Dibiretea st. Joseph church

Dibiretea st. Joseph church God Is The Great Power Over The World

28/12/2020
ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ ሊቀጳጳሳት ዘካቶሊካውያንየ2012 ዓ.ም. ዐብይ ጾም መግቢያን አስመልክተው ያስተላለፉት ሐዋርያዊ መልእክት፦🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀💐🥀💐🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀ከሁሉ አስቀድሜ በሀገር ውስጥ...
27/02/2020

ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ ሊቀጳጳሳት ዘካቶሊካውያን
የ2012 ዓ.ም. ዐብይ ጾም መግቢያን አስመልክተው ያስተላለፉት ሐዋርያዊ መልእክት፦
🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀💐🥀💐🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀

ከሁሉ አስቀድሜ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገራት ለምትኖሩ ካቶሊካውያን ምእመናን እና በጎ ፈቃድ ላላችሁ ሁሉ እንኳን ለ2012 ዓ.ም. ዐብይ ጾም በሰላም አደረሳችሁ እያልኩ የተቀደሰ የተባረከ የጾም ጊዜ እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ፡፡
ዐብይ ጾም እግዚአብሔር ዘወትር ወደ እርሱ እንድንመለስ ለሚያቀርብልን ጥሪ በተዐቅቦ፣ በጸሎት እና በልግስና ምላሽ የምንሰጥበት እጅግ የተቀደሰ ወቅት ነው፡፡ ሁላችንም ኃጥያትን ሠርተናል፡፡ ኃጥያት በቤተሰባችን እና በማህበረሰባችን ውሰጥ ያስከተለውን መበታተንም
እንገነዘባለን፡፡ በኃጥያታችን ምክንያት ወደ ዓለም የገባውን ጥል፣ መለያየት እና ደም መፋሰስ አስቀርተን በይቅርታ፣ በዕርቅ፣ በፍቅር በመኖር የክርስትና ጉዟችንን የምንመሰክርበት እና ሀገራችን የምትገኝበትን ነባራዊ ሁኔታዎች ለመለወጥ የምንተጋበት ዕድል ይህ የዐብይ ጾም ነው፡፡
የጾም ወቅት የልብ መለወጥ ወቅት ነው፡፡ እግዚአብሔር ሕይወታችን ፍጹም እንዲለወጥ ይፈልጋል፡፡ በዐብይ ጾም በሥርዓተ ሊጡርጊያችን የምናነባቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ንባባት ሁላችንም ለቅድስና የተጠራን መሆኑን ያረጋግጡልናል፡፡ ለዚሕ በጎ የሕይወት ፍጻሜ እንድንተጋም
ያሳስቡናል፡፡ ወደ ቅድሰና በምናደርገው የጋራ ጉዞ ከእግዚአብሔር እና ከሰዎች ጋር ያለንን መልካም ግንኙነት በእግዚአብሔር ጸጋ በመመርመር ከኃጥያት ተመልሰን ሰላም እና ዕርቅን በማስፈን ለወንጌሉ ቃል ታማኝነታችንን ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው፡፡
ጾም ለክርሰቲያናዊ ቤተሰብ የተለየ ዕድልን ይዞ ይመጣል፡፡ ቤተሰብ ሰፊ ጊዜ አብሮ እንዲያሳልፍ፣ አብሮ እንዲጸልይ፣ እና ለልጆችም የመሥዋዕትነትን ትርጉም በተግባር እንድናስተምር ይረዳናል፡፡ ወላጆች ለልጆቻቸው መልካም ሥነምግባራትን በማስተማር፣ በቤት ውስጥ የተጣለባቸውን የኃላፊነት ድርሻ እንዲወጡ በማበረታታት፣ በዘመን አመጣሽ ቴክኖሎጂ በመጠመድ የሚያባክኑትን ጊዜ በአግባቡ
እነዲጠቀሙበት በመቆጣጠር፣ ሌሎችን እንዲንከባከቡ እና ያላቸውን ተካፍለው እንዲጠቀሙ በማለማመድ ይህንን ቅዱሰ ጊዜ በጋራ በማሳለፍ ልዩ በረከትን ያገኙበታል፡፡
ጾም ለብቻ ተዘግቶ በመቆዘም የምናሳለፈው ጊዜ አይደለም፡፡ ይልቁንም አገልግሎታችን እና እንክብካቤያችን ወደ ሚያስፈልጋቸው ለመድረስ ወደ ሌሎች የምንሄድበት፣ ለራሳችን ብቻ ከማሰብ ወጥተን በእግዚአብሔር ምህረት የተነሣ ያገኘነውን የመንፈስ እርካታ በዙሪያችን ወደ ሚኖሩ
ሰዎች የምናስተላልፍበት፣ የመቀራረብ፣ የመተሳሰብ፣ የመዋደድ እና እርስ በእርስ በይቅርታ የመጎበኛኘት ጊዜ ነው፡፡
ይህ ወቅት ደቀ መዛሙርት ለጌታ “እንዴት መጸለይ እንዳለብን አናውቅም፤ እባክህ አስተምረን?” በሚል ያቀረቡትን ጥያቄ ደግመን የምናቀርብበት ጊዜ ነው፡፡ በማይነገር መቃተት የሚማልድልን መንፈስ ቅዱስ ራሱ ድካማችንን ይሞላል (ሮሜ። 8፡26)፡፡ በዚህ በጾም ወቅት መሥዋዕተ ቅዳሴን፣ ምሥጢረ ንሰሃን እና ምሥጢረ ቁርባንን ማዘውተር ይገባናል፡፡ በየዕለቱም ከቅዱሰ ወንጌል እያነበብን በቤተሰብ መካከል የእግዚአብሔርን ቃል ማዳመጥ ጠቃሚ ነው፡፡ መዝሙረ ዳዊትን፣ የእመቤታችንን የመቁጠሪያ ጸሎት እና ውዳሴ ማርያምን መድገምም የበለጠ ወደ እግዚአብሔር እንድንቀርብ ይረዳናል፡፡
በየቁምስናችን በምናደርሳቸው የፍኖተ መስቀል ጸሎቶች የገዛ ራሳችንን መስቀል ከክርስቶስ መስቀል ጋር እናስታርቃለን፡፡ የኑሮ ውጣ ውረዶቻችንን

እንካን ለብርሀነ ጥምቀቱ በሰላም አደሳቹ "ጌታ ሆይ! ከዚህ በፊት በሆነው ፤ አሁንም እየሆነ ባለው እና ወደፊትም በሚሆነው ነገር ፤ ክብሩን ሁሉ አንተ ውሰድ ።" አሜን!    የተወደዳችሁ የ...
19/01/2020

እንካን ለብርሀነ ጥምቀቱ በሰላም አደሳቹ
"ጌታ ሆይ! ከዚህ በፊት በሆነው ፤ አሁንም እየሆነ ባለው እና ወደፊትም በሚሆነው ነገር ፤ ክብሩን ሁሉ አንተ ውሰድ ።" አሜን!

የተወደዳችሁ የጌታችን የመድሃኒታችን የክርስቶስ ኢየሱስ አፍቃሪዎች የእናቱ የቅድስት ድንግል ማርያም ወዳጆች/ልጆች፥ቤተሰቦች/ ሠላም ያዉላችሁ መልካም ዕለተ ሰንበት፡፡ ፡፡🌹✝🌹

Address

Dibrtea, Endibir, Wolikite
Wolkite
26

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dibiretea st. Joseph church posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share