ሳሌም ሚዲያ የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሚዲያ/Salem Gurage Diocese Media

  • Home
  • Ethiopia
  • Welk'it'e
  • ሳሌም ሚዲያ የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሚዲያ/Salem Gurage Diocese Media

ሳሌም ሚዲያ የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሚዲያ/Salem Gurage Diocese Media ይህ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሳሌም የጉራጌ ሀገረ ስብከት የፌስቡክ ገጽ ነው።

፪ ቀን ቀረው
12/08/2026

፪ ቀን ቀረው

08/08/2026

ልዩ መንፈሳዊ ጉባኤ በወልቂጤ ደብረ ታቦር እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን
ከነሐሴ 8-10

‎በጉራጌ ሀገረ ስብከት የ5ኛው ዙር የክረምት ተተኪ መምህራን ሥልጠና ዛሬ ተጀመረ‎ነሐሴ ፩ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም‎በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጉራጌ ሀገረ ስብከት በብጹዕ አቡ...
07/08/2026

‎በጉራጌ ሀገረ ስብከት የ5ኛው ዙር የክረምት ተተኪ መምህራን ሥልጠና ዛሬ ተጀመረ

ነሐሴ ፩ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም

‎በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጉራጌ ሀገረ ስብከት በብጹዕ አቡነ መልከጼዴቅ መመሪያ ሰጪነት እና በሀገረ ስብከቱ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ዋና ክፍል አስተባባሪነት የተዘጋጀው 5ኛው ዙር የክረምት ተተኪ መምህራን ሥልጠና ዛሬ ተጀምሯል።

‎በዚህ ሥልጠና ላይ ከሁሉም ወረዳ ቤተክህነት የተመለመሉ በሰንበት ትምህርት ቤት አገልግሎት ንቁ ተሳትፎ ያላቸው በርካታ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ተገኝተዋል።

‎የዚህ ሥልጠና ዋና ዓላማ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ተዘጋጅቶ የወረደውን ከ1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያለውን የሰንበት ትምህርት ቤት አዲሱን ሥርዓተ ትምህርት በተግባር ለማስተግበርና መምህራኑን በብቃት ለማዘጋጀት እንደሆነ ተገልጿል። ሠልጣኞቹ በሥልጠና ቆይታቸው የሥርዓተ ትምህርቱ መጽሐፍት ላይ ይዘት ላይ ዳሰሳ የሚደረግ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ ሠልጣኞች የተግባር ትምህርቶችን የሚወስዱ ይሆናል።

‎በማስጀመሪያው መርሃ ግብር ላይ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መጋቤ ጥበብ ታምሩ አበራና የመንፈሳዊ ዘርፍ ሓላፊ ሊቀ ኅሩያን መሠረት ዳኘው ተገኝተው «ዘመኑን እየዋጃችሁ በጥበብ ተመላለሱ» በሚል መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሪ ቃል ለሠልጣኞች መንፈሳዊ መልዕክት አስተላልፈዋል።

‎በተጨማሪም የጉራጌ ሀገረ ስብከት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ዋና ክፍል ኃላፊ መጋቤ ሃይማኖት ብሥራት ገብረ ሥላሴ የሠልጣኞችን የቆይታ ጊዜና የሥልጠናውን ዝርዝር ሂደት አስመልከተው ማብራሪያ ሰጥተዋል።

‎በዚህ የማስጀመሪያ መርሐ ግብር ላይ የሀገረ ስብከቱ ልዩ ልዩ የሥራ ኃላፊዎች፣ የመንበረ ጵጵስና ወረዳ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የክፍል ሓላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት።«በዚያን ጊዜ እኔ ዳንኤል ሦስት ሱባኤ ሁሉ ሳዝን ነበርኩ» (ዳን 10፥2)​በጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም ሰላምና ፍቅር...
06/08/2026

የብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት።

«በዚያን ጊዜ እኔ ዳንኤል ሦስት ሱባኤ ሁሉ ሳዝን ነበርኩ» (ዳን 10፥2)

​በጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም ሰላምና ፍቅር የተወደዳችሁ ኦርቶዶክሳውያን ካህናትና ምዕመናን ​በቅዱሳን አባቶቻችን ሐዋርያት ቀኖና መሠረት ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዕረፍት፣ ትንሣኤና ዕርገት መታሰቢያ ለሆነው ለዚህ ለተቀደሰ የፍልሰታ ጾምና የተቀደሰ አገልግሎት ሱባኤ እንኳን በሰላም አደረሳችሁ!

​በየዓመቱ ከነሐሴ 1 እስከ ነሐሴ 14 ባሉት ቀናት ሁለት ሱባኤዎች ይገኛሉ። ሱባኤ ማለት ፍጹም ቁጥር የሆነው የሰባት ቁጥር ብዜት ማለት ነው። እነዚህ የሱባኤ ቀናት በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ቀኖና መሠረት ጾም የምንጾምባቸውና ለሃይማኖት አብልጠን የምንገዛባቸው ቀናት ናቸው።

​በእነዚህ የሱባኤ ቀናት ራሳችንን ከዓለም ሁከትና ግርግር ነፃ በማድረግ፤ በጾም፣ በጸሎት፣ በምስጋና፣ በስግደት፣ ራስን በመግዛት እና ጊዜን ለመንፈሳዊ አገልግሎት በመስጠት መንፈሳዊ ኃይል የምንመላበት የተቀደሰ ጊዜ መሆኑን መገንዘብ ይጠበቅብናል። ባለፈው ጊዜ በሠራነው ኃጢአት በመጸጸትና ለመጪው ጊዜ ደኅንነታችን በመጸለይ የሱባኤን ወቅት ማሳለፍ ከመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን የተገኘ ቅዱስ ትውፊት ነው። አርቆ አሳቢ በመሆን ከራስና ከቤተሰብ ጀምሮ ለመላው ዓለም በሰላም መጠበቅ በጸሎታችን ፈጣሪአችንን ማሳሰብ የሱባኤ ወቅት ተጠባቂ አገልግሎት ነው። ​ነቢዩ ዳንኤል "ሦስት ሱባኤ ሙሉ ሳዝን ነበርሁ” ብሎ ሱባኤንና ሥርዓቱን እንዳስተማረን።

​ስለሆነም የተወደዳችሁ የመንፈስ ልጆቻችን ኦርቶዶክሳውያን፤ ​የዚህ የተቀደሰ ወቅት ባለቤት የሆነው እግዚአብሔር አምላካችን ጾማችንንና ጸሎታችንን ይቀበል፤ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም እናትነት፣ አማላጅነትና በረከት አይለየን። በዚሁ በሱባኤያችን ወቅት የምናቀርበው ልመናና ምልጃ፣ የምንጾመው ጾም፣ ለምስኪኖች የምንዘረጋው የምጽዋት እጅ ሁሉ በልዑል እግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት አግኝቶ ለሀገራችን ዘላቂ ሰላምን፣ ለሕዝባችን ፍቅርንና አንድነትን፣ ለነፍሳችን ደግሞ የዘላለም ድኅነትን የሚያስገኝ ያድርግልን።

አባ መልከጼዴቅ የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
ሐምሌ ፴ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም

“መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ"በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሓዱ አምላክ፣ አሜን !በሀገር ውስጥና በመላው ዓለም የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች ...
06/08/2026

“መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ"
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሓዱ አምላክ፣ አሜን !

በሀገር ውስጥና በመላው ዓለም የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች በሙሉ!

የሰውን ወገን ለማዳን የልጁ ማደሪያ ትሆን ዘንድ ድንግል ማርያምን የመረጠ መፍቀሬ ሰብእ እግዚአብሔር ኣምላካችን እንኳን ለሁለት ሺሕ ዓሥራ ስምንት ዓመተ ምሕረት ጾመ ማርያም ኣደረሰን ኣደረሳችሁ!
“ወእመሰ ታፈቅሩኒ ዕቀቡ ትእዛዝየ፡- ከወደዳችሁኝስ ትእዛዜን ጠብቁ" (ዮሐ.14፥15)፤
ፍቅር የሕያዋን ኣካላት ረቂቅ መገናኛ ነው፣ ሕያዋን ኣካላት በውጫዊው ግዙፍ ኣካላቸው በተወሰኑ ጊዜያትና ቦታ ይገናኛሉ ፤ ስለ ጋራ ጉዳያቸውም በጋራ ይመክራሉ፤ ይበልጥም ይቀራረባሉ፡፡

ይሁንና የሕያዋን ኣካላት ግንኙነት በኣካል በጊዜና በቦታ ብቻ የተወሰነ ኣይደለም፣ በፍቅረ መንፈስ ተገናኝተውም ይግባባሉ፣ ከኣካላዊ ግንኙነት በላይ የበለጠም ይኸው ፍቅረ መንፈስ ነው፤ ከዚህ ኣንጻር እግዚአብሔርንም ማግኘት የምንችለው በዚሁ ፍቅረ መንፈስ ሆነን በእምነት ዓይን ነው!

ይህም በመሆኑ ሓዋርያው ቅዱስ ዮሓንስ በመልእክቱ “በፍቅር የሚኖር በእግዚአብሔርይኖራል፣ እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል" በማለት ያስተምረናል፣ (1ዮሐ. 4፥16) ይህም ማለት ከሱ ጋር በፍቅር ስንገናኝ፤ እሱም በኛ፣ እኛም በእሱ የመኖሩ ኩነት ይፈጠራል ማለት ነው፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!

ጌታችን “አፍቅሮ ለእግዚአብሔር ኣምላክከ፤- አምላክህን እግዚአብሔርን ውደደው" በማለት በፍጹም ልባችን እንድንወደው፣ እንደዚሁም ራሳችንን በምንወድበት መጠን እርስ በእርሳችን እንድንዋደድ ማዘዙን እናውቃለን፤

የመውደዳችን መለኪያ ሚዛንና መገለጫ ምልክትም ትእዛዙን ማክበርና መጠበቅ እንደሆነ “ብትወዱኝስ ትእዛዜን ጠብቁ” በማለት ኣስተምሮናል
ከዚህ ኣኳያ ጌታን መውደድ ማለት ትእዛዙን በመጠበቅ የሚገለጽ ግዙፍ ነገር እንጂ ምናባዊና የማይታይ ድብብቆሽ ነገር ኣይደለም ማለት ነው፣

ጌታችንን የመውደድ ነገር ትእዛዙን በመጠበቅ የሚገለጽ ከሆነ ትእዛዙ ምንድን ነው? የሚለውን ማየት ኣስፈላጊ ይሆናል፤ ትእዛዙን በጥቅል ስናይ እግዚአብሔርንና ባልንጀራን በመውደድ እንደሚጠቃለል ራሱ ጌታችን ኣስገንዝቦናል፣

በተለይም በባልንጀራችን ላይ የምንከተለው መውደድ ከላይ እንደተገለጸው “እንደራስህ ኣድርገህ ውደድ" ተብለ በግልጽ ተቀምጦኣል፤
የሰው ባልንጀራ እነማን ናቸው? በሕይወት ያሉት ናቸው? ወይስ የሞቱት? ወገን ዘመድ? ወይስ የሰው ወገን በሙሉ የሚለውንም ማወቅ ኣስፈላጊ ነው፡፡

ጌታችን ነገሩን በዚህ ደረጃ ለያይቶ ኣላስቀመጠም፣ ለምን? ቢባል ባልንጀራ ማለት የተወሰነን የማኅበረ ሰብ ወገን የሚያሳይ ሳይሆን መላውን የሰው ወገን የሚገልጽ በመሆኑ፤ እንደዚሁም የሞቱም ሆኑ ያለነው ሁላችን በእሱ ፊት ሕያዋንና እርስ በእርሳችን ባልንጀሮች በመሆናችን ነው፤

በመሆኑም መዋደዳችንም ሆነ መከባበራችን በሕይወተ ሥጋ ሳለን ብቻ ሳይሆን ከዚያም በኋላ እስከ በሌለው ዕድሜ በመሆኑ ጌታችን በጊዜ በቦታና በከፊል ለይቶ ኣላስቀመጠም፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት !

ከነሐሴ ፩ ቀን ጀምሮ ለ፲፭ ቀናት የምንጾመው የጾመ ማርያም መነሻ ምክንያቱ የእግዚአብሔርትእዛዝና ፍቅር ነው፣

እግዚአብሔር ሰውን በኣጠቃላይ በተለይም ደግሞ እንደፈቃዱ የኖሩ ቅዱሳንን እንድናከብርኣዞናል ክቅዱሳን ፍጥረታት መካክል ደግሞ ቅድስት ድንግል ማርያም የመጀመሪያውን ደረጃ ትይዛለች፤

ይህም በመሆኑ ከፍጥረት ወገን ከሏ ክብር የሚደርስ ባለመኖሩ ከሁሉም ኣብልጠን እናክብራታለን፤

ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዚህ ደረጃ የድንግል ማርያምን ክብር ስትገልጽ ክእግዚአብሔርና ለባስያነ እግዚአብሔር ክሆኑ ቀደምት ኣበው ተምራ ነው!

በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረው ዕውቁ ቅዱስና ዓለም ዓቀፋዊው አባት ቅዱስ ኤፍሬም የድንግል ማርያምን ክብር! ቅድስና እና ልዕልና ሲናገር “ይእቲ ተዓቢ እምኪሩቤል፡ ወትፈደፍድ እምሱራፌል፣ እስመ ኮነት ታቦተ ለአሓዱ ዘእምቅድስት ሥላሴ- እሷ ከኪሩቤል ትበልጣለች! ከሱራፌልም ትልቃለች፣ ከቅድስት ሥላሴ ኣንዱ ለሆነው ታቦት ወይም ማደሪያ ሆናለችና" በማለት አስተምሮናል፡፡

በመሆኑም ለስሟ መታሰቢያ በሆነው በዚህ ጾም ድንግል ማርያምን በዚህ ደረጃ ስናክብርትእዛዙን እንጠብቃለን፤ ትእዛዙን በመጠበቃችን ደግሞ እሱን መውደዳችንን እናረጋግጣለን ! እኛ ድንግል ማርያምን እንድንወዳት "እናታችሁ'' ብሎ እንዳዘዘ፣ እሷም ልትወደን “ልጆችዅ ተብላ ታዛለችና ስለኛ ትጸልያለች፡፡

በጸሎቷም ከመከራ ትታደገናለች፤ በኣጠቃላይ በእግዚአብሔር' በቅዱሳንና በእኛ መካከል ያለው ግንኙነት በዚህ ትእዛዝና ፍቅር በትዕይንተ ዓለም ባለች ቤተ ክርስቲያን ዘንድ የተሳሰረ ነው፡፡

ስለሆነም በዚህ የጾመ ፍልሰታ ለማርያም ሱባዔ የተራቡትን በመመገብ፣ የታረዙትን በማልበስ፣ የተጣሎትን በማስታረቅ፤ የታመሙትንና የታስሩትን በመጠየቅ፤ ቅዱስ ቍርባንን በመቀበልና ለኃጢኣታችን የንሥሐ ሥርየትን በመለመን ሱባዔውን ልናሳልፍ ይገባል፡፡

በመጨረሻም

በሀገራችንም ሆነ በዓለም ዙሪያ ከባድ ስጋት የሆነው የፍጥረት ኣውዳሚ ጦርነትን በመለኮታዊ ጥበቡና ሥልጣኑ እንዲያስቆምልን በቅን ልቡና፤ በትሑት ሰብእና ሆነን እግዚአብሔርን በዚህ ሱባዔ እንድንጠይቀው ኣደራ ጭምር ኣባታዊ መልክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፤

የተባረከና የተቀደስ ጾም ያድርግልን፤

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፣ አሜን!

አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእስ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘኣኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

ነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ
© የኢኦተቤክ መገናኛ ብዙኀን

ለጾመ ፍልሰታ በሁሉም የሀገረ ስብከቱ አድባራት የሚፈጸም የአገልግሎት መርሐ ግብር።
05/08/2026

ለጾመ ፍልሰታ በሁሉም የሀገረ ስብከቱ አድባራት የሚፈጸም የአገልግሎት መርሐ ግብር።

ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በብፅዓት ለቤተ ክርስቲያን ለተሰጠው ሕፃን ጸሎት አደረጉ። ሐምሌ ፳፰ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም​በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ረጅም ዘመናት ታሪክ ውስጥ የልጆ...
05/08/2026

ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በብፅዓት ለቤተ ክርስቲያን ለተሰጠው ሕፃን ጸሎት አደረጉ።

ሐምሌ ፳፰ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም

​በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ረጅም ዘመናት ታሪክ ውስጥ የልጆችን ሕይወት ለፈጣሪ አገልግሎት በብፅዓት (በስእለት) መስጠት ጥልቅ መንፈሳዊ ትርጉም ያለውና የቤተሰብን አጽንኦተ ሃይማኖት የሚያሳይ ታላቅ ማዕረግ ነው። በአትርፎ ደብረ ወርቅ የተከናወነው ድንቅ ክስተትም የዚሁ መንፈሳዊ ተግባር ሕያው ማረጋገጫ ሆኗል።

​ዕድሜው ገና 12 ዓመት የሆነው ሕፃን በቤተሰቦቹ አማካኝነት ለአትርፎ ደብረ ወርቅ ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል በብፅዓት የተሰጠ ሲሆን፣ ይህንኑ አጋጣሚ አስመልክቶ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ለሕፃኑ ልዩ ጸሎት አድርገውለታል። ብፁዕነታቸው ሕፃኑን በባረኩበት ወቅት የቤተሰቦቹን ታላቅ እምነትና የሕፃኑን ብሩህ ተስፋ በሚገልጽ መልኩ የሚከተለውን አባታዊና ትንቢታዊ ቃል አስተላልፈዋል፡

​አንተ እድለኛ ነህ፤ ቤተሰቦችህም የታደሉ ናቸው። ይህም የሚደንቅ ሃይማኖት እንዳላቸው ያመላክታል። ጎብዘህ ትምህርትን ተምረህ ትልቅ የእግዚአብሔር አገልጋይ ትሆናለህ! ብለዋል።

​ይህ የቡራኬ ቃል የሕፃኑን የወደፊት መንፈሳዊና ትምህርታዊ ሕይወት መመሪያ የሚቀይስ ከመሆኑም በላይ፣ በዛሬው ዘመን እጅግ አልፎ አልፎ የሚታየውን የቤተሰቦች ጥልቅ እምነት ያደነቀ አባታዊ ምስክርነት ነው።

​ብፁዕነታቸው ለሕፃኑ ያደረጉትን ጸሎትና ቡራኬ ተከትሎ፣ የካቴድራሉ አስተዳዳሪ ሕፃኑን እንዲጠብቁ፣ የትምህርትና የመንፈሳዊ እድገት ፍላጎቶቹን እንዲያሟሉለት፣ እንዲሁም የሚያስፈልገውን እንክብካቤ ሁሉ እንዲያደርጉለት መመሪያ ሰጥተዋል።

​ይህ መመሪያ ቤተ ክርስቲያን ለተተኪው ትውልድ የምትሰጠውን ከፍተኛ ትኩረት የሚያሳይ ሲሆን፣ ሕፃኑ በዕውቀትና በሞራል ታንጾ ለታላቅ አገልግሎት እንዲበቃ ሁለንተናዊ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ያለመ ነው።

ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በገዳማትና አድባራት የሚካሄዱ የመኸር የግብርና ሥራዎችን ጎበኙ፤ ሐምሌ 28/2018 ዓ.ም ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ዜና ማርቆስ...
05/08/2026

ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በገዳማትና አድባራት የሚካሄዱ የመኸር የግብርና ሥራዎችን ጎበኙ፤

ሐምሌ 28/2018 ዓ.ም

ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ዜና ማርቆስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ሓላፊ በገዳማትና አድባራት የሚካሄዱ የመኸር የግብርና ልማት እንቅስቃሴዎችን በአካል ተገኝተው በመጎብኘት ለሥራው ውጤታማነት የሚረዳ አባታዊ መመሪያ አስተላለፉ።

ብፁዕነታቸው በጉብኝታቸው ወቅት በገዳማትና አድባራት የተዘሩ ሰብሎችን ሁኔታ የተመለከቱ ሲሆን፣ በጸሎትና በትጋት የሚከናወኑ የልማት ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

በጉብኝታቸው ማጠቃለያ ላይ ብፁዕነታቸው ባስተላለፉት አባታዊ መመሪያ፣ በቀጣይ የሚከናወኑ የግብርና ሥራዎች ወቅቱንና አየር ጠባዩን ጠብቀው እንዲከናወኑ አሳስበዋል። ገዳማቶቻችንና አድባራታችን በመንፈሳዊው አገልግሎት ብቻ ሳይሆን በልማቱም አርአያ መሆን አለባቸው፤ በመሆኑም በቀጣይ የሚከናወኑ የሰብል እንክብካቤና አረም የማረም ሥራዎች ወቅታቸውን ጠብቀው ሊከናወኑ ይገባል ብለዋል

በተለይም ሰብሉ ከተባይና ከተለያዩ የበሽታ ስጋቶች እንዲጠበቅ አስፈላጊው ክትትል እንዲደረግና የመኸር ምርትን በብቃት ለመሰብሰብ የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት ከወዲሁ እንዲደረግ አባታዊ መመሪያ ሰጥተዋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ገዳማትና አድባራት ከጥንት ጀምሮ "ጸልዮ ማጸለይ፣ ሠርቶ ማሥራት" የሚለውን መርህ በመከተል በግብርናው ዘርፍ ጉልህ አስተዋጽኦ ሲያደርጉ የቆዩ ሲሆን፣ አሁን በሀገረ ስብከቱ በብፁዕነታቸው መመሪያና በ10 ዓመቱ መሪ ዕቅድ መሠረት የተጀመሩት የልማት ሥራዎችም ይህንን በጎ ባህል አጠናክረው የሚያስቀጥሉ መሆናቸው ተመልክቷል።

ለፈጣን መረጃ ሳሌም የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሚዲያ። ቤተሰብ ይሁኑ። የማኅበራዊ ሚዲያዎቻችን።
Facebook; https://www.fb.com/GurageDiocese
Telegram; https://t.me/GurageDiocese
Tiktok; tiktok.com/
Instagram; instagram.com/gurage_diocese
YouTube; https://youtube.com/

ከብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የጉራጌ ሀገረ ስብከት የተሰጠ የሀዘን መግለጫሐምሌ 27/2081 ዓ.ምበታላቋና በታሪካዊቷ ጻድቃኔ ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም ገዳም** ለጸበል፣ ለሱባኤና ለመሳለም ...
03/08/2026

ከብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የጉራጌ ሀገረ ስብከት የተሰጠ የሀዘን መግለጫ

ሐምሌ 27/2081 ዓ.ም

በታላቋና በታሪካዊቷ ጻድቃኔ ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም ገዳም** ለጸበል፣ ለሱባኤና ለመሳለም ተሰብስበው በነበሩ ወገኖቻችን ላይ በተከሰተው ድንገተኛ የመሬት መንሸራተትና ርዕደ መሬት አደጋ የ14 ወገኖቻችን ሕይወት ማለፉን እንዲሁም በሌሎች ላይ ጉዳት መድረሱን በመስማታችን የተሰማንን ጥልቅና መሪር ሐዘን እንገልጻለን።

ይህ ድንገተኛ አደጋ የመላው ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንና የምእመናን ልብ የሰበረ ቢሆንም፣ በፈተና ወቅት የሚያጽናና አምላካችን እግዚአብሔር መጽናናትን ይሰጠን ዘንድ ጸሎታችን ነው።

ልዑል እግዚአብሔር ያረፉትን የ14ቱን ወገኖቻችንን ነፍስ በገነት፣ በአብርሃም፣ በይስሐቅና በያዕቆብ አጠገብ ያሳርፍልን፤ በአደጋው ለተጎዱት ምሕረቱንና ሙሉ ጤንነቱን ይላክላቸው። ለወዳጅ ዘመዶቻቸው፣ ለሀገረ ስብከቱና ለመላው የጻድቃኔ ማርያም ወዳጆች እግዚአብሔር
መጽናናትን ያድልልን።

ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ

በጉራጌ ሀገረ ስብከት በጌታ ወረዳ ቤተክህነት የወረዳው አብያተ  ክርስቲያናት የአንድነት ማኅበር ምሥረታ በዓልን አከበረ።በዚህ የመሥረታ በዓል ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ የጉራጌ ሀገረ ስብከት ...
02/08/2026

በጉራጌ ሀገረ ስብከት በጌታ ወረዳ ቤተክህነት የወረዳው አብያተ ክርስቲያናት የአንድነት ማኅበር ምሥረታ በዓልን አከበረ።

በዚህ የመሥረታ በዓል ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ በመንበረ ፓትርያርክ የጠቅላይ ቤተክህነት የስብከተ ወንጌል መመርያ ኃላፊ መጋቤ ሐዲስ ጸጋው ወልደ ትንሣኤ እና የሀገረ ስብከቱ ምክትል ሥራ እስኪያጅ መልአከ ሰላም ካሱ መኮንን የሀገረ ስብከቱ የማኅበራት ምዝገባና ክትትል ዋና ክፍል ኃላፊ እና የጌታ ወረዳ ቤተክህነት ሥራ አስኪያጅ መጋቤ ትፍሥሕት ባሕራን ሀብቴ በተገኙበት በአዲስ አበባ በአዲሱ ሚካኤል ስብከተ ወንጌል አዳራሽ ምሥረታው ተከናውኗል

በመርሃ ግብሩ ብፁዕነታቸው በሚል ርእስ በመነሳት ሃይማኖታቸውን እንዲያጠናክሩ ወረዳውን እንዲያሳድጉ፣ የተመሠረተው ማኅበር ዓላማውን እንዳይስት፣ህጉን ጠብቆ መዋቅሩን ተከትሎ መሥራት አለበት በማለት ሰፊ የሆነ ትምህርትና መመርያ አስተላልፈዋል።

በተመሳሳይ መርሃ ግብር በቸሃ ወረዳ የዶሮ ገብያ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ማኅበር 27 ተኛውን የምሥረታ በዓላቸውን አክብረዋል ብፁዕነታቸው በዚህም በዓል በመገኘት ለማኅበሩ ምክርና ቃለ ምእዳን ሰጥተዋል።

Address

Welk'it'e
366

Telephone

+251909019988

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሳሌም ሚዲያ የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሚዲያ/Salem Gurage Diocese Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share