LUC / GHLU

LUC / GHLU Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from LUC / GHLU, Religious organisation, 2088 south Vaughn way, 304, .

12/01/2026
12/01/2026

ሰኞ, ጥር 4 / 2018
ይህ ጽሑፍ ባለፉት 20 ዓመታት ውስጥ በጌታ ፀጋ እና ምህረት ለክርስቶስ አካል እንዲሁም ለመላው ህብረተሰብ ከሰራናቸው ስራዎች እጅግ ጉልህ እና አስደናቂ ሥራዎች ውስጥ ከፍተኛውን ስፍራ የያዘ ነው። "ዐበይት ክርስቲያናዊ የሆኑ ፖለቲካዊ እና ማኅበራዊ ሚናዎች / መንግስት እና ቤተክርስቲያን" የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን ቁልፍ የሃይማኖት አመራር ላይ ላሉ ሰዎች እና የመንግስት ባለ ስልጣናት ላይ በማተኮር ለፖሊሲ ጥናት እጅግ በጣም ጥሩ ምንጭ ሆኖ ያገለግላል።

በይበልጥም በሃገራችን እና ከሃገራችን ውጭ ያሉ የአብያተ ክርስቲያናት ህብረቶች እና ሚኒስቲሪዎችን ይመለከታል።

የጋራ ህልማችን በሆነው “በኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች ካውንስል” በሁለንተናዊ አገልግሎት ዙሪያ ላይ በሚሰራቸው እንዲሁም ወደ ፊት ሊያከናውናቸው በሚገባው ዙሪያ ጥናታዊ ምክር አዘል ስራዎችን በውስጡ የያዙ መፅሐፍት ናቸው። ተመሳሳይነት ያላቸው ዓለም አቀፋዊ ተቋማት ተመክሮን ከሃገራችን ውቅታዊ ሁኔታዎች ጋር በይበልጥም ከእኛ አውድ ጋር በማመሳከር በርካታ መንፈሳዊ እና ሃገራዊ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዬች ላይ ትኩረት የያዙ ሰፊ የምርምር ጥናት ያዘሉ ሆነው ቀርበዋል። በወቅቱ የተሰጡኑን እድሎችን እንዴት ባሉ መንገዶች በፍቅር እና በአንድነት ለጌታ ክብር እንወጣ በሚለው ጠቃሚ እና በሳል የነፍስ መብል ሰንቀው የያዙ ጥናታዊ መፅሐፍቶች ሆነው ቀርበዋል። የካውንስሉም አመራሮች በሚገባ ይመለከቱታል አባታዊ ምክራቸውንም እንወስዳለን።

አንጋፋ የተባሉ የወንጌላውያን አማኞች [ቃለ ሕይወት ፥ ሙሉ ወንጌል፥ መካነ ኢየሱስ እና መሰረተ ክርስቶስ የመሳሰሉት] እንዲመለከቱት ይደረጋል።

ከሰላም ሚኒስቴር የሚመለከታቸው መሪዎች፥ ከሐይማኖት ተቋም የሚመለከታቸው መሪዎች፥ ከተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ቅርጫፍ ከሚገኙ ሙህራን እና በለሞያዎች እንዲሁም ከፍተኛ ተወካዮች በአጠቃላይ እና ከ30 በላይ ከተለያየ ጎራ የሚገኙ በዚህ ዙሪያ አቅም ያላቸው እና ሊፈትሹት ለሚችሉ ሊሂቃን ይህንን መጽሐፍ ለማንበብ እና አስተያየታቸውን እንዲሰጡ ይደረጋል።

ሁል ግዜም በመጀመሪያ አስጠርዘን እንልካለን። በመጨረሻ ደግሞ የእነርሱን በሚሰጠን መንፈሳዊ እና ሞያዊ አስተያየት ተነስተን የመጨረሻ ረቂቅ ስራው አስጠርዘን ወደ እትመት የሚሄድበትን መንገድ እየሰራን እንገኛለን።

ይህ መጽሐፍ "መንግስት እና ቤተክርስቲያን" ከሰባት ዓመታት በላይ የቆየ እድሜ ያለው ነው። በጌታ ፀጋ ለምወዳት ሃገሬ እና ለሕዝቤ እንዳዘጋጅ አቅሙን ለሰጠኝ ጌታንላመሰግነው እወዳለ። እኔ እና ቤቴ እንዲሁም አብረውኝ ያሉ በዚህ ስራ የተጠመዱ ሁለ ጋር ብዙ ችግሮችን ከወጣን በኋላ ይህንን በማየቴ በጣም ተደስቻለሁ። እውቀትን በፍቅር ከጥናታዊ ይዘቱ ጋር አይን ገላጭ እና ትውልድ ላይ ተፅእኖ የሚፈጥር እንደ ሆነ ምንም ጥርጥር የለኝም።

በብርቱ ፀልዩልን!

https://www.youtube.com/live/uMyKxd8fVgA?si=Mq1q6pESevkE268z
07/01/2026

https://www.youtube.com/live/uMyKxd8fVgA?si=Mq1q6pESevkE268z

ተስፋ ያላት ሴት አትፍሩ ታላቅ ደስታ የምስራች አምጥቻለሁ እና በሚል እርስ የእህት እየሩሳሌም ሀይሉ ጋር ቆይታDecember 26th 2023 time at 5:00 P.M / ማክሰኞ ታኅሣሥ , 16 , 2015 (በኢትዮጵያ ከቀኑ 10፡00 ሰዓ...

እንኳን ለአዲሱ ዓመት [2026] አደረሰን! በዚህ አዲስ አመት (2026) በክብሩ እውቀት ብርሃን ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን እንባረካለን ስንል በጌታ ፀጋ እና የሐይሉ ችሎት ተማምነን ነ...
03/01/2026

እንኳን ለአዲሱ ዓመት [2026] አደረሰን! በዚህ አዲስ አመት (2026) በክብሩ እውቀት ብርሃን ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን እንባረካለን ስንል በጌታ ፀጋ እና የሐይሉ ችሎት ተማምነን ነው።

አይናችን ከሙታን ተነስቶ በአብ ቀኝ በተቀመጠው በውድ ልጁ ላይ ብቻ ነው። በዚህ አዲስ አመት በጌታ ፀጋ እና በትንሳኤው ሐይል ህብረተሰባዊ በሆኑ አጀንዳዎች ዙሪያ ከምናቀርባቸው 8 መፅሐፍት መካክል እነዚህ አራቱ መፅሐፍ ይገኛሉ። እያንዳዳቸው 500 ገፅ በላይ ሲሆኑ ለረጅም አመታት ከሊሂቃኑ ጋር አብረን የሰራነው ድንቅ ስራዎች ናቸው።

ምህረቱን ከእኛ ያላራቀ እግዚአብሔር በ 2026 አጠናቅቀን እና ለትውልድ እንድናቀርብ ስለ ረዳን በሁላችሁ ፊት የፀጋ ባላቤት የሆነውን የእናንተ እና እኔ አምልካን ላመሰግነው እወዳለሁ።
ይህን ለእናንተ ያቀረብንበት ምክንያት አብረን በመተባበር ትውልዱን ለመድረስ በፀሎት እንድትቆዩ እንድትደግፉን በሚል ቅን ልብ ነው። እኛ የምንታመነው ሁሉን በስልጣኑ እጅ በደገፈው እና ሐጢያታችንን በደሙ አንፅቶ በአብ ቀኝ በተቀመጠው በአንዱ ልጁ ባለ እምነት በኩል ነው። የእግዚአብሔር ቃል በመካከላችን ከፍተኛውን ስፍራ ሲይዝ የሐይላችን ምንጭ እየሆነ፥ እያሸነፈ፥ እየገዛም እና እየበዛም ይሄዳል!

በእርግጥም በማይመስል ሁኔታ ውስጥ እየተገኘ፤ በድንቅ እና በታዕምራት ከብዙ ሞት መከራ እያሳለፈ፥ ይሄው የጌታን እጅ እያየን እና ፍቅሩንም እያጣጣምን ስለሆነ ጌታዮን በእናንተ ፊት ከልቤ አመሰግናለሁ። እኔ እና ባለቤቴም ከወትሮ ዛሬ አይናችን ሁሉን በሚችል በልዑል እግዚአብሔር፥ በውድ ልጁም እና በመንፈስ ቅዱስ ላይ ሆነ ነፍሳችን አረፈች። እናንተም ሳትታክቱ ከጎናችን ሆናችሁ እየፀለያችሁ ለምትገኙ ወንድሞቼ እና እህቶቼ ጌታ ዘመናችሁን ይባርክ።

ባንዝልም በግዜው እናጭዳለን!

የበለጠ ለመረዳት ከታች ያለውን ቪዲዎ ይመልከቱ

ወንድማችሁ አዲ

Address

2088 South Vaughn Way, 304

80014

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when LUC / GHLU posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to LUC / GHLU:

  • Want your place of worship to be the top-listed Place Of Worship?

Share