Bazen Media - ባዜን ሚዲያ

Bazen Media - ባዜን ሚዲያ █▓▒F░O░L░L░O░W▒▓█።𝑷𝒂𝒈𝒆
።።Bazen Media - ባዜን ሚዲያ።።።
(6)

አርባ ምንጭ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤልሐምሌ 19/2018 ዓ/ም
26/07/2026

አርባ ምንጭ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል
ሐምሌ 19/2018 ዓ/ም

እንኳን ለመልአኩ ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን❤🙏
26/07/2026

እንኳን ለመልአኩ ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን❤🙏

 #ሀዋሳ ቅዱስ ገብርኤል የአመቱ ሰው ይበለን
26/07/2026

#ሀዋሳ ቅዱስ ገብርኤል የአመቱ ሰው ይበለን

19🕯🕯🕯መላእኩ ቅዱስ ገብርኤል ሆይ! አናንያን፣አዛርያን፣ሚሳኤልን ከሚነድ እሳት እንዳወጣሃቸው እኛንም ልጆችህን ከሚያስፈራን የሚያስጨንቀን ነገር ሁሉ ጠብቀን፣ ከገባንበት እሳት አውጣን አሜን...
25/07/2026

19🕯🕯🕯
መላእኩ ቅዱስ ገብርኤል ሆይ! አናንያን፣አዛርያን፣ሚሳኤልን ከሚነድ እሳት እንዳወጣሃቸው እኛንም ልጆችህን ከሚያስፈራን የሚያስጨንቀን ነገር ሁሉ ጠብቀን፣ ከገባንበት እሳት አውጣን አሜን!
በችግራችን ጊዜ ከሰው አለቃ ይልቅ የመላእክት አለቃ ከእሳት ከመከራ የሚያወጣው ቅዱስ ገብርኤል ይድረስልን።

 #ከፊቴ ቀደመ ደመናን ዘርግቶ እንዳልደናቀፍ ጉድባዎቼን ሞልቶ ዛሬ ላለሁበት ብሩቱ ጉልበት ሆነኝ ሰው ለመባል በቃሁ ሚካኤል ደገፈኝይበራል በክንፉ ምልጃውም ፈጣን ነው የአምላክ ስም አለበት ...
19/07/2026

#ከፊቴ ቀደመ ደመናን ዘርግቶ እንዳልደናቀፍ ጉድባዎቼን ሞልቶ ዛሬ ላለሁበት ብሩቱ ጉልበት ሆነኝ ሰው ለመባል በቃሁ ሚካኤል ደገፈኝ
ይበራል በክንፉ ምልጃውም ፈጣን ነው የአምላክ ስም አለበት ስሙ ሚካኤል ነው ያሳደገኝ መልአክ ዛሬም ከኔ ጋር ነው(፪)

ሐምሌ 12/2018   👉በስመ   አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን   በመልአኩ ስም ለምናመሰግንበት ለመልአኩ   ወርሐዊ መታሰቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን 👉ሐምሌ ዐሥራ ሁለት...
18/07/2026

ሐምሌ 12/2018


👉በስመ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን በመልአኩ ስም ለምናመሰግንበት ለመልአኩ ወርሐዊ መታሰቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

👉ሐምሌ ዐሥራ ሁለት በዚህች ቀን የከበረ መልአክ የመላእክት አለቃ #የሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው በዚች ቀን የፋርስ ንጉሥ ወደ ሆነ ወደ ሰናክሬም ሠራዊት #እግዚአብሔር ላከው ከሰናክሬም ሠራዊትም መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ አርበኞች ወንዶችን ገደለ

👉ይህም እንዲህ ነው ሰናክሬም #ኢየሩሳሌምን በከበባት ጊዜ ሕዝቅያስንና ፈጣሪው #እግዚአብሔርን እየዘለፈ ወደ ሕዝቅያስ መልእክተኞችን ላከ እንዲህም አለ እግዚአብሔር ያድናችኋል እያለ ሕዝቅያስ አያስታችሁ ከእጄ የሚያድናችሁ ማን ነው

👉የይሁዳ ንጉሥ #ሕዝቅያስም እጅግ አዘነ ወገኖቹንና ሀገሩ ኢየሩሳሌምንም ያድን ዘንድ ማቅ ለብሶ ወደ #እግዚአብሔር ፀለየ እግዚአብሔርም ልመናውን ተቀብሎ ወደ ፋርስ ንጉሥ ወደ ሰናክሬም ሠራዊት የመላእክት አለቃ #ሚካኤልን ላከለት ድንቅ ሥራንም ሠርቶ ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ሰዎች ሁሉ አዳናቸው

👉ስለዚህም የከበረ መልአክ የመላእክት ሁሉ አለቃ የሆነ #የሚካኤልን በዓል መታሰቢያ በዚች ቀን እናደርግ ዘንድ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አዘዙ

👉የመልአኩ ጥበቃና ተራዳኢነት አይለየን ረድኤትና በረከቱ ለሁላችንም ይድረሰን የተባረከ የተቀደሰ ይሁንልን

👉 #የእግዚአብሔር አብ ፀጋ የወልድ ፍቅር የመንፈስ ቅዱስ አንድነት የእናታችን ማርያም አማላጅነት የቅዱሳን መላዕክት ጥበቃ የቅዱሳን አባቶቻችን እናቶቻችን ረድኤት በረከት ጥርጥር የሌለባት የመንግስተ ሰማያት መዉረሻ ንፅህት ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነታቸው ከኛ ጋር ፀንታ ትኑር "አሜን"

ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል የልባችሁን መልካም መሻት ይሙላላችሁ🙏ሚካኤል ማለት “ከመ እግዚአብሔር” እንደ እግዚአብሔር ያለ ማነው?” ማለት ነው፡፡ ይህም የእግዚአብሔርን ገናንነትና እሱን የሚ...
13/07/2026

ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል የልባችሁን መልካም መሻት ይሙላላችሁ🙏

ሚካኤል ማለት “ከመ እግዚአብሔር” እንደ እግዚአብሔር ያለ ማነው?” ማለት ነው፡፡ ይህም የእግዚአብሔርን ገናንነትና እሱን የሚመስል አምላክ እንደሌለ የሚያመለክት ነው፤ እንደ እግዚአብሔር ያለ ቅዱስ ንጹሕ ርህሩህ ኃይል ረቂቅ ማነው? መልሱ የለም ነው፡፡ በትህትናው ልዕልናን ያገኘው ቅዱስ ሚካኤል በእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠው ክብር ከማንኛውም መልአክ የበለጠ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ አስቀምጦታል፡፡ ቅዱስ ሚካኤል የስሙ ዘርፍ ሆነው የሚጨመሩ መጠሪያዎች አሉት እነዚህም ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠውን የባለሟልነትና ክብር የሚገልጹ ናቸው፡፡ ይኸውም መልአከ ኃይል፣ መጋቤ ብሉይ፣ መልአከ ምክሩ ናቸው፡፡ መልአከ ኃይል የተባለው እግዚአብሔር በሱ አማካይነት ታላላቅ ሥራዎችን በመሥራት ኃይሉን ስለገለጸ፣ ዲያብሎስን ከነሠራዊቱ ስላሸነፈ ነው፡፡

መላእክትን ማክበርና መታዘዝ እንደሚገባ እግዚአብሔርም ነግሮናል፡፡ በዘጸ.23÷20-22 “በመንገድህ ይጠብቅህ ዘንድ ወዳዘጋጀሁትም ሥፍራ ያገባህ ዘንድ እነሆ እኔ መልአክን በፊትህ እሰዳለሁ፤ በፊቱ ተጠንቀቁ፤ ቃሉንም አድምጡ፤ ስሜም በእርሱ ስለሆነ ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት፤ አንተ ግን ቃሉን ብትሰማ፣ ያልሁህንም ሁሉ ብታደርግ፣ ጠላቶችህን እጣላቸዋለሁ፣ የሚያስጨንቁህንም አስጨንቃቸዋለሁ፣ መልአኬ በፊትህ ይሄዳል” በማለት ለሙሴ ተናግሯል፡፡ ይህ ቃል ለሙሴና ለሕዝቡ ብቻ ተነግሮ ያበቃ ሳይሆን እስከዛሬና ወደፊትም የሚቀጥል ነው፡፡ መጋቤ ብሉይ የተባለበት ምክንያት በብሉይ ኪዳን ውስጥ ከእግዚአብሔር እየተላከ ብዙ ታላላቅ ሥራዎችን የሠራ በመሆኑ ነው፡፡

መልአከ ምክር ወይም የእግዚአብሔር የምክሩ አበጋዝ የተባለበት ምክንያት፣ እግዚአብሔርን በምክሩ ይረዳዋል ለማለት ሳይሆን እግዚአብሔር የሚሠራውን ሥራ ለወዳጁ ለቅዱስ ሚካኤል ይገልጽለታል በሱም አማካኝነት ይሠራል ለማለት ነው፡፡ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ የሚለው በመላእክት ሁሉ ላይ በእግዚአብሔር የተሾመ ማለት ነው፡፡ መላእክት አለቆቻቸውን ያከብራሉ፤ ለእነሱም ይታዘዛሉ፡፡ ቅዱስ ሚካኤል የመላእክት ሁሉ አለቃ ስለሆነ ከትእዛዙ አይወጡም፤ ሠራዊተ መላእክት የሚያከብሩትንና የሚታዘዙለትን የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልን እኛም እንደ እነርሱ እናከብረዋለን እንታዘዘዋለን፡፡ ይህን ያመኑ ገዳማውያንም ሌሊትና ቀን ሚካኤል ሆይ አማልደን ይሉታል፡፡ ከጸሎታቸው በረከት እንድንካፈል ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

ሐምሌ 6/2018                                    👉በስመ   አምላክ አሜን በሞቱ ወደ ክብራችን ለመለሰን  #በትንሣኤዉ ላከበረን    እንዲሁም ለእናታችን     ወርሐዊ...
13/07/2026

ሐምሌ 6/2018








👉በስመ አምላክ አሜን በሞቱ ወደ ክብራችን ለመለሰን #በትንሣኤዉ ላከበረን እንዲሁም ለእናታችን ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

👉እኛ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አማኞች

#ኢየሱስ ስንል አምላከ አማልእክት የአማልክት አምላክ #ኢየሱስ ስንል እግዚእ ወአጋእዝት የጌቶች ጌታ #ኢየሱስ ስንል ንጉሠ ነገሥት የነገሥታት ንጉሥ #ኢየሱስ ስንል አልፋና ኦሜጋ መጀመሪያና እና መጨረሻ የሌለዉ ፊተኛዉና ኋለኛው ማለታችን ነዉ

👉 #ኢየሱስ ስንል ንጉሠ ሰማይ ወምድር የሰማይና የምድር ንጉሥ #ኢየሱስ ስንል ኤልሻዳይ ኹሉን ቻይ

👉 #ኢየሱስ ስንል መድኃኔዓለም #ኢየሱስ ስንል ወልደ አብ ወልደ ማርያም የአብ ልጅ የማርያም ልጅ በተዋሕዶ ልደት የከበረ

👉 #ኢየሱስ ስንል ፈጣሬ ኩሉ ኹሉን የፈጠረ #ኢየሱስ ስንል #እግዚአብሔር ማለታችን ነው ስሙን ስንጠራ ይኽ ሁሉ በልባችን ሰሌዳ ተፅፎ ነዉ

👉አምላካችን መድኃኒታችን በምህረቱ አይኑ ይጎብኘን ይመልከተን "አሜን"

✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

👉ቁስቋም እናታችን ማርያም ርጉም በሆነ በሔሮድስ ዘመን ከእርሱ ጋር ከሀገር ወደ ሀገር ስትሸሺ ካንቺ ጋራ መሰደዱን አሳስቢ

👉 ከአይኖችሽ የፈሰሰዉንና በተወደደ ልጅሽ ፊት የወረደዉን መሪር እንባ አሳስቢ

👉 ረኃቡንና ጥሙን ችግሩንና ሀዘኑን ከርሱ ጋር የደረሰብሽንም ጭንቅ ሁሉ አሳስቢ

👉 ጥፋትን ያይደለ ይቅርታን አሳስቢ መአትን ያይደለ ምህረትን አሳስቢ

👉 ለፃድቃን ያይደለ ለኃጥአን አሳስቢ ለንፁሃን ያይደለ ለተዳደፉት አሳስቢ

👉እናታችን በመከራ ያለችዉን የርስት ሀገርሽን #ኢትዮጲያን ልጅሽ መድኃኒታችን በቸርነቱ ይመለከታት ዘንድ ለምኝልን

👉በስደት የመታሠቢያ በአሏ የምናስባት እናታችን ቁስቋም በምልጃ ፀሎቷ ሁላችንንም ትጠብቀን የሰማዕቷ ረድኤት በረከት ምልጃ እና ፀሎት ከኛ ጋር ይሁን

👉 #የእግዚአብሔር አብ ፀጋ የወልድ ፍቅር የመንፈስ ቅዱስ አንድነት የእናታችን ማርያም አማላጅነት የቅዱሳን መላዕክት ጥበቃ እና የቅዱሳን አባቶቻችን እናቶቻችን ረድኤት በረከት ጥርጥር የሌለባት ድል አድራጊዋ የመንግስተ ሰማያት መዉረሻ ንፅህት ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነታቸው ከኛ ጋር ፀንታ ትኑር "አሜን"

☞አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ያደረገው ተአምር ይህ ነው፡፡☞ብዙ መድኃኒት የሚያደርግ አምልኮ ባዕድ የሚወድ፤ ብዙጊዜ ዝሙትየሚፈጽም አንድ ኅጢአተኛ ሰው ነበር፡፡☞አንድ ቀንም ንዑድ ክ...
11/07/2026

☞አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ያደረገው ተአምር ይህ ነው፡፡
☞ብዙ መድኃኒት የሚያደርግ አምልኮ ባዕድ የሚወድ፤ ብዙጊዜ ዝሙት
የሚፈጽም አንድ ኅጢአተኛ ሰው ነበር፡፡
☞አንድ ቀንም ንዑድ ክብር የሚሆን የአባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ የገድሉ
መጽሐፍ በሚነበብበት መጋቢት 5 ቀን ሔደ፡፡
☞ጌታ ለሰዎች የምሕረት ቃል ኪዳን እንደገባለት የቃልኪዳኑ መጽሐፍ በእዝነ
ልቡናው አደመጠ(ሰማ) በልቡም ያ ኃጢአተኛ መነኩሴም በሕሊናው እኔ
መታሰቢያውን አደርጋለሁ፤በጸሎቱም እታመናለሁ ብሎ አሰበና የአባታችን
የገድሉን መጽሐፍ ተሳልሞ ወጣ፡፡
☞ከዚያም ተነሥቶ፤ ሲሔድም በመንገድ ወንቤዴዎች አገኙት፤በታላቅ ዱላም
ደብድበው ልብሱን ገፈፋት፤በደም እየተጠመቀም ወደ ቤቱ ገባ፡፡
☞በዚያች ሌሊትም በእግዚአብሔር ፈቃድ ሞተ፤መላእክተ ጽልመትም መጥተው
ያችን ነፍስ ከበቡአት ወሰደውም ወደ እግዚአብሔር ፊት አደረሷት፡፡
☞እግዚአብሔርም መላእክተ ጽልመት ሒዱ ይህችን ነፍስ ወደ ሲኦል
ውስዷት፤በክፋ ሽታዋ ሰማይን (መካነ ነፍሳትን) አታርክስ ወደ ሲኦልም አስገቧት
አለ፡፡
☞ያን ጊዜም መላእክተ ጽልመት ያችን ነፍስ ወደ ሲኦል ወሰዷት አባታችን ገብረ
መንፈስ ይህን ነገር በመንፈስ ቅዱስ ዐወቀ፤ ከብርሃን ማደሪያው ተነሥቶ
በእግዚአብሔር ፊት ሰገደና አቤቱ፤ ሰማይ ምድር በቃል ኪዳንህ ጸንተው
ይኖራሉ፤ቃልህ ለምን ይታበላል፤ አቤቱ ከአንደበትህ የወጣው የሰጠኸኝን ቃል
ኪዳን አሰብ አለው፡፡
☞ጌታም መልሶ ወዳጄ ምን ዋሽውህ አለው፤ አባታችንም ክፋዎች መላእክተ
ጽልመት የወሰዱት ይህ ሰው በጸሎቴ ተማፅኖ እርሱ መታሰቢያዬን አደርጋለሁ
ብሎ ነበር ሞቱም በዕረፍቴ ቀን ሆኗል አለው፡፡
☞ያን ጊዜም የዚያ ሰው ኅጢአቱ ብዙ ስለሆነ ጌታ ዝም አለ፤ አባታችንም፤
በዙፋኑ ሰገደና ይህን ሰው መማር ካልወደድክ ከእርሱ ጋር ጨምረኝ አለው፡፡
☞ያን ጊዜም እግዚአብሔር መልአኩ ቅዱስ ሚካኤልን ፈጥነህ ሒድና ወደ
ሲኦል ሳይጨምሯት አምጣት አለው፤
☞ቅዱስ ሚካኤል ሄዶ በእሳት ባሕር ዳር አገኛትና መልሶ ወደ እግዚአብሔር
ፊት አደረሳት፡፡
☞እግዚአብሔር ያችን ነፍስ ለወዳጄ ለገብረ መንፈስ ቅዱስ ምን ረድርገሽለታል
አላት፡፡
☞ያች ነፍስም የገድሉን መጽሐፍ በሰማሁ ጊዜ ልቡናዬ ደስ አሰኘኝ፤ በልቤም
መታሰቢያውን ላደርግ አሰብኩ፤ ልቡናዬም በፍቅሩ ተቃጠለ፤ ገድሉንም ተሳልሜ
ሔድኩ፤ በዚያች ቀንም ሽፍቶች ገደሉኝ፤ ወደ አንተም ደረስኩኝ አለችው፡፡
☞እግዚአብሔርም ያችን ነፍስ እርሱን በመውደድ ልብሽ ከተቃጠለ፤በጸሎቱም
ከተማፀንሽ እኔም ኅጢአትሽን ይቅር ብየሻለሁ፣ በደልሽንም ደምስሼልሻለሁ
አላት፡፡
☞ይህንም ተናግሮ ወደምእመናን ጻድቃን መኖሪያ እንዲወስዷት አዘዘ፤ ፈጥነው
ወሰዷት፤ አባታችን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስም ተደሰተ ፊቱ በራ፡፡
☞የጻድቁ አባታችን የአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ጸሎቱና በረከቱ ከሁላችን ጋር
ይሁን፡፡
☞(ገድ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ)
☞ሲራክ ተክለጻዲቅ የተዋህዶ ልጅ

 #የዘረጋሁት እጄ ተሞላማርያም ሆናልኝ ጥላ ከለላየውስጤ ፀሎት ዛሬ ሌላ ነውየድንግል ክብር ምልጃ ቀየረውዛሬ ጎጆዬ አንፀባረቀችያማረ ሰንፔር ዕንቁ መሰለችክንዴ ከፍ ከፍ አለልኝናሰዋሁ ለድንግ...
09/07/2026

#የዘረጋሁት እጄ ተሞላ
ማርያም ሆናልኝ ጥላ ከለላ
የውስጤ ፀሎት ዛሬ ሌላ ነው
የድንግል ክብር ምልጃ ቀየረው
ዛሬ ጎጆዬ አንፀባረቀች
ያማረ ሰንፔር ዕንቁ መሰለች
ክንዴ ከፍ ከፍ አለልኝና
ሰዋሁ ለድንግል ይህን ምስጋና
Bazen Media - ባዜን ሚዲያ

Address

A
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bazen Media - ባዜን ሚዲያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share