08/08/2026
Brother Endash
እግዚአብሔር ያየውን ማየት !
-ሸክም እንድሸከም እግዚአብሔር ልብ ያዘጋጀናል
ዕብራውያን 12:1-2 እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና።
1-ነህምያ አዘነ
2-ልቡ ለስራው ተነሳ
3-ልባቸው ለስራ ተዘጋጀ
4-ስራውን ጨረሰ
5-እግዚብሔር ህዝቡን ወደራሱ መለሰ
6-
-ነህምያ አንዱ እንደደመና ከከበቡንአንዱ ነው
-የብዙ የእምነት አባቶች የእምነት ታሪክ በዚህ ስፍራ ተፅፏል ታሪክ ብቻ ሳይሆን እንድናደርገው ነው
-ነህምያ የሰውን ሁሉ ጉድት አይቶ ቪዥን ያዘ
-1&2 ነህምያ ሸክሙን ለመፀም ተጋ አስተባበረ ተቃውሞ ተነሳበት
-ህዝቡ ከእዚ ጋር ቃል ኪዳ አደረጉ
-ነህምያ በእግዚአብሔር ታዞ ሳይሆን በሰማ ግዜ አዝኖ ነው አዝኖ ነው
-ነህምያ በትክክል ኖሮ ያለፈ ሰው ነው ይህን ከእርሱ ልንማር ይገባል
-የክርስትና እምነን ልዩ የሚደርገው እግዚአብሔር የተናገረን በመፈፀማችን ነው
-እግዚአሔር ሸክምን ከመስጠቱ በፊት ልብን ያዘጋጃል
-እግዚአብሔር ቃል ኪዳኑን ይጠብቃል ግን ትእዛዙን እንዲጠብቁለ ይፈልጋል
-ነህምያ የፈሰውን ቅጥሩን ብቻ ሳይሆን የሰዎችንም ጉዳት ነው
-ሙሴ ልክ እንደ ነምያ ከህዝቡ ጋር መከራን ተቀበለ
-እየሱስ እንዲሁ እረኛ እንደሌቸው አይቶ አዘነላቸው
-ነህምያ 1:8-9 አሁንም፡— ብትተላለፉ በአሕዛብ መካከል እበትናችኋለሁ፤ ወደ እኔ ብትመለሱ ግን ትእዛዜንም ብትጠብቁ ብታደርጓትም፥ ከእናንተ ሰዎች እስከ ሰማይ ዳርቻ ድረስ ምንም ቢበተኑ ከዚያ እሰበስባቸዋለሁ፥ ስሜም ይኖርበት ዘንድ ወደ መረጥሁት ስፍራ አመጣቸዋለሁ ብለህ ለባሪያህ ለሙሴ ያዘዝኸውን ቃል እባክህ አስብ።
-ነህምያ ጸሎት ብዙ ነገር የያዘ ነው ኪዳኑን ማስታወስ , አምኮ ነው, ኮንፌሽን ነው
- እየሱስም ሸክም ነበረው
- ሉቃስ 6:12 በነዚህም ወራት ይጸልይ ዘንድ ወደ ተራራ ወጣ፥ ሌሊቱንም ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ሲጸልይ አደረ።
- ነህምያ ከህዝቡ ጋር ቆመ ከተቸገሩጋ
-
- ነህምያ 1:6 እኔ ባሪያህ ዛሬ በፊትህ ስለ ባሪያዎችህ ስለ እስራኤል ልጆች ሌሊትና ቀን የምጸልየውን ጸሎት ትሰማ ዘንድ ጆሮህ ያድምጥ፥ ዓይኖችህም ይከፈቱ፤ በአንተ ላይም ያደረግነውን የእስራኤልን ልጆች ኃጢአት እናዘዝልሃለሁ፤ እኔና የአባቴም ቤት በድለናል።
ዳንኤል 9:5 ኃጢአትን ሠርተናል፥ በድለንማል፥ ክፋትንም አድርገናል፥ ዐምፀንማል፥ ከትእዛዝህና ከፍርድህም ፈቀቅ ብለናል፤
ነህምያ 2:2 ንጉሡም፡— ሳትታመም ፊትህ ለምን አዘነ? ይህ የልብ ኅዘን ነው እንጂ ሌላ ነገር አይደለም፡ አለኝ። እጅግም ብዙ አድርጌ ፈራሁ።
ነህምያ 2:3 ንጉሡንም፡— ንጉሡ ሺህ ዓመት ይንገሥ፤ የአባቶቼ መቃብር ያለባት ከተማ ተፈትታለችና፥ በሮችዋም በእሳት ተቃጥለዋልና ፊቴ ስለ ምን አይዘን? አልሁት።
-መለኮታዊ እድልም ነው እንድንሰራ በመመረጣችን ልክ እንደ ነህምያ
-ነህምያ መለኮታዊ እድልን መጠቀም አለብን
-እግዚአብሔር እናንተን ምክንያት ብዞዎችን ለማዳን ነው
አስቴር 4:14 በዚህ ጊዜ ቸል ብትዪ ዕረፍትና መዳን ለአይሁድ ከሌላ ስፍራ ይሆንላቸዋል፥ አንቺና የአባትሽ ቤት ግን ትጠፋላችሁ፤ ደግሞስ ወደ መንግሥት የመጣሽው እንደዚህ ላለው ጊዜ እንደ ሆነ ማን ያውቃል?”
ነህምያ 1:4 ይህንም ቃል በሰማሁ ጊዜ ተቀምጬ አለቀስሁ፥ አያሌ ቀንም አዝን ነበር፤ በሰማይም አምላክ ፊት እጾምና እጸልይ ነበር፥
ለሚወድዱህና ትእዛዝህን ለሚያደርጉ
ነህምያ 1:5 እንዲህም አልሁ፡— አቤቱ የሰማይ አምላክ ሆይ፥ ለሚወድዱህና ትእዛዝህን ለሚያደርጉ ቃል ኪዳንንና ምሕረትን የምትጠብቅ፥ ታላቅና የተፈራህ አምላክ ሆይ፥
ስለታደሰችው ከተማ እና እየሱስ ስራ !
ዘፍጥረት 3:15 በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፥ አንተም ሰኰናውን ትቀጠቅጣለህ።”
ራእይ 21:3 ታላቅም ድምፅ ከሰማይ፡— “እነሆ፥ የእግዚአብሔር ድንኳን በሰዎች መካከል ነው ከእነርሱም ጋር ያድራል፥ እነርሱም ሕዝቡ ይሆናሉ እግዚአብሔርም እርሱ ራሱ ከእነርሱ ጋር ሆኖ አምላካቸው ይሆናል፤
-እግዚአብሔር በየዘመኑ ኪዳኑን ያስባል
-እሱ መረጠን
ዮሐንስ 15:16 እኔ መረጥኋችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ አብም በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ እንዲሰጣችሁ፥ ልትሄዱና ፍሬ ልታፈሩ ፍሬአችሁም ሊኖር ሾምኋችሁ።
-እንደ ነህምያ እግዚአብሔር የነውን ማየት አለብን
-ስራው ተሀድሶ ንው አዲስ ስራ አይደለም
ምሳሌ 21:1 የንጉሥ ልብ እንደ ውኃ ፈሳሾች በእግዚአብሔር እጅ ነው፤ ወደ ወደደውም ያዘነብለዋል።
ነህምያ 2:17 እኔም፡— እኛ ያለንበትን ጕስቍልና ኢየሩሳሌም እንደ ፈረሰች፥ በሮችዋም በእሳት እንደ ተቃጠሉ ታያላችሁ፤ አሁንም ከእንግዲህ ወዲህ መሳለቂያ እንዳንሆን ኑና የኢየሩሳሌምን ቅጥር እንሥራ፡ አልኋቸው።
ነህምያ 2:18 የአምላኬም እጅ በእኔ ላይ መልካም እንደሆነች፥ ንጉሡም የነገረኝን ቃል ነገርኋቸው። እነርሱም፡— እንነሣና እንሥራ፡ አሉ። እጃቸውንም ለበጎ ሥራ አበረቱ።
-የጠላት መሳለቅያሆነናኔ ብሎ አለ
-ነህምያ 4:1 ሰንባላጥም ቅጥሩን እንደ ሠራን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቈጣ፥ ተበሳጨም፥ በአይሁድም አላገጠ።
ነህምያ 4:2 በወንድሞቹና በሰማርያ ሠራዊትም ፊት፡— እነዚህ ደካሞች አይሁድ የሚሠሩት ምንድር ነው? ይተዉላቸዋልን? ይሠዋሉን? በአንድ ቀንስ ይጨርሳሉን? የተቃጠለውንስ ድንጋይ ከፍርስራሹ መልሰው ያድኑታልን? ብሎ ተናገረ።
ነህምያ 4:3 አሞናዊውም ጦብያ በአጠገቡ ቆሞ፡— በድንጋይ በሚሠሩት ቅጥራቸው ላይ ቀበሮ ቢመጣበት ያፈርሰዋል፡ አለ።
-የእግዚአብሔርን ነገር ሲልቅ ጥላን ይናደዳል
-ነህምያ 6:15 ቅጥሩም በኤሉል ወር በሀያ አምስተኛው ቀን በአምሳ ሁለት ቀን ውስጥ ተጨረሰ።
ነህምያ 6:16 ጠላቶቻችንም ሁሉ ይህን በሰሙ ጊዜ በዙሪያችን የነበሩ አሕዛብ ሁሉ ፈሩ፥ በራሳቸውም አሳብ እጅግ ተዋረዱ፥ ይህም ሥራ በእግዚአብሔር እንደ ተደረገ አወቁ።
- የነህምያ ታሪክ ለእየሱስ መምጣት ምክንያት ነው
- በዚህ ዘመን እኛ እራሳችንን ስራውን ለመስራት እናዘጋጃለን