Emmanuel Evangelical Church in Sydney

Emmanuel Evangelical Church in Sydney We are a multicultural church with a passion to see people brought close to the source of all life & hope, JESUS.

06/04/2026
25/03/2026

Exciting News! Our New Church Website is Live!
We are thrilled to announce the launch of the official Emmanuel Evangelical Church Sydney website!
🌐 https://emmanuelchurch.au/

You can find:
- Service times and weekly programs
- Latest sermons and worship recordings
- Upcoming events and announcements
- Information about our ministries
- Ways to give and get connected

We are also excited to share that the website is available in Amharic (አማርኛ), Tigrinya (ትግርኛ), and Oromo (Afaan Oromoo) so that everyone in our community can access it in their preferred language. Simply click the language button at the top of the page to switch.

Visit us online today and share this with family and friends!
👉 https://emmanuelchurch.au/

May God continue to bless our church and community.
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን በሲድኒ
Emmanuel Evangelical Church Sydney

መልካሙን ሥራ በሕይወትህ የጀመረውም የሚጨርሰውም እርሱ ነው።«በእናንተ መልካምን ሥራ የጀመረው እስከ ኢየሱስ ክርስቶስ ቀን ድረስ እንዲፈጽመው ይህን ተረድቼአለሁና።» ፊልጵስዩስ 1:6ጳውሎስ ...
21/02/2026

መልካሙን ሥራ በሕይወትህ የጀመረውም የሚጨርሰውም እርሱ ነው።

«በእናንተ መልካምን ሥራ የጀመረው እስከ ኢየሱስ ክርስቶስ ቀን ድረስ እንዲፈጽመው ይህን ተረድቼአለሁና።»
ፊልጵስዩስ 1:6

ጳውሎስ ይህንን የጻፈው ከእስር ቤት ሆኖ ነው። በእጆቹ ላይ ሰንሰለት እያለ፣ እርግጠኛ ባልሆነ ሁኔታም ተከቦ፣ ሆኖም ግን ልቡ በልበ ሙሉነት (በድፍረትና በእምነት) ተሞልቶ ይህንን መልዕክት ይጽፋል። ይህ ልበ ሙሉነት በሁኔታዎች ላይ ሳይሆን በእግዚአብሔር ሉዓላዊ ጸጋ ላይ የተመሠረተ ነው።

ቅዱስ ቃሉ በማያሻማ ሁኔታ እንደሚነግረን መልካሙን ሥራውን በእኛ የጀመረው ራሱ እግዚአብሔር እንደሆነ ነው። የእኛ መዳን ከራሳችን የመነጨ አይደለም። የእኛ ጥበብ፣ ጥንካሬ ወይም ሃይማኖታዊ ጥረት ውጤትም አይደለም። ይህ «መልካም ሥራ» ሙሉ ለሙሉ የጸጋ ሥራ ነው። ይህ ዳግም ልደት፣ እምነት፣ ንስሐ እና ቀጣይነት ያለው መቀደስን ደግሞ ያካተተ ነው።

ይህ ጥቅስ ከሁለት አደጋዎች ይጠብቀናል፡-
1ኛ ከትዕቢት ፦ ምክንያቱም መዳናችንን የጀመርነው እኛ አይደለንምና።
2ኛ ከተስፋ መቁረጥ ፦ ምክንያቱም መዳናችንን በገዛ ጉልበታችን የማስቀጠል ኃላፊነት የለብንምና። እናድርገውም ብንል አይቻለንምና።

ወገኖቼ በመንፈሳዊ እድገታችን የዘገየን ሊመስለን ይችላል። የምንመኘውም መንፈሳዊ ሥፍራ ላይም አልተገኘን ይሆናል ፥ የሚያበሳጩ ድክመቶችንም በሕይወታችን ደጋግመን እንመለከትም ይሆናል። ነገር ግን መቀደስ ድንገተኛ ሳይሆን ተራ በተራ የሚቀጥል ሂደት ነው። ያጸደቀን ያው ሉዓላዊው ጸጋ ፤ አሁንም በክርስቶስ መልክ እኛን ለመቅረጽ በትጋት እየሠራ ነው።

ወገኖቼ የጳውሎስ መታመን የተመሠረተው እርሱ ክርስቶስን ሙጥኝ በማለቱ ላይ ሳይሆን፣ ክርስቶስ እርሱን አጥብቆ በመያዙ ላይ ነው። የተጀመረው መልካሙ ሥራ ግቡም (መዳረሻው) ግልጽ ነው። «በኢየሱስ ክርስቶስ ቀን» ፍጻሜውን ያገኛል።

ወገኖቼ እግዚአብሔር ለዘላለም ሕይወት እያዘጋጀን ነው። እያንዳንዱ ፈተና፣ እያንዳንዱ ተግሣጽ እና እያንዳንዱ የማይታይ ተጋድሎ ለክብር እየቀረጸን ነው።ስለዚህም ዛሬም በዚህ እውነትና እምነት እረፍት እናደርጋለን። ለነፍሳችንም እንዲህ እንላታለን . . . በእኔ መልካሙን ሥራ የጀመረው እግዚአብሔር ፍጹም ታማኝ ነው። በክርስቶስ ኢየሱስም ቀን ይፈጽመዋል።

ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።

ወንድም ክሪስ

17/02/2026

“በእግዚአብሔር ፊት ዝም እንበል”

“ዝም በሉ፥ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ እወቁ።”--- መዝሙር 46:10

በተለይ በዚህ በፍፃሜው ዘመን ሕይወት አልፎ አልፎ ነው ፍጥነቷን የምትቀንሰው። ኃላፊነቶች እየተደራረቡ ይጫጫኑናል ፣ ወሬዎች ያስደነግጡናል ፣ ከዚህም የተነሳ ልብም ዕረፍት ያጣል። ነገር ግን በዚህ ሁሉ ትርምስ ውስጥ እግዚአብሔር አንድ አስገራሚ ትእዛዝ ለልጆቹ ሰጥቷል፦ ዝም በሉ!

ይህ ዝምታ እንዲሁ የአካል ፀጥታ ብቻ አይደለም፤ መንፈሳዊ እጅ መስጠት እንጂ። በጭንቀት ከመኳተን መታቀብ ማለት ነው። የነገሮችን ውጤት በቁጥጥራችን ሥር ለማድረግ ከመጣር መቆጠብ ማለት ነው። እግዚአብሔር አምላክ እንደሆነ... እኛ ግን እንዳልሆንን ማስታወስ ማለት ነው።

መዝሙር 46 የምድርን መናወጥ፣ የውኃዎችን መጮህና የመንግሥታትን መናወጥ ይገልጻል። በሌላ አነጋገር አለመረጋጋትን ውርክብን ይገልጻል። ሆኖም እግዚአብሔር ራሱን “መጠጊያችንና ኃይላችን፥ በሚደርስብን መከራ ሁሉ ታላቅ ረዳታችን” እንደሆነ ይናገራል (ቁ. 1)። ዓለም ቢናወጥም የእግዚአብሔር ዙፋን ግን አይናወጥም። ክብር ለስሙ ይሁን።

“እኔ አምላክ እንደሆንሁ እወቁ” ማለት ፣ በእርሱ የበላይ ሉዓላዊነት መታመን፣ በጥበቡ ማረፍ እና ለቃል ኪዳኑ ታማኝነት እራስን መስጠት ማለት ነው። እርሱ ሁሉን በስልጣኑ ሥር እንዳስገዛ እዚሁ አጠገባችን በዙሪያችን በውስጣችንም አለና።

ወገኖቼ ዛሬም ሰላማችን የሚመነጨው ከተስተካከለ ሁኔታ ሳይሆን፣ ፍጹም በሆነው ንጉሥ በጌታ ላይ ባለን መተማመን ነው።

ዛሬም በቁጥጥራችን ሥር ለማድረግ እየታገልንበት ያለውን ሽክም ለእርሱ አስረክበን ነፍሳችንን እንዲህ ብለን እናሳስባት፦ እግዚአብሔር በየትኛውም ሁኔታዎቼ ላይ ንጉሥ ነው።

አዎን ጌታ ሆይ :- ፀጥታ የእምነት ተግባር ነውና በፊትህ ዝም ማለትን አስተምረኝ። ጭንቀቴን ወደ ዝማሬ ለውጥልኝ ፣ በፊትህም እንዳርፍ እርዳኝ። ሰላሜ በሆነው በክርስቶስ ኢየሱስ ሥም ፣ አሜን።

ፀጋና ሰላም ይብዛላችሁ።

ወንድም ክሪስ

ዛሬ ምን አይነት ሁኔታ ውስጥ ይሆን ያሉት? በጣም ደስ ብሎታል? ወይንስ ከፍቶታል? ቃሉ በየትነኛውም ሁኔታ ውስጥ ሁልጊዜ የጌታን ፊት እንድንፈልግ እንድናመሰግነው ያበረታታና ፈቃዱ ነውና። 1...
28/01/2026

ዛሬ ምን አይነት ሁኔታ ውስጥ ይሆን ያሉት? በጣም ደስ ብሎታል? ወይንስ ከፍቶታል? ቃሉ በየትነኛውም ሁኔታ ውስጥ ሁልጊዜ የጌታን ፊት እንድንፈልግ እንድናመሰግነው ያበረታታና ፈቃዱ ነውና።

1 ተሰሎንቄ 5:17—18 ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና።

Are you joyful today—or feeling overwhelmed?

God invites us to seek Him and give thanks in every situation. This isn’t just good advice—it’s His will for us in Christ.

1 Thessalonians 5:17–18

Some days feel heavy — and that’s okay. The good news? Our God doesn’t back away when life gets hard. He comes closer.🤍 ...
14/01/2026

Some days feel heavy — and that’s okay. The good news? Our God doesn’t back away when life gets hard. He comes closer.

🤍 You’re not alone today.

“The Lord is close to the brokenhearted.” — Psalm 34:18

አንዳንድ ቀናት ከባድ ይሆናሉ — እንዲያም ቢሆን ምንም አይደል። ሁሉ ነገር ከበድ ሲል
አምላካችን ግን አብዝቶ ይቀርባል።

🤍 ዛሬ ብቻዎትን አይደሉም!

“እግዚአብሔር ልባቸው ለተሰበሩ ቅርብ ነው።” መዝሙር 34፥18

Then Jesus said, “Come to me, all of you who are weary and carry heavy burdens, and I will give you rest.” ‭‭Matthew‬ ‭1...
11/01/2026

Then Jesus said, “Come to me, all of you who are weary and carry heavy burdens, and I will give you rest.” ‭‭Matthew‬ ‭11‬:‭28‬ ‭NLT‬‬

No matter where you’re from/at or what you carry today, Jesus invites you to Himself.

Where do you need His rest this week?

እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ። ማቴዎስ 11:28

በየትኛውም ስፍራ ብንሆን ምንም አይን ሸክም ቢከብደን ኢየሱስ ወደ ራሱ ይጋብዘናል።

በዚህ ሳምንት የእሱን እረፍት የት(ምን ጉዳይ ላይ) ያስፈልግዎታል?

Hello family! We value your input and would love to engage with you on this platform. What would you like to see feature...
10/01/2026

Hello family! We value your input and would love to engage with you on this platform. What would you like to see featured or participate in?

ሰላም ቤተሰቦች!! የእናንተን አስተያየትና ሃሳብ ትልቅ ዋጋ እንሰጠዋለን እናም በዚህ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ከእናንተ ጋር ንቁ ተሳትፎ ለማድረግ እንወዳለን። በምን ጉዳይ ላይ ትኩረት ቢሰጥ ወይም መሳተፍ ይፈልጋሉ?

Just a small correction: the program starts at 8:00 PM. We can't wait to see you there!ትንሽ እርማት - ፕሮግራሙ የሚጀምረው ከምሽቱ 8፡00...
24/12/2025

Just a small correction: the program starts at 8:00 PM. We can't wait to see you there!

ትንሽ እርማት - ፕሮግራሙ የሚጀምረው ከምሽቱ 8፡00 ሰዓት ላይ ነው። እስከዚያ ድረስ በጉጉት እንጠብቃለን!!

✨🙏 You’re Invited! 🙏✨Join us tomorrow for our weekly Prayer Night🕕 Time: 6:00 PM – 8:00 PM📍3/40 Sterling Rd, Minchinbury...
07/09/2025

✨🙏 You’re Invited! 🙏✨

Join us tomorrow for our weekly Prayer Night
🕕 Time: 6:00 PM – 8:00 PM
📍3/40 Sterling Rd, Minchinbury, Sydney

📖 Matthew 18:20
“For where two or three gather in my name, there am I with them.”

🙌 Join us tomorrow!“I rejoiced with those who said to me, “Let us go to the house of the Lord.””‭‭Psalms‬ ‭122‬:‭1‬ ‭NIV...
06/09/2025

🙌 Join us tomorrow!

“I rejoiced with those who said to me, “Let us go to the house of the Lord.””
‭‭Psalms‬ ‭122‬:‭1‬ ‭NIV‬‬

!

Address

3/40 Sterling Road, Minchinbury NSW 2770
Sydney, NSW
2170

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Emmanuel Evangelical Church in Sydney posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Emmanuel Evangelical Church in Sydney:

Share