Pastor Tamirat Haile

Pastor Tamirat Haile Official page of Pastor Tamirat Haile
(1)

የመላ ካናዳ አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት "ለኅብረት ተጠርተናል" በሚል በቶሮንቶ ከተማ ባዘጋጁት  በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ ታላቅ ኮንፈረንስ ላይ እንድናገለግል በተጠራንበት፣ በኮንፈረንሱ ም...
08/08/2026

የመላ ካናዳ አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት "ለኅብረት ተጠርተናል" በሚል በቶሮንቶ ከተማ ባዘጋጁት በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ ታላቅ ኮንፈረንስ ላይ እንድናገለግል በተጠራንበት፣ በኮንፈረንሱ ምጨረሻ ላይ "የአገልግሎትህን 50ኛ ዓመት" በሚል በድንገት ሰርፕራይዝ አደረጉን።
"ብርሃነ ወንጌል" በተሰኘች ቤተክርስቲያን በመዘምራን ቡድን የተሰለፍኩበት ዓመት ተጨምሮ ሲሰላ በእርግጥም 50 ዓመት መሙላቱን ያስተዋልኩት በኋላ ነው። እነዚህ 50 ዓመታት የሙላት፣ የሙቀትና የምቾት ዓመታት ብቻ አልነበሩም። የምንኖርባት ምድር ጠፍጣፋ (Flat) ብቻ ሣትሆን ወጣገባ እንደሆነች ሁሉ፣ ሕይወትም እንዲሁ ውጣ ውረድ የበዛበት ቢሆንም ቅሉ፣ ጌታን ለመከተል የመጀመሪያዋን እርምጃ እግሬን ካንሣሁበት ዕለት ጀምሮ እስከዚህች ሰዓት ድረስ በማንከስም፣ በዳዴም ሆነ በሩጫ ዘመን እጄን ይዞ የመራኝን እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ፣ ይህን የሰማ ሁሉ ያመስግንልኝ።

ወንድሜ ሸዋዬ ዳምጤ እንዳዜመው፣ "ቀሪ ዘመኔን" እንዲባርክልኝ እለምነዋለሁ፣ እናንተም ለምኑልኝ።
"ተነሥተንም ወደ ቤቴል እንውጣ፤ በዚያም በመከራዬ ጊዜ ለሰማኝ፥ በሄድሁበትም መንገድ ከእኔ ጋር ለነበረው ለእግዚአብሔር መሠውያን አደርጋለሁ" (ዘፍ. 35:3) "አቤቱ አንተ ተስፋዬ ነህና፥ እግዚአብሔር ሆይ፥ ከታናሽነቴ ጀምረህ መታመኛዬ ነህና።
አምላኬ፥ ከታናሽነቴ ጀምረህ አስተማርኸኝ፤ እስከ ዛሬም ተአምራትህን እነግራለሁ" (መዝ. 71:5 ፣ 17)

የካናዳ አብያተ ክርስቲያናት እና በክርስቶስ ቤተሰቦቻችን በመላ፣ እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይባርካችሁ እላለሁ።

የDNA of the Kingdom ministries 8ኛ ዙር ዓለም እቀፍ ጉዟችን የሚጀምረው ከፊታችን መስከረም 1/2019 (September 8/2026) በመሆኑ እንደተለመደው በጸሎታችሁ አብራችሁን እንድትጓዙ ግብዣዬ ነው።

ወንጌል ያሸንፍ! የሰው ዋጆች ሁሉ በአዳኙ ኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ከእግዚአብሔር ጋር ይታረቁ! አብያተ ክርስቲያናት በሠላም ይኑሩ፣ ይታነጹም!ለምድራችንና ለሕዝባችን ሠላም ይሁን!!! ታምራትና ቤተሰቡ፣ ከአገልግሎት አጋሮች ሁሉ ጋር።

ሙሉ የሶሻል ሚዲያ ሊንኮቻችን
https://linktr.ee/TamiratHaile

የዝማሬ ቻናል: 👇👇
youtube.com/

የትምህርትና የሌሎች መልዕክቶች ቻናል👇👇

https://youtube.com/

የፌስቡክ ገፅ: http://facebook.com/OfficialPastorTamiratHaile

ዌብሳይት:- http://dnakingdomministries.org

ፍቅራችሁ፣አክብሮታችሁና አለን ባይነታችሁ ያልተለየን፣ ቤተሰቦቻችን፣ የጌታ ጸጋና ሠላም ይብዛላችሁ! በኢትዮጵያ 14፣ በደቡብ አፍሪካ 14፣ በአውሮፓ (ኖርዌይ) 2፣ በድምሩ 30   ከተሞችንና...
04/03/2026

ፍቅራችሁ፣አክብሮታችሁና አለን ባይነታችሁ ያልተለየን፣ ቤተሰቦቻችን፣ የጌታ ጸጋና ሠላም ይብዛላችሁ!

በኢትዮጵያ 14፣ በደቡብ አፍሪካ 14፣ በአውሮፓ (ኖርዌይ) 2፣ በድምሩ 30 ከተሞችንና አብያተክርስቲያናትን የደረስንበት የ 7ኛው ሚሲዮናዊ ጉዟችን፣
የቤተክርስቲያናትና የሚኒስትሪ መሪዎች፣የመዝሙርና አምልኮ አገልጋዮች፣የሙሉ ጊዜ ወንጌል አገልጋዮች፣ ሁሉም ዓይነት አገልግሎት ተሣታፊዎችና ከጋብቻ በፊትና በጋብቻ ያሉ ቤተሰቦች ትምህርቶችና ሥልጠናዎች የተሠጡበት፣ በውጤቱም፣ አብያተ ክርስቲስይናቱ ሁሉ በንስሀና በተሀድሶ መንፈስ የተነቃቁበት፣ አገልጋዮች በተሻለ መረዳትና መሠጠት ለማገልገል የወሰኑበት፣ እንደዚሁም፣ በድምሩ ከ1250 በላይ ነፍሣት ወደ መንግሥቱ የተጨመሩበት፣ በልማት በኩልም ሕንጻው በተማሪዎች ላይ ሊወድቅ የደረሰ አንድ የገጠር ትምህርት ቤት አፍርሰን በሁለት ወር ብቻ መልሰን ገንብተን ያስመረቅንበትና ሌላም እንደዚሁ መውደቅ የጀመረ ትምህርት ቤት አፍርሰን መልሰን ለመገንባት የቁፋሮ ሥራና አንዳንድ የግንባታ ዕቃዎች ማቅረብ የጀመርንበት የድልና የስኬት ጉዞ ተጠናቆ ወደ ጊዜያዊ መኖሪያችንና ለቀጣዩ ጉዞ ዝግጅት ወደ ምናደርግበት ቀዬያችን ተመልሰናል።

የጉዟችን ማሣረጊያ በመለኮት ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን በሲልቨር ስፕሪንግ ሜሪላንድ ከዓርብ March 27 – 29 የነበረን ድንቅ ኮንፈረንስ ሲሆነ፣ ያገለገልንበት ብቻ ሣይሆን በረጅሙ ጉዞ የደከመ ሰውነታችን ያገገመበትም ጭምር ነበር። የቤተክርስቲይስኒቱ መጋቢ ወርቁ ለገሠ፣ መሪዎችና መላው አባላት ወጣቶችም ጭምር ያሣዩንን ፍቅር ልንረሣው አንችልም። በተለይም፣ 40ኛ ዓመት ጋብቻችሁን እናክብር ብለው በድንገት Surprise ሲያደርጉን ድንጋጤም ደስታም የቀላቀለ ክስተት ሆኖልናል። እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርክልን!

በጠቅላላው፣ በዚህ ዙር የሰባት ወራት ጉዞ የረገጥንበት ከተማና ቤተክርስቲያን ሁሉ ያሣዩን ፍቅር፣ አክብሮትና ርህራሄ እኛንም መልሶ ሠርቶናል።
እኛ ዋሽንግተን ዲሲ በገባንበት ሰዓት እዚህ ደግሞ ሴት ልጆችን ወንድ ልጅዋን በሠላም ተገላግላ ደስታ ተጨምሮልናልና አመስግኑልን።
ሁላችሁንም እግዚአብሔር አምላክ ይባርክልን ከማለት በቀር የአድናቆታችንን ልክ የምንገልጽበት በቂ ቃል የለንም። ስለ ፍቅራችሁና ድጋፋችሁ ሁሉ የሥራው ባለቤት ብድራታችሁን ይክፈል! የላካችሁንም፣ በጸሎት የተከተላችሁንም ሁላችሁንም እግዚአብሔር በማይነጥፍ በረከቱ ይባርክ እንላለን።

” እኛ ማንጠቅም ባሪያዎችች ነን" (ሉቃ. 17:10) ክብሩ ለእግዚአብሔር ይሁን!
ጽጌና ታምራት፣ ከአብሮ ሠራተኞች ጋር. ፎቶዎች የመጨረሻዎቹ የደቡብ አፍሪካ ሳምንቶች ፍሬዎችን ያሳያል

ይህ ሳምንት የጌታን ምሕረት፣ ፈውስና በረከቱን የምንቀበልበት ሳምንት ነው። አርብ ምሽት በ 7:00 Pm እና እሁድ ማለዳ 10:00 Am በሜሪላንድ 13321 New Hampshire Avenue,...
03/27/2026

ይህ ሳምንት የጌታን ምሕረት፣ ፈውስና በረከቱን የምንቀበልበት ሳምንት ነው።

አርብ ምሽት በ 7:00 Pm እና እሁድ ማለዳ 10:00 Am በሜሪላንድ
13321 New Hampshire Avenue, Silver Spring, MD 20904

አድራሻችን እንዲሁም ቅዳሜ ከሰዓት 4:00 Pm እና እሁድ ከሰ ዓት 4:30 Pm at
4613 Pinecrest Office Park Drive, Suite H, Alexandria, VA 22312

በቨርጂኒያ አጥቢያ እንገናኛለን።

“የእየሱስ አዳራሽ አይጠበንምና ሰው እንጋብዛለን ዛሬም እንደገና/2 ብለው እንደተቀኙለት አባቶች! እንጋብዛችኋለን

በድንቅ አጠራርህ || ይሄን ኢየሱሴን ምን ላድርገው || አኬልዳማ || Pastor Tamirat Haile and Pastor Agegnew Yideg Part 2...
03/15/2026

በድንቅ አጠራርህ || ይሄን ኢየሱሴን ምን ላድርገው || አኬልዳማ || Pastor Tamirat Haile and Pastor Agegnew Yideg Part 2...

በእኔ ስም የተከፈቱ ብዙ ተከታይ ያላቸው Fake account ስላሉ... እነዚህን ከታች ያሉትን ትክክለኛ ገፆቻችንን በመቀላቀል እና ለሌሎችም ሼር በማድረግ አገልግሎቶቻችንን ያግኙ:: ሙሉ ...

SouthAfrica republic🇿🇦    የ፯ኛው ዙር ሚሲዮናዊ ጉዞአችን ሊጠናቀቅ ሁለት ሣምንት ብቻ ቀረው። ጊዜ እንደዚህ ነው የሚፈጥን። ከሠራንበት ምንም አይደል።  ያለፉት የደቡብ አፍሪካ...
03/11/2026

SouthAfrica republic🇿🇦

የ፯ኛው ዙር ሚሲዮናዊ ጉዞአችን ሊጠናቀቅ ሁለት ሣምንት ብቻ ቀረው። ጊዜ እንደዚህ ነው የሚፈጥን። ከሠራንበት ምንም አይደል።
ያለፉት የደቡብ አፍሪካ የአገልግሎት ቆይታ ሣምንቶቻችን እጅግ ድንቅ ነበሩ። ነፍሶች ድነዋል፣ አገልጋዮች ስልጥነው ለስራ ተነሳስተዋል፣ ጋብቻዎች በትምህርት ታድሰዋል፣ቤተክርስቲያናት በተሀድሶ መንፈስ ተነቃቅተዋል፣ በአምልኮ የእግዚአብሔርን መገኘት አይተናል።
የአንዳንዶቹ ከተሞች አገልግሎቶቻችን እስከ ሰባት ቀናት ያለ ዕረፍት የዘለቁ ነበሩ። አንድም የከሠረ ቀን አልነበረም። "ለእግዚአብሔር የሥራ ጊዜ ነው" (መዝ ፩፩፱:፩፪፮)የሚለዉ መግለጫ (Declaration) በትክክል ሠርቶአል።
እናንተ ሁላችሁ በያላችሁበት ሣምንቶቹ እንዴት አለፉ ይሆን? ጊዜ ተመጥኖ የተሠጠንና ሳይሠራበት ከሄደም የማይመለስ ጨካኝ መሆኑን አንርሣ። ለቀሩን ሁለት ሣምንቶችና ቀጣይ ምዕራፎች እንዳስለመዳችሁን በፀሎት አብራችሁን ቁሙ።

በተገቢው ቀን ተገቢውን ካደረግን እሱ ቢመጣም፣ እኛ ብንሄድም አይቆጨንም። እንወዳችሁአለን።
ፅጌና ታምራት

ጌታ ሁላችሁንም ይባርክ!!!

ሙሉ የሶሻል ሚዲያ ሊንኮቻችን
https://linktr.ee/TamiratHaile

የዝማሬ ቻናል: 👇👇
youtube.com/

የትምህርትና የሌሎች መልዕክቶች ቻናል👇👇

https://youtube.com/

የፌስቡክ ገፅ: http://facebook.com/OfficialPastorTamiratHaile

ዌብሳይት:- http://dnakingdomministries.org

Part 2በድንቅ አጠራርህ || ይሄን ኢየሱሴን ምን ላድርገው || አኬልዳማ ..የተለያዩ መዝሙሮች እንዴት እንደተሰሩ ያወጋንበት ክፍል 2 እነሆ👇👇
03/10/2026

Part 2

በድንቅ አጠራርህ || ይሄን ኢየሱሴን ምን ላድርገው || አኬልዳማ ..
የተለያዩ መዝሙሮች እንዴት እንደተሰሩ ያወጋንበት ክፍል 2 እነሆ👇👇

በእኔ ስም የተከፈቱ ብዙ ተከታይ ያላቸው Fake account ስላሉ... እነዚህን ከታች ያሉትን ትክክለኛ ገፆቻችንን በመቀላቀል እና ለሌሎችም ሼር በማድረግ አገልግሎቶቻችንን ያግኙ:: ሙሉ ...

Address

Sacramento, CA
95829

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Pastor Tamirat Haile posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Pastor Tamirat Haile:

Shortcuts

Share