ወልድያ መሠረተ ሕይወት ሰንበት ት/ቤት

ወልድያ መሠረተ ሕይወት ሰንበት ት/ቤት የወልድያ መንበረ ንግሥት ደብረ ገሊላ ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን

የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የዕርገት በዓል በደመቀ ኹኔታ ተከብሯል።ነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ/ም (መሠረተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት፤ ወልድያ)በየዓመቱ የሚከበረውና በክ...
22/08/2026

የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የዕርገት በዓል በደመቀ ኹኔታ ተከብሯል።

ነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ/ም (መሠረተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት፤ ወልድያ)

በየዓመቱ የሚከበረውና በክርስቲያኖች ዘንድ ተወዳጅ የኾነው የጾመ ፍልሰታ ወቅት ከነሐሴ 01-16 ቀን ድረስ በጾምና በጸሎት ሕጻናት ጭምር የሚያሳልፉት ኦርቶዶክሳዊ በዓል ነው።

በኹሉም አብያተክርስቲያናት ዘንድ የሚከበረው ይኽ ተወዳጅ በዓል በወልድያ መንበረ ንግሥት ደብረ ገሊላ ኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን ዛሬ ነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ/ም ተጠናቅቋል።

በዓሉ የተከበረው የእመቤታችንን ዕርገት በማሰብ እንደመኾኑ መጠን የርሷን በረከት ለመቀበል ከጾምና ጸሎት ጋር በቅዱስ ቍርባን ተወስነው ይኽን ኹለት ሱባኤ ያሳለፉ ኦርቶዶክሳውያን ጥቂት የማይባሉ ናቸው።

የሰሜን ወሎ ሀገረስብከትና የወልድያ ከተማ አስተዳደር ቤተክህነት የሥራ ክፍል ኀላፊዎችና ሠራተኞች፣ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፣ የደብሩ አገልጋዮችና ልዩ ልዩ ሠራተኞች፣ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላትና ምእመናን/ት በተገኙበት ታቦተ ሕጉ ሥርዐተ ዑደቱን ጨርሶ በአባቶች ጸሎት ተጠናቅቋል።

መልካም በዓል ይኹንልን!

!
ርስዎም ቤተሰብ ይኹኑ!
and በማድረግ፥ አገልግሎታችንን ያግዙ!
~ YouTube፡ http://www.youtube.com/
~ Facebook፡ https://www.facebook.com/MesereteHiwotSS
~ Instagram፡ https://instagram.com/woldiamhss
~ Telegram፡ https://t.me/MesereteHiwotSS
~ TikTok፡ https://www.tiktok.com/
~ Twitter፡ https://twitter.com/WoldiaMHss

እንኳን ለእመቤታችን የዕርገት በዓል አደረሳችሁ!🙏የቅዳሴው መርሐግብር ተጠናቅቆ የትምህርትና ልዩ ልዩ መርሐግብሮች እየቀጠሉ ነው።መልካም በዓል ይኹንልን! !ርስዎም ቤተሰብ ይኹኑ!  and   ...
22/08/2026

እንኳን ለእመቤታችን የዕርገት በዓል አደረሳችሁ!🙏

የቅዳሴው መርሐግብር ተጠናቅቆ የትምህርትና ልዩ ልዩ መርሐግብሮች እየቀጠሉ ነው።

መልካም በዓል ይኹንልን!

!
ርስዎም ቤተሰብ ይኹኑ!
and በማድረግ፥ አገልግሎታችንን ያግዙ!
~ YouTube፡ http://www.youtube.com/
~ Facebook፡ https://www.facebook.com/MesereteHiwotSS
~ Instagram፡ https://instagram.com/woldiamhss
~ Telegram፡ https://t.me/MesereteHiwotSS
~ TikTok፡ https://www.tiktok.com/
~ Twitter፡ https://twitter.com/WoldiaMHss

21/08/2026

የደብራችን የቅኔ መምህር የኔታ መርዓዊ ብርሃን የነሐሴ ኪዳነምሕረት (የፍልሰታ ለማርያም) የማኅሌት አገልግሎት ላይ ያቀረቡት ቅኔ በከፊል

ነሐሴ 16/2018 ዓ/ም

የመንፈሳዊ ጉባኤ ጥሪእንኳን አደረሳችሁ እያልን በወልድያ መንበረ ንግሥት ደብረ ገሊላ ኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን ከነሐሴ 15-17/2018 ዓ/ም መንፈሳዊ ጉባኤ ተዘጋጅቷል። በጉባኤው ተገኝተው...
20/08/2026

የመንፈሳዊ ጉባኤ ጥሪ

እንኳን አደረሳችሁ እያልን በወልድያ መንበረ ንግሥት ደብረ ገሊላ ኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን ከነሐሴ 15-17/2018 ዓ/ም መንፈሳዊ ጉባኤ ተዘጋጅቷል። በጉባኤው ተገኝተው ቃለ እግዚአብሔርን እየተመገቡ ይቀደሱ!

!
ርስዎም ቤተሰብ ይኹኑ!
and በማድረግ፥ አገልግሎታችንን ያግዙ!
~ YouTube፡ http://www.youtube.com/
~ Facebook፡ https://www.facebook.com/MesereteHiwotSS
~ Instagram፡ https://instagram.com/woldiamhss
~ Telegram፡ https://t.me/MesereteHiwotSS
~ TikTok፡ https://www.tiktok.com/
~ Twitter፡ https://twitter.com/WoldiaMHss

19/08/2026

የብርሃነ መለኮቱ (ቡሄ) ታላቅ በዓል በልዩ የ2ወር የክረምት ተማሪዎች በድምቀት ተከብሮ ዋለ(ነሐሴ 13/12/2018ዓ.ም ወልድያ መሠረተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት) ፦  ​በጌታችን በወልደ አምላክ ...
19/08/2026

የብርሃነ መለኮቱ (ቡሄ) ታላቅ በዓል በልዩ የ2ወር የክረምት ተማሪዎች በድምቀት ተከብሮ ዋለ
(ነሐሴ 13/12/2018ዓ.ም ወልድያ መሠረተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት) ፦

​በጌታችን በወልደ አምላክ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበትንና ክብረ መንግሥቱን ያሳየበትን ታላቁን የደብረ ታቦር (ቡሄ) በዓል ምክንያት በማድረግ፣ የክረምት ልዩ የመሠረተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ህፃናት ተማሪዎቻችን የተሳተፉበት እጅግ ድንቅና መንፈሳዊ ስሜትን የሚቀሰቅስ ልዩ መርሃ ግብር በተሳካ ሁኔታ ተካሂዷል። ይህ መርሃ ግብር የሁለት ወር የክረምት ስልጠና አካል እንደመሆኑ መጠን፣ ህፃናቱ ሃይማኖታዊ እውቀትንና ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባርን በተግባር እንዲለማመዱ፣ የቤተክርስቲያንን አስተምህሮ በጥልቀት እንዲረዱና በበዓሉ ምስጢራዊ ትርጉም ላይ ግንዛቤ እንዲያገኙ ታስቦ የተዘጋጀ ነው። ህፃናቱ የበዓሉን ምሳሌያዊና ታሪካዊ ትርጉም በሚገልጽ መልኩ በገዛ እጃቸውና በቤታቸው ያዘጋጁትን ሙልሙል ዳቦና የብርሃን ምሳሌ የሆነውን ችቦ ሰርተው በማምጣት የመርሃ ግብሩ ድምቀት የሆኑ ሲሆን፣ ዕለቱንም ሙሉ በተለያዩ ስነ-ጽሁፎች፣ መንፈሳዊ መልእክት ባላቸው ድራማዎች፣ በሚያነቃቁ ትምህርቶች እንዲሁም ልብን በሚነኩ የምስጋና ዝማሬዎች ታጅበው አሳልፈውታል።
በዚህም አማካኝነት ህፃናቱ የእለቱን ታሪካዊነትና ምሳሌያዊ ትርጉሞች በጥልቀት የተረዱ ሲሆን፣ በለጋ አእምሮአቸው ላይ መልካም፣ በጎና የተቀደሰ አስተሳሰብ እንዲቀረፅ ተደርጓል። ህፃናቱ በዝግጅቱ ወቅት በነበራቸው ንቁ ተሳትፎ፣ በዝማሬዎቻቸውና በእልልታቸው የከንፈራቸውን መስዋዕት ያቀረቡ ሲሆን፣ የቤተክርስቲያኗን አስተምህሮ ሰምተው፣ ፈጣሪያቸውን አመስግነውና ዘምረው፣ ጥበብና እውቀትን ጨብጠው በመጨረሻም በታላቅ ደስታና በጥሩ ስሜት ተሞልተው ወደየቤታቸው በጸሎተሸኝተዋል። ይህም በእውነትም በሰንበት ትምህርት ቤታችንም ሆነ በህፃናቱ ህይወት ውስጥ ትልቅ ታሪካዊና መንፈሳዊ አሻራን ያሳረፈ፣ የወደፊት መልካም ዜጎችንና አገልጋዮችን ለማፍራት የተደረገ ስኬታማ መርሃ ግብር ነበር።

!
ርስዎም ቤተሰብ ይኹኑ!
and በማድረግ፥ አገልግሎታችንን ያግዙ!
~ YouTube፡ http://www.youtube.com/
~ Facebook፡ https://www.facebook.com/MesereteHiwotSS
~ Instagram፡ https://instagram.com/woldiamhss
~ Telegram፡ https://t.me/MesereteHiwotSS
~ TikTok፡ https://www.tiktok.com/
~ Twitter፡ https://twitter.com/WoldiaMHs

16/08/2026
  - ጾመ ፍልሰታን ከእኛጋ ያሳልፉ። (የወልድያ መሠረተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት)~   (1ተሰ 5፥17)።እንኳን ለጾመ ፍልሰታ አደረሳችሁ እያልን ከዐርብ ነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ/ም ሠ...
05/08/2026

- ጾመ ፍልሰታን ከእኛጋ ያሳልፉ። (የወልድያ መሠረተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት)

~ (1ተሰ 5፥17)።

እንኳን ለጾመ ፍልሰታ አደረሳችሁ እያልን ከዐርብ ነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ/ም ሠርክ (ማታ) 11፡00 ጀምሮ ሰንበት ትምህርት ቤታችን ባዘጋጀው የጸሎት መርሐግብር በሰንበት ትምህርት ቤቱ የስብከተ ወንጌል አዳራሽ ተገኝተው ከእግዚአብሔር ጋር በጸሎት ይነጋገሩ ዘንድ ተጋብዘዋል፤ ይኽን መንፈሳዊ ግብዣ ለሌሎችም በማጋራትም ይሳተፉ።

መልካም ጾመ ፍልሰታና ሱባኤ ይኹንልን!🙏

!
ርስዎም ቤተሰብ ይኹኑ!
and በማድረግ፥ አገልግሎታችንን ያግዙ!
~ YouTube፡ http://www.youtube.com/
~ Facebook፡ https://www.facebook.com/MesereteHiwotSS
~ Instagram፡ https://instagram.com/woldiamhss
~ Telegram፡ https://t.me/MesereteHiwotSS
~ TikTok፡ https://www.tiktok.com/
~ Twitter፡ https://twitter.com/WoldiaMHss

የመሠረተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት የበጀት ዓመቱን የአገልግሎት እቅድ አፈጻጸም ዛሬ ገምግሟል።ሐምሌ 26 ቀን 2018 ዓ/ም (መሠረተ ሕይወት ሰንበት ት/ቤት፤ ወልድያ)በኢትዮጵያ ኦርቶዶክ...
02/08/2026

የመሠረተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት የበጀት ዓመቱን የአገልግሎት እቅድ አፈጻጸም ዛሬ ገምግሟል።

ሐምሌ 26 ቀን 2018 ዓ/ም (መሠረተ ሕይወት ሰንበት ት/ቤት፤ ወልድያ)

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሰሜን ወሎ መንበረ ጵጵስና ሀገረስብከት በወልድያ ከተማ አስተዳደር ቤተክህነት በመንበረ ንግሥት ደብረ ገሊላ ኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን የመሠረተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት የበጀት ዓመቱን የአገልግሎት እቅድ አፈጻጸም በተመለከተ ዛሬ በሰንበት ትምህርት ቤቱ የስብከተ ወንጌል አዳራሽ ገምግሟል።

በ2018 በጀት ዓመት ሊሠሩ የሚገባቸውን ተግባራት በመለየት ዓለም ዐቀፍ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የላከውን የ5 ዓመታት ሥልታዊ እቅድ መሠረት በማድረግ እንደ ሰንበት ትምህርት ቤቱ ነባራዊ ኹኔታ በመቃኘት ዓመታዊ እቅዱን አቅዶ ወደ ተግባር የገባው የወልድያ መሠረተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት፥ በመልካም ውጤት የተተገበሩና ያጋጠሙ ችግሮችን በመጠቆም የተወሰዱ የመፍትሔ ርምጃዎችን በግምገማው አንሥቷል።

እንደ ደብሩ ሰበካ ጉባኤና ስብከተ ወንጌል ክፍል፣ እንደ ሰንበት ት/ቤቱ ሥራ አስፈጻሚ ጉባኤና እንደ አባላት የታዩ ጥንካሬዎችና ድክመቶች ሰንበት ትምህርት ቤቱ ባቀረበው የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ ላይ ተመላክቷል።

በሰንበት ትምህርት ቤቱ ጸሓፊ በወንድማችን ዐዲሱ ኀይሌ በኩል ሥራ አስፈጻሚ ጉባኤው ያቀረበውን የአገልግሎት እቅድ አፈጻጸም ያደመጠው የጠቅላላ ጉባኤም መልካም ተግባራትን በማውሳት ያጋጠሙ ችግሮችን በመቀነስ ለቀጣይ የአገልግሎት ርምጃ ገንቢ ይኾናሉ ያላቸውን ሐሳቦችን አቅርቧል።

ሊመለሱና ሊነሡ የሚገባቸው ጥያቄዎችና ሐሳቦችም በክፍል ተጠሪዎች በኩል ቀርበው የሚወሰዱ ሐሳቦችን በመውሰድ ለጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።

የደብሩን ሰበካ ጉባኤ ወክለው የተገኙት የሰበካ ጉባኤው ጸሓፊና ቍጥጥር አቶ አለበል ደምሌ ተገኝተው የቀረበውን የአገልግሎት እቅድ አፈጻጸም ካደመጡ በኋላ መልካም አገልግሎቶችን በማድነቅ ለቀጣይ መፍትሔ ይኾናሉ ያሏቸውን ሐሳቦች አቅርበዋል።

ሰበካ ጉባኤው በደብሩ ያሉ መዋቅሮችን በቻለው ዐቅም እየደገፈ ነው ያሉት አቶ አለበል ደምሌ፥ ሰንበት ትምህርት ቤቱ ትውልድ ላይ እየሠራ ያለውን አገልግሎት ሰበካ ጉባኤው በበጀት ዓመቱ ካደረገው እገዛ በላይ በሚቀጥለው በጀት ዓመትም በባለቤትነት ሰንበት ትምህርት ቤቱን እንደሚያግዝ አስረድተዋል።

በመጨረሻም በሰንበት ትምህርት ቤቱ ምክትል ሰብሳቢ ወንድማችን ዮናታን ታደሰ የማጠቃለያ ሐሳብ ቀርቦ የእቅድ አፈጻጸም ግምገማው በጸሎት ተጠናቅቋል።

!
ርስዎም ቤተሰብ ይኹኑ!
and በማድረግ፥ አገልግሎታችንን ያግዙ!
~ YouTube፡ http://www.youtube.com/
~ Facebook፡ https://www.facebook.com/MesereteHiwotSS
~ Instagram፡ https://instagram.com/woldiamhss
~ Telegram፡ https://t.me/MesereteHiwotSS
~ TikTok፡ https://www.tiktok.com/
~ Twitter፡ https://twitter.com/WoldiaMHss

Address

Woldiya Menbere Nigist Debre Gelila Kidane Mihret Church
Woldia
251

Telephone

+251996423219

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ወልድያ መሠረተ ሕይወት ሰንበት ት/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to ወልድያ መሠረተ ሕይወት ሰንበት ት/ቤት:

Shortcuts

Share