Ancient Orthodox/ጥንታዊቷ ኦርቶዶክስ

Ancient Orthodox/ጥንታዊቷ ኦርቶዶክስ ይህ Ancient Orthodox/ጥንታዊቷ ኦርቶዶክስ ፔጅ ነው ✅ Follow ✅share ✅Like በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
(1)

07/19/2026

#ከፊቴ ቀደመ ደመናን ዘርግቶ እንዳልደናቀፍ ጉድባዎቼን ሞልቶ ዛሬ ላለሁበት ብሩቱ ጉልበት ሆነኝ ሰው ለመባል በቃሁ ሚካኤል ደገፈኝ
ይበራል በክንፉ ምልጃውም ፈጣን ነው የአምላክ ስም አለበት ስሙ ሚካኤል ነው ያሳደገኝ መልአክ ዛሬም ከኔ ጋር ነው(፪)

ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤል ከክፉ ነገር ሁሉ ይከልለን፤ምልጃው እና ረድኤቱም አይለየን🙏ድርሳነ ሩፋኤል ላይ ተጽፎ እደምናገኘው 7 ሊቃነ መላዕክት ሲኖሩ አለቃቸው ቅዱስ ሚካኤል ነው፤ የስሙ ት...
07/18/2026

ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤል ከክፉ ነገር ሁሉ ይከልለን፤ምልጃው እና ረድኤቱም አይለየን🙏

ድርሳነ ሩፋኤል ላይ ተጽፎ እደምናገኘው 7 ሊቃነ መላዕክት ሲኖሩ አለቃቸው ቅዱስ ሚካኤል ነው፤ የስሙ ትርጓሜም “እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው” ማለት ነው። ከእግዚአብሔር ዙፋን ስር ትዕዛዝ በወጣ ግዜ ኪሩቤል ተቀብለው ለሱራፌል ያስተላልፋሉ፤ ሱራፌልም ለሚካኤልና ለገብርኤል ለሩፋኤልም ያደርሳሉ፡፡ ሚካኤል ለፍጥረቱ በጎም ይሁን ክፉ ትዕዛዙን ይፈጽሙ ዘንድ መላዕክትን ያዛቸዋል፤ ኪሩቤልና ሱራፌል መላዕክቱም ሁሉ አቤቱ የእጅህን ስራ አታጥፋ እያሉ ቀንና ከማታ ይለምናሉ። የመላዕክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ከዲያቢሎስ ጋር በተከራከረ ጊዜ እግዚአብሔር ይገስፅህ አለው እንጂ የስድብን ቃል አልተናገረውም ሲባል ሰምተናል፡፡ ሊቀ ነብያት ሙሴ እጅግ ታዛዥና የዋህ ስለነበርና ከንዓንን ለማየት ወደ ናባው ተራራ ሲወጣ 2 መላዕክት በአረጋውያን ተመስለው መቃብር ሲቆፍሩ ቢያይ ላግዛቹ ብሎ መቆፈሪያውን ተቀበላቸው፡፡

በመጨረሻ “ሰውየው በአንተ ልክ ነውና እስቲ ገብተህ ለካልን” አሉት፡፡ እሱም በየዋህነቱ ጉድጓዱ ውስጥ ገብቶ እንደተኛ እንደ እንቅልፍ አሸልቦት በዚያው ዐረፈ፤ መላዕክቱም ቀበሩት። እስራኤላዊያን ሙሴን እጅግ ስለሚወዱት የሙሴን መቃብር እንደ ጣዖት እንዳያመልኩት እግዚአብሔር የሙሴን መቃብር ሰወረው፤ ነገር ግን ጠላት ዲያቢሎስ ሊያሳያቸው በመነሳቱ ቅዱስ ሚካኤል ተቃወመው፡፡ በመጨረሻም ቅዱስ ሚካኤል ዲያቢሎስን እግዚአብሔር ይገስጽህ ብሎ ከእርሱም ሰወረበት። በሐዋርያው ይሁዳ መልዕክት ቁጥር 8 የሚገኘው ቃል የቅዱስ ሚካኤልን ትዕግስት ያሳያል፡፡ ዳግመኛም በወቅቱ የነበሩት ፈጣሪን በሰቀሉት ጊዜ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል በቁጣ ሰይፉን አወጣ፤ ቅዱስ ሚካኤል ግን በድርጊቱ አዝኖ ፈጣሪን ፍጡራን ሰቀሉት እያለ በአርምሞና በትዕግስት አያቸው ይላል ድርሳኑ።

ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በመዝሙር 33÷7 “የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል ያድናቸውማል” ይለናል፡፡ በትንቢተ ዳንኤል 10÷13 እና 10÷21 ደግሞ የስሙ ትርጉም እግዚአብሔር ዳኛዬ ነው የተባለው ነብዩ ቅዱስ ዳንኤልም ስለ ቅቅዱስ ሚካኤል እንዲህ ሲናገር ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ፣ በተዘጋ ጉድጓድ ሲያጽናናው ደግሞ “ከሚካኤል በቀር የሚያጽናናኝ የለም” አለ፡፡ በዓለም ፍፃሜም ስለህዝቡ የሚቆመው ሚካኤል ይነሳል። በማለትረ በምዕራፍ 12÷1 ጽፎልናል፡፡ በራዕይ 8÷3 “የቅዱሳኑ ፀሎት ከዕጣኑ ጢስ ጋር ከመልአኩ እጅ ወደ እግዚአብሔር ፊት ወጣ” ተብሎ እንደተጻፈውም መላዕክት የቅዱሳኑን ጸሎት ወደ እግዚአብሔር ያሳርጋሉ፡፡ ገዳማውያን የሚያደርጉት ጸሎትና የሚያቀርቡት መስዋዕት በእርሱ ምልጃ ያርጋልና ገዳማቸውን እየረዳን በዓታቸውን እያጠናን የበረከታቸው ተካፋይ እንሁን፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

06/17/2026
ግንቦት 1/2018                                👉በስመ   አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን   በከበረዉ  #ትንሣኤው ለምናከብርበት ለእናታችን   አመታዊ የልደ...
05/08/2026

ግንቦት 1/2018


👉በስመ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን በከበረዉ #ትንሣኤው ለምናከብርበት ለእናታችን አመታዊ የልደት መታሠቢያዋ ክብረ በዐል እንዲሁም አመታዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

" ዮም ፍስሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም"

👉ጴጥርቃ እና ቴክታ የሚባሉ ሰዎች #በኢየሩሳሌም በአንድነት ተጋብተው ይኖሩ ነበር

👉እነዚህም #በእግዚአብሔር የሚያምኑ የተወደዱ ጻድቃን ደግ ሰዎች ነበሩ እነዚህም ሰዎች በእግዚአብሔርም በሰውም ዘንድ ባለፀጎች ነበሩ ነገር ግን ሐብታቸዉን የሚወርሳቸው ልጅ አልነበራቸውም መካን ነበሩ አንድ ቀን ጴጥርቃም ቴክታን እህቴ ሆይ ይህን ሁሉ የሰበሰብነውን ገንዘባችንን ምን እናደርገዋለን ልጅ የለን የሚወርሰን

👉 አንቺም መካን ነሽ እኔም ካንቺ በቀር ሌላ ሴት አላውቅም አላት እርሱአም ወንድሜ ሆይ ለኔ ልጅ ቢነሳኝ አንተም እንደኔው ሆነህ ትቀራለህን ከሌላ ደርሰህ ውለድ እንጂ ብላ ብታሰናብተው እንደዚ ያለ ነገር እንኩአንስ ላደርገው በልቦናዬ እንዳላስበው ያውቅብኛል አላት

👉እርሱዋም የሚያደርገውን የሚያውቅ የለም ትላንትና ማታ በህልሜ ነጭ ጥጃ ከማህፀኔ ስትወጣ ያችም ነጭ ጥጃ ሌላ ነጭ ጥጃ ስትወልድ እንዲሁ እስከ 7ት ትውልድ ሲዋለድ ሰባተኛይቱ ጨረቃን ስትወልድ ጨረቃዋም ፀሃይን ስትወልድ አየሁ አለችው

👉እርሱም በጠዋት ከህልም ፈቺ ዘንድ ሂዶ የነገረችውን ሁሉ ነገረው ያም ህልም ፈቺ #እግዚአብሔር በምህረቱ አይቱአቹሀል በሳህሉ መግቡአችሁአል 7 አንስት ጥጆች መውለዳቹ 7 ሴቶች ልጆች እና የልጅ ልጆች ትወልዳላቹ ከቤታቹ ሰባተኛይቱ ጨረቃ መውለዱአ ከሰው የበለጠች #ከመላእክትም የከበረች ደግ ፍጥረት ትወልዳላቹ የፀሃይ ነገር ግን አልታወቀኝም አለው

👉እርሱም የነገረውን ሁሉ ሄዶ ነገራት እርሷም እንጃ አምላከ #እስራኤል የሚያደርገውን ማን ያውቃል ብላ ዝም አለች

👉ከዛም ፀንሳ በ9 ወሯ ሴት ልጅ ወለደች ስሙአንም ሄሜን ብለው አወጡላት ሔሜንም አድጋ ለአካለ መጠን ስደርስ አጋብተዋት በስምንተኛ ቀኑአም ደርዲ ብለው ስም አወጡላት

👉ደርዲም አድጋ እንዲሁ ሴት ወለደች እና ቶና አለቻት ቶናም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሲካር አለቻት ሲካርም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሴትና አለቻት ሴትናም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሄርሜላ አለቻት ሄርሜላም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ንጽህት ቅድስት ክብርት የምትሆን #እመቤታችንን የምትወልደውን #ሃናን ወለደች

👉ከጴጥርቃና ከቴክታ የተወለዱ 67 ወንዶች ልጆች አሉ ትውልድ ለመቁጠር ትንቢት አልተነገረላቸውም ሱባኤ አልተቆጠረላቸውምና አልተፃፈም ይህቺም ሃና በስርአት በቅጣት አደገች ለአእምሮ ስትበቃ አካለ መጠን ስደርስ ከቤተ መንግስት ወገን ከነቅዱስ ዳዊት ወገን ከሆነው(መጽሃፍ ቅዱስ ይገልጸዋል) ከቅዱስ እያቄም ጋር አጋቡአት

👉 እነዚህ ቅዱሳን #እያቄም እና #ሃና በአንድነት ተጋብተው ሲኖሩ ልጅ አጡ ከእለታት አንድ ቀን ወደ ቤተ እግዚአብሄር ሂደው ሲፀልዩ ሲያዝኑ ዋሉ












ሚያዚያ 2/2018                                                            የማይሞት እርሱ ሞተ ሞትን ይሽረዉ ዘንድ ሞተ                     ...
04/10/2026

ሚያዚያ 2/2018


የማይሞት እርሱ ሞተ ሞትን ይሽረዉ ዘንድ ሞተ
ሙታንን ያድናቸዉ ዘንድ ሞተ

👉የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን #የክርስቶስ ሕማምና መከራውን ለማሰብ ከሆሳዕና ሰንበት ጀምሮ እስከ ትንሳኤ ያለውን ሳምንት ብላ ትጠራዋለች በእዚህ ሳምንት ውስጥ ያሉ ቀናት ሁሉ እያንዳንዳቸው የተለያየ ምስጢር ተፈፅሞባቸዋል ዕለተ አርብ ግን የሁሉ ነገር መገባደጃ ጌታችን አምላካችን ነገረ ድህነቱን የፈፀመበት በመሆኑ ይለያል

👉ቤተክርስቲያንም በዓል አድርጋ አይሁድ ያደረሱበትን ስቃይ ፣ መገረፍና መመታቱን ፣ መቸንከርና መሰቀሉን ፣ ፈጣሪ ሆኖ ሳለ እያሰበች በልዩ ሥርዓት ታከብረዋለች

👉ይህ ይባላል ምዕመናን ይህን በዓል እንደሌላው ጊዜ በመብል በመጠጥ ሳይሆን በፆምና በስግደት ያከብሩታል የበረቱት ከሌሊት ጀምሮ የዘገዩም ከእኩለ ቀን በፊት ባሉት ሰዓታት ቀድመው በየአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ይሰባሰባሉ

👉በዚህች ዕለት በቤተ መቅደስ ውስጥ በምሳሌና በምስጢር የተዋበ ሥርዓት ይከናወናል አገልግሎቱን የሚመሩት ካህናትና ዲያቆናት ከተገኘ ሐዘን ነውና የመቅደሱ (የቅድስተ ቅዱሳኑ) መጋረጃም እንዲሁ ይለብስና ይዘጋል ከፊቱም እንደ አልጋ ያለ ነገር መጎናፀፊያ ተነጥፎበት ይዘጋጅና በላዩ ላይ ቅዱስ ወንጌል ፣ ጻሕልና ጽዋዎች ይቀመጣሉ

👉የሞቱ ምሳሌ የሆነ በዚያው ላይ ይዘረጋል በራስጌና በግርጌውም የወርቅ ለምድ ይደረጋል ከእነዚህ ሁሉ ንዋያተ ቅዱሳት ጋር ሦስት የመፆር መስቀሎችም እንዲሁ በመካከል ፣ በቀኝና በግራ አብረው ይቆማሉ በመካከለኛው መስቀል ላይ ይደረግበታል

👉ከዚሁ ጎንና ጎን ደግሞ በገመድ እየሳቡ የሚያጥኑባቸው ፅንሐዎች በተዘጋው የመቅደስ መጋረጃ ላይ በገመድ ታስረው ይሰቀላሉ ይህም ጌታችን በሰቃዮቹ አይሁድ እጁ በገመድ ታስሮ ወደፊትና ወደኋላ እየተጎተተ መንገላታቱን ለማሳየት ነው ይህ ሁሉ በአምላካችን ላይ የሆነውን ለማሰብ ነው

👉ምንባባቱ ፣ በዕዝል የሚዜመው ዜማ በየሰዓቱ የሚደረገው እያንዳንዱ ክንውን ሲታከልበት ደግሞ ይህች ቤተ ክርስቲያን ምን ያህል መሆኗን ፤ ይህ ሁሉ የሚከወንባት ዕለተ እንደሆነች እንረዳለን

👉እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ፃማ ወድካም አመ ከመ ዮም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሣኤሁ እግዚአብሔር በፍስሐ ወበሰላም "አሜን ኪራላይሶን"

















❗️እናታችን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም❗️ የቃል ኪዳን ልጆችሽንና የአሥራት ሀገርሽን ኢትዮጵያን ታደጊ! አሜን!!እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይሀገራችን ኢትዮጵያ ሰላም እና ፍቅ...
03/30/2026

❗️እናታችን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም❗️


የቃል ኪዳን ልጆችሽንና የአሥራት ሀገርሽን ኢትዮጵያን ታደጊ! አሜን!!

እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ

ሀገራችን ኢትዮጵያ ሰላም እና ፍቅር አንድነትን ይሰጠን ዘንድ ከልጅሽ ከወዳጅሽ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
ለምኝልን አሜን አሜን አሜን🙏❤

🚸🚸🚸

Address

New York, NY

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ancient Orthodox/ጥንታዊቷ ኦርቶዶክስ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share