08/03/2026
"መልካሙን ገድል ተጋድያለሁ፥ ሩጫውን ጨርሻለሁ፥ ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ፤ ወደፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል።" (፪ኛ ጢሞ. ፬፡፯)
ለዘመናት ያለመታከት የእግዚአብሔርን መንግሥት ወንጌል ሲሰብኩ፣ የታወከውን ልብ በቃለ እግዚአብሔር ሲያረጋጉ፣ የጠፋውን ሲፈልጉና ቅድስት ቤተክርስቲያንን በቅንነትና በታማኝነት እንዲሁም በትጋት ሲያገለግሉ የኖሩት ታላቁ የወንጌል አርበኛ መምህር ዘለዓለም ወንድሙ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።
መምህር ዘለዓለም ለብዙዎቻችን የመንፈስ አባት፣ ለምእመናን ብርታት፣ ለወጣቶች ደግሞ አርአያ በመሆን የክርስትናን ሕይወት በተግባር ያስተማሩ የቤተክርስቲያናችን ብርሃን ነበሩ።
ዛሬ ነፍሳቸው ወደ አምላኳ ብትሄድም በአካለ ስጋም ከኛ ቢለዩብም፣ የዘሩት የወንጌል ዘር ግን በትውልድ ልብ ውስጥ ሲያፈራ ሲያብብ እንደኖረ አሁንም ለዘላለም ፍሬ ሲያፈራ ይኖራል።
ቀንዲል ሚዲያ በዚህ መሪር ሀዘን ወቅት፦
ለቅድስት ቤተክርስቲያን
ለተማሪዎቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው
እንዲሁም ለቤተሰቦቻቸው በሙሉ መጽናናትን እንዲሰጠን የእርሳቸውንም ነፍስ በገነት በቅዱሳኑ ዕቅፍ ዘንድ እንዲያስርፍልን የልብ ጸሎታችን ነው💔 ነፍስ ይማርልን💔
የተወሰደ