12/15/2025
‼️ **አስቸኳይ የወንድማችንን አፋልጉን ጥሪ** ‼️
ስልክ ቁጥር፡ 👇
📞 **+251920256451 (ቤተሰቦቹ)**
‼️ **አስቸኳይ የወንድማችንን አፋልጉን ጥሪ** ‼️
**የህዝብና የመንግስት ትብብር እንሻለን!**
ውድ ቤተሰቦቻችን፣ ጓደኞቻችን እንዲሁም የሰው ሀዘን ሀዘናችሁ የሆነ ደግ ኢትዮጵያውያን በሙሉ፤ ወንድማችን **አቶ አደራጀው የሺዋስ (ኤዲ)** ይባላል። ትውልደ ኢትዮጵያዊ ሲሆን ዜግነቱ አሜሪካዊ ነው። ከመኖሪያ ቤቱ እንደወጣ እስካሁን አልተመለሰም።
እኛ ቤተሰቦቹ በራሳችን መንገድ ከመፈለግ ባሻገር፤ ጉዳዩን ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ማለትም ለአዲስ አበባ ፖሊስ እና ለፌዴራል ፖሊስ ያሳወቅን ሲሆን፤ በፌዴራል ፖሊስ የጠፉ ሰዎች ማፈላለጊያ መተግበሪያ (App) ላይ እንዲመዘገብና እንዲለጠፍ አድርገናል። **ከዚህ በተጨማሪም ጉዳዩን ለሚመለከተው የአሜሪካን ኢምባሲ በአካል እና በስልክ አመልክተናል።
ሆኖም ግን እስካሁን ድረስ ምንም አይነት ፍንጭ ልናገኝ አልቻልንም።
ስለሆነም ጉዳዩ አሳሳቢ በመሆኑ፤ መላው የኢትዮጵያ ህዝብና የጸጥታ አካላት ወንድማችንን እንድታፋልጉን በትህትና እንጠይቃለን። ከህዝብና ከመንግስት የሚደበቅ የለምና፤ እባካችሁ ያለበትን የምታውቁ ወይም የት እንደታየ ትንሽም ቢሆን ጥቆማ ወይም ፍንጭ ያላችሁ ከታች በተቀመጠው ስልክ በአስቸኳይ አሳውቁን። ለምታደርጉልን ትብብር ሁሉ በፈጣሪ ስም እናመሰግናለን!
ስልክ ቁጥር፡ 👇
📞 **+251920256451 (ቤተሰቦቹ)**