29/04/2026
#ወዳጅ ሆይ፤ መንገዱን ታውቀዋለህ? ኢየሱስ እንዲህ ሲል ነግሮናል፤ "እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም" (ዮሐ. 14፥6)። ማንም ሰው የክርስቶስን ምህረት ለማግኘትና ወደ አስደናቂ ህልውናው ውስጥ ለመግባት አልረፈደበትም። በሕይወታችን ጉዞ ያሳለፍነውን ወደ ኋላ ዞር ብለን ስንመለከት ሰለምርጫዎቻችን እንጸጸት ይሆናል፤ ግን ልብ በሉ ያ #ያኔ ነው.. . .ይህ አሁን ነው። ቤተሰቦቻችን ያስቀየምንበት ጊዜ ይኖር ይሆናል፤ ነገር ግን ያ #ያኔ ነው . . . #ይህ ግን አሁን ነው። ይህን ጽሑፍ የሚያነቡ አንዳንዶች እንዲህ ይሉ ይሆናል፤ "ሕይወቴን በሙሉ ክርስቶስን አልተከተልኩም። አሁን ለእኔ ረፍዶብኛል።" ወዳጆቼ፤ እኔ ግን እላችኋለሁ ያ #ያኔ ነው . . . ይህ ግን አሁን ነው። የመጽሐፍ ቅዱስ ኪዳኖች ያኔም እውነት ናቸው፤ አሁንም ናቸው፤ ለዘለዓለምም ይሆናሉ። "እነሆ የተወደደ ሰዓት አሁን ነው፤ #እነሆ የመዳን ቀን አሁን ነው" (2ቆሮ. 6፥2)።
እናንተ እጅግ ውድ የሆነውን የክርስቶስን የሚዋጅ ደም ስጦታ የተቀበላችሁ . . . የመንግስተ ሰማይን ክብር ለማየት የምትጓጉበት ምክንያት አላችሁ፤ ምክንያቱም ፍጹም ትሆናላችሁ፤ ደስተኞች ትሆናላችሁ፤ ደግሞ በሥራ ላይ ትሆናላችሁ፤ እንዲሁም አሁኑኑ ወደ አባታችሁ(እቤታችሁ) እየቀረባችሁ መሆናችሁን እርግጠኛ መሆን ትችላላችሁ።