EOTC Clergies and Parishioners Assocation

EOTC Clergies and Parishioners Assocation Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from EOTC Clergies and Parishioners Assocation, Eastern Orthodox church, Washington D.C., DC.

https://youtu.be/sbeygxUzchs
11/11/2025

https://youtu.be/sbeygxUzchs

በርዕሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በምሥራቅ አርሲ በግፍ ለተጨፈጨፉት ሰማዕታት መታሰቢያ የጸሎተ ፍትሃት እና የምኅላ መርኅግብር ተከሄዷል፤ በፕሮግራሙ ላይ...

https://youtu.be/YXD3QF1iXAc
11/11/2025

https://youtu.be/YXD3QF1iXAc

ዲያቆን ፋሲካው ካሣው በርእሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ዋሺንግተን ዲሲ ላይ ለምሥራቅ አርሲ በሰማእትነት ዋጋ ለከፈሉ ኦርቶዶክሳውያን የፍትሃት እና ጸሎተ ምኅላ በተደረገ.....

https://youtu.be/5ikwOSDufZY
11/11/2025

https://youtu.be/5ikwOSDufZY

በዋሺንግተን ዲሲ ርእሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን በምሥራቅ አርሲ ሰማእትነት ለተቀበሉት ሰማእታት የፍትሃት እና የጸሎት መርሃግብር በተካሄደበት ወቅት መጋ....

https://youtu.be/r_AhXzy4ihYReflection and Prayer for the Victims in Eastern Arsi, EthiopiaReflection:Last Sunday Novemb...
11/11/2025

https://youtu.be/r_AhXzy4ihY
Reflection and Prayer for the Victims in Eastern Arsi, Ethiopia

Reflection:
Last Sunday November 9, 2025, we gather in the light of candles — small flames that push back the darkness of sorrow and injustice. We remember the men, women, and children of the Ethiopian Orthodox Church who lost their lives in Eastern Arsi. Their faith, their courage, and their humanity are not forgotten.

We grieve as Catholics, Protestants, Orthodox, Muslims, and people of every conscience — for when one community suffers, the whole body of humanity feels the pain. No government, no plan, and no hatred can extinguish the light of truth, compassion, and faith that lives in the hearts of the Ethiopian people.

May our prayers tonight be a cry for peace — for an end to killing, for healing among all faiths, and for justice rooted in love, not vengeance.
Prayer:

Lord of mercy and peace,
We lift up to You the souls of the faithful departed in Eastern Arsi —
innocent lives taken by hatred and violence.
Receive them into Your eternal light.

Comfort their families, strengthen the Church,
and move the hearts of leaders to repent of cruelty and seek peace.

Let Your Spirit of unity flow among all Ethiopians —
Orthodox, Catholic, Protestant, Muslim, and all who call You by name —
that they may live not as enemies, but as one people in Your love.

Teach us, O God, to be peacemakers.
To speak for the voiceless, to heal wounds, and to guard the dignity of every life.

In Your mercy, Lord, let the light of these candles
be a sign of hope that no darkness can overcome.

Amen.

በኢትዮጵያ ሃገራችን በምሥራቅ አርሲ ደማቸው እንደ ጎርፍ የሚፈሰው ሰማእታትን ለማሰብ ኢትዮጵያውያን በዋሺንግተን ዲሲ የሻማ ማብራት ባዘጋጁበት ወቅት አንድ አሜሪካዊ ለተሰዉት ሰማዕ....

ዛሬ ጥቅምት ፴ ቀን ፳፻፲፰ ዓም (October 9, 2025) በዋሺንግተን ዲሲ ዋሺንግተን ሞናመንት ላይ "ስለ ቤተክርስቲያን ዝም አንልም" በሚል በምሥራቅ አሩሲ በግፍ ደማቸውን ስላፈሰሱት ሰ...
11/10/2025

ዛሬ ጥቅምት ፴ ቀን ፳፻፲፰ ዓም (October 9, 2025) በዋሺንግተን ዲሲ ዋሺንግተን ሞናመንት ላይ "ስለ ቤተክርስቲያን ዝም አንልም" በሚል በምሥራቅ አሩሲ በግፍ ደማቸውን ስላፈሰሱት ሰማዕታት የሻማ ማብራት ሥነ ስርዓት ተካሂዶ ነበር፤ በዚህ ሥነ ስርዓት ላይ ጥቂት የቤተ ክርስቲያን አባቶች በጣት የሚቆጠሩ ቁጥራቸውም 3 ብቻ እንዲሁም በርከት ያሉ ምዕመናን እና ምዕመናንት ተገኝተው ተሳትፈዋል፤
በሃገራችን ኢትዮጵያ መንግሥት መር የሆነ ጭፍጨፋ እና ግድያ እየተካሄድ ባለበት ወቅት አልሰማንም አላየንም ብሎ ማለፍ በእውነት ብዙዎችን ያሳዘነ ክስትተ ነው፤ በአሩሲ የሚጨፈጨፉት ክርስቲያኖች ወደው ፈቅደው ሳይሆን በሰላም በቤታቸው በተቀመጡበት ነው በግፈኞች ጂሃዲስቶች ግፍ እየተፈጸመባቸው ያለው፤ ይሄንን ሰምቶ አለማዘን እና ኤሎሄ ብሎ ወደ ፈጣሪ አለማሳሰብ በእውነት ያስተዛዝባል፤

https://youtu.be/81Q-2lo27H4
12/24/2024

https://youtu.be/81Q-2lo27H4

በዋሺንግተን ዲሲ እና አካባቢዋ ለምትኖሩ ኢትዮጵያውያን በሙሉ በመጪው አርብ በሀገራችን ኢትዮጵያ ያለገደብ ለሚፈሰው የንጹሐን ደም፣ ካህናት አባቶች፣ ምእመናን ወምእመናን በየእለቱ ....

October 12, 2024 4:17:23 pm. በመጬው ረቡዕ የዋሺንግተን ዲሲና አካባቢው የካህናት እና የምእመናን ኅብረት፤ በአካባቢያችን ካሉት የተለያዩ የማኅበረሰብ እና ሲቪክ ማኅበራት ጋር...
10/12/2024

October 12, 2024 4:17:23 pm.

በመጬው ረቡዕ የዋሺንግተን ዲሲና አካባቢው የካህናት እና የምእመናን ኅብረት፤ በአካባቢያችን ካሉት የተለያዩ የማኅበረሰብ እና ሲቪክ ማኅበራት ጋር በመተባበር ታላቅ የሰላምዊ ሰልፍ ተዘጋጅቷል፤ በሀገራችን ኢትዮጵያ በፋሽቱ መንግሥት የሚፈሰው የንጹሐን ደም፣ የድሮን ድብደባውን፣ የካሕናት መታረድ፣ የንጹሐን ዜጎች በተለያዩ ቦታዎች በእሥር መንገላታት፣ የዜጎችን በልማት ሰበብ ጎዳና ተዳዳሪ ማድረግ የመሳሰሉትን በመንግሥታዊ የሆንውን ጥፋት እና ግድያ ለአለም ሰላም ወዳድ ማኅበረሰብ ለማሳወቅ እና ተቃውሟችንን ለመግለጽ በOctober 16, 2024 at State Department 2201 C Street, NW. Washington, DC የተቃውሞ ሰልፍ ተዘጋጅቷል፤
ኢትዮጵያውያን በሙሉ ድምጽ ለሌለው ወገናችን ድምጽ እንሁን በማለት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፤ ማንም ሰው በተቻለው መጠን ይሄንን ግፍ እና እንግልት የሚቃወም በሙሉ በዚህ ሰልፍ ላይ ታዳሚ እንዲሆን በአክብሮት እንጋብዛለን።
በዚህ ቀን በተለያዩ ከተሞች በተመሳሳይ ጊዜ ተቃውሞው የደረጋል፤ ከነዚህም መካከል
በለንደን በጀርመን
በካናዳ

አዘጃጆች ፡
* የዋሺንግተን የካህናት እና ምእመናን ኅብረት
* የዋሺንግተን ዲሲ የጋራ ግብረኃይል
* EAPAC (American Ethiopian Public Affairs Committee)
* WAAA (Washington Area Amhara Association)
* ዓለም አቀፍ የአማራ ኅብረት
* አማራ ትንሣኤ

you can watch live
09/07/2024

you can watch live

እና የአካባቢው ኦርቶኦርቶዶክሳውያን እና ሊቃውንት! በኢትዮጵያ ሰዓት ከምሽቱ 3፡00 ጀምሮ!የዋሽንግተን ዲሲ ኦርቶዶክሳውያን ወሳኙን ምእራፍ ጀ...

ነገ ጳጉሜ ፪ ቀን ፳፻፲፮ ዓም ከ2፡00 ፒኤም ጀምሮ ጉባኤ ዘኦርቶዶክስ በደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል ዋሺንግተን ዲሲ ይደረጋል፤ ብንችል በአካል፤ ካልቻልን ግን በዙም በመገኘት የጉ...
09/07/2024

ነገ ጳጉሜ ፪ ቀን ፳፻፲፮ ዓም ከ2፡00 ፒኤም ጀምሮ ጉባኤ ዘኦርቶዶክስ በደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል ዋሺንግተን ዲሲ ይደረጋል፤ ብንችል በአካል፤ ካልቻልን ግን በዙም በመገኘት የጉባኤው ተሳታፊ እንዲሆኑ በአክብሮት ተጠርተዋል፤
ብፁዕ አባታችን አቡነ ሉቃስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የአውስትራሊያ እና ኒውዝላንድ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በቦታው በመገኘት ቡራኬ እና ቃለ ምዕዳን ይሰጣሉ፤ በርከት እና ጠንከር ያሉ ወቅታዊ የቤተክርስቲያን ችግሮች ከነ መፍትሄዎቻቸው ይቀርባሉ፤ ለቅድስት ቤተክርስቲያን መፍትሄ መፈለግ የሁላችንም ኦርቶዶክሳውያን መብትም ግዴታም ነው፤ ስለዚህ በቦታ ተገኝተው የመፍትሄው አካል ይሁኑ።
Meeting ID: 833 4475 6991
Passcode: EOTC
2:00 pm - 6:00 pm
አብዛኛውን ጊዜ የውይይት፣ የጥያቄ እና መልስ በመሆኑ በቦታው በመገኘት የመፍትሄው አካል ይሁኑ፤
የካህናት እና ምዕመናን ኅበረት በዋሺንግተን ዲሲ

July 15, 2024 9:15 PM በመጪው ወር ማለትም ነሐሴ ፲፰ ቀን ፳፻፲፮ ዓም (August 24, 2024) ታላቅ መንፈሣዊ ጉባኤ ይደረጋል፤ በጉባኤም ላይ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ዘማሪያን፣ ሰባ...
07/26/2024

July 15, 2024 9:15 PM
በመጪው ወር ማለትም ነሐሴ ፲፰ ቀን ፳፻፲፮ ዓም (August 24, 2024) ታላቅ መንፈሣዊ ጉባኤ ይደረጋል፤ በጉባኤም ላይ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ዘማሪያን፣ ሰባኪ ወንጌላውያን፣ የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች፣ ተጋባዥ እንግዶች፣ ምዕመናን እና ምዕመናት፤ ይገኛሉ፤
ስለወቅቱ የቤተክርስቲያን ፈተናዎች እና መፍትሔዎቻቸው በተጋባዥ የጥናት ጽሑፍ አቅራቢዎች ዳሰሳ ይደረጋል፤ አብዛኛውን ጊዜ ምዕመናን እና ምዕመናት በሚሰጡት የመፍትሔ ሃሳቦች እና የሚሰጡትን አቅጣጫዎች ያገናዘበ ሰፊ የውይይት ጊዜ ይኖረናል፤ እዳያመልጥዎት፤ እንላለን።
አምላከ ቅዱሳን ለሃገራችን ሰላምን፣ ለቤተክርስቲያንም ትንሣኤዋን ያቅርብልን አሜን።
ጉባኤው የሚደረገው በደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል ዋሺንግተን ዲሲ ነው
2601 Evarts Street. NE.
Washington, DC
የካህናት እና ምዕመናን ኅብረት በዋሺንግተን ዲሲ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የካህናት እና ምዕመናን ኅብረት በሰሜን አሜሪካ ባለፈው ሚያዚያ 17 ቀን 2016 ማለትም April 25, 2024 ባደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በኢት...
05/14/2024

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የካህናት እና ምዕመናን ኅብረት በሰሜን አሜሪካ ባለፈው ሚያዚያ 17 ቀን 2016 ማለትም April 25, 2024 ባደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በኢትዮጵያ ውስጥ በተደጋጋሚ የሚከሰቱትን የሰብዓዊ ጥሰቶች እና የዘር ማጽዳት ዘመቻ በመንግሥት አካላት ሲፈጸም እና ይሄንንም እያየ እና እየሰማ የአሜሪካን መንግሥት ዝምታውን መምረጡን ቅሬታችንን በደብዳቤ አያይዘን በስቴት ዲፓርትመንት የአፍሪካ ጉዳዮች ሃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ሞሊ ፊ የተባሉ የቢሮው ሃላፊ እና የስቴት ዲፓርትመን ስፔሻል አሲስታንት የሆኑት ለደብዳቤያችን ምላሽ በMay 9, 2024 መልስ ሰጥተውናል፤ ለዚህም ምስጋናችን የላቀ ነው፤ በደብዳቤውም ላይ የአፊሪካ ቢሮ ሃላፊዋም የአሜሪካን መንግሥትም ያለውን አቋም ለኢትዮጵያ መንግሥት እንዳሳወቀ እና በዚህ የዘር ማጥፋት ዘመቻ ላይ የሚሳተፉትንም ከተጠያቂነት እንደማያመልጡ እና የአሜሪካንም መንግሥት ተከታትሎ ጉዳዩን ለኢትዮጵያም መንግሥት እንደሚያስውቁ በመጥቀስ ደብዳቤያቸውን አጠቃለዋል፤

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የካህናት እና ምዕመናን ኅብረት በሰሜን አሜሪካ በቀጣይነት የተለያዩ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ አባላትን እና የአሜሪካን የኮንግረስ አባላትን በማነጋገር በኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈጸሙትን ወንጀሎች እያንዳንዱን በሰነድ በተደገፈ በማሳየት እና በማሳወቅ ለዚህም የአሜሪካን ታክስ ከፋይ ለዚህ ወንጀል ተባባሪ መሆን እንደሌለበት በደብዳቤዎቻን በመግለጽ እያነጋገርን እንገኛለን።
ለምታደርጉት ትብብር በሙሉ ከልብ እናመሰግናለን።
የደብዳቤውን ሙሉ ቃል በዚህ ያገኙታል

Address

Washington D.C., DC

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when EOTC Clergies and Parishioners Assocation posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to EOTC Clergies and Parishioners Assocation:

Share