25/05/2026
ሰላም ቅዱሳን!
ትውልድን ማገልገል የነገ ቤተ ክርስቲያንን ማዘጋጀት ነው።
በወላይታ ቀጣና ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ትኩረት ከተሰጣቸው አገልግሎች አንዱ የወጣቶች አገልግሎት ሲሆን በወጣቶች ዘርፍ ከሚከናወኑ ተግባራት ቀዳሚው የተማሪዎች እና ምሩቃን አገልግሎት በመሆኑ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን አባል ተማሪዎች ኀብረት በቀን 14/09/2018 ዓ.ም ዓመታዊ የአንድነት ጊዜአቸውን በሶዶ ስታዲየም አጥቢያ በማካሄድ ተመራቂ ክርስቲያን ተማሪዎች ሽኝትም በማድረግ ፕሮግራሙ በስኬት የተጠናቀቀ ስለሆነ የተማሪዎች ኅብረት መሪዎችና አስተባባሪን እንዲሁም የሶዶ ስታዲየም አጥቢያ ቃለ ሕይወት ቤ/ክ መሪዎችን ከልብ እናመሰግናለን።
"...ማናቸውን ነገር ብታደርጉ ሁሉን ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት።" 1ቆሮ 10:31
ጠረጴዛ ወላይታ ሶዶ ኢትዮጵያ