ዱባይ ደብረ መዊዕ ቅ/ሚ/ወቅ/አ/ቤ/ክ/ሰ/ት/ቤ/ት

ዱባይ ደብረ መዊዕ ቅ/ሚ/ወቅ/አ/ቤ/ክ/ሰ/ት/ቤ/ት የዱባይ ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤልና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን ክብረ ቅዱሳን ሰንበት ትምህርት ቤት

08/04/2023
07/04/2023

ይህንን ማስታወቂያ ለኦርቶዶክሳውያን በሙሉ ያጋሩ።

ኦርቶዶክሳውያን ይህን ማስታወቂያ ለሌሎች አጋሩ።
07/04/2023

ኦርቶዶክሳውያን ይህን ማስታወቂያ ለሌሎች አጋሩ።

11/05/2022

በስመ አብ፣ወወልድ፣ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
በሊባኖስ፣ በተባበሩት ዓረብ ኢምሬትስ እና በመካከለኛው ምሥራቅ ሀገረ ስብከት ለምትገኙ የአድባራት አስተዳዴሪዎች፣ ማኅበረ ካህናት፣የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶችና ማኅበረ ምእመናን በሙሉ።
ጉዳዩ፦ ስለ ሀገራችን ኢትዮጵያ እና ሕዝቧ የሦስት ሱባኤ ጥብቅ ምህላና ጸሎት ስለ መያዝ ይሆናል።

“ጸግዋ ሰላመ ለሀገሪትነ ኢትዮጵያ ለታዕካሃ፣ ወለሠራዊታ፣ወለመኳንንታ፣ወለሕዝባ- ለሀገራችን ለኢትዮጵያ፣ላንድነቷ፣ለሠራዊቷም፣ለመኳንንቷም፣ለሕዝቧም ሰላም ስጣት ” ሥርዓተ ቅዳሴ
እግዚአብሔር አምላክ ምድርን የሰው ልጆች ጊዜያዊ መኖሪያ አድርጎ ከሰጠ በኋላ የሰው ዘር ተባዝቶ፣ ሀገር አቅንቶ፣ አንድነት አጽንቶ፣ በመሪዎች ምሪት፣በሀገሩ ሕዝብም መፈቃቀርና መተሳሰብ ሰላምን ገንዘብ አድርጎ መኖር ከጀመረ ብዙ ሺ ዓመታት ተቆጥረዋል።
ቅድስት ሀገራችን ኢትዮጵያ ልዩ ልዩ ሃይማኖት የሚከተሉ እና የተለያዩ ቋንቋዎችን የሚናገሩ ሕዝብቦች መኖሪያ ስትሆን።አንድነቷን ያጸኑ፣ በመሪነት ሀገርና ሕዝብን ሲያገለግሉ የነበሩና ለሰው ልጅ ታላቅ ክብር የነበራቸው ሕዝቦቿ ኢትዮጵያን አስከብረው፣በአንድነታቸው ተከትረው በሰላም ኖረዋል። ይህ ማለት ግን ችግሮች አልገጠሟቸውም ማለት አይደለም። በሕዝብና በሀገር ላይ የመጣውን ችግር ሁሉ እንደ ሕዝብና ሀገር ምላሽ እየሰጡ አንድነታቸውን ጠብቀው ሰላማቸውን ታጥቀው ኖሩ እንጅ።

የተወደዳችሁ የቅድስት ቤተክርስቲያን ልጆች የቀደሙት ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ለአንድነታቸውና ለሰላማቸው መሠረት ያደረጉትም የአንድነት መንፈስን፣ ጾምን፣ጸሎትን፣ ፈሪሃ እግዚአብሔርን ነበር። ከእነርሱ በተቀበልነው ሃይማኖታዊ ትምህርትና ሥርዓት መሠረትም እንዲሁ እያደረግን እስከዛሬ በአንድነት አለን።
ኢትዮጵያውያን ልዩ ልዩ ቋንቋ ቢናገረም፣ክርስቲያኖቹ በቤተክርስቲያን እስላሞቹ በመስጊድ እየጸለዩ፣ በኑሮ ደረጃቸው ከዝቅታ እስከ ከፍታ እየኖሩ በኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያውያን ጉዳይ ግን እንድነታቸውን እንደ ዐይን ብሌን ተጠንቅቀውለት ኖረዋል፤ እየኖርን ነው። የአንድነታቸውን ጥብቀት እና ጥልቀት ቤተክርስቲያን ሲታነጽ እስላሞቹ ማሠራታቸው፣መስጊድ ሲሠራ ክርስቲያኖች ማዋጣታቸው፣ በሁለቱ ሃይማኖቶች በዓላትም ተጠራርተው ማክበራቸው ጉልህ ማሳያ ነው። ይህ በሌላው ዓለም የለም።
ቅድስት ሀገራችን በአሁኑ ወቅት ያለችበት ሁኔታ ጥብቅ የሆነ ጾምና ጸሎት፣ በወሬ የማይፈታ አንድነት፣ በታማኝነት፣በሀገርና ሕዝብ ፍቅርና ቁርጠኝነት የተታታ ሀገር አቀፋዊ አንድነትና መተሳሰብ የሚፈልግ ነው። በዚህ አስቸጋሪ ወቅት እንደ ሀገር ማሰብ ካልተቻለ ችግሩ ችግር እየወለደ ለመቋጨት የሚያስቸግር መከራ ይዞ ሊመጣ ይችላል። ይህ እንዳይሆን ቤተ ክርስቲያን በጸሎት፣ በአንድነት እና በመመካከር ለችግሩ መፍትሔ ይመጣ ዘንድ ዘወትር ትጸልያለች።
ምንም እንኳን ያለንበት ወቅት ወርኃ ትንሣኤ በመሆኑና ጾምና ንስሐ የማይሰጥበት ጊዜ ቢሆንም የጸሎት አዋጅ ግን የማይቋረጥ የቤተክርስቲያናችን አዋጅ በመሆኑ እግዚአብሔር አምላክ ለሀገራችን ሰላም እንዲያወርድ፣በሕዝባችን መካከል የገባው የመለያየት እና የመከፋፋት መንፈስ እንዲወገድ፣እግዚአብሔር መአቱን በትግስት ቁጣውን በምህረት ይቅር እንዲለን ከግንቦት 1/2014 ዓ.ም ጀምሮ በሀገረ ስብከታችን በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ስለ ሀገራችን ኢትዮጵያና ስለ ሕዝቧ ጥብቅ የሆነ የሦስት ሱባኤ ምህላና ጸሎት እንዲያዝ አውጀናል።
ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን።

Address

Oud Metha
Dubai

Telephone

+971554629521

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ዱባይ ደብረ መዊዕ ቅ/ሚ/ወቅ/አ/ቤ/ክ/ሰ/ት/ቤ/ት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to ዱባይ ደብረ መዊዕ ቅ/ሚ/ወቅ/አ/ቤ/ክ/ሰ/ት/ቤ/ት:

Share