26/04/2026
በቀን 18/08/2018ዓ.ም በይርባ ቤቴል ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን እሁድ በመደበኛ ፕሮግራም ላይ የተማርነው የእግዚአብሔር ቃል:
🔶የዕለቱ አገልጋዮች
📖 #መልዕክት አቅራብ:-
#ወ/ዊ ጌቱ አማኑኤል
#በመዝሙር:- /መዘመራን
#ፓ/ር_ዘማሪ_ኤርምያስ_ጴጥሮስ
➥ፕሮግራምን በመምራት :- አቶ አምባይቸው አበበ
#የመልዕክቱ ርዕስ:- ስለ ክርስቶስ ዋጋ ለመክፈል መዘጋጀት።
👉መነሻ ጥቅስ፦ 1ጴጥ 4:12-19
#መግቢያ:-
ሐዋሪያ ጴጥሮስ የኢየሱስ ሐዋሪያት መካከል አንዱ ስሆን ይህን መጽሐፍ የፃፈውም እርሱ ነው። የተፃፈበትን ጊዜ በተመለከተ ከ65-67ዓ.ም ገደማ የተፃፈ እንደሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ታርካዊ ዳራው ያሳያል።
➥የመጽሐፉ ተቀባዮች ስለ ክርስቶስ መከራ እየተቀበሉ በተለያዩ ሀገራት ውስጥ ተሰዶ ለተበተኑት ነው።
➥የመጽሐፉ ዓላማው:- በልዩ ልዪ መከራና ስደት ውስጥ እንኳን ብሆኑ በተከተሉት እውነተኛ ሕይወት ወደኋላ እንዳይሉ ፣ በእምነታቸው እንድፀኑ ለማበረታታት።
በዚህ ክፍል ጴጥሮስ ከእርሱ ጋር የእግዚአብሔርን መንግስት ክብር ለመውረስ በክርስቶስ የተጠሩትን እስከ መጨረሻ ድረስ መሄድ እንድችሉ መመሪያ ይሰጣቸዋል።
ጴጥሮስ በዚህ ቦታ ስለ መከራ ፤ ስለ ፈተና ፣ ስለ ፍርድ ይናገራል። በዚህ ሕይወት ስታልፉ ለማንም ያልደረሰ አስጨናቅ ነገር እንደደረሰባችሁ አርጋችሁ አትደነቁ ብሎ ይመክራቸዋል።
📌ስለ መከራ፦ የክርስቶስን መከራ መካፈል (ስለ ኢየሱስ መከራን መቀበል) ክብሩን እንድንካፈልና በመጨረሻም የክርስቶስን ደስታ እንድንካፈል ያደርገናል። መከራውን ታግሶ የማይካፈል የመጨረሻውን ክብርና ደስታ ሊካፈል አይችልም።
✔ጌታችን ኢየሱስ በሥጋው መከራን እንደተቀበለ መጨረሻም እንደ አሸነፈ አሸናፊ ለመሆን መከራን መቀበልም እንዳለ ማወቅ ያስፈልገናል።ቁ.1
📌ስለ ፈተና ፦ ከእኛ በፊት ተፈትኖ ያለፈ የከበረ ጌታ አለን።
እግዚአብሔር ሰውን ይፈትናልን?
➥አዎ ግን በክፉ አይፈትንም ይልቁንስ ክብሩን ለመግለጥ ፣ እምነታችንን ለማጽናት እንደ አብርሃም ፣ እንደ ኢዮብ ለመልካም ይፈትናል። በእግዚአብሔር ተፈትኖ የሚሸነፍ ፣ የሚወድቅ የለም። ምክንያቱም በፈተና ጊዜ እርሱ አብሮት ሆኖ ስለምረዳው።
✔ስለ ፍርድ፦ 1) ከእርሱ ጋር መከራን ለምቀበሉት እና በልዩ ልዩ ፈተና ለሚያልፉት ክርስቶስ በጽድቅ ይፈርድላቸዋል። ከፍርዱ የተነሳ ይከብራሉ ይደሰታሉ።
2) ለወንጌል እውነት የማይታዘዙ እና ልባቸውን ላደነደኑ ዓመፀኞችና ኃጢአተኞች እርሱ በጽድቅ ስፈርድ መገኛቸው ያስፈራል። ለእነርሱ የፍርዱ ውጤት እጅግ አስፈር ይሆንባቸዋል።(ከቁ.17-18)
በዚህ ሁሉ ስናልፍ እንደ እሳት በሚያቃጥል መከራና ፈተና ውስጥ ብናልፍም የምረዳንና የሚያጸናን የእግዚአብሔር መንፈስ ስላለን አንጠፋም።
" ስለ ክርስቶስ ስም ብትነቀፉ የክብር መንፈስ የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ ላይ ያርፋልና ብፁዓን ናችሁ።"(ከቁ.14)
ስለዚህ እየተፈተንክም እየተጨነክም ስለ ክርስቶስ መከራን ተቀበል ትከብራለህና።