Yewula Debre Medhanit Kidane-Mihiret

Yewula Debre Medhanit Kidane-Mihiret “ኃጢአተኞችን ወደ ንስሐ እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁም።”
— ሉቃስ 5፥32

06/07/2024

ኬሚስትሪውም እምነቱም ያልገባቸው ወገኖች ደግሞ "የውሃ ሳይንስ" ብለው ከተፍ አሉ!

ጌታ ሆይ አልበዛም ግን?

ይህ ትውልድ አበሳው አሳሩ መብዛቱ!

05/29/2024

ማርያም!

05/27/2024
  ቅኔ በሊ/ጉ ቆሞስ አባ ገብረ ማርያም መንግስቴ(መምህረ ቅኔ ወሐዲስ ኪዳን)   በዚች እለት ማህሌታዊው ቅዱስ ያሬድ የተሰወረበት እለት ነው ይህም ቅዱስና ሊቅ አባቱ አዳም እናቱ ታውክልያ ...
05/18/2024

ቅኔ በሊ/ጉ ቆሞስ አባ ገብረ ማርያም መንግስቴ
(መምህረ ቅኔ ወሐዲስ ኪዳን)







በዚች እለት ማህሌታዊው ቅዱስ ያሬድ የተሰወረበት እለት ነው ይህም ቅዱስና ሊቅ አባቱ አዳም እናቱ ታውክልያ ይባላሉ፡፡
ያሬድ ማለት፦ ሙራደ ቃል ማለት ሲሆን ብሔረ ሙላዱ ከዘርዓ ሌዋውያን አኩሱም ነው የተወለደውም በ505 ዓ.ም ነው፡፡
ቅዱስ ያሬድ ቅኔንም ቢሆን አሙልቶና አስፍቶ ባይናገረው እንጅ ደራሲው እርሱ ነው ዜማውም ሶስት አይነት እንደሆነ ይታቃል ይሄውም ግእዝ፤እዝል፤አራራይ ነው፡፡ ምሳሌነቱም፦ግእዝ የአብ ፤ እዝል የወልድ ፤ አራራይ የመንፈስ ቅዱስ ምሳሌ ነው፡፡

የታላቁ ኢትዮጵያዊ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ በረከቱ ለዘለዓለም ይደርብን፡፡



⚜️ ጉባኤ ቃና 💚💛❤

◈ ◈ ፩ኛ . . .

መፍትው ወርትዕ ብሂለ ያሬድ ማዕምር
ማርያም ቅኔ ዘጌዴዎን ጸምር

◈◈ ፪ኛ . . .

ውሉዱ ለያሬድ መስፍነ ብዙህ ተአውቆ
ኅሱ መጻሕፍተሙሴ መንግሥቶ ወጽድቆ

◈◈ ፫ኛ . . .

አኅዘነነ ያሬድ ወአተከዘ አዕላፈ
እስመ እድሜ ያሬድ ሐልቀ እንዘ የአቅብ አዕዋፈ

◈◈ ፬ኛ . . .

ውስተ ሐመረ ኖኅ ያሬድ ዘአክበርዎ አዕላፍ
ተጋብዑ በበዘመዶሙ ቅኔያት አዕዋፍ

◈◈ ፭ኛ . . .

መኑመ ያሬድ ዘይብልዎ አዝማደ ያሬድ ልዑል
ቶታነ እግሩ ኦሪት ወአሳዕነ እግሩ ወንጌል

◈◈ ፮ኛ . . .

ማርያም ምሥጢር ወላዲተአምላክ አምላኩ
ለያሬድ ሱራፊ አዝዚዮ እስኩ

◈◈ ፯ኛ . . .

ይብል ያሬድ ዘዓለማተ ፈጠረ
አምላኪየ ዜማ ሰማየ ሳረረ

◈◈ ፰ኛ . . .

አመ ተናገረ ያሬድ ሰማዔቃለአብ አቡሁ
ኢተረክበ ሐሰተ ኑፋቄ እምአክሱም አፉሁ

◈◈ ፱ኛ . . .

ዮም ያሬድ ዘመነክረት ማዕምር
እስመኦደ ላዕለደብረሐዊ ደመና ምሥጢር

◈◈ ፲ኛ . . .

ገብረ መስቀልኑ የዋህ ዘዓለማተ ፈጠረ
ዘበሕሊናሁ ለያሬድ እስመገብረመስቀል አዕመረ

⚜️ ዘአምላኪየ 💚💛❤

◈◈ ፩ኛ . . .

እግዚአ ነቢያት ያሬድ ለአርዳዒሁ ይብሎሙ
ሰላምየ ቅኔ አኀድግ ለክሙ
ወሎቱ ለአብ ተዕዛዛቲሁ ፈጽሙ

◈◈ ፪ኛ . . .

እግዚአ ነቢያት ያሬድ ለአርዳዒሁ መፍጠኔ
ይቤሎሙ ኢይደንግጽክሙ ልብክሙ ቅኔ
እስመ ኃይለ ሞት ዓለም ምንትኒ ወአልብክሙ ኩነኔ

⚜️ ሚበዝሁ 💚💛❤

◈◈ ፩ኛ . . .

ይቤለኪ ጽዮን ገዳመ ሐዊ ክርስቶስ
ኪያኪ ዘአዕመረ
ሰላምኪ ያሬድ እምአዕይንትኪ ተሰወረ
ወይበጽሐኪ ለኪ ዘመነ ምንዳቤ ወግፍዕ ዘልቡናኪ ኢሠምረ

◈◈ ፪ኛ . . .

ነበርነ ነህነ ወበከይነ ንህነ በከመ ኤርምያስ ገሊላዊ
ሶበተዘከርና ፍጡነ ለጽዮን ደብረሐዊ
ወዕንዚራቲነ ክብረ ወተፋቅሮ ሰቀልነ በከመ ዳዊት ዜናዊ

◈◈ ፫ኛ . . .

ኀረያ ፍጡነ እግዚአ ነቢያት ያሬድ ምስለ መንፈስ ቅዱስ መንፈሳዊ
ማህደሮ ትኩኖ ጽዮን ደብረሐዊ
ወይቤ ፍጡነ ምዕራፍየ ሊተ ወማህደርየ ነፍሳዊ

◈◈ ፬ኛ . . .

ይብል ያሬድ ተሠየምኩ አነ በከመነቢይ ቀዳማዊ
በደብረ መቅደሱ ምስጢር ወበጽዮን ደብረሐዊ
ከመ እንግር አነ ዜና ነቢያት ምስጢረ ዘበነቢያት ሀላዊ

◈◈ ፭ኛ . . .

ምስጢረ መጻሕፍት እሳት ቅድመገጸወልድ ያሬድ ወመንፈስ ቅዱስ ማህየዊ
ስነስብሐቲሁ ምስጢር እምጽዮን ደብረሐዊ
ወይጼውዓ ለምድር ልሳነ ሊቃውንት አበው
ዘበመንፈስ ቅዱስ ሀላዊ

◈◈ ፮ኛ . . .

ሐዋርያ ጽድቅ ያሬድ ለአርድዒሁ ይብሎሙ
አንትሙ ህዝበሌዊ
በጻሕክሙ እንከ ኀበጽዮን ደብረሐዊ
ወበውስቴታ ሀለዉ መላእክት አዕላፍ ሊቃውንተሮም ሮማዊ

◈◈ ፯ኛ . . .

እግዚአ ነቢያት ይብል በልዋ ካዕበ
ጠበብተ እስራኤል እስራኤላዊ
ኢትፍርሒ እንከ ጽዮን ደብረሐዊ
እስመንጉሥኪ ያሬድ ዲበዕዋለ አድግ ምስጢር እንዘይጼዓን
ከዋዊ

◈◈ ፰ኛ . . .

ሶበቀዳሚ ተቀጥሉ ሊቃውንት ሰማዕት ሰማዕተ ድካም ወጻማ
አዕዋፈ ሰማይ ጸግቡ እምነሥጋሆሙ ዜማ
ይቤለነ ለነ ወልደ ነጎድጓድ ያሬድ ለኢትዮጵያ ስዩማ

◈◈ ፱ኛ . . .

አበዊነ ይብሉ ለነገርክሙ ያሬድ ኢትትናገርዎ በጎጉኦ
ለነገርክሙ ያሬድ እስመ ኦፈሰማይ ያወጽኦ
ወወስተልብክሙ ይንበር ነገረኩልክሙ ያሬድ
ከመ ኢያምጽእ ተገፍኦ

◈◈ ፲ኛ . . .

ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ምስጢር ተውህቦ ለያሬድ ከመ ያእምር አሐተኔ
ምኅዋረ ፀሐይ ማኅሌት ወምኅዋረኮከብ ምስጠረቅኔ
ማዕከለ ዘመን ማኅሌት ወጥንተማዕከል ምስጢር እስመየአምር መፍጠኔ

◈◈ ፲፩ኛ . . .

መፍቀሪተቤቱ ለያሬድ ገዳመሐዋ ወላድ ትብል በአፉሃ
ኩሉ ይብለኒ ኢትመኒ ያሬድሃ
እስመ ያሬድ ያሬድ እንዘ ይኔጽሮ ለሄኖክ የኀድገኪ አሜሃ

⚜️ ዋዜማ 💚💛❤

◈◈ ፩ኛ . . .

እግዚአ አበዊነ ቅኔያት ዜማያሬድ ጴጥሮስ ድኅረ አስተርአይከ ኩሎ
ኅርድ አዕዋፈሰማይ ወብላእ ይቤሎ
ቃለ መጻሕፍት መልአክ ዘበሐዋርያት ሀሎ
ወዘያጠፍኦ ፍጡነ እስመ መሰሎ
ኢተወክፈ ወኢሰምአ ቃሎ

◈◈ ፪ኛ . . .

ያሬድ ዘተመነየ ንዋየ ካልዑ እርገተ ዘአይሁዳዊ ሀደገ
ኢሀለየ ወኢተዘከረ ሞተ አቤል ሕገ
ወኢፈርሐ ያሬድ መጻሕፍተ ሙሴ አዕሩገ
ወተለወ ያሬድ ዘእዝራ ፈለገ
ወምስሌሁ ደብረ ሄኖክ አርገ

⚜️ ሥላሴ 💚💛❤

◈◈ ፩ኛ . . .

ያሬድ ይቤሎሙ ለአግብርተ ያሬድ ቅኔያት ኀቤየ ንዑ ወተጋብዑ አሚረ
እስመአነ እዜንወክሙ ዐቢየ ምሥጢረ
ወአዲ ብዙኀ ቃለ መጻሕፍት ምክረ
ዘበሐዋርያት ኢተነግረ
ወሰማዕተ ቃሉ ለያሬድ ተጋብዑ ምዕረ
እስመእሉ የሐስሱ ክብረ

⚜️ ዘይዕዜ 💚💛❤

◈◈ ፩ኛ . . .

ዘመንከ ያሬድ ዘመነስፍን ወሚ መጠን ኑኃእድሜከ ኀላፊ
እስመአንተ ትቤ ቢጽየ ሱራፊ
ወሰብአ ቤትየ ሊተ ኪሩብ ተወካፊ
ቃለ እግዚኡ ለያሬድ እምኀበይሰፊ
ክንፈ መላእክት ካህናት ጸሐፍተ ያሬድ ጸሐፊ
ቃለ እግዚኡ ለያሬድ እምኀበይሰፊ

◈◈ ፪ኛ . . .

ለጳውሎስ ያሬድ ዘበንጽሕና እግዚአ ነቢያት ምሥጢር ዘበነቢያት ሀሎ
በርእስከ ዜማ ተአመን ይቤሎ
አምጣነ ምሑር አንተ ወብርሃነጽድቅ ተጋድሎ
ይቤለከ ኤልሳዕ ነቢየሴሎ
ወተመይጠ ያሬድ ድኅረ ተዘከረ ቃሎ
ይቤለከ ኤልሳዕ ነቢየሴሎ

⚜️ መወድስ 💚💛❤

◈◈ ፩ኛ . . .

ፍሬጻማሁ ለአሞን ኢትዮጵያዊ እምነማዕረር ያሬድ ኢያስተርአየ ውስቴቱ
እስመ አመ ወጠነ ይፍረይ ፍሬቃለወንጌል ዘቦቱ
መጽኡ አዕዋፈሰማይ ወበልእዎ ሎቱ
ወኀልቀ በጽጌሁ ማዕረረጽድቅ ያሬድ
ፍሬድንቃዌልብ እንተአልቦቱ
ያሬዳሂ ተክለ ንጽሕና ዘበተዋሕዶ ሕይወቱ
ፍሬቃለወንጌል ከመይፍረይ ይፈቅድ ወይፈቱ
ወበተክለ ንጽሕ ያሬድ ዘአዕጹቂሁ ሰለስቱ
ይትፌስሑ ብዙኃን አምጣነ በጽሆሙ በረከቱ

◈◈ ፪ኛ . . .

ለሰብአዛቲ ኤፌሶን አዕዋፈሰማይ ይቤሎሙ ያሬድ ጳውሎስ ዘፈቀደ
ምስጢረ ሰማይ ይትናገር ማዕከለ አይሁድ አይሁደ
እምዮም ወእምይእዜሰ ኢኮንክሙ ነግደ
ወአንትሙ ሰብአቤቱ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጢር ዘበኀቤነ ተግሕደ
ህንጻ መንፈስ ቅዱስ ምስጢረቅኔ እስመኮንክሙ ፈድፋደ
መለኮትሂ ምስጢረዜማ ምስሌነ ተወሐደ
እስመኮነ ንህነ ዘመንፈስ ቅዱስ ማህፈደ
ጸላዒነሂ መርገመሥጋ ማዕከሌነ ተዋረደ

⚜️ አጭር መወድስ 💚💛❤

ተናገረ ያሬድ በእንተ እርገቱ ብሂለ
ዘካርያስ ዕጼ ኮነኒ አምሳለ

የቅዱስ ያሬድ አምላክ ሀገራችንን ቤተክርስቲያናችንን ከክፉ ህዝቧንም ከስደት ይሰውርል ሀዘኑ ረሃቡ ሞቱ ይበቃችዋል ይበለን የሊቃውንቱን ከደብሩ ካህናቱን ከመንበሩ አያሳጣን እግዚአብሔር በሰጣቸው እውቀት እንዲህ በቅኔ ለሚራቀቁ ሊቃውንት አባቶች እድሜውን ይስጥልን።

ለአመቱ በሰላም ያድርሰን መልካም በዓል🙏🙏

ከማትያስ_አስቻለው

05/13/2024
05/06/2024

Don't watch this, go to Comedian Eshetu's YouTube channel and watch that.

Thanks for for doing this!

`   ✅➕እለተ አርብ የጌታችን ስቅለት የሚታሰብበት ቀን   ጌታችንና መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በእለተ አርብ ያያቸው ስቃይና መከራ   "ተጨነቀ ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም ፤ ለመታረድ ...
05/03/2024

` ✅➕እለተ አርብ የጌታችን ስቅለት የሚታሰብበት ቀን

ጌታችንና መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በእለተ አርብ ያያቸው ስቃይና መከራ

"ተጨነቀ ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም ፤ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት ፥ በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም። " 《ትንቢተ ኢሳይያስ 53 : 7》
===================================
13ቱ ህማማተ መስቀል

✅1➡እራስን በዘንግ መመታት፦ ተፉበትም መቃውንም
ይዘው እራሱን መቱት ። 《ማቴ 27÷30》
✅2➡ በጥፊ ተመታ፦በጥፊም ይመቱት ነበር።
《ዮሐ 19 ÷ 4》
✅3➡ ምራቅ ተፉበት፦ ተፉበትም መቃውንም ይዘው
እራሱን መቱት።《 ማቴ 27÷30》
✅4➡ የሾክ አክሊል ጎንጉነው በእራሱላይ አቀዳጁት
{ማቴ 27 ፥ 29}
✅5➡ መራራ ሀሞት መጠጣት፦በሀሞት የተደባለቀ
የወይን ጠጅ ሊጠጣ አቀረቡለት፤ ቀምሶም
ሊጠጣው አልወደደም ። 《ማቴ 27÷34 》
✅6➡ ጀርባን መገረፍ፦በዚያን ጊዜም ጲላጦስ
እየሱስን ይዞ ገረፈው ። 《ዮሐ 19÷1》
✅7➡ ጎኑን በጦር መውጋት፦ ነገር ግን ከጭፈራዎቹ
አንዱ ጎኑን በጦር ወጋው ወድያውም ደምና
ውሃ ወጣ። 《ዮሐ 19÷34 》
✅8➡ ወደ ኃላ መታሰር፦ የሾለቃውና ጭፍሮቹ
የአይሁድም ሌሎችም እየሱስን ይዘው
አሰሩት ።《ዮሐ18÷12 》
===================================
5ቱ ቅንዋተ መስቀል ችንክሮች ሳዶር ፣ አላዶር ፣ ዳናት ፣ አዴራ እና ሮዳስ ይባላሉ።

✅1➡ ሳዶር ፦ ማለት ቀኝ እጁ የተቸነከረበት
✅2➡ አላዶር፦ ማለት ግራ እጁ የተቸነከረበት
✅3➡ ዳናት ፦ ማለት እግሮቹ የተቸነከረበት
✅4➡ አዴራ ፦ ማለት ደረቱን የተቸነከረበት
✅5➡ ሮዳስ ፦ ማለት ከወገቡ(እብርቱ) አጣብቆ
እንዲይዝ የተቸነከረበት
===================================
ሞትን ይሽረው ዘንድ የማይሞተው ሞተ መከራን ታገሰ

✅ሁሉን የያዘውን እርሱን ያዙት
✅ሁሉን የሚገዛውን እርሱን የአምላካችንን እጅ አሰሩት
✅ሀጥያትን የሚያስተሰርይ እርሱን ሀጢያት አሉት
✅የማይገረፍ አምላክ እርሱን የሰውን ስጋ በመልበሱ
ገረፉት
✅እንደ መብረቅ የሚያንፀባርቀውን ነጭ ልብስ
የሚያለብስ አምላክ እርሱን ቀይ ግምጃ አለበሱት።
✅በእሳት በተጋረዱ ዙፋን ላይ የሚቀመጥ እርሱን
በመዘባበቻ ወንበር ላይ አስቀመጡት።
✅እንደ ድንኳን ሰማይን የዘረጋ እርሱን በመስቀል
ላይ ሰቀሉት
✅የመላይክትን አለቆች በፊቱ በመፍራት የሚቆሙለት
እርሱን በጲላጦስ ፊት አቆሙት
✅በህይዋንና በሙታን ላይ የሚፈርድ እርሱን
እንደበደለኛ ተፈረደበት
✅አለምን ሁሉ በቅፅበት የፈጠረ እርሱ በስጋው ሞተ
በመለኮት ህያው ሆነ
==================================
1ኛ ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ከ6-9 ስአት በመስቀል ላይ ሳለ የተናገራቸው 7ቱ የፍቅር ቃላት

✅1➡ ኤሉሄ ኤሉሄ ለማስበቅታኒ (አምላኬ አምላኬ
ለምን ተውኸኝ 《ማቴ 27÷46 》
✅2➡ እውነት እውነት እልሃለሁ ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር
ትኖራለህ።《ሉቃ 23÷43》
✅3➡ አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ።
《ሉቃ 23÷43》
✅4➡ አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር
በላቸው። 《ሉቃ 23÷34》
✅5➡ እናትህ እንኃት እንሆ ልጅሽ።《 ዮሐ 19÷26-27》
✅6➡ ተጠማሁ።《ዮሐ 19÷28》
✅7➡ ተፈፀመ። 《ዮሐ 19÷30》
===================================
2ኛ ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሳለ የተፈፀሙ 7ቱ ታአምራት

✅1➡ ፅሀይ ጨለመች
✅2➡ ጨረቃ ደም ለበሰች
✅3➡ ከዋከብት ብርሃናቸውን ነሱ
✅4➡ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከሁለት ተከፈለ
✅5➡ አለቶች ተሰነጣጠቁ
✅6➡ መቃብራን ተከፈቱ
✅7➡ የሞቱት ተነሱ
===================================
ክብርና ምስጋና አምልኮትና ውዳሴ ስግደት ዝማሪ ይድረሰው ለአምላካችን ለመድኃኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ።

አቤቱ አምላካችን ሆይ በመንግስትህ በመጣህ ጊዜ አስበን። አሜን (፫)!

ወስብአት ለእግዘያብሔር
ወወላዲቱ ድንግል
ወለ መስቀሉ ክቡር

sirgut_yemedhanialem

Yewula Debre Medhanit Kidanemihiret
02/22/2024

Yewula Debre Medhanit Kidanemihiret

01/25/2024

የኦርቶዶክስ ሀይማኖት ተከታይ #የኦሮሞ እህት ወንድሞቻችን እምነቱን እርሱት (ተውት) እባካችሁ ስጋዊ ህይወችሁን ከዚህ አደገኛ አካሄድ (የጅምላ ፍጅች) አድኑ። ይህ መልዕክት የደረሳችሁ እህት ወንድሞች እባካችሁ ለምታውቋቸው ወገኖቻችሁ መልዕክቱን አድርሱ።

ከአንድ የፔንትኮስታል (ፔንጤ) እምነት ተከታይ ወዳጃችን የደረሰን መልዕክት "እኔ የእምነቱ ተከታይ አይደለሁም ቤተሰቦቼ ግን ናቸው። አይኔ እያየ ጆሮየ እየሰማ ቤተሰቦቼን እና የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ወደጆቼን ማጣት አልፈልግም። የታቀደው በኢትዮጵያ ምድር ከፕሮቴስታንት እምነት ውጪ ሌላ እምነት እንዳይኖር ነበር። ነገር ግን በአምሐራ ህዝብ በኩል ፓለቲካው ስለተበላሸ ይህ የሚቻል አልሆነም። ያለው አማራጭ ለኦሮሞ ህዝብ ተቆርቋሪ በመምሰል እቅዳችንን ለማሳከት መሞከር ነው። ባጭሩ ይሄን ይመስላል የተያዘው እቅድ። ወንድማችሁ!"

Yewula Debre Medhanit Kidanemihiret

Mahibere Kidusan - ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማዕከል
Janderebaw Media
የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት አዳሪ የአብነት ትምህርት ቤት
ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ
Ethiopian Orthodox Tewahedo Page

01/24/2024

General knowledge: there are 365 days in a year and the word "DO NOT FEAR" has been listed 365 times in the Bible.

"Do not fear!"

ነገር ግን አምላካችሁን ተደፋፈሩ ማለት እንዳይደለ ልብ በሉ። የመንበረ ጴጥሮስ ሲኖዶስ ከመዘባረቁ በፊት እወቁት ለማለት ነው። በመንበረ ጴጥሮስ በአለ ሲመት ሁሉም ጳጳስ፣ አቡን፣ ቆሞስ፣ መሪጌታ፣ ....ተዘርዝሮ የማያልቅ ክህነት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ይታደላል። ዝማሬና ዘፈን አይለይም፤ ምዕመንና ካህን አይለይም፤ ቤተክርስቲያን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ስለሆነች ቤተክርስቲያን ሊኖር ግድ አይሆንም (በብዛት አዳራሽ፣ ማንም መክፈት ይችላል)፤ ስርዓት የሚባል አይኖርም፤ የኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ያበቃና አዲስ የዘመን አቆጣጠር ወይም የምዕራቦችን የዘመን አቆጣጠር መከተል ግድ ይሆናል፤ ... ብቻ ብዙ ብዙ ተዓምራቶች ይሆናሉ።

ይህ ሁሉ የሚሆን ግን ህዝቡ ከሰውነት ወጥቶ እንስሳዊ ባህሪ ሲኖረው ብቻ ነው!!!

Yewula Debre Medhanit Kidanemihiret

Address

Houston, TX
10664

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yewula Debre Medhanit Kidane-Mihiret posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Yewula Debre Medhanit Kidane-Mihiret:

Share