08/26/2026
ዋዜማ ራድዮ እንደዘገበው፣ የሶማሌ ክልላዊ መንግሥት፣ የተለየ ፍላጎት አላቸው ያላቸው አካላት ሰሞኑን በጅግጅጋ ከተማ የመድሃኒአለም ቤተክርስቲያን ያስገነባውን መቃኞ ማፍረሳቸውን ኮነነ። የድርጊቱ ፈጻሚዎች "የሐይማኖት ጸብ" ለማስነሳትና የክልሉን መልካም ገጽታ ለማጠልሸት ሞከረዋል በማለት የወነጀለው የክልሉ መንግሥት፣ ፖሊስ የድርጊቱን ፈጻሚ አካላት በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ መጀመሩን ገልጧል። መቃኞው የተገነባበት ቦታ፣ በግለሰብ ስም የተመዘገበ ይዞታ መኾኑን ማረጋገጡንም የክልሉ መንግሥት ጠቅሷል።