San Jose Debre Yibabe Parish- በሳን ሆዜ የቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ምእመናን

San Jose Debre Yibabe Parish- በሳን ሆዜ የቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ምእመናን Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from San Jose Debre Yibabe Parish- በሳን ሆዜ የቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ምእመናን, Religious organisation, San Jose, CA.

04/26/2026

ክፍል 5 (ማጠቃለያ)- የመፍትሄ ሀሳቦች
------------------------------------

"ቢቻላችሁስ በሰላም ኑሩ::" ሮሜ 12:18
"ከሁሉ ጋር ወደ ሰላም ሩጡ ቅድስናችሁንም አትተው::" ዕብ. 12:14

ቅዱስ መፅሀፋችንና ቤተክርስቲያን ሁልጊዜ የምታስተምረን ለሰላም ዝግጁ እንድንሆንና ፀብና ክርክርን ከመካከላችን እንድናርቅ ነው::ለአለፋት ጥቂት እመታት በቤተክርቲያናችን ውስጥ ለተነሱ ችግሮች ዘላቂ መፍትሄ ያላመጡ የውሸትና የለበጣ የመሰሉ የእርቅ ሂደቶች ቢደረጉም ውጤቱ ዛሬ የደረስንበት ደረጃ ላይ ልንደርስ ችለናል::ለዚህም አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ እንዲሉ ጥልቅ ውይይት የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮችና ችግሮች ቂምን ክፋትንና ጥላቻን እንዲወልዱ ሆኗል::

ዛሬ በሀገራችን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች በእምነታቸው ብዙ በደልና ግፍ ሲደርስባቸው አቤቱታ የሚያቀርቡበት ሰሚ ባጡበት ዘመንና ከሩቅ ሆነን እያየንና እየተቆጨን ባለበት ሰአት እኛ እዚህ ሀገር ህግና ስርአት ከመናገር ነፃነት ጋር ባለበት ቦታ ሆነን ምእመናን ለማፈን እየተኬደ ያለው እንቅስቃሴ ሊወገዝ የሚገባው የአምባገነኖች አካሄድ ነው::

ቢሆንም ግን ማንኛውም የሀገርም ሆነ የቤተክርስቲያን ችግሮች በውይይት ቢፈቱ ዘላቂ የሆነ መፍትሄ ያመጣሉ ብለን ምእመናን እናምናለን::በእርግጥ ከውይይትና ከሰላም ንግግሮች አናተርፍም ብለው ጠብና ብጥብጥን ሁልጊዜም የሚመርጡ እንዳሉ ሳንገነዘብ ቀርተን አይደለም: ነገር ግን መፅሀፍ "እነዚህ የገዛ መንገዳቸውን መረጡ ነፍሳቸውም በርኩሰታቸው ደስ ይላታል" ኢሳ 26:3 እንዲል ፍርዱን ለእግዚአብሔር በመተው ነው::

በዚህ በደብረ ይባቤ ቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስትያን ውስጥ ዘላቂ መፍትሄ እንዲመጣ ከተፈለገ ከዚህ በታች የተጠቀሱት ነጥቦችን እንደ መፍትሄ ለማቅረብ እንወዳለን::ይህንን ስንል ግን እስከ ዛሬ ብዙ ጥያቄዎች ሲነሱ ሰበካ ጉባኤውና አጠቃላይ መስተዳደሩ ለህዝብና ለቤተክርስቲያኑ የቆየ ታሪክ ሲያሳዩ የሰነበቱትን ንቀትና ማን አለብኝነት ከመቀመጫቸው አስፈንጥሮ ለሰላምና ለውውይይት ይመጣሉ ብለን በቀቢፀ ተስፋ ተነሳስተን ሳይሆን ሁልጌዜም ምእመናን ሰላምና ውይይት የመጀመሪያ ምርጫችን እንደሆነ በእግዚአብሔርም በሰውም ፊት ለመመስከር ነው:: በዚህም መሠረት እነዚህን የአጭርና የረጅም ጊዜ የመፍትሄ ሀሳቦችን እንደሚከተለው እናቀርባለን::

1. አዲስ ቤተክርስትያን በመግዛት ስም አሁን ያለንበትንም በመሸጥ ምእመኑን ለመበተን እየተደረገ ያለው ማንኛውም እንቅስቃሴ በአስቸኳይ እንዲቆም::
2. በተደጋጋሚ እንደተገለፀው የቤተክርስቲያኑ አስተዳዳሪ የችግሮች በዚህ ደረጃ መድረስና በህዝበ ክርስቲያኑም ውስጥ መከፉፈል እንዲኖር ያላቸውን ሚና ከዚህ ቀደም ገልፀናል:: ስለዚህም ግለሰቡ ከማንኛውም የአስተዳደር ሀላፊነት ገለል እንዲሉና ዘላቂ መፍትሄ እስኪገኝ ከሁለቱ ሌሎች ካህናት ጋር በቀጣይ ምን መደረግ እንዳለበት በተለይም ሀይማኖታዊ ሀላፊነቶች እንዴት ማስቀጠል እንደሚቻል ምክክር ቢደረግ::
3. ምንም እንኳ ሰበካ ጉባኤው የስራ ዘመኑን እየጨረሰ ቢሆንም በምርጫ ሰበብ ሌላ ግርግርና ሁከት ከማስነሳት ይልቅ ህዝበ ክርስቲያኑ ገለልተኛ ናቸው ብሎ የሚያምንባቸውን ስዎች ወደፊት እምጥቶ አስተዳደሩን ለተወሰነ ጊዜ እንዲረከቡ ማድረግ::
4. ከአንድ አመት ተኩል በላይ ረፍዶ የቀረበው የሂሳብም ሆነ የቁጥጥር ክፍል ሪፖርቶች ብዙ ግድፈቶችና ግልፅነት የጎደላቸው እንደነበሩ ለሁላችንም ግልፅ ነው::ስለዚህም የውጭ ኦዲተርም በመቅጠርም ይሁን በሌሎች ባለሙያዎች የቤተክርስቲያኑ የሂሳብ አያያዝ በአግባቡ እንዲመረመር::
5. ቤተክርስቲያኑ ውስጥ የግለሰቦችን ፈቃድ ወይም በህግ አገላለፅ consent ሳይጠይቁ የሚደረጉ ማንኛውም የምስልም ሆነ የድምፅ ቀረፃ በአስቸኳይ እንዲቆም::
6. በደህንነት ስም ለአንድ ግለሰብ የተሰጠን የካሜራ እይታ ፈቃድ በአስቸኳይ እንዲነሳ::ግለሰቡ ከዚህ ቀድም የነበረው ፈቃድ ለምን እንደተነጠቀ የሚያመለክት መረጃ ማቅረብ እንደሚቻል ማሳወቅ እንፈልጋለን::

በመጨረሻም ምእመናንና ቤተክርስትያንን በመናቅ እየተደረጉ ያሉት ህገወጥ ድርጊቶች ብዙ ዋጋ ሊያስከፍላችሁ እንደሚችል አምናችሁ ጉዳዮ የሚመለከታችሁ ሁሉ ወደልቦናችሁ እንድትመለሱ እንመክራለን::

ወስብሀት ለእግዚአብሔር!!

04/25/2026

ክፍል 4
-----------
ጥብቅ ማሳሰቢያ ለምእመናን!!!

ከውስጥ በወጡና ከታመኑ ምንጮች ባገኘናቸው መረጃዎች መሰረትእሁድ ሊካሄድ በተጠራው ስብሰባ ላይ የተለየ ሀሳብ ሊሰጡ ይችላሉ ተብለው በታሰቡ ሰዎች ላይ የሚከተሉት እንቅስቃሴዎች እንዲደረጉ ምክክር መደረጉን ደርሰንበታል::

1. ግለሰቦችን እናግዳለን restraining order እናወጣለን ብለው እላይ እታች ሲሉ የከረሙት ተመሳሳይ ሰዎች ለስድብና ለሁከት የመለመሏቸው ሰዎች እንዳሉ ደርሰንበታል::ስለዚህ ማንኛውም ምእመን የዚህ ሴራ ኢላማ እንዳይሆንና በቤ/ክ ውስጥ ከእነዚህ ግለሰቦች ጋር ምንም አይነት ውዝግብ ውስጥ እንዳትገቡ እናሳስባለን::

2. ስብሰባው ፖለቲከኞቹ ብልፅግናና ዳንኤል ክብረትን የሚያስቀና የመብት እረገጣ "የስነ-ስርአት" ደንብ የወጣበት ህገወጥና ዘላቂ መፍትሄን የማያመጣ ስለሆነ ምእመናን ተአምረ ማርያም ሰምታችሁ ወደቤታችሁ ብትሄዱ ይመረጣል::

3. በስብሰባው ላይ እንደሁልግዜም አምቧ ጏሮ ለመፍጠርና አለባበሳቸውም አስተሳሰባቸውም የቤተክርስቲያን ያልሆነ ግለሰቦች ቀረርቶና ፉከራ ያሰማሉ ተብሎ ይጠበቃል::

4. የሞዴስቶ ግብረ ሀይልም ድጋፉን እንዲሰጥና አለሁ ባይነቱን ለማሳያት በሌሊት ገስግሶ እንዲደርስ መመሪያ ተሰጥቶታል::ማንነታቸውንና ምንነታቸውን ወደፊት በሌላ ክፍል በዝርዝር እንመለስበታለን::

5. እዚህ መድረክ እየተነሱ ባሉ ጥያቄዎችና አስተያየቶችም ላይ የተወሰነ የአምባገነኖች የመሰለ ዲስኩሮችና ዛቻዎች እንደሚሰጡ ይታሰባል::

6. በዚህ መልኩ ወርደን እንዳንነጋገር ለአለፉት ሁለት አመት በላይ ሀገረ ስብከቱን ጨምሮ በተለያየ መንገድ የተሞከረ ቢሆንም በውስጣቸው ቂምና ተንኮል ይዘው በሚዞሩ ጥቂት ግለሰቦች ምክንያት ብዙ አመት የተለፋበት ቤተክርስቲያንና ማህበራዊ እሴት እንደዚህ አደጋ ላይ ሊወድቅ ችሏል::

በመጨረሻም ህዝበ ክርስቲያኑ ሀሳቡን እንዳይገለፅ ከ3 ቀን በፊት ያወጃችሁ መሆኑ እንዳለ ሆኖ ነገር ግን ሰላም በአንጻራዊነት እንዴት ሊመጣ ይችላል በሚሉ ሀሳቦች ላይ የመፍትሄ ጥቆማዎችን ይዘን በክፍል 5 እንመለሳለን::

በተጨማሪም እንደ አስፈላጊነቱ ምክትል ሊቀመንበሩና አንጃዎቹ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ቤተክርስቲያኑን ማወካቸው ሳያንስ አውደ ምህረት ላይ ቆሞ በውሸት የገፅ ግንባታ ሊያደርግ የሞከረውንና እስካሁን አደባባይ ያልወጡ እኩይ ስራዎች እንደ አስፈላጊነቱ በመረጃና በማስረጃ ለህዝበ ክርስቲያኑ ይፋ ይሆናል::
#ሳንሆዜ #ቁልቢ #ገብርኤል

04/24/2026
04/24/2026

ክፍል 3
---------------
የቤተክርስቲያኑ አስተዳደርና የጥቅም ተካፋዮች በጨረባ ለጠሩት የእሁድ ስብሰባ ላይ በ"ስነስርአት" ሽፋን እንዳይነሱ የሚፈሯቸው የህዝብ ጥያቄዎች:
1. የቤተክርስቲያኑ ሰበካ ጉባኤም ሆነ ገለልተኝነት የጎደለው የቁጥጥር ክፍል አቀረብነው ባሉት የሂሳብ ሪፖርቶች ላይ ለነበሩ ጥያቄዎች ግድፈቶች በአደባባይ ጥያቄ ለመቀበልና መልስ ለመስጠት ለምን ፈሩ?
2. ቁጥጥር ክፍሉም ሆነ ሰበካ ጉባኤው የአባላት ክፍያ ቀንሶብናል ገብያችን $5ሺ ወጪያችን $$15ሺ ብለው ባቀረቡት ሪፓርት የ$40ና $50ሺ የወር ሞርጌጅ የሚያስከፍል የ$9 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ቤት እንገዛለን ብሎ ህዝብን ማሸበር ከጀርባው ያለው ድብቅ አላማ ምንድነው?
3. ችግሮች ሁሉ የሚመነጩና መዳረሻቸውም ከአንድ አካል እንደሆነ እየታወቀ በመቀጠልም ከመቅደስ እስከ ፅህፈት ቤት ህዝብን በማሸበርና በመከፋፈል ለአለፉት አመታት የሚባዝኑት "የመንጋው ጠባቂና አስተዳዳሪ" ለምን ተጠያቂ ሊደረጉ እንዳልተቻለ ማብራሪያ ቢሰጥበት::
4. ከሞዴስቶ እስከ ሳንሆዜ የተደራጀው የረብሻና የሁከት ቡድን ከቤተክርስቲያኑ ሽያጭና ግዢ የሚያገኘው ጥቅም ምድነው?
5. መቅደስ ውስጥ ህፃናት ዲያቆናትን ደብድበው ከቤተክርስቲያኑ እስከነቤተሰባቸው የሸሹ ወላጆች እንዳሉ እናውቃለን ለዚህ የአስተዳደሩ መልስ ምድነው?
6. አስተዳዳሪው ቤተክርስቲያኑ ከከተማ ውጭ ወደሆነ ቦታ ቤተክርስቲያኑ ሲገነባም ሆነ ሲሰራ አንድ ጠጠር ያላቀበሉበትን ቦታ ሸጠው ለመሄድ ያነሳሳቸው የግል ፍላጎት ምንድነው?
7. ከሁሉም በላይ ለዘላቂ ሰላምና እውነተኛ ውይይት ለአመታት ዝግጁ ከመሆን ይልቅ ለፀብና ሁከት ቤተክርስቲያኑን መፈንጫ ያደረጋችሁት ለምንድነው?

ሌሎች ከምእመናን የሚመጡ ጥያቄዎችን በቀጣይ ክፍሎች እናቀርባለን::
#በቀጣይ

ክፍል 2---------------እነዚህ ግለሰቦች ከዚህ ስራቸው እንዲቆጠቡም በአክብሮት እንደዚህ ጠይቀናቸው ነበር::የአፀፋ መልሳቸው በግለሰቦች ላይ የማስፈራሪያ ደብዳቤ መፃፍና የአውደምህረት...
04/24/2026

ክፍል 2
---------------
እነዚህ ግለሰቦች ከዚህ ስራቸው እንዲቆጠቡም በአክብሮት እንደዚህ ጠይቀናቸው ነበር::የአፀፋ መልሳቸው በግለሰቦች ላይ የማስፈራሪያ ደብዳቤ መፃፍና የአውደምህረት ላይ ዛቻ ነው የቀጠለው::ዝርዝሩን በሚቀጥለው ይጠብቁን::

ክፍል 1------------የምእመንን መብት ለመርገጥ የሚታታሩ ቤተመንግስት ብቻ ሳይሆን ቤተመቅደስም የተሸሸጉ እንደነዚህ አይነት ጉደኞች ናቸው:ሊያውም በአሜሪካን ሀገር::እዚህ ቤተክርስቲያን...
04/24/2026

ክፍል 1
------------
የምእመንን መብት ለመርገጥ የሚታታሩ ቤተመንግስት ብቻ ሳይሆን ቤተመቅደስም የተሸሸጉ እንደነዚህ አይነት ጉደኞች ናቸው:ሊያውም በአሜሪካን ሀገር::እዚህ ቤተክርስቲያን ለአለፉት ሁለት እመት በላይ በተወሰኑ ሰዎች እየተፈፀሙ ያሉ ህገወጥና ስርአት አልበኝነትን ወደፊት እያመጣን ለምእመናን ማሳወቅ እንጀምራለን::

Address

San Jose, CA
95112

Opening Hours

Saturday 5am - 10am
Sunday 4:30am - 11am

Telephone

+14082899277

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when San Jose Debre Yibabe Parish- በሳን ሆዜ የቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ምእመናን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to San Jose Debre Yibabe Parish- በሳን ሆዜ የቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ምእመናን:

Featured

Share