ምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም

  • Home
  • ምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም

ምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም, Convent and monastery, .

የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በአዲስ አበባ  የሰላምና የያብሮነት የጸሎት መርሐ ግብር " ሃይማኖታዊ እሴቶቻችን ለዘላቂ ሰላማችን  " በሚል መሪ ቃል ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና የ...
24/05/2026

የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በአዲስ አበባ የሰላምና የያብሮነት የጸሎት መርሐ ግብር " ሃይማኖታዊ እሴቶቻችን ለዘላቂ ሰላማችን " በሚል መሪ ቃል ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና የሌሎች ሃይማኖት ተቋማት ተወካዮች በተገኙበት አደረገ።

ግንቦት 16 /2018 ዓ/ም
ምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም

በአራዳ ፓርክ በተከናወነው ጸሎት መርሐ ግብሩ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፤ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፤አገኘሁ ተሻገር የፌዴሬሽን ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ፣ ንቡረዕድ ኤልያስ አብርሃ የጠቅላይ ቤተክህነት የመንፈሳዊ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ : መልአከ ምሕረት ቆሞስ አባ ገብረ መድኅን ንጉሤ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያው ሓላፊዎች የየገዳማት አስተዳዳሪዎች እንዲሁም ሌሎች የመንግሥት ተወካዮች ተገኝተዋል።

በሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የተዘጋጀው ሀገር አቀፍ ልዩ የጸሎት መርሐ ግብር ላይ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ባደረጉት ንግግር ዘጠና ስምንት በመቶ አማኝ ህዝብ ያለበ ሀገር ዎች እንደመሆኑ መጠን የሃይማኖት መሪዎች ለሀገር ሰላም በአብሮነት መቆም አስፈላጊ በመሆኑ በአንድነት ለሀገር ሰላም ልንጸልይ ይገባል ብለዋል ።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሊቃነጳጳስ ፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያው ሓላፊዎች እና የአድባራት አስተዳዳሪዎች የመሐረነ አብ ጽሎት ያደረሱ ሲሆን በብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ቃለምዕዳን እና ቡራኬ ተሰጥቷል።

©EOTC TV

የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም 81ኛ ዓመት  የአንድነት ኑሮ ምሥረታ ክብረ በዓል ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት ተከብረ ።  ምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም     ግንቦት...
24/05/2026

የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም 81ኛ ዓመት የአንድነት ኑሮ ምሥረታ ክብረ በዓል ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት ተከብረ ።

ምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም
ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ.ም

የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም 81ኛ ዓመት የአንድነት ኑሮ ምሥረታ ክብረ እጅግ ባማረ በድምቀት ተከብረ በበዓሉም ላይ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም የበላይ ኃላፊ ፣ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ የማይጨው አላማጣ እና ራያ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቤተ መጻሕፍት ወመዘክር እና ማኅበራት ምዝገባ ክትትል እና ቁጥጥር መምሪያ የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያው የሥራ ኃላፊዎች ፣ አበው መነኮሳት ፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ፣ ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች ተገኝተዋል ።

በዕለቱም በሚያዚያ 27 ቀን 2018 ዓ.ም የ76 ኛ ዓመት የቅዳሴ ቤቱ ክብረ በዓል በማስተባበር እንዲሁም ልዩ አስተዋፅኦ ላደረጉ የገዳሙ ባለሟሎች የሰርተፍኬት ስጦታ ተበርክቶላቸው በጸሎት የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል ።

በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት የለገጣፎ ኆኅተ ገነት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን ቅዳሴ ቤት ተከበረ።ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ.ምምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም ቅዳሴ ቤቱ ...
24/05/2026

በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት የለገጣፎ ኆኅተ ገነት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን ቅዳሴ ቤት ተከበረ።

ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ.ም
ምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም

ቅዳሴ ቤቱ ሲከበር ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፤ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፤ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፤ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፤ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መገናኛ ብዙኀን ድርጅት የበላይ ሓላፊ የሰሜንና ምሥራቅ አፍሪካ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስን ጨምሮ ሌሎችም ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተገኝተዋል።

በተጨማሪ የሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት የሥራ ሓላፊዎች ፤ መልአከ ገነት መምህር ኤርምያስ ውብሸት የለገጣፎ ኆኅተ ገነት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ፤ አገልጋይ ካህናትና ፤ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ፣ ዘማሪያንና በርካታ ምእመናን ቅዳሴ ቤቱ ሲከበር የበረከቱ ተካፋይ ሁነዋል።

በዚሁ መርሐ ግብር ታቦተ ሕጉ ከመንበሩ ወጥቶ ምእመናንን የባረከ ሲሆን በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን እና በሰንበት ትምህርት ቤት ዘማርያን ሕንጻ ቤተክርስቲያኑ ቅዱስ ፓትርያርኩን ጨምሮ በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ቡራኬ ለምርቃት መብቃቱንና የቅዳሴ ቤቱ መከበሩን የሚያዘክር ያሬዳዊ ጥዑመ ዜማ ቀርቧል።

ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መገናኛ ብዙኀን ድርጅት የበላይ ሓላፊ የሰሜንና ምሥራቅ አፍሪካ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በሰጡት ትምህርት ደግሞ በአዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን "ቅዳሴው በሊቃነ ጳጳሳት ተቀድሶበታል ፣ሕፃናት አረጋዊያንም ቆርበውበታል ፣ከዚህ የበለጠ ደስታ ምንም ነገር የለም ፣ እንኳን ደስ ያላችሁ" ብለዋል።

ብፁዕነታቸው አክለውም ይህ ሕንጻ ቤተክርስቲያን እንዲጠናቀቅ መመሪያ ሰጥተው ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ.ም ቅዳሴ ቤቱ እንዲከበር ላደረጉት ለብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና ሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ምስጋና ይገባቸዋል ሲሉም ተደምጠዋል።

ከዚህ በመለስ የለገጣፎ ኆኅተ ገነት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን ግንባታ ለፍፃሜው እንዲበቃ ገንዘባቸውን ፣ እውቀታቸውንና ጊዜያቸውን በበጎ ፈቃደኝነት የሰጡ እንዲሁም በአስተባባሪነት ፣ በልዩ ልዩ የሥራ ድርሻዎችና ሓላፊነቶች የጎላ ድርሻ የነበራቸው ሁሉ ከቅዱስ አባታችን ሽልማት ወስደዋል።

በመጨረሻም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፤ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በሰጡት ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ "እግዚአብሔር አምላክ ይህንን ሕንጻ ቤተክርስቲያን ለማነፅ አነሳስቶ ስላስፈፀማችሁ እንኳን ደስ ያላችሁ" ብለዋል።

ቅዱስ አባታችን ለለገጣፎ ኆኅተ ገነት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን ምእመናን "ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተላለፈ ለብዙ ዘመናት መገልገያ የሚሆናችሁን እግዚአብሔርን የምታመሰግኑበት ፣ የምትቆርቡበትን ሕንፃ ቤተክርስቲያን ነው የገነባችሁትና እንኳን ደስ ያላችሁ" ሲሉም አክለዋል።

ቅዱስነታቸው "ከዛሬ ጀምሮ ይህንን አዲስ ሕንጻ ቤተክርስቲያን ካቴድራል ብለነዋል" ያሉ ሲሆን ቤተክርስቲያኑ በስያሜው ልክ መሆን ስለሚገባው ትምህርት ቤትና ሌሎችንም ከዚህ የበለጠ ልማት ሊሰራበት እንደሚገባ አመላክተዋል።

ከ፻ ሚሊየን ብር በላይ ፈሰስ ተደርጎበት ለምርቃት የበቃው የለገጣፎ ኆኅተ ገነት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን ጥር 29 ቀን 2002 ዓ.ም በብፁዕ ወቅዱስ ዶክተር አቡነ ጳውሎስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፤ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዚደንት፣ የዓለም ሃይማኖቶች ምክር ቤት ለሰላም የክብር ፕሬዚደንት፣ የዓለም የሰላም አምባሳደር የመሰረት ድንጋይ ተቀምጦለት ግንባታው መጀመሩ ይታወቃል።

Miidiyaa Shaggar/ሸገር ሀገረ ስብከት ሚዲያ/
የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት/ EOTC Broadcasting Service Agency/

23/05/2026

with CameraFi Live

የለገጣፎ ኆኅተ ገነት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት  ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።ግንቦት 15 ቀን 2018 ዓ.ም ምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም በሸ...
23/05/2026

የለገጣፎ ኆኅተ ገነት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።

ግንቦት 15 ቀን 2018 ዓ.ም
ምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም

በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት፣ በለገጣፎ ለገዳዲ እና ኩራ ጂዳ ቤተ ክህነት ስር የሚገኘው የለገጣፎ ኆኅተ ገነት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ቡራኬ ተመረቀ።

Miidiyaa Shaggar/ሸገር ሀገረ ስብከት ሚዲያ/

ወር በገባ በ14ኛው ቀን የሚደረገው ልዩ መንፈሳዊ ጉባኤ በምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ተከናወነ ግንቦት 14ቀን 2018 ዓ/ ም ምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም በምስካየ ኅዙናን መ...
22/05/2026

ወር በገባ በ14ኛው ቀን የሚደረገው ልዩ መንፈሳዊ ጉባኤ በምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ተከናወነ

ግንቦት 14ቀን 2018 ዓ/ ም
ምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም

በምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም ስብከተ ወንጌል ክፍል ወር በገባ 04 ,14 እንዲሁም በ27 ወርሃዊ የመድኃኒ ዓለም መታሰቢያ ምክንያት በማድረግ የሚዘጋጅው ልዩ ጉባኤም ሲሆን ይህንንም ምክንያት በማድረግ ከምዕመናን ለሚጠየቁ ግልጽ ያልሆኑ ማብራሪያ የሚያስፈልጋቸውን ጥያቄዎች ፀጋው የበዛላቸው መምህራንን በመጋበዝ ለምዕመናን መልስ በመስጠት ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን ።

በዛሬው ዕለትም ከምዕመናን በተጠየቁት አባ ኃይለ ገብርኤል ግርማ (ፕሮፌሰር) የቅድስት ሥላሴ ዩንቨርስቲ አካዳሚክ ም/ፕሬዚደንት ከምዕመናን የተጠየቁ ጥያቄዎችን ሰፊ ማብራሪያ እንዲሁም ምክረ ሀሳብ ሰጥተዋል።
ምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም

21/05/2026

🔴 ይህን መንፈሳዊ ቻናል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዶግማ ቀኖና ትውፊት መሰረት ተደርጎ የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም offical youtube channal ሲሆን በዚህ ቻናል ትም.....

በጣና ሐይቅ ላይ በደረሰ ድንገተኛ የጀልባ መስመጥ አደጋ የብዙዎች ሕይወት አለፈ😭ግንቦት 13፤ ባሕር ዳር የእናታችን የቅድስት ክርስቶስ ሠምራን ዓመታዊ የዋዜማ በዓል ለማክበር በጣና ሐይቅ ላ...
21/05/2026

በጣና ሐይቅ ላይ በደረሰ ድንገተኛ የጀልባ መስመጥ አደጋ የብዙዎች ሕይወት አለፈ😭

ግንቦት 13፤ ባሕር ዳር የእናታችን የቅድስት ክርስቶስ ሠምራን ዓመታዊ የዋዜማ በዓል ለማክበር በጣና ሐይቅ ላይ በጉዞ ላይ የነበሩ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮችን የጫነች ጀልባ ድንገተኛ የመስመጥ አደጋ ደርሶባታል።

በደረሰው አሳዛኝ አደጋ ምክንያት ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የብዙ ወገኖቻችን ሕይወት ማለፉ ተረጋግጧል።

ከተለያዩ አካባቢዎች እየወጡ ያሉ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፣ ጀልባዋ በርካታ ሰዎችን አሳፍራ በመጓዝ ላይ ሳለች ነው ይህ ድንገተኛ አደጋ ሊከሰት የቻለው።

ይህንን አስደንጋጭ እና ልብ ሰባሪ ዜና የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም የገለጸ ሲሆን፣ በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ ወንድሞችና እህቶች እግዚአብሔር አምላክ ነፍሳቸውን በቅዱሳኑ እቅፍ ያሳርፍ ዘንድ ምኞቱን ገልጿል።

በዚህ አስከፊ አደጋ የተሰማንን ጥልቅ ኀዘን እየገለጽን፣ ለሟች ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶችና ለመላው የእምነቱ ተከታዮች መጽናናትን እንመኛለን።

ፈጣሪ የሟቾችን ነፍስ በአብርሃም፣ በይስሐቅና በያዕቆብ እቅፍ ያኑርልን!

@ የባሕር ዳር ፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል ሰንበት ትምህርት ቤት

አርገ እግዚአብሔር በይባቤ ወእግዚእነ በቃለ ቀርን ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ "አምላክ በዕልልታ  እግዚአብሔር በመለከት ድምጽ ዐረገ›› መዝ.፵፮ (፵፯)፥፭)እንኳን ለአምላካችን ለመድኃኒታችን ለ...
21/05/2026

አርገ እግዚአብሔር በይባቤ
ወእግዚእነ በቃለ ቀርን
ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ "

አምላክ በዕልልታ እግዚአብሔር በመለከት ድምጽ ዐረገ›› መዝ.፵፮ (፵፯)፥፭)
እንኳን ለአምላካችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ዕርገት አደረሳችሁ !!!
ግንቦት 13ቀን 2018
ምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም

ቅዱስ ያሬድ ዝማሬ መላዕክትን መድረሱ፣ መጻሕፍተ  ትርጓሜያትን  መተርጕሙ ፣የድጓ የጾመ ድጓ ፣ ዝማሬ ፣ መዋሥዕት ምዕራፍ መጻሕፍት ደራሲ ፣ ዜማን ማስተማሩ ፣ ወደ ሰማይ መነጠቁ ፣ በማሕሌ...
18/05/2026

ቅዱስ ያሬድ ዝማሬ መላዕክትን መድረሱ፣ መጻሕፍተ ትርጓሜያትን መተርጕሙ ፣የድጓ የጾመ ድጓ ፣ ዝማሬ ፣ መዋሥዕት ምዕራፍ መጻሕፍት ደራሲ ፣ ዜማን ማስተማሩ ፣ ወደ ሰማይ መነጠቁ ፣ በማሕሌት ማገልገሉ፣ መመነኑ ፣ መሰወሩ ፣ የመንፈስ ቅዱስ ምግብን የጠገበ ፣ ሃሌ ሉያ በሚል ምስጋና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማሕሌትን በሚያምር ምስጋና ያስጌጠ፣ ጉድለት በሌለበት በብዙ ድካም ወደ ዛፍ ግንድ ጫፍ ላይ ትል ሲወጣ ተመልክቶ ኮብልሎ ከኼደበት ለትምህርት የተመለሰ ፣ የቅኔ መሥራች ፣የቤተ ክርስቲያን ባለውለታ መምህር ፣ ሐዋርያ ግንቦት 11 በዚህች ዕለት ወደ ብሔረ ሕያዋን የተሰወረበት ዕለት ሲሆን
ረድኤት በረከቱ በሁላችን ላይ አድሮ ይኑር ለዘላለሙ አሜን !!!
ግንቦት 11 ቀን 2018ዓ/ም
ምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም

የዓለምገና ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ዘመናዊ የስብከተ ወንጌል አዳራሽ በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ቡራኬ ተመረቀ።ግንቦት 09 ቀን 2018 ዓ.ም ምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም በሸገ...
17/05/2026

የዓለምገና ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ዘመናዊ የስብከተ ወንጌል አዳራሽ በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ቡራኬ ተመረቀ።

ግንቦት 09 ቀን 2018 ዓ.ም
ምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም

በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት በሰበታ ገላን ጉዳ እና ፉሪ ክፍለ ከተማ ሥር የሚገኘው የዓለምገና ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ያስገነባው ዘመናዊ የስብከተ ወንጌል አዳራሽ በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ቡራኬ ተመረቀ።

በዚሁ ታላቅ የምረቃ መርሐ ግብር ላይ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ፣ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንትና የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ በተጨማርም የኤድመንተንና የመካከለኛው ካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም፣ የሲያትልና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ፣ የምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ፣ የዳውሮና ኮንታ አህጉረ ስብከት ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጤሞቴዎስ፣ የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ መ/ሰላም አለማየሁ ተፈራ፣ እንዲሁም የሀገረ ስብከቱ የሥራ ኃላፊዎች፣መ/ኃይል አባ አፈወርቅ ዮሐንስ በሸገር ሀገረ ስብከት የ3ቱ ክ/ከተማ እና በአዲስ አበባ የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ሥራ አስኪያጅ፣ የደብሩ አስተዳዳሪ፣ እንዲሁም ሊቃውንተ አባቶች፣ የሰ/ት/ቤት ዘማርያን እና በርካታ ምዕመናን ተገኝተዋል።

በዕለቱ የደብሩ አስተዳዳሪ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ያቀረቡ ሲሆን፣ ለሕንጻው መገንባት በእውቀት፣ በጉልበትና በገንዘባቸው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ምዕመናን የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።

ብፁዕነታቸው ባስተላለፉት መልእክት፤ አዳራሹ ከስብከተ ወንጌል አገልግሎት ባለፈ ቤተክርስቲያኑ በሚታደስበት ወቅት እንደ ቤተ መቅደስ ሊያገለግል የሚችል ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ የተሠራው ሥራ ትልቅ መሆኑን ገልጸዋል። ሕንጻው እስኪጠናቀቅ ድረስ የነበሩትን ውጣ ውረዶች በማለፍ ዛሬ አዳራሹን እንድጠናቀቅ የለፉትን በሙሉ ምስጋና አቅርበዋል።

በዕለቱ በብፁዕነታቸው ጋባዥነት የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ “የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራ ታዩ ዘንድ ኑ” በሚል ኃይለ ቃል ሰፊ የወንጌል ትምህርት ሰጥተዋል። ብፁዕነታቸው በትምህርታቸው ወቅት ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በልማትና በወንጌል ማስፋፋት ረገድ እያከናወኑት ያለውን ተግባር አድንቀው፤ ብፁዕነታቸው ብዙ ማውራትን ሳይሆን ብዙ መሥራትን የሚወዱ አባት በመሆናቸው ቅድስት ቤተክርስቲያንና ቅዱስ ሲኖዶስ ይኮሩባቸዋል” ብለዋል።

በተለይም ምዕመናን በቋንቋቸው የወንጌልን ቃል እንዲማሩ እያደረጉት ያለው ጥረትና በቅርቡ አንድ ፓስተር ከተከታዮቻቸው ጋር ከ75 በላይ ነፍሳትን ይዞ መመለሳቸውን ተከትሎ፣በዛሬው በዕለት ደግሞ ከ29 በላይ አዲስ አማንያን መጠመቃቸውን መስማት ትውልድን የማዳን ትጋታቸው ማረጋገጫ መሆኑን ገልጸዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት በብፁዕነታቸው መልካም ፍቃድ ከማኅበረ ቅዱሳን ወሊሶ ማዕከል ጋር በመተባበር በአፋን ኦሮሞ አገልግሎት የሚሰጡ 15 ተተኪ መምህራንን አስመርቋል።

ተመራቂዎቹ ለሦስት ወራት ያህል የግብረ ዲቁና፣ የኪዳን፣ የሊጦን፣ የመስተበቁዕ፣ የመልክዓ ሥዕል፣ የመልክዓ ቁርባን፣ የመልክዓ ውዳሴ፣ የመልክዓ ማርያምና የመልከዓ ኢየሱስ ጸሎታትን በአፋን ኦሮሞ የተማሩ ሲሆን፤ በተጨማሪም ነገረ ሃይማኖት፣ የቤተክርስቲያን ታሪክ፣ የስብከት ዘዴ፣ ሐዋርያዊ ተልዕኮ፣ ነገረ ቅዱሳን፣ ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር እና ሥርዓተ ቤተክርስቲያን ኮርሶችን በሚገባ ያጠናቀቁ መሆናቸው ተገልጿል።

በመጨረሻም መርሐ ግብሩ በብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ጸሎትና ቃለ ቡራኬ ፍጻሜ አግኝቷል።

Miidiyaa Shaggar/ሸገር ሀገረ ስብከት ሚዲያ/

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Want your place of worship to be the top-listed Place Of Worship?

Share