Miskay Hizunan Medhanialem & Tsedenia Kidist Mariam Church Vancouver

Miskay Hizunan Medhanialem & Tsedenia Kidist Mariam  Church Vancouver Miskay Hizunan Medhanialem & Tsedenia Kidist Mariam Ethiopian Ortodocx Church Vancouver BC
(1)

This is a group to gather Ethiopian Orthodox Tewahedo Christians in the greater Vancouver, BC area. We want to concentrate on teaching the youth about the apostolic teachings and tradition of our Holy Church.

ሁላችሁም በእመቤታችን ስም ተጋብዛችኋል ። ኑና በአዲስ ልብ፣ በአዲስ ሃሳብ፣ በአዲስ ቦታ በቅኔና ዝማሬ አብረን እናመስግን።ሌሊቱን በማህሌት፣ ቀኑን በዝማሬ፣ አብረን እናክብር። ማንም በውጭ ...
09/15/2026

ሁላችሁም በእመቤታችን ስም ተጋብዛችኋል ። ኑና በአዲስ ልብ፣ በአዲስ ሃሳብ፣ በአዲስ ቦታ በቅኔና ዝማሬ አብረን እናመስግን።
ሌሊቱን በማህሌት፣ ቀኑን በዝማሬ፣ አብረን እናክብር።

ማንም በውጭ አይቅር። ወደቤቱም ይግባ።

09/12/2026

"በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ" (መዝ 64:11)።

የተወደዳችሁ የክርስቶስ ቤተሰቦች የድንግል ማርያም ወዳጆች፣
እንኳን ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ በሰላም አሸጋገረን!

ቸርነቱ የማያልቅበት፣ የዘመናት ባለቤት፣ በርኅራኄው ጠብቆ፣ ያለፈውን ዘመን በሰላም አሳልፎ፣ ከክፉ ነገር ሰውሮ፣ ለዛሬው ስላደረሰን ክብርና ምስጋና ለቅዱስ ስሙ ይሁን።

በዚህ አዲስ ዓመት፣ በአዲስ ልብና በአዲስ አስተሳሰብ እንድንገኝ እንመኝ። በመካከላችን ያለ ማንኛውም ልዩነት ተወግዶ እርቅና ሰላም እንዲፈጠር፣ ፍቅርና አንድነት የሰፈነበት ዓመት ይሁንልን፤ ቤተ ክርስቲያንም እጇን ዘርግታ ሁላችንንም በይቅርታ ትቀበላለች።

አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የምሕረትና ይቅርታ ዘመን ይሁንልን! አሜን!

09/09/2026

የሰላም የእርቅና የፍቅር አዲስ ዓመት ይሁንልን፡፡

ቤተክርስቲያናችን በገጠማት ፈተና ምክንያት ምእመናን አዝነዋል፤ ሕፃናት አልቅሰዋል፤ አብዛኞቻችንም ግራ ተጋብተናል፡፡ መነሻው ምንም ይሁን አሁን ያለንበት ቦታ አድርሶናል፡፡ የ2018ቱን አሮጌ ዘመን ያቀረበልንን ሁሉ በጸጋ ተቀብለን፤ የሚመጣውን አዲስ ዓመት በተስፋ እንቀበላለን፡፡ የቤተክርስቲያናችን አዲስ የማምለኪያ ስፍራ ከስፋቱና ከአመቺነቱ አንጻር ለሁላችንም ይበቃናል፡፡ በአዲሱ ዓመት ሁላችንም በአዲስ ቦታ እንደበፊቱ ተሰባስበን የምናመልክበት የእርቅ፤ የሰላምና የፍቅር ዓመት ያድርግልን፡፡

በብፁዕ አቡነ መቃርዮስ ጸሎትና ቡራኬ የአጥቢያው ምእመናን ሁሉ ያለምንም ልዩነት በአንድ ቦታ በመሰባሰብ የሚገዛውን አዲሱን የቤተክርስቲያን ሕንፃ በአንድነት ሆናችሁ እንድታስፈጽሙ ብለው በሰጡን መመሪያ መሠረት፤ ሁላችሁም በቤተክርስቲያን በመገኘት ሰላምን፣ እርቅንና ፍቅርን እንድትካፈሉ ስንል በታላቅ መንፈሳዊነት ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

አድራሻችን፡ 726 12th Street, NW.

እግዚአብሔር ዘመኑን የሰላም፣ የእርቅና የፍቅር ያድርግልን፡፡ መልካም አዲስ ዓመት ይሁንላችሁ፡፡

09/02/2026
08/18/2026

የምስጋናና የደስታ መልእክት።

ከረጅም የፈተናና የመከራ ጊዜ በኋላ፣ ዛሬ ነሐሴ አሥር በአዲስ በተከራየንበት የአምልኮ ሥፍራችን አገልግሎታችንን በደስታ ጀምረናል።

ዛሬ የታየው ደስታ በቃላት ብቻ የሚገለጽ አልነበረም። በርካታ ምእመናን ተገኝተው፣ በእንባ በዝማሬ፣ በጸሎትና በምስጋና እግዚአብሔርን አመስግነዋል።

የተለያዩ የቤተሰብ ትውልዶች በአንድ ላይ ተሰብስበው ሲያመሰግኑ ማየት ራሱ ታላቅ በረከት ነበር።

ሕፃናት በደስታ ቦርቀዋል፤ ወጣቶች በዝማሬ ተሳትፈዋል፤ አረጋውያን በደስታ ልባቸው ተሞልቷል።

ይህ ሁሉ ቤተ ክርስቲያን ማለት ሕንፃ ብቻ ሳይሆን፣ በእምነት የተሰበሰበ አንድ ቤተሰብ መሆኗን ያሳየ ዕለት ነበር።

በተለይም ቅዱሳን ታቦታችንን በከፍተኛ የንግሥ ሥርዓት ወደ አዲሱ መንበራቸው በደስታና በክብር ማስገባታችን የዛሬውን ቀን የበለጠ የተባረከ አድርጎታል።

ይህ ቀን ያስተማረን አንድ ታላቅ ነገር እግዚአብሔር በፈተና ጊዜ አይተወንም የሚል ነው። የሰው ዓይን መንገድ ባያይም፣ የእግዚአብሔር እጅ ግን ከሕዝቡ ጋር ነበር።

ዛሬ የደረስንበትን ደስታ ስንመለከት ለተራዳን እግዚአብሔር ምስጋና ልናቀርብ ይገባናል።

አሁን ደግሞ ከዚህ በኋላ የሚጠብቀን ታላቅ የደስታ ቀን አለ። የፄዴንያ ቅድስት ማርያምን ዓመታዊ ክብረ በዓል በታላቅ ድምቀት፣ በፍቅር፣ በአንድነትና በመንፈሳዊ ደስታ እናከብራለን።

ስለዚህ የተወደዳችሁ ምእመናን፣ ዛሬ የጀመርነውን የደስታ ጉዞ በጋራ እንቀጥል። ቤተ ክርስቲያናችንን በጸሎት፣ በፍቅር፣ በአገልግሎትና በአንድነት እንጠንክር። የቀደመውን ፈተና ትተን፣ ወደፊት በተስፋ እንመልከት።

እግዚአብሔር ይመስገን!

እንኳን ለዚህ ታላቅ የምስጋና ቀን አደረሰን፤ እንኳንም ለፄዴንያ ቅድስት ማርያም ክብረ በዓል አደረሳችሁ!

ከዚህ በኋላ የቫንኮበር ምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለምና ፄዴንያ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን አገልግሎት 726 12th Street, New Westminster, BC መሆኑን ለሌሎችም እንድታሳውቁ እንጠይቃለን፡፡ የዘወትር እሁድ አገልግሎታችን በዚህ ቦታ ይቀጥላል፡፡

የምስራች ማስታወቂያበአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሐዱ አምላክ።የተወደዳችሁ የቤተ ክርስቲያናችን ምእመናን፣ቤተ ክርስቲያናችን ከሕንፃው አከራይ ጋር የነበራት የኪራይ ውል ከሰኔ ፳፬ ቀን ...
08/14/2026

የምስራች ማስታወቂያ

በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሐዱ አምላክ።

የተወደዳችሁ የቤተ ክርስቲያናችን ምእመናን፣

ቤተ ክርስቲያናችን ከሕንፃው አከራይ ጋር የነበራት የኪራይ ውል ከሰኔ ፳፬ ቀን ጀምሮ በመቋረጡ፣ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎታችን ተስተጓጉሎ ታቦታቱ፣ ካህናቱና ምእመናኑ ከቀድሞው የአምልኮ ሥፍራችን ተለይተው በአስቸጋሪ ሁኔታ ለመቆየት መገደዳቸው ይታወሳል።

በዚህ አስቸጋሪ ወቅት፣ በሀገረ ስብከታችን ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ፣ የምዕራብ ካናዳና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል እና የቋሚ ሲኖዶስ አባል፣ በጸሎት፣ በቡራኬና በአባታዊ ምክር ከእኛ ጋር በመቆማቸው እግዚአብሔርን እያመሰገንን፣ አሁን ለመላው ኦርቶዶክሳውያን ታላቅ የምስራች ለማብሰር ደስታ ይሰማናል።

እግዚአብሔር በረዳንና በጸሎታችን የተፈጠረውን ፈተና አልፈን፣ አዲስ የአምልኮ ሥፍራ አግኝተናል!

ስለሆነም በቫንኩቨርና በአካባቢዋ የምትገኙ ኦርቶዶክሳውያን ሁሉ፣ ከዚህ በታች በሚቀርበው ፖስተር ላይ በሚገኘው አድራሻ በመገኘት፣ አዲሱን የአምልኮ ሥፍራችንን በመቀላቀል ከእኛ ጋር የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት እንድትሳተፉ የምንጋብዛችሁ መንፈሳዊ ጥሪ ነው።

ይህ አዲስ የአምልኮ ሥፍራ የአንድ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ሳይሆን፣ በክርስቶስ አንድ ሆነን የምንሰበሰብበት፣ በቅዱስ ቁርባን የምንሳተፍበት፣ በጸሎትና በመዝሙር እግዚአብሔርን የምናመሰግንበት የኦርቶዶክሳዊያን የአንድነት ማዕከል እንዲሆን በጋራ እንሠራለን።

የእግዚአብሔር ጸጋና ቸርነት ከእኛ ጋር ሆኖ እስከዚህ እንዳደረሰን እያሰብን፣ ይህንን የምስራች በደስታ እንቀበል፤ በአዲሱ የአምልኮ ሥፍራችንም በአንድ ልብ፣ በአንድ እምነትና በአንድ መንፈስ እንሰባሰብ።

እንኳን ደስ አለን!
እንኳን ደስ አላችሁ!
እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያናችንን ይጠብቅ፣ አገልግሎታችንንም ይባርክ።

የቤተ ክርስቲያኗ የሰበካ አስተዳደር

08/03/2026

በ«ተሐድሶ» መሰሪ እንቅስቃሴ ላይ ዛሬም እንንቃ!



«ተሐድሶ» የተባለው በተለያዩ መናፍቃን የሚደገፍ፣ ተቋማዊ ሆኖ ያልተደራጀ፣ ወጥ አስተምህሮ የሌለው፤ ነገር ግን ኦርቶዶክሳዊ ነኝ ብሎ የተሰለፈ፤ በየትኛውም መንገድ የቀጠሩትን የተለያዩ የመናፍቃን ፍላጎት ለማርካት ቤተክርስቲያንን ለመቆጣጠር በውስጥና በውጭ ያሸመቀ ኃይል ነው። ከዚህ ቀደም ይህንኑ በኅቡዕ የተደራጀ የተወሰኑ መነኮሳት፣ መርጌቶችና የዲያቆናት የተላላኪነትና የምንፍቅና አካሔድን ከተጋለጠ ጀምሮ ግን ካህናትና ምእመናን ጉዳዩን ወደ ማጤን እንዲገቡ አስገድዷል።

ይህን ድብቅ እንቅስቃሴያቸውን በመከታተላችን፤ እያንዳንዱን እንቅስቃሴ መፈተሽ በመጀመራችን ለስውር እንቅስቃሴአቸው በር እየተዘጋ መምጣቱን ተረዱ። በመሆኑም ያላቸው ብቸኛ አማራጭ የቤተክርስቲያንን መዓርጋት በስማቸው እየቀጸሉ፡ በቤተክርስቲያን አስተዳደር ችግር አለ በማለት ኦርቶዶክሳዊ ገጽታ እያላበሱ በግልጽ ፕሮቴስታንታዊ ተግባራትን መዝራት ጀመሩ። በመሆኑም የ«ተሐድሶ»ን እንቅስቃሴ እውነተኛ ምንነትና በቤተክርስቲያን ጠላትነት የተሰለፈ ኃይል እንጂ የቤተክርስቲያን አስተዳደር እንዲሻሻል የሚጠይቅ አለመሆኑን በራሳቸው እንቅስቃሴ ግልጽ አደረጉ።


በቤተክርስቲያን አስተዳደር ችግር ላይ የተመሠረተው የተሐድሶ ተከታታይ እንቅስቃሴ ዋጋ እያጣ ሲመጣ ክርክራቸውን ወደ መተዳደርያ ደንብ (bylaws) በማዞር ምእመኑን በግራና በቀኝ አቧድነው ማነታረክ ጀመሩ፡፡ ገንዘብ ካገኙ ሰይጣንንም ያገለግላሉ የተባሉትን ጥቂት ካህናት መርጠው ከጎናቸው አሰለፉ፡፡ በዚህም መሰረት በህቡዕ በድብቅ ያዘጋጁትን ቡድን በሀገሪቱ ህግ ሰርተፊኬት አውጥተው “የቀራኒዮ መድኃኔዓለም ማህበር” ብለው ተደራጁ፡፡ በዋናው ስም “ምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለምና ፄዴንያ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን” ውስጥ ሆነው የቀራኒዮ መድኃኔዓለም ማህበርን አዋለዱ፡፡

ይህንን ድብቅ ሤራቸውን ለም እመናን ስናሳውቅ፤ የቀራኒዮ መድኃኔዓለም ማህበር ሰርተፊኬት ውሸት ነው ማለት ጀመሩ፡፡ በሌላ በኩል ሰርተፊኬቱን ያወጣነው የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓልምና ፄዴንያ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን፤ ከቤተክርስቲያኑ ህንጻ ባልቤት ጋር ያለውን ሊዝ (የኪራይ ውል) ለማዳን የተጠቀምነው እንጂ ሌላ ማህበር ለመመስረት ፈልገን አይደለም በማለት ግራ የማጋባት ሥራ ሰሩ፡፡

ለአሥርተ አመታት በድብቅ ሲዘጋጁበት ቆይተው ... ይቀጥላል፡፡

08/01/2026

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜነ

የተወደዳችሁ የቤተክርስቲያናችን ምእመናን፣

በቅርቡ በማህበራዊ ሚዲያ በቤተክርስቲያናችን ስም የምህላ ጸሎት ጥሪ ተላልፏል የሚል ጥያቄ ከበርካታ ምእመናን ደርሶናል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሥርዓት መሠረት፣ የምህላ ጸሎት የሚደረገው በተገቢው ምክንያት እና በቅዱስ ሲኖዶስ ወይም በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ፈቃድ ብቻ ነው።

በመሆኑም፣ ቤተክርስቲያናችን እስከዚህ ሰዓት ድረስ በስሟ ማንኛውንም የምህላ ጸሎት ጥሪ አላስተላለፈችም፤ እንዲሁም ማንኛውም ከቤተክርስቲያናችን ይፋዊ መግለጫ ውጭ የሚቀርብ ጥሪ የቤተክርስቲያናችንን አቋም እንደማይወክል ለሁላችሁም እናሳውቃለን።

በተጨማሪም፣ በአሁኑ ወቅት ቤተክርስቲያናችን በጊዜያዊነት የምንገለገልበትን የኪራይ ቤተ ክርስቲያን እና በቋሚነት ለመግዛት የምንጥቀምበትን ቦታ በተመለከተ ሥራዎች በመጠናቀቅ ላይ ይገኛሉ። የሚያስፈልጉት ዝግጅቶች እንደተጠናቀቁ፣ የአዲሱን የአምልኮ ሥፍራ አድራሻ እና የአገልግሎት መጀመሪያ ቀን በይፋ ለሁላችሁም እናሳውቃለን።

አገልግሎታችንም በእግዚአብሔር ፈቃድ፣ በአባቶቻችን በረከት፣ በአካባቢው ካህናት፣ በምእመናን፣ በሀገረ ስብከቱ አመራሮች እና በተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በታላቅ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ይጀመራል።

ስለዚህ ይህን ታሪካዊ ቀን በደማቅ ሁኔታ ለማክበር በሚቋቋመው የመስተንግዶና የዝግጅት ኮሚቴ አማካይነት በፍቅርና በትብብር እንድትሳተፉ በአክብሮት እንጋብዛለን።

እግዚአብሔር በፈተናችን ጊዜ አጽንቶ ይጠብቀን፤ ቤተክርስቲያናችንን በሰላም፣ በአንድነት እና በፍቅር ያኑራት።
አሜን።

A few weeks ago, one of the parishioners from the Catholic church down the street passed by our church while we were ins...
04/19/2026

A few weeks ago, one of the parishioners from the Catholic church down the street passed by our church while we were installing the new road signage. After expressing his admiration for the new sign, he mentioned that the rotten wood sitting in front of the building looked terrible. He shared that he had been passing by for many years and had always noticed this eyesore, and he asked if we were planning to remove it. He also reminded us that this is the house of God and should be kept clean, as the wood made the building look very unappealing.
I thanked him for his comments and promised that we would take care of the rotten wood this summer.
As it turns out, God works in mysterious ways. Earlier this week, Biya from the Orthodox Youth Vancouver group reached out and said that he and his team would like to help clean up the rotten wood in front of the building and transform the area into a garden. They also offered to cut the overgrown vegetation on the west side and clean the backyard.
Today, around 10 members of the Orthodox Youth Vancouver group showed up and did an amazing job.
Phase One included:
• Removing and disposing of all the rotten wood in front of the building
• Patching holes on the front wall
• Cutting overgrown trees in front of the building
• Clearing overgrown vegetation in the west-side garden
• Removing leaves from the sides and back of the building
• Completely cleaning the backyard
The results speak for themselves—the outside of the church now looks amazing. You can view the transformation here:
https://photos.app.goo.gl/u21nkySuVGD24hiGA
It was truly a delight to see these young people working together as a team. Their friendship, respect, and love for one another were clearly visible. I was very impressed with the Orthodox Youth Vancouver group and look forward to seeing Phase Two of their work.
May God bless you all for what you have done today for the church. We deeply appreciate the hard work you put in.

Tap to view!

ከጥቂት ሳምንታት በፊት፣ ከመንገዱ በታች ያለው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አንድ አባል እኛ አዲሱን የመንገድ ምልክት ሲጫን እያለን በአጠገባችን አለፈ። አዲሱን ምልክት ካየ በኋላ እጅግ አድናቆ...
04/19/2026

ከጥቂት ሳምንታት በፊት፣ ከመንገዱ በታች ያለው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አንድ አባል እኛ አዲሱን የመንገድ ምልክት ሲጫን እያለን በአጠገባችን አለፈ። አዲሱን ምልክት ካየ በኋላ እጅግ አድናቆት አሳየ፣ ነገር ግን በህንጻው ፊት ያለው የተበላሸ እንጨት እጅግ መጥፎ እንደሚታይ አስተያየት ሰጠ። ለብዙ ዓመታት ሲያልፍ ይህን የዓይን መከራ እንደሚያይ ገልጾ፣ መውገዱን እቅድ እንዳለን ጠየቀ። እንዲሁም ይህ የእግዚአብሔር ቤት እንደሆነ ስለሆነ ንጹሕ መሆን እንዳለበት አስታወሰን፣ እንጨቱም ሕንጻውን እጅግ መጥፎ እንደሚያሳይ ገለጸ።
እኔም ለአስተያየቱ አመሰገንኩት እና በዚህ በበጋ ወቅት የተበላሸውን እንጨት እንደምንወግድ ተስፋ ሰጠሁ።
እንደሚባለውም እግዚአብሔር በምስጢራዊ መንገድ ይሰራል። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ቢያ ከOrthodox Youth Vancouver ቡድን ጋር ተገናኝቶ እርሱና ቡድኑ በሕንጻው ፊት ያለውን የተበላሸ እንጨት ለማጽዳት እና ቦታውን ወደ አትክልት ለመቀየር እንደሚፈልጉ ነገረን። በተጨማሪም በምዕራብ ጎን ያለውን የበዛ ዕፅዋት ለመቁረጥ እና የኋላውን ቦታ ለማጽዳት ተነሱ።
ዛሬ ከ10 ያህል የOrthodox Youth Vancouver አባላት መጥተው እጅግ ጥሩ ስራ አከናውነዋል።
የመጀመሪያ ደረጃ ስራዎች እነዚህን አካትተዋል፦
• በሕንጻው ፊት ያለውን የተበላሸ እንጨት ማስወገድና መጣል
• በፊት ግድግዳ ላይ ያሉ ጉድጓዶችን መሙላት
• በፊት ያሉ የበዛ ዛፎችን መቁረጥ
• በምዕራብ ያለውን የአትክልት ቦታ ማጽዳት
• ከጎኖችና ከኋላ ያሉ ቅጠሎችን ማስወገድ
• የኋላውን ቦታ ሙሉ በሙሉ ማጽዳት
ውጤቱ በራሱ ይናገራል—የቤተ ክርስቲያኑ ውጫዊ ክፍል አሁን እጅግ ቆንጆ ሆኗል። የለውጡን ፎቶዎች ከዚህ ሊንክ ማየት ትችላላችሁ፦

https://photos.app.goo.gl/9EYHndyVt8AZUoZd9

እነዚህ ወጣቶች በአንድነት ሲሰሩ ማየት በእውነት ደስ የሚያሰኝ ነበር። ጓደኝነታቸው፣ ክብራቸው እና ፍቅራቸው በግልጽ ይታይ ነበር። ከOrthodox Youth Vancouver ቡድን በጣም ተደንቄአለሁ እና የሁለተኛ ደረጃ ስራቸውን ለማየት እጠብቃለሁ።
እግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያኑ ያደረጋችሁትን ሁሉ ይባርካችሁ። ያደረጋችሁትን ከባድ ስራ በጣም እናመሰግናለን።

Tap to view!

Address

726 12th Street
New Westminster, BC
V3M4J9

Opening Hours

6am - 10am

Telephone

+16042560217

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Miskay Hizunan Medhanialem & Tsedenia Kidist Mariam Church Vancouver posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share