Christian Post ክርስቲያን ፖስት

Christian Post ክርስቲያን ፖስት በቃሉ እመራለሁ፤ በደሙ ድኛለሁ።
የክርስቲያን ፖስት መንፈሳዊ ገጽ ነው ቤተሰብ ይሁኑ ! Zema yube መንፈሳዊ መረጃ የሚለቀቁበት ገጽነው

08/27/2026

የድሮ አምልኮ ሥርዓት 😢

08/27/2026

ትላንትን

08/27/2026
08/26/2026

የስልክ ልውውጡ ቅጂ ይኸው

መግቢያ

ይህ ከስር የተያያዘው ድምፅ 5 ደቂቃ ከ23 ሰከንድ የሚሆን በሁለት ሰዎች መካከል የተደረገ የስልክ ንግግር ቅጂ ነው። ይህንን የድምፅ ቅጂም ወዲህ ማምጣት ያስፈለገው በሁለት ምክንያት ነው። አንድ፤ ለወንጌል ንፅህና ግድ የሚላችሁ ወገኖች ይህንን የድምፅ ቅጂ ሰምታችሁ የችግሩን ስር ሰደድነት ተርድታችሁ የራሳችሁን አቋም እንድትወስዱ ለማበረታታት ነው። ሁለት፤ የሚመለከታችሁ የመንግስት አካላት ጉዳዩን እንድትመረምሩት። በተለይም ደግሞ የቃለ ህይወት መሪዎች ጉዳዩን በደንብ እንድታጣሩ እና የሚገባችሁን እንድታደርጉ ከታሪክ እና ከእግዚአብሔር ፍርድ ተጠያቂነት እንድታመልጡ ለማሳሰብ ነው።

ነገር ግን ልብ ማለት የሚያስፈልገው፤ ይህንን የድምፅ ቅጂ እንዳለ አቀረብሁላችሁ እንጂ በነገረ ጉዳዩ ላይ እኔ የራሴን ድምዳሜም ሆነ ፍርድ አላቀረብሁም። ይህንን ማሳወቅ እፈልጋለሁ። መረጃውን እንዳለ ከነነፍሱ ነው ያቀረብሁት። ሰሚው ይመርምር፣ ይፍረድም።

እውነት ለመናገር ይህንን ላለመለጠፍ ከራሴ ጋር ብዙ ተሟግቻለሁ። ነገር ግን የበርካታ ሃሳውያንን ማንነት ህዝብ እንዲያውቅ በማስረጃ ስናጋልጥ ከርመን ይህንን እጃችን ላይ የደረሰውን መረጃ የምንደብቅበት ምንም ምክንያት አይኖርም በሚል ለጥፌዋለሁ።

ሌላው፤ ይህ እዚህ የቀረበው የድምፅ ቅጂ እና ትናንት ዘሌ Zelalem Mengistu በገፁ ያጋራው ሰነድ እጃችን ላይ ከገቡት የድምፅና የሰነድ ማስረጃዎች መካከል ጥቂቶቹ መሆናቸው ለመግለፅ እወድዳለሁ። የተኙ ይነቁ ዘንድ እንደ አስፈላጊነቱ ሌሎቹም ማስረጃዎች የሚለቀቁ ይሆናል።

ወገኖቼ፤ የወቅቱ ፈተና ወንጌልን መስበክ ሳይሆን ወንጌልን መጠበቅ ነው። የምንለው በምክንያት ነው።

"አንተ የምትተኛ ንቃ" (ኤፌ 5:14)

"ፕሬዘዳንቱ ተጠያቂ መሆን አለባቸው"ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ከመሠረተ ክርስቶስ መሪዎች አንዱ ከሆኑት ወንድም የተላለፈ መልዕክት:-.......በመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያንበአዲስ አበባ...
08/05/2026

"ፕሬዘዳንቱ ተጠያቂ መሆን አለባቸው"

ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ከመሠረተ ክርስቶስ መሪዎች አንዱ ከሆኑት ወንድም የተላለፈ መልዕክት:-.......

በመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን
በአዲስ አበባ ክልል ስር የሚገኙት የአርባ ሦስት አጥቢያ መሪዎች፤ አንዳንድ የሜኖናይት ዓለም አቀፍ ቤተ ክርስቲያን አባል "አብያተክርስቲያናት" ግብረ*ሰዶማ*ዊነትን በግልጽ መቀበላቸውን ተከትሎ የመሰረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ዋናው ቢሮ አስፈጻሚው አካል (ፕሬዝዳንቱ) መተዳደሪያ ደንቡን በመጣስ ከዚሁ አካል ጋር በፈጠሩት ህገወጥ ግንኙነት/ህብረት ዙሪያ ሐምሌ 24-25/2018 ዓ.ም ጽኑ የተቃውሞ አቋም የመውሰዳቸው ዜና በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተንሸራሸረ ይገኛል፡፡

ነገር ግን የቤተ ክርስቲያኒቱን ፌስ ቡክ ገጽ የሚቆጣጠሩት ፕሬዝዳንቱ ግን ይህንን ጉዳይ በመሠረተ ክርስቶስ ኦፊሻል ገፅ እንዲዘገብ ያደረጉት በተዛባ መንገድ ነው። ማለትም ውሳኔውን በውሳኔነቱ ሳይሆን፣ «በመጪው ነሐሴ ወር መጨረሻ በሚካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እንዲታይ ጥያቄ ቀርቧል» የሚል አሻሚ ሐረግ በመጠቀም አቅርበውታል። ፕሬዘዳንቱ ይህንም እንዲፃፍ ያደረጉት የክልሉ ውሳኔ በማህበራዊ ሚዲያ መሰራጨት ከጀመረ በኃላ ያንን ለማስተባበል ፈልገው ነው። ይህንንም የጉባኤው ተሳታፊ ከነበሩት ከክልሉ የአስተዳደር መሪዎች ጉባኤ አባላት እና በጉባኤው ተሳታፊ ከነበሩ የየአጥቢያው መሪዎች መረዳት ይቻላል።

በመመረተ ክርስቶስ የፌስ ቡክ ገፅ ከተለጠፈው መረዳት እንደሚቻለው "የተጣሰው የመተዳደሪያ ደንብ ወደ ቦታው ይመለስ" ያሉትን የአርባ ሦስቱን የአዲስ አበባ ክልል አጥቢያዎች "ውሳኔ" ከውሳኔነት ወደ "ጥያቄነት" ዝቅ በማድረግ ፕሬዘዳንቱ ራሳቸው እና የመአመጉ ሰብሳቢ የሚቆጣጠሩትን ጠቅላላ ጉባኤ ደግሞ ጥያቄውን ተመልካች አድርጎ ለማቅረብ ተሞክሯል። ይህም ፕሬዝዳንቱና የመአመጉ ሰብሳቢ በራሳቸው ላይ የሚቀርበውን ሕጋዊ ተጠያቂነት ለመሸሽና ከዚህም በፊት እንደሚያደርጉት ሥልጣናቸውን ያለአግባብ ለመጠቀም ያደረጉት ይህ ስልታዊ አካሄድ ግልጽ የሕግ ጥሰት ነው።

በመሠረተ ክርስቶስ ኦፊሻል ገፅ ላይ ቃል በቃል “...ጉባኤው በልዩ ልዩ አጀንዳዎች ላይ የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ከመሠረታዊ የመፅሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ካፈነገጡ የሜኖናይት ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር የሚኖራትን ግንኙነት አስመልክቶ በመጪው ነሐሴ ወር መጨረሻ የቤተክርስቲያኒቱ 95ኛው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ትኩረት ተሰጥቶት እንዲታይ ጥያቄ ቀርቧል” በሚል አስፍሯል።

እዚህ ላይ በአስፈጻሚው አካል (በፕሬዘዳንቱ) የቀረበው እንዲህ ያለው የማሳሳቻ ዜና እና በ 43ቱ አጥቢያዎች ውሳኔ መካከል ሁለት መሰረታዊ ልዩነቶች ጎልተው የሚታዩ ሲሆን እነርሱም:-

1. የአጥቢያዎቹ አቋም ላለፉት ዓመታት በፕሬዝዳንቱ ሲደረግ የነበረው ህገወጥ ግንኙነት «ይቋረጥ» የሚል ጽኑ ውሳኔ ሲሆን፤ የፕሬዝዳንቱ አቀራረብ ግን ሐረጉን ከ«ነበረው» ወደ «የሚኖራት» ግንኙነት በመቀየር ጉዳዩን ስለ ያለፈው ግንኙነት መቋረጥ ሳይሆን ወደፊት ስለሚኖራት ግንኙነት የሚመክር አድርጎ አቅርቦታል። በዚህም የቤተ ክርስቲያኒቱ ዋና ቢሮ ፕሬዝዳንት ከእነዚህ አካላት ጋር ለወደፊቱም ቢሆን መተዳደሪያ ደንቡ እንደተጣሰ ግንኙነቱ እንደሚቀጥል ለማመልከትና የተፈጸመውን የሕግ ጥሰት ኃላፊነት ለመሸሸግ ተሞክሯል፡፡

2. የአዲስ አበባ ክልል አጥቢያዎች ውሳኔ እንጂ የወሰኑት፣ ጥያቄ አይደለም የጠየቁት። የወሰኑት ውሳኔ «መተዳደሪያ ደንብ ተጥሷል፤ ስለዚህ ወደ ቀደመው አካሄድ ተመለሱ» የሚል ውሳኔ ተግባራዊ እንዲሆን እንጂ ለጠቅላላ ጉባኤ «እንውጣ ወይስ አንውጣ» እያሉ የሚጠይቁት የውይይት አጀንዳ አይደለም። ነገር ግን ፕሬዝዳንቱ በኦፊሻል ፔጁ እንደ ጥያቄ አድርጎ እንዲቀርብ ማድረጉ፣ ጠቅላላ ጉባኤው ጥያቄውን የመቀበልም ሆነ የመቃወም ፍጹም መብት እንዳለው በማስመሰል የፕሬዝዳንቱን ግልጽ የመተዳደሪያ ደንብ ጥሰትና ተጠያቂነት በመሸፈን የአርባ ሦስት አጥቢያዎቹን ሕጋዊ ውሳኔ የማሳነስ ስልታዊ አካሄድ ተደርጎ ይወሰዳል።

የመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን መተዳደሪያ ደንብ «ቤተ ክርስቲያኗ በመሠረተ እምነቷና ትምህርቷ ከሚስማሟት፣ ከሜኖናይት ቤተ ክርስቲያናት ጋር ግንኙነት ይኖራታል» በማለት በግልጽ ይደነግጋል። የሜኖናይት ዩኤስኤ እና የሜኖናይት ካናዳ አካላት ግብረሰዶማዊነትን በይፋ መቀበላቸውን አረጋግጠውና አምነው እያለ፣ የመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ዋና ቢሮ ፕሬዝዳንት ግንኙነቱን ከማቋረጥ ይልቅ ላለፉት ሰባት ዓመታት ማጠናከሩ ከመተዳደሪያ ደንቡ ውጭ መሄዱን በግልጽ ያሳያል።

ከዚህም በላይ ከዚህ ህብረት ቤተ ክርስቲያኒቱ እንድትወጣ በአደባባይ የወተወቱትን ወገኖች ከመአመጉ ሰብሳቢ በወጣ ደብዳቤ ከቤተ ክርስቲያን ተሰርዛችኋል መባሉ ፕሬዝዳንቱና የመአመጉ ሰብሳቢ ምን ያህል ከሕግ በላይ እንደሆኑኑ መተዳደሪያ ደንቡ ይከበር ያሉትን ጭምር በመሰረዝ ከህግ በላይ መሆናቸውን ያሳየ ትልቅ ክስተት ነው፡፡ የጠቅላላ ጉባኤውንም የሚሰበስቡት እነዚሁ አካላት ራሳቸው መሆናቸው ችግሩን የበለጠ አባብሶታል። ይህ አሰራር ፕሬዝዳንቱና የመአመጉ ሰብሳቢ ሕግን ጥሰው ሲገኙ በራሳቸው ላይ ተጠያቂነት እንዳይመጣ የመከላከል ግልጽ አዝማሚያ ያሳያል።

«እንውጣ ወይስ አንውጣ» የሚል አጀንዳ ለጠቅላላ ጉባኤው ማቅረብ ራሱ መተዳደሪያ ደንቡ ተጥሶ ይቀጥል ወይስ ወደ ቦታው ይመለስ የሚል አግባብነት የሌለው ጥያቄ ነው። «እንቀጥል» ማለት መተዳደሪያ ደንቡ ተጥሶ ይቀጥል ማለት ሲሆን፣ «እንውጣ» ማለት ግን መተዳደሪያ ደንቡ ይከበር ማለት ነው። የአዲስ አበባ አርባ ሶስት አጥቢያዎች መተዳደሪያ ደንቡ ይከበር ነው ያሉት፡፡ ስለሆነም ለጠቅላላ ጉባኤው አጀንዳው ከቀረበለት የመተዳደሪያ ደንቡን የጣሱ አስፈጻሚ አካላት ተጠያቂ ሊደረጉ ይገባል የሚል ብቻ መሆን አለበት።

ይህ ጉዳይ በመሠረታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ማዕቀፍ ውስጥ የሚታይ እና መተዳደሪያ ደንብ የማክበር ወይም የማስከበር ጉዳይ እንጂ «ከዚህ በኋላ ከእነሱ ጋር ምን ዓይነት ግንኙነት ይኑረን?» በሚል ለቀጣይ ውይይት የሚቀርብ አዲስ አጀንዳ አይደለም። ለጠቅላላ ጉባኤው አጀንዳው የሚቀርብ ከሆነ የቤተ ክርስቲያኒቱን መተዳደሪያ ደንብ የጣሱ አስፈጻሚ አካላት ተገቢውንና ተመጣጣኝ ተጠያቂነት እና እርምጃ ለማስወሰድ መሆን አለበት። ነገር ግን አስፈጻሚው አካል ሕግ አውጪ፣ ሕግ አስፈጻሚና ሕግ ተርጓሚ በመሆን የተለያዩ የቤተ ክርስቲያኒቱን አካላት በመጨፍለቅ መተዳደሪያ ደንቡን ካወጡ በኋላም ያወጡትን መተዳደሪያ ደንብ ቢጥሱ የሚጠይቃቸው አካል ባለመኖሩ፣ ፕሬዝዳንቱና የመአመጉ ሰብሳቢ የፈጸሙትን የሕግ ጥሰት ተጠያቂነት በማስቀረት ላይ ያተኮረው ይህ አካሄድ ቤተ ክርስቲያናችን ሁለንተናዊ ታድሶ እንደሚያስፈልጋት በግልጽ ያሳያል።

በማጠቃለያም፣ የአዲስ አበባ ክልል አርባ ሦስት አጥቢያዎች ያስተላለፉት መልእክት «መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ከናዱ አካላት ጋር ግንኙነት አይኖረንም፤ በፕሬዝዳንቱ አማካይነት የተፈጠረው ህገወጥ ግንኙነት ቶሎ ይቋረጥ» የሚል ጽኑ ውሳኔ ነው። ነገር ግን የቤተ ክርስቲያኒቱ ኦፊሻል ገጽ ጉዳዩን እንደ አዲስ «ጥያቄ» እና «ስለወደፊት ግንኙነት የሚመክር» አድርጎ ማቅረቡ የቃላት መሻሻል ብቻ ሳይሆን፣ የአርባ ሶስት አጥቢያዎችን ውሳኔ ክብደት የመቀነስ እና አስፈጻሚው አካል (ፕሬዝዳንቱ) እና የመአመጉ ሰብሳቢ የፈጸሙትን ግልጽ የመተዳደሪያ ደንብ ጥሰት ተጠያቂነት የመሸፈን አዝማሚያ እንዳለው በግልጽ መረዳት ይቻላል። ስለዚህም የቤተ ክርስቲያኒቱ መሪዎች ሕግንና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረትን ባከበረ መልኩ የፕሬዝዳንቱንና የመአመጉ ሰብሳቢን ሕገወጥ ተግባር እና ተጠያቂነት የሚያረጋግጡ ግልጽ እርምጃዎችን መውሰድ ይጠበቅባቸዋል።

የመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን መተዳደሪያ ደንብ የጣሱ አስፈጻሚ አካላት (በዋናነት ፕሬዘዳንቱ) ተጠያቂ መሆን አለባቸው።

ከመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን መሪዎች አንዱ።

08/04/2026

እግዚአብሔርን የምትፈሩት ሲዖል እንዳትገቡ ነው ?

የምስራች ከመሠረተ ክርስቶስበመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የአዲስ አበባ ክልል አርባ አንድ አጥቢያዎችን የወከሉ መሪዎች ሐምሌ 24 እና 25/2018 ዓ.ም ለሁለት ቀናት ስብሰባ አድርገው ነ...
08/02/2026

የምስራች ከመሠረተ ክርስቶስ

በመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የአዲስ አበባ ክልል አርባ አንድ አጥቢያዎችን የወከሉ መሪዎች ሐምሌ 24 እና 25/2018 ዓ.ም ለሁለት ቀናት ስብሰባ አድርገው ነበር።

በስብሰባቸውም መሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ግብረ*ሰዶማ*ውያን ተቋማትን ከሚቀበለው ከዓለም አቀፉ የሜኖናይት ኮንፍረንስ (MWC) አባልነት እንድትወጣ በሙሉ ድምፅ ወስነዋል።

ያለ አግባብ ከአባልነት የተሰረዙት እነ ዶ/ር ስዩም አንቶኒዮስም ስረዛው እንዲነሳላቸው ወስነዋል።

በቀጣይም በየተራ በሚደረጉት የምስራቅ አዲስ አበባ ክልል መሪዎች እና አገር አቀፍ የመሪዎች ስብሰባም ላይ ተመሳሳይ ወሳኔ ይወሰናል ተብሎ ይጠበቃል።

07/31/2026

አንድ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ ዳግም ከተወለደ በዘርም በሕግም የሚተላለፍ እርግማን ነጻ ነው እርግማናችንን ኢየሱስ ወስዶታል ።

“በእንጨት ላይ የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፏልና ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ ከሕግ እርግማን ዋጀን” (ገላትያ ፫ : ፲፫ )

የጌታችን የኢየሱስ ፀጋ እና ሠላም ከእናንተ ጋር ይሁን

Address

America
Los Angeles, CA

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Christian Post ክርስቲያን ፖስት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share