St. George Ethiopian Orthodox Tewahedo Church-Brisbane Australia

St. George Ethiopian Orthodox  Tewahedo Church-Brisbane Australia St George Ethiopian Orthodox Tewahedo Church in Brisbane Australia. Established in 2010.... Established in 2010, the St.
(1)

George's Ethiopian Orthodox Church has been serving the Brisbane Ethiopian Orthodox community and surrounding cities for over 4 years.

1. To expand the words of God according to the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church doctrine and teachings.

2. To provide the congregation with quality sacramental and liturgical services.

3. To construct/buy a new church building, this can accommodate bigger congregation

16/09/2022
02/09/2022
25/06/2022

✏በግፍ ለተገደለ ወገኞች ድምፅን ማሰማት በቤተክርስቲያን ተጀምሯል

👉በዋሽንግተን ዲሲ የድብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል ዛሬ ከቅዳሴ በኃላ ለተዋሕዶ ልጆች ጥሪ አቅርበዋል ፣ ይህ እጅግ በጣም የሚያስመሰግን ነው

👉በቀጣይ ሁሉም በዚህ መልክ መሄድ አለበት ከማንም በፊት ቤተክርስቲያን ድርጊቱን ማውገዝ አለባት ፣ ለዓለም ሕዝብ የግፍ ጭፍጨፋውን ማሳወቅ ተገቢ ነው ፣ ማነህ ባለሳምንት ••••ይቀጥላል•••••

👉ክብር እና ምስጋና ለካቴድራሉ አገልጋይ አባቶች ፣ካህናት እና ዲያቆናት እንዲሁም ለሰበካ ጉባኤው አባላት እና አጠቃላይ ለደብሩ ምዕመናን

24/06/2022
27/11/2021

ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበሉ! - የዕለቱ መልእክትበመምህር ዶ/ር ዘበነ ለማቅንብር:- e-BZ SolutionsNovember 2021 - Washington DC

26/11/2021

... ‼️
ሐሳብ አስተያየታችሁን አካፍሉን ሼር ሼር ሼር

በእልፍኛችሁ የምትመክሩብንን በአደባባይ
የሚገልጥልን የታመነ ነው ‼️
2ኛ ነገ 6÷11

የእሥራኤልን ንጉሥ ለመግደል በድብቅ ያሴረው የሶሪያ ንጉሥ በተደጋጋሚ ሊያገኘው አልቻለምና ልቡ ታውኮ

ባሪያዎቹንም ጠርቶ፦ ከእኛ ዘንድ ከእስራኤል ንጉሥ ጋር የተወዳጀ እንዳለ አትነግሩኝምን? አላቸው።

ከባሪያዎቹም አንዱ፦ ጌታዬ ሆይ፥ እንዲህ እኮ አይደለም፤ ነገር ግን በእልፍኝህ ውስጥ ሆነህ የምትናገረውን በእስራኤል ዘንድ ያለ ነቢይ ኤልሳዕ ለእስራኤል ንጉሥ ይነግረዋል አለው።

ይሄን የነብዩን የኤልሣዕን ብቃት አይቶ ልቡን ያልመለሰው ንጉሥ የመጨረሻው ውርደት ክፍሉን እንብባችሁ ስትጨርሱ ታገኙታላችሁ !!

በኢትዮጵያ ላይ በጓዳቸው ተደብቀው የሚመክሩባትን የአጋንንት ልጆች እግዚአብሔር በአደባባይ አጋልጦ አዋርዷል ።

እንደ ንጹህ ሰው ቤቴ ተፈተሸ ብላ እሪሪሪ ስትል የነበረች ባለጌና ዘረኛዋ እሌኒ ገ/መድህን ፣ የሽማግሌ አገር አፍራሽ ኤፍሬም ይስሐቅ ፣ ከዋናው የጅንታ ክንፍ ብርሃነ እና ከጋላቢዎቻቸው ጋር ቁጭ ብለው የመከሩብንን የምናመልከው አምላክ አሳልፎ ሰጥቶናል !!

የምንዋጋችሁ እየጸለይን እንጂ እያሴርን አይደለም !!

https://youtu.be/NYOOEts_b-o

14/11/2021

ስለ አቡነ በርናባስ የቱ ነው እውነቱ?

አቡኑ በሀገረ ስብከታቸው በአገልግሎት ላይ ናቸው የሚለው ዜና በተደጋጋሚ እየተሰማ ነው። በተለይም መምህር በላይ ወርቁ ቅርበት ያላቸውን ሦስት ሰዎች ጠቅሶ ያስተላለፈው መልእክት የተሻለ የቅርብ ዜና ነው።

፩. ከምንም በላይ ደኅንነታቸው ይቀድማል። ክፉ አይንካቸው። ከራሳቸው በላይ ለሕዝቡ ያስፈልጉታል። ታፈኑ ተብሎ ተነግሮ ሊገኝ ከሚችለው የፕሮፓጋንዳ ጥቅም ይልቅ ነገሩ ሐሰት ሆኖ የሚገኘው ጥቅም ይበልጣል ይመረጣልም። ይህን የማይረዱ ሰዎች እልፍ ቃላት ቢናገሩ አምስት የልብ ቃላት ይመረጣሉ።

፪. አልታፈኑም ነበር ወይም ማስፈራሪያ አልደረሰባቸውም ያለ እስካሁን አልተገኘም። በድርጊታቸው ከተቆጡ ለጊዜውም ቢኾን አፍነው ወይም ከዕይታ ሰውረው ሊያስፈራሯቸው ሊያንገላቷቸው ከዚያም ሊመልሷቸው ይችላሉ። ስለዚህ መታየታቸው ብቻ ላለመታፈናቸው ብቸኛ አስረጂ ላይኾን ይችላል።

፫. አልታፈንሁም ብለውናል ያሉ ሰዎች እስካሁን አልሰማንም።

፬. አቡኑ ቢታፈኑ እንኳ ለሕዝቡ ደኅንነት ሲሉ ያለመናገራቸው ዕድል ሰፊ ነው። አባታችን ለምን ይነካሉ? የሚል አይጠፋምና ያኔ የሚመጣውን መከራ ለመከላከል ሲሉ በልባቸው ወደመጠበቁ ሊያዘነብሉ ይችላሉ።

ታፍነዋል የሚለውም አልታፈኑም የሚለውም ወገን የሚሔዱበት የመረጃ አሰባሰብ ተመሳሳይ መኾኑ ግንዛቤ ውስጥ ይግባ። ለጊዜው ግን የወንድማችን የበላይ ወርቁን ቃል መያዝ የሚሻል ይመስለኛል።

እውነቱ እስኪጣራ ከአጓጉል ድምዳሜ ራስን ማራቅ ይመከራል። ብፁዕ አባታችን ባሉበት ደኅና ይኹኑልን ቡራኬአቸውም ትድረሰን።
Kassie

26/09/2021

‎እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ በሰላም አደረሰን፡፡

ከመ/ር ሸዋንዳኝ አበራ

«የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና።»
(፩ኛ ቆሮንቶስ ፩፥፲፰)

ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ ሲል ቤዛ የሆነበት ቅዱስ መስቀል ከጌታ ትንሣኤና ዕርገት በኋላ ተአምራትን በማድረግ ሙታንን ማስነሣት፥ በሽተኞችን መፈወስ፥ አጋንንትን ማውጣት ስለጀመረ አይሁዶች በምቀኝነት ተነሣስተው የጌታን በሰቀሉበት ከኢየሩሳሌም ከተማ ዳርቻ በዕብራይስጥ ጎልጎታ በጽርዕ ቀራንዮ (ራስ ቅል) ከተባለው ኮረብታ ላይ ቀብረው ቦታውንም የከተማው ቆሻሻ መጣያ ስፍራ አደረጉት፡፡

ከ፫፻ ዓመታት በኋላ እግዚአብሔር ንጉሥ ቆስጠንጢኖስን አስነሣ፡፡ቆስጠንጢኖስ መክስምያኖስ ከሚባል ጠላቱ ጋር አስጨናቂ የሆነ ጦርነት ላይ በነበረበት ወቅት በሰማይ ላይ ብርሃናዊ የመስቀል ምልክት ታየው፤ «ከዚያም በዚህ ምልክት ጠላትህን ታሸንፋለህ፡፡» የሚል ድምፅ ከሰማይ ሰማ፡፡ (ይህ የሆነው ቆስጠንጢኖስ ለብቻው ሁኖ በተመስጦ እያሰበ ሳለ ነው፡፡) ምንም እንኳን ንጉሡ አባቱ ከአህዛብ ወገን ቢሆንም እናቱ እሌኒ ልጇን ቆስጠንጢኖስን ቅዱስ ወንጌልን በማስተማርና በክርስቲያናዊ ሥነምግባር ያሳደገችው በመሆኑ ወዲያውም የክርስትናን እምነት ተቀበለ፤ መስቀልን የመንግሥቱና የሠራዊቱ አርማ አደረገ፡፡ በሠራዊቱ ልብሶች፣ የጦር ዕቃዎች፣ ፈረሶች ሁሉ ላይ የመስቀልን ምልክት አድርጎ ጠላቱን በመዋጋት ድል አደረገ፤ ለክርስቲያኖች ነጻነትን ሰጠ የዘመነ ሰማዕታት ፍጻሜ ሆነ፤ ክርስቲያናዊ መንግሥትም በአውሮጳ ተመሠረተ፡፡

በ፫፻፳፮ ዓ.ም. የሮሜው ቄሳር ቆስጥንጢኖስ ቀዳማዊ (Constantine I ) እናት ንግሥት እሌኒ በሃይማኖትም በምግባርም ፍጹም ነበረችና የጌታን መስቀል ከተቀበረበት ለማስወጣት ወስና ወደ ኢየሩሳሌም በመሄድ መስቀሉ የተቀበረበትን ሥፍራ ስታጠያይቅ ኪራኮስ እና አሚኖስ የተባሉ ዕብራውያን አረጋውያንን አገኘችና ጌታን የሰቀሉት የት ነው ብላ ጠየቀቻቸው፤ ኪራኮስም አባቴ እንደነገረኝ ሥፍራው ዕብራውያን ጎልጎታ በሚሉት በጽርዕ ቀራንዮ በሚባለው የራስ ቅል ተብሎ በሚታወቀው ሥፍራ ነው በማለት ገለጸላት፡፡

በኪራኮስ ጥቆማ መሠረት በጎልግታ (በቀራንዮ) ተራራ ላይ ቁፋሮ ቢጀመርም መስቀሉ ሊገኝ አልቻለም፡፡ በኋላ አባ መቃርስ የተባለው የኢየሩሳሌም ኤጲስ ቆጶስ አይሁድ መስቀሉን አስቀብረው ቦታውን የቆሻሻ መጣያ እንዳደረጉትና ቦታውም በተራራው ላይ ባሉት ኮረብታ መሰል ክምሮች አንዱ እንደሆነ ነገራት፡፡ ይሁን እንጂ በጎልጎታ (በቀራንዮ) ተራራ ላይ በርካታ ትናንሽ ኮረብታዎች ክምሮችን በመኖራቸው መስቀሉ ያለበት ሊታወቅ አልቻለም፡፡

ንግስት እሌኒ ሱባኤ ገብታ ጸሎት ማድረግ ጀመረች፡፡ በሱባኤዋም ወቅት መልአክ ተገልጦ ደመራ አስደምራ ዕጣን ብትጨምርበት ጢሱ መስቀሉ ያለበትን እንደሚያመለክታት ነገራት፡፡

በዚህም መሠረት መስከረም ፲፮ ቀን ታላቅ ደመራ አስደምራ እሳት አስለኩሳ በጣም ብዙ ዕጣን ጨመረችበት የዕጣኑ ጢስም ወደ ሰማይ ወጥቶ ተመልሶ መስቀሉ ወዳለበት በጎልጎታ (ቀራንዮ) ኮረብታ ተመለሰና መስቀሉ ያለበትን አመለከተ፡፡ በማግስቱ መስከረም ፲፯ ቀን በቁፋሮ ፍለጋው ተጀመረ፡፡ (‎ደመረ ማለት አንድ ሆነ፣ ጨመረ፣ ሰበሰበ ማለት ሲሆን ደመራ ደግሞ መሰብስብ፣ መጨመር፣ መከመር የሚል ትርጓሜ አለው፡፡)

ከስድስት ወር ትጋት በኋላ በመጋቢት ፲ ቀን የጌታችንና አብረውት የተሰቀሉት ሁለቱ ወንበዴዎች ሦስት መስቀሎች ተገኙ፡፡ ከነዚህም የጌታችን መስቀል ሙት በማስነሣቱና ድውያንን በመፈወሱ ተለይቷል፡፡ መስቀሉ የተገኘበት የመጋቢት ወር የታላቁ የጌታ ጾም ወቅት ስለሆነና በዚህ ወቅትም ታላላቅ በዓላትን ማክበር ስለማይገባ የመስቀል በዓል ቁፋሮው በተጀመረበት ዕለት መስከረም ፲፯ ቀን እንዲከበር አባቶች በጉባኤ ወሰኑ፡፡

በዚሁም መሠረት በአገራችን ደመራን በዕለቱ መስከረም ፲፮ ቀን እንዲሁም መስቀልን ፍለጋው በተጀመረበት ዕለት መስከረም ፲፯ በብሔራዊ ደረጃ ስናከብር መጋቢት ፲ ቀን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንችን ዕለቱን በማኅሌትና በቅዳሴ ስታከብር፥ በተለይም በመስቀለ ክርስቶስ በተሰየሙ አድባራት ታቦተ ሕጉን በማውጣት በንግሥ ይከበራል፡፡ ንግስት እሌንም በዚህና በሌሎችም ምግባሯ የቅድስና ማዕረግ ተሰጥቷታል፡፡

በኢትዮጵያ የበዓሉ አከባበሩ ከሌላው የዓለም ክፍል የተለየ የሆነበት ምክንያት ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የሐዋርያት ትምህርት ይዛ መቀጠሏ ነው፤ ይህ በዓል በኢየሩሳሌም በተመሳሳይ ሲከበር ቆይቶ በ፲፩፻፸ዎቹ ኢየሩሳሌም በኦቶማን ሥር በመውደቋ ይህንና ሌሎች የክርስትና በዓላትና ሥርዓቶች በገዢዎቹ እስላሞች ተጽእኖ ምክንያት ተቋረጡ፡፡ የአርሜንያ ኦርቶዶክስ ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንየመስቀል በዓልን በኛ መስከረም ፲፯ (27 September) ስታከብር ይህን ታላቅ የጌታችንን መስቀል በዓል ለማክበር ለጌታችን ክብር ሲሉ በዓሉን አምስት ቀን በመጾም ይቀበሉታል፡፡ በሌላውም የዓለም ክፍልም ቢሆን ሀገራቱ በቅኝ ገዢዎች ሥር ስለወደቁና ገዢዎቹም የእስልምና፥ የካቶሊክና የፕሮቴስታንት ሃይማኖት ተከታዮች በመሆናቸው የሐዋርያትና ሐዋርያዊ ትውፊቶች እንዲቀሩ በመደረጉ በርካታ ሃይማኖታዊው እና ባህላዊ ሥርዓቶችና ቅርሶች ከማንነት ጋር እንዲጠፉ ተደርጓል፡፡

ኢትዮጵያችን ግን በልዑል እግዚአብሔር እርዳታና በጀግኖች አባቶቻችን ደም፥ አጥንትና ሕይወት መስዋዕትነት በነጻነት ስለኖረች ከነዚህ መሰል ጫናዎች ውጭ ያላገኛት በመሆኑ ሃይማኖታዊና ባህላዊ ሥርዓቶቻችን መሠረታቸውን ሳይለቁ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሊሸጋገሩ ችለዋል፡፡

እኛም በመስቀል ላይ የተከፈለልንን ዋጋ እያሰብን እንደ አባቶቻችን «እሰግድ ለመስቀለ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘተሰቅለ ቦቱ ለቤዛ ኵሉ ዓለም፥ መስቀል ኃይልነ፥ መስቀል ጽንዕነ፥ መስቀል ቤዛነ፥ መስቀል መድኃኒተ ነፍስነ፥ አይሁድ ክሕዱ ንሕነሰ አመነ ወእለ አመነ በኀይለ መስቀሉ ድኅነ፡፡» እንላለን፡፡

የመስቀሉ በረከት በሁላችንም ላይ ይደርብን፡፡

ልዑል እግዚአብሔር
ሃገራችን፥ ወገኖቻችንና ቤተ ክርስቲያናችንን ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቀን፡፡

19/09/2021

አንቺ ኢትዮጵያ እናቴ ለምን እንደማትፈርሺ ልንገርሽ!በመምህር ዶ/ር ዘበነ ለማSeptember 2021 - Washington DC

04/11/2019

Address

15 Eric Crescent
Annerley, QLD
4103

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when St. George Ethiopian Orthodox Tewahedo Church-Brisbane Australia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share