Uriel Amene

Uriel Amene ኢየሱስ ክርስቶስ ያድናል ዛሬም በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ከየትኛውም ጥያቄ ያሳርፋል ። የእግዚአብሔርን መንግስት በቅንነት የማገልገል የክርስቶስ ባሪያ የመንፈስ ቅዱስ ወዳጅ ባለራዕይ ወጣት

11/04/2024

ሙሉ ቀን_ወዳጆን_እንዲጋብዙ_ግብዣችን_ነው!!

"መንፈስ ቅዱስህን ከእኔ አትውሰድብኝ!"ለእኔ የመጨረሻው ትልቁ ሥጦታ መንፈስ ቅዱስ ነው። አንድ ሰው መንፈስ ቅዱስ ተሰጥቶት ሌላ ነገር የሚለምን ከሆነ ይገርመኛል። በነገራችን ላይ ለእኔ እግ...
30/10/2023

"መንፈስ ቅዱስህን ከእኔ አትውሰድብኝ!"

ለእኔ የመጨረሻው ትልቁ ሥጦታ መንፈስ ቅዱስ ነው። አንድ ሰው መንፈስ ቅዱስ ተሰጥቶት ሌላ ነገር የሚለምን ከሆነ ይገርመኛል። በነገራችን ላይ ለእኔ እግዚአብሔር ሊሰጠኝ የሚችለውን የመጨረሻውን ጥግ ስጦታ ሰጥቶኛል፣ መንፈስ ቅዱስን! ሌላው በዓለም ላይ የማየው ነገር ሁሉ "ቱል ቦክስ" ወይም መፍቻዎች ያሉበት ሳጥን ዓይነት ነው። እና "ቱል ቦክስ" ያስጨንቅሀል? ልብህን ይይዛል? በህልምህ ይመጣል? የለም! "ቱል ቦክስ" ስትፈልገው ብቻ የምትጠቀምበት ነገር ነው።

በዓለም ላይ ያለው ነገር ሁሉ ለእኔ እንደዚያ ነው። እንደ "ቱል ቦክስ" ነው የሚታየኝ። ስፈልገው ብቻ ነው የማነሳው፣ ሲያስፈልገኝ ብቻ የምጠቀምበት እንጂ ለእኔ ምኔም አይደለም። ለእኔ ትልቁ ሥጦታ መንፈስ ቅዱስ ነው። ዳዊት ሲጸልይ "የሠጠኸኝን መንግሥቴን አትውሰድብኝ፣ የሰጠኸኝን ሚስቶች፣ ልጆች አትውሰድብኝ" አላለም፥ "መንፈስ ቅዱስህን ከእኔ አትውሰድብኝ" ነው ያለው።

ስለዚህ ከጌታ ጋር ባሳለፍኩት ዘመን የኖርኩትን ኑሮ ሁሉ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ነው የኖርኩት። ይኼን የእግዚአብሔር ስጦታ በሕይወቴ ካየሁ በኋላ በጣም የሚገርም ልምምድ ውስጥ ገባሁ። በዚያ ወቅት በምጸልይበት ጊዜ ሁሉ የእግዚአብሔር መገኘት፣ "ፕረዘንሱ" ለአካላቴ ጭምር በጣም ነበር የሚሰማኝ። ተንበርክኬ ስጸልይ እጆቼን አንድ ላይ ማገናኘት እንኳ አልችልም ነበር፤ እሳት ነው የሚሆነው፣ ይቃጠላል። አንዳንዴ የተቃጠለ እየመሰለኝ ዓይኖቼን ከፍቼ አይም ነበር።

ከዚህም የተነሳ ደግሞ በጣም ብዙዎች በአገልግሎቴ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልተዋል። ምናልባት በሺህ የሚቆጠር፣ በጣም ብዙ ሕዝብ፤ በኢትዮጵያ ዙሪያ፣ በዓለም ዙሪያ ሁሉ። ለእኔ መንፈስ ቅዱስ የጸጋ ስጦታ አይደለም፤ የጸጋ ስጦታን ይሰጣል እንጂ እርሱ ፐርሰን [አካላዊ ማንነት ያለው] ነው።

ወንጌላዊ ያሬድ ጥላሁን!
⏰⏰⏰

🤚 እኔም እላለሁ ፦"መንፈስ ቅዱስህን ከእኔ አትውሰድብኝ"

🙏አሜን!

© ሽመልስ ይፍሩ

29/10/2023
22/10/2023

ዘዳግም 32 (Deuteronomy)
9፤ የእግዚአብሔር እድል ፈንታ ሕዝቡ ነው፤ ያዕቆብም የርስቱ ገምድ ነው።
10፤ በምድረ በዳ በጥማት፥ የነፋስ ጩኸትም በሞላበት ውድማ አገኘው፤ ከበበው ተጠነቀቀለትም፤ እንደ ዓይን ብሌን ጠበቀው።
11፤ ንስር ጫጩቶቹን እንደሚያወጣ፥ በእነርሱም ላይ እንደሚሰፍፍ፥ ክንፎቹን ዘርግቶ ወሰዳቸው፥ በክንፎቹም አዘላቸው።
12፤ እግዚአብሔር ብቻውን መራው፤ ከእርሱም ጋር ሌላ አምላክ አልነበረም።

22/10/2023

19/10/2023


   🖐 (በቴሌግራም አገልግሎት)ጥቅምት 5/2016 ( Oct 16/2023) 🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐በሀልዎት_አማኑኤል_ህብረት_ቤክ_የሚተላለፈውን_የቴሌግራም_አገልግሎት_ለመቀላቀል_ሊንኩን_ይ...
16/10/2023


🖐
(በቴሌግራም አገልግሎት)
ጥቅምት 5/2016 ( Oct 16/2023)
🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐
በሀልዎት_አማኑኤል_ህብረት_ቤክ_የሚተላለፈውን_የቴሌግራም_አገልግሎት_ለመቀላቀል_ሊንኩን_ይጫኑ! 👇
https://t.me/+7EPva304eNE0ZTI0
🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐
እስከዛሬ የተላለፉትን መልዕክቶች ለማግኘት ደግሞ ቻናሉን ይቀላቀሉ
https://t.me/halwotchurch
🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐

🖐 የማይወሰድ ሠላም፣ የእርሱ የመሆናችሁ ማሳያ የሆነ ሰላም ለእናንተ ይሁን፣ ሰላም ለእናንተ ይሁን፣ ለቤታችሁ ይሁን፣ ይህ የጌታዬ ሰላም በትዳራችሁ፣ በኑሯችሁ፣ በብዙ ፈተና ላላችሁ ሰላም ለእናንተ ይሁን
🖐 በአለም ተረጋግታችሁ የምትኖሩበት ሰላም ለእናንተ ይሁን፣ በፈተናዎች መሐል የምትጸኑበት ሰላም፣ በብዙ አሳዛኝና ልብን በሚያወርዱ ዜናዎች መካከል የምትኖሩበት ሰላም፣ በአለም ሆናችሁ የምትኖሩበት ሰላም ለእናንተ ይሁን፣ ይንካችሁ፣ ሙቀታችሁ ይሁን፣ አለማችሁ ይሁን፣ ይህ ሰላም ለእናንተ ይሁን
🖐 በምትሔዱበት፣ በቀራችሁ እድሜ የተሰጣችሁን ተልዕኮ፤ ስራዎቻችሁን፤ እድሜዎቻችሁን ስትፈጽሙ፤ እግዚአብሔር በዚህ ምድር ኑሩ ያላችሁን እድሜ ስትኖሩ፣ ስሩ ያላችሁን ስራ ስትሰሩ፣ ፈጽሙ ያላችሁን ስራ ስትፈጽሙ፣ ውጡ ባላችሁ ቦታ ስትወጡ፣ ግቡ በተባላችሁበት ቦታ ስትገቡ፣ ስትመላለሱ በመንፈስ ቅዱስ መጽናናት በመሔድ ተባረኩ በኢየሱስ ስም
🖐 በስደት መሐል መጽናናት፣ በክፉ ወሬ መሐል መጽናናት፣ በፈተና መሐል መጽናናትነ፣ ነገር ሁሉ በሚቀየር ሰአት መጽናናት፣ መንፈስ ቅዱስ በሚሰጠው መጽናናት ይሁንላችሁ በኢየሱስ ስም፣ በዚህ ሰላም ውጡ፣ ግቡ፣ "አጽናኙን እልክላችኋለሁ" እንዳለ በተላከልን፣ በተቀበልነው፣ በዚህ መንፈስ ቅዱስ መጽናናት፤ መሔድ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይሁንላችሁ
🖐 በዚህ አለም የምትኖሩ ግን የዚህ አለም እንዳልሆናችሁ አስታውቁ፣ በተጠበቀ ሰላም በመንፈስ ቅዱስ መጽናናት እየሔዳችሁ ተልዕኮቻችሁን የምትፈጽሙ፤ የምትኖሩ ይሁንላችሁ፣ አለም የምትነካው፣ የሷ ያልሆነ ይህ ሰላም፤ ይህ የመንፈስ ቅዱስ መጽናናት በእናንተና በቤታችሁ ላይ ይሁን
🖐 የተባረከ ሳምንት፣ የተባረኩ ቀኖችን፤ ለሊቶችን አሳልፎ በሰላም ኑሩ፤ በሰላም አገልግሉ፣ ተጠበቁ፣ እግዚአብሔር ከክፉ ይጠብቃችሁ የአምላክ ደግነት በእናንተና በቤታችሁ ላይ ይሁን፣ አይዟችሁ! ኢየሱስ ተመልሶ ቶሎ ይመጣል! ደግሞ መለዋወጥ፣ መፈራረቅ ወደሌለባት አለም፤ ወደላይኛይቱ ምድር፤ ወደላይኛይቱ አገር፤ አምላክ ወዳዘጋጀልን ከተማና አገር እንገባለን፤ ወደዛችኛይቱ ከተማ እንገባለን፤ ኢየሱስ ዘላለማችንን በዚህ ይጠብቃል ተባረኩ! ውጡ፣ ታምናችሁ ተሰማሩ፣ የተባረከ ቀን፤ የተባረከ ሳምንት ይሁንላችሁ🙏
🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐
በኢትዮጵያ አማኑኤል ኅብረት ቤተክርስቲያን ሀልዎት አጥቢያ
አድራሻ፦ ወሎ ሰፈር ጎርጎሪዮስ አደባባይ ፊውቸር ታለንት ት/ት ቤት አጠገብ
☎️ +251118633493 📱+251 973 422024

Address

Jemo
Jemo

Telephone

+251912628330

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Uriel Amene posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Uriel Amene:

Share