Apostle Ermias Sorsa

Apostle Ermias Sorsa Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Apostle Ermias Sorsa, North Parramatta, Sydney.

የሉቃስ ወንጌል 8:1 ከዚህም በኋላ እየሰበከና ስለ እግዚአብሔር መንግሥት የምሥራች እየተናገረ በየከተማይቱ በየመንደሩም ያልፍ ነበር፤ And it came to pass afterward, that he went throughout every city and village, preaching and shewing the glad tidings of the kingdom of God: and the twelve were with him,

06/09/2026

ትንቢተ ኢሳይያስ 27:6 ፤ በሚመጣው ዘመን ያዕቆብ ሥር ይሰድዳል፥ እስራኤልም ያብባል ይጨበጭብማል፤ በፍሬያቸውም የዓለሙን ፊት ይሞላሉ። He shall cause them that come of Jacob to take root: Israel shall blossom and bud, and fill the face of the world with fruit.
Note:”I do not own the rights to this music”

🔑“እርቃንህ እንዳይታይ የእፍረትህን እርቃን የሚሸፍን ነጭ ልብስ ከእኔ ግዛ።”  ራእይ 3፥18አዳምና ሔዋን ኃጢአት ከሠሩ በኋላ እርቃናቸውን አወቁ፤ የሰው ዓይን የሚያፍርበትን ነገር ራሳቸውም...
10/08/2026

🔑“እርቃንህ እንዳይታይ የእፍረትህን እርቃን የሚሸፍን ነጭ ልብስ ከእኔ ግዛ።” ራእይ 3፥18

አዳምና ሔዋን ኃጢአት ከሠሩ በኋላ እርቃናቸውን አወቁ፤ የሰው ዓይን የሚያፍርበትን ነገር ራሳቸውም ተመለከቱ። ራሳቸውንም በቅጠል ለመሸፈን ሞከሩ። ነገር ግን የሰው ሽፋን የእፍረትን ምንጭ ሊያስወግድ አልቻለም። እግዚአብሔር ግን በምሕረቱ “የቆዳ ልብስ አድርጎ አለበሳቸው።” ዘፍጥረት 3፥21

ከዚያም የምበልጥ በመስቀል ላይ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ልብሱን ተከፋፍሎ እርቃኑ ተጋለጠ (ማቴዎስ 27፥35) ። እርሱ ግን የእኛን የኃጢአት እፍረት ተሸክሞ፣ እኛን በጽድቅ ልብስ ሊያለብሰን ነበር።

ስለዚህ ክርስቶስ እንዲህ ይለናል፦ “እርቃን እንዳይታይ የእፍረትህን እርቃን የሚሸፍን ልብስ ከእኔ ግዛ።” ራእይ 3፥18፤ ይህ ልብስ የሰው ልብስ አይደለም፤ የጽድቅ ልብስ ነው።

ሰይጣን የሰውን ውርደት ለማሳየት ይፈልጋል፤ ክርስቶስ ግን ውርደቱን ወስዶ ክብርን ይሰጣል።ሰይጣን የሰውን እርቃን ይጠቁማል፤ እግዚአብሔር ግን ይሸፍናል።ሰይጣን ያሳፍራል፤ ክርስቶስ ያከብራል።

ስለዚህ የሌላን ሰው እርቃን ለማጋለጥ አትፈልግ፤ የሌላን ውድቀት ለማሳየት አትቸኩል። ዛሬ የሌላውን እርቃን የሚያይ ሰው ነገ የራሱ እርቃን ሊገለጥ እንደሚችል ይወቅ።

ሰውን ማጋለጥ ቀላል ነው፤ መሸፈን ግን ፍቅር ነው። የወደቀን መጠቆም ቀላል ነው፤ ማንሳት ግን ክርስቶስን መምሰል ነው። የደከመን መንቀፍ ቀላል ነው፤ ለእርሱ መጸለይ ግን ፍቅር ነው።
"እርስ በርሳችሁ ተሸካከሙ፤ እንዲሁም የክርስቶስን ሕግ ፈጽሙ።” ገላትያ 6፥2
🔑እወዳቿለሁ ተባረኩ!

🔑እግዚአብሔር ከፍ ለማድረግ ዝቅ ያደርጋል!🫴በሕይወታችን ውስጥ የሚያጋጥሙን ለውጦች ሁሉ ፈጽሞ የማይለወጠው አምላክ በእኛ ላይ ያለው መልካም ፈቃድ ውጤቶች ናቸው። ሀብታምና የበለጠግን ብንሆን...
05/08/2026

🔑እግዚአብሔር ከፍ ለማድረግ ዝቅ ያደርጋል!

🫴በሕይወታችን ውስጥ የሚያጋጥሙን ለውጦች ሁሉ ፈጽሞ የማይለወጠው አምላክ በእኛ ላይ ያለው መልካም ፈቃድ ውጤቶች ናቸው። ሀብታምና የበለጠግን ብንሆን የእርሱን በረከት አይተን እናመሰግናለን፤ በተመሳሳይ ሁኔታ ቢንደኸይም ወይም ዝቅ ብንል የእርሱን ሰጪና በጊዜው ከፍ የሚያደርገውን እጁን አይተን በሙሉ ልባችን እናመሰግነዋለን።በዓለም ላይ ዝቅ ስንልም ሆነ ከፍ ስንል ነገሩ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው፤ ስለዚህ ዝቅ ማለታችንን በትዕግሥት ከፍ ማለታችንን ደግሞ በምስጋና እንቀበላለን። በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ነገሩን ያደረገው እግዚአብሔር ነው፤ እርሱ ያደረገው ነገር ደግሞ ሁልጊዜ መልካም ነው።

🫴የእግዚአብሔር መንገድ ሊያነሣቸው ያሰባቸውን አስቀድሞ ዝቅ ማድረግ፣ ሊያለብሳቸው ያሰባቸውንም አስቀድሞ ማራቆት ይመስላል። መንገዱ የእርሱ ከሆነ ደግሞ ፍጹም ትክክልና ጥበብ የሞላባት ምርጡ መንገድ እርሱ ብቻ ነው። አሁን ዝቅ ለማለት እየተለማመድን ከሆነ ይህም ዝቅ ማለት ወደፊት ለሚመጣው ታላቅ ከፍታ መግቢያ እንደሆነ አይተን በደስታ ልንሞላ ይገባል። በጸጋው ዝቅ ባልን ቁጥር፣ በክብሩ የበለጠ ከፍ እንላለን፤ መጨረሻው ለበረከታችን የሚሆነው ጊዜያዊ እጦታችንም በፍቅር ልንቀበለው የሚገባን ነው።

እግዚአብሔር አንዳንድ ጊዜ ውድቀታችንንና ኃጢአታችንን እንድንረዳና የራሳችንን ታናሽነት እንድናውቅ ያደርገናል። ይህም በተለምዶ የሚያስደስት ልማድ ባይሆንም የበለጠ ትልቅ ደስታንና አገልግሎትን ለመሸከም ብቁ የሚያደርገን መለኮታዊ ዝግጅት ነው።እኛ ዝግጁ ስንሆንም እርሱ በጊዜው ከፍ ያደርገናል።

⁷ እግዚአብሔር ያደኸያል፤ ያበለጽጋልም፤ ያዋርዳል፤ከፍ ከፍም ያደርጋል።
(መጽሐፈሳሙኤል ቀዳማዊ 2)
👉እንፀልይ ከኔ ጋር!
እግዚአብሔር ሆይ! ታናሽነታችንንና ጉድለታችንን ስላሳየኸን እናመሰግንሃለን።ይህ ዝቅ ማለታችን በሕይወታችን ፍሬ የሚያፈራ ይሁንልን፤ ለታላቁ አገልግሎትህም ብቁ አድርገን። በኢየሱስ ስም!አሜን።

✅ከእግዚአብሔር መራቅ የሚያቀርበን ወደ  ዲያቢሎስ ነው::               👉ነገሮች ምንም ያህል ብከበደን እንኳን ከ እግዚአብሔር አንራቅ!
26/07/2026

✅ከእግዚአብሔር መራቅ የሚያቀርበን ወደ ዲያቢሎስ ነው::
👉ነገሮች ምንም ያህል ብከበደን እንኳን ከ እግዚአብሔር አንራቅ!

👉በዚህ ሰዓት ከአቅማችሁ በላይ የሆነ ጉዳይ ያጋጠማችሁ እና ተስፋ በመቁረጥ ዉስጥ ያለችሁ፣መጽሐፈ አስቴር 9:1የንጉሡ ትእዛዝና አዋጅ ሊፈጸምበት በነበረው ቀን፥ የአይሁድ ጠላቶች ሊሠለጥኑባቸ...
30/06/2026

👉በዚህ ሰዓት ከአቅማችሁ በላይ የሆነ ጉዳይ ያጋጠማችሁ እና ተስፋ በመቁረጥ ዉስጥ ያለችሁ፣

መጽሐፈ አስቴር 9:1
የንጉሡ ትእዛዝና አዋጅ ሊፈጸምበት በነበረው ቀን፥ የአይሁድ ጠላቶች ሊሠለጥኑባቸው በነበረው ቀን፥ አይሁድ በጠላቶቻቸው ላይ እንዲሠለጥኑ ነገሩ ተገለበጠ።

5 ኢያሱም ሕዝቡን፦ ነገ እግዚአብሔር በመካከላችሁ ድንቅ ነገር ያደርጋልና ተቀደሱ አለ።

25/06/2026

Psalm- መዝሙረ ዳዊት
103:13 አባት ለልጆቹ እንደሚራራ፡
እንዲሁ እግዚአብሔር ለሚፈሩት ይራራል፤

👉ጌታ ተወኝ የምትሉ እግዚአብሄር በፍፁም አይተዋችሁም።ወላጅ እንደሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ። (ዮሐንስ 14:18)
03/06/2026

👉ጌታ ተወኝ የምትሉ እግዚአብሄር በፍፁም አይተዋችሁም።

ወላጅ እንደሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ። (ዮሐንስ 14:18)

👉ሕይወትን በተስፋ መቁረጥ አትገድባት፣ነገህን የምታገኘው ተስፋ ሲኖርህ ብቻ ነው።👉ያም ተስፋ ደግሞ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነዉ፣በ እርሱ የሚያምኑ አያፍሩምና እናንተም አታፍሩም አትዋረዱምም።👉ዉርደ...
25/05/2026

👉ሕይወትን በተስፋ መቁረጥ አትገድባት፣
ነገህን የምታገኘው ተስፋ ሲኖርህ ብቻ ነው።
👉ያም ተስፋ ደግሞ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነዉ፣በ እርሱ የሚያምኑ አያፍሩምና እናንተም አታፍሩም አትዋረዱምም።
👉ዉርደትህን የጠበቁ ሁሉ ክብርህን ያያሉና በርታ፣ፅና፣ እጅ አትስጥ አንድ ቀን ሁሉም ያልፍና ለካ ለዚህ ነዉ የምትልበት ቀን ሩቅ አይደለም።

18/05/2026
🔑ሰው የሳቅኩበትን ቀን ያውቃል፤ አንተ ግን ያለቀስኩበትን ምሽት ታውቃለህ።🔑ሰው የደረስኩበትን ያያል፤ አንተ ግን ያለፍኩበትን መሰናክል ታውቃለህ።ጌታ ሆይ ዙሪያዬ በጨለማ ሲከበብ ብርሃን የሆ...
17/05/2026

🔑ሰው የሳቅኩበትን ቀን ያውቃል፤ አንተ ግን ያለቀስኩበትን ምሽት ታውቃለህ።
🔑ሰው የደረስኩበትን ያያል፤ አንተ ግን ያለፍኩበትን መሰናክል ታውቃለህ።
ጌታ ሆይ ዙሪያዬ በጨለማ ሲከበብ ብርሃን የሆንከኝ፣ በምሕረትህ የምታኖረኝ፣ በቸርነትህ የጠበቅኸኝ አሁንም ወደፊትም የማትተወኝ አንተ ከኔ ጋራ ነህና አመሰግንሃለሁ።
🔑በምትችሉት ቋንቋ ሁሉ ያለአንዳች መከልከል ነገሮች ባይመቹም ብመቹም በ ህይዎት መኖራችሁ በራሱ ተዓምር ነዉና ተመስገን በሉት!

Address

North Parramatta
Sydney, NSW

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Apostle Ermias Sorsa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Apostle Ermias Sorsa:

Shortcuts

Share