጉዳዩ በጣም ስለተናደደችና ስለተማረረችም እኔን በሀገሬው ሕዝብ ልታስጠላኝና መቀበርያም ጭምር ልታሳጣኝ ነው እንዴ እንዲህ ዓይነቱ ፈተና ውስጥ የከተትከኝ ፤ በል ሂድ ከተደበቅህበትም ውጣና ማድረግ የሚገባህን አድርግላቸው ፣ እኔ አላውቅልህም ትለዋለች :: ሰውየውም የሚስቱን መጨነቅ ተመልክቶ እርሷን ለማረጋጋት እሺ ይላታል :: ከዚያም ጋቢውን ይለብስና ጉዳዩን የሚፈጽም ሰው መስሎ ይወጣል ፤ ነገር ግን በጋቢው ወስጥ አጭር ቆመጥ ወይንም የፖሊስ ዱላ ዓይነት ይዟል ፤ ከዚያም ታቦቱ ያለበት ቦታ ድረስ በመሄድ ወደ ሕዝቡ ሲደር ሕዝቡ ሁሉ እርሱን አይቶ በደስታ ይሞላል :: እርሱም እሺ የሚፈለገውን አደርጋለሁ አንዴ ግን ታቦቱ ወዳለበት ጋር አስጠጉኝ ቄሱን በምስጢር የማዋያቸው ጉዳይ አለኝ ይልና ሕዝቡና ካህናቱም ጭምር ታቦቱን ወደ ተሸከሙት ካህኑ ጋር ያስጠጉታል:: ከዚያም ይህ ሰው ካህኑን ጠጋ ብሎ ታቦቱ አልሄድ አልዎት እንዴ ሲላቸው አዎን ይሉታል :: እርሱም በመቀጠል ቆይ እኔ አኬደዋለሁ ይልና ዘወር ብሎ ታቦቱን የተሸከሙትን ቄስ በዚያ ቆመጥ ሁለቴ ቢዠልጣቸው ሰውየው ታቦቱን ይዘው እግሬ አውጪኝ ሲሉ ፈትለክ አሉ :: ያኔ የታቦቱን መጓዝ የተመለከተ ሕዝብ ታቦቱ ተንቀሳቀሰ በማለት በዕልልታና ቦሆታ በጭፈራም ጭምር ከታቦቱ ጋር መጓዝ ጀመረ ይባላል ::ይህም ሰው በሬውን ከማረድ ዳነ ::

ወዳጆቼ የጨነቀው እርጉዝ ያገባል እንዲሉ ፣ የሰው ልጅ ከዓቅሙ በላይ የሆነ ነገር ውስጥ ከገባ አይደለም ይሄን ከዚህም የባሰ ነገር ሊያደርግ ይችላል ፤ ስለዚህ ይህንን ምሳሌ ያቀረብኩት ኮመዲያን እሼንም ልታከስሩትና እንዲህ ዓይነቱ ነገር ውስጥ ልትከቱት ካልሆነ በስተቀር ምሳና እራት ሊሆን አይችልም ለማለት ነው :: ሌላው ግን የሀገራችን የኢኮኖሚ ሁኔታም የሚፈቅድ ባለመሆኑ ያለንን ፣ ያገኘነውንም ተመስገን ስንል በልተን ጠጥተን ከምንኖር ውጪ እንኳን የሸመተ ያረሰም አይችልህ ነውና ነገሩ ለኮመዲያን እሼም ሆነ ለሁላችን አዋጭ አይደለም ::

ወደ መጽሐፉ ቃል ስንመለስም የተራቡትን በበጎ ነገር አጥግቦአል፤ ባለ ጠጎችንም ባዶአቸውን ሰዶአቸዋል እንዲለን ቃሉ ( የሉቃስ ወንጌል 1 ፥ 53 ) ፣ የተራቡትን በበጎ ነገር የሚያጠግብ እግዚአብሔር ብቻ ነው :: የሰው ልጅ ግን ይሄን ማድረግ አይችልም ፤ ለዚህም ነው በትንቢተ ኤርምያስ 48 ፥ 33 ላይ ሐሤትና ደስታ ከፍሬያማው እርሻና ከሞዓብ ምድር ጠፍተዋል፤ ጠጁን ከመጥመቂያው አጥፍቻለሁ፤ ጠማቂውም በእልልታ አይጠምቅም፥ እልልታቸውም እልልታ አይሆንም ካለን በኋላ በ2ኛ ነገሥት 6 ፥ 27 ላይ ደግሞ እርሱም፦ እግዚአብሔር ያልረዳሽን እኔ እንዴት እረዳሻለሁ፧ ከአውድማው ወይስ ከመጥመቂያው ነውን ? አለ የሚለን :: ሃሳቡን ይበልጥ ለመረዳት 2ኛ ነገሥት 6 ን በሙሉ እናንተ አንብቡት :: ሃሳቡን ወደ ውስጥ ገብቼ እንዲህና እንዲያ ነው ስል ማብራራት ግን ለእኔ አይጠበቅብኝም :: ታድያ መጽሐፍቅዱሱን እናንሳ ካልን የነኤልያስን ፣ የሰራፕታዋን መበለት እና የመሣሠሉትን ሁሉ ማንሳት እችላለሁ ፤ ስለዚህ ይሄ ጌታ በደግነቱ ካላጠገበን በስተቀር ሰዎች ተነስተው ምሳና እራት ሊሆኑን ሊያጠግቡንም አይችሉም :: ታድያ አሁንም አፌን ሞልቼ መናገር እችላለሁ ፤ ለኮመዲያን እሼ የተሰጠች መዝሙር መሠል ዘፈን ግን አሁም ከደጀ ሰላም እና ከእርሱም አልፎ በየ ሰንበቴ ቤቱ ፣ በየማህበር ቤቶችም ጭምር የተጀመረችና ፉት በተባለው ነገር ሞቅ ካላቸው ከካህናቱ የተኮረጀች ቀረርቶ ናት :: ተገቢ ምስጋና ግን ልንላት በፍጹም አንችልም :: ማመስገን ከተፈለገ ወንድማችን ኮመዲያን እሸቱን እግዚአብሔር ይባርክህ ሲሉ ማመስገንና ሲያስፈልግም እጅ ጭኖ መጸለይ ይቻላል :: እንዘምርለታለን ሲሉ መድረቅና ክች ማለት ግን ምስጋናዬን ለሌላ አልሰጥም ካለው ከትልቁ እግዚአብሔር ጋር ጭምር መጣላት ነው ትንቢተ ኢሳይያስ 42 : 8 :: እንኩዋን አጠገባችን ላለው ፣ በዓይናችንም ለምናየው ለእሼው ቀርቶ ለነ አርሴማ ለነ ጊዮርጊስ ለነ መርቆሬዎስና ለመሣሠሉትም መዘመር ተገቢ ባለ መሆኑ ዛሬ ባታቆሙት ወደፊት የግድ ታቆሙታላችሁ እንደገናም ብቻውን ጌታና አዳኝ ለሆነው ለኢየሱስም ማንም ሳይላችሁ ትዘምራላችሁ :: ጽሑፌን ጨርሻለሁ ተባረኩልኝ ::

Address

Ottawa, ON
K1Z8N5

Telephone

+16137221737

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Aba Yonas word of God Preaching Page posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Aba Yonas word of God Preaching Page:

Share