Shone City Meserete Kirstos Church

Shone City Meserete Kirstos Church ይህ የሾኔ ከተማ መሠረተ ክርስቶስ አጥቢያ ቤተክርስቲያን የFacebook ገፅ ነው።

27/08/2026

27/08/2026

🙌🙌

26/08/2026

#ኢየሱስ 🙌🙌

25/08/2026

#ተወዳጆች
ነገ(ዕሮብ) የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታችን 1ጴጥ 2:13-18 ያለውን ክፍል ከሰአት ከ10:30 ጀምሮ በህብረት ስለምናጠና #ተጋብዛችኋል!

‎ ‎  በሚል ርዕስ ከማቴዎስ 6:8-13 ካለው የቃል ክፍል ተምረናል።‎ #በዕለቱም የአምልኮ እንዲሁም የጸሎት ጊዜ ነበረን....ያገለገላችሁን ሁሉ ጸጋ ይብዛላችሁ ተባረኩልን።‎
24/08/2026


‎ በሚል ርዕስ ከማቴዎስ 6:8-13 ካለው የቃል ክፍል ተምረናል።
‎ #በዕለቱም የአምልኮ እንዲሁም የጸሎት ጊዜ ነበረን....ያገለገላችሁን ሁሉ ጸጋ ይብዛላችሁ ተባረኩልን።

19/08/2026


18/08/2026

#ተወዳጆች
ነገ(ዕሮብ) የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታችን 1ጴጥ 2:9-12 ያለውን ክፍል ከሰአት ከ10:30 ጀምሮ በህብረት ስለምናጠና #ተጋብዛችኋል!

‎ ፥‎ ? ‎ :11-18‎‎👉 ሰው ጊዜውን የሰጠበት ጉዳይ ማንነቱ ነው። ‎👉 ሰው ብዙ አይነት ፍላጎትም በውስጡ አለው፤ ለዛ ጉዳይ ጊዜውን ከሰጠ ግን ያገኘዋል።‎‎❗️ መግደላዊት ማርያም ኢየ...
17/08/2026

‎ ፥
‎ ?
‎ :11-18

‎👉 ሰው ጊዜውን የሰጠበት ጉዳይ ማንነቱ ነው።
‎👉 ሰው ብዙ አይነት ፍላጎትም በውስጡ አለው፤ ለዛ ጉዳይ ጊዜውን ከሰጠ ግን ያገኘዋል።

‎❗️ መግደላዊት ማርያም ኢየሱስን ፈልጋ ሄዳ ምን ልታገኝ ቻለች?❗️
‎1. ኢየሱስን እንድታገኝ በፅናት ጠብቃ ራሱን ኢየሱስን አግኘች። 20፥14-15
‎2. ድምፁንም ለይታ አወቀች። 20፥16
‎3. ትክክለኛ የኢየሱስ ክርስቶስ መልዕክተኛ ሆነች። 20፥17

‎ #በዕለቱ ያገለገላችሁ ሁሉ ፀጋ ይብዛላችሁ ተባረኩልን🙏
‎ /ክ/ቤ/ክርስቲያን_ወጣቶች ዘርፍ

  #ተጋብዛችኋል
13/08/2026


#ተጋብዛችኋል

1ኛ ጴጥሮስ 2፥4-8 ............ ሐዋርያው ጴጥሮስ ለወንድማማች ከልብ ለሆነ ፍቅር እና በድነታቸው እንዳያድጉ እንቅፋት{ማነቆ} ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮችን አስወግዱ ካላቸው በኋላ አሁን ...
13/08/2026

1ኛ ጴጥሮስ 2፥4-8 ............

ሐዋርያው ጴጥሮስ ለወንድማማች ከልብ ለሆነ ፍቅር እና በድነታቸው እንዳያድጉ እንቅፋት{ማነቆ} ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮችን አስወግዱ ካላቸው በኋላ አሁን ደግሞ
በወቅቱ መከራና ስደት እየተቀበሉ ላሉ አማኞች ፣ በምሳሌያዊ አነጋገር ክርስቶስን “ሕያው ድንጋይ” በማድረግ እና አማኞችንም “እንደ ሕያዋን ድንጋዮች” በመንፈሳዊ ቤት ለመሆን እንዲገነቡ '' ተሠሩ'' በማለት ትዕዛዛዊ በሚመስል መልኩ መልዕክቱን ያስተላልፋል።
፦ይህም ብቻ ሳይሆን እነዚህ በመከራ እና በስደት ላይ ያሉ መጻተኞች በእንግድነታቸው ወራት እንዴት መኖር እንዳለባቸው ያስተውቃል ።

እንዴት እንኑር ?
➢ሁልግዜ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ በመቅረብ {ቁ4}

📍ሐዋሪያው በእንግድነት ወራታቸው እንዴት መኖር እንዳለባቸው ብዙ እና የተወሳሰብ ነገር አይነግራቸውም፣ ይልቁንም አንድ ነገር ብቻ ይላቸዋል '' ቅረቡ'' ይላቸዋል ።

ታዲያ ለምንድነው ሁልግዜ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ የምንቀርበው ?
1)እርሱ በሰው ዘንድ የተናቀ ስለሆነ (ቁ4)
፨በሰው ዘንድ የተናቀ የሚለው የጴጥሮስ አውድ የሚያመለክተው የማያምኑትን ነው።
ምክንያቱም ከታች በሉት ቁጥሮች እነዚህ የናቁት ባለማመናቸው እንደሆነ በግልጽ ያስቀምጣል ።

2)እርሱ በእግዚአብሔር ዘንድ የተመረጠ እና ክቡር ስለሆነ(ቁ4)
3)በእርሱ በኩል እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መስዋዕት ለማቅረብ(ቁ5)
4)በእርሱ ቅዱሳን ካህናት ለመሆን(ቁ5)
5)በእርሱ መንፈሳዊ ቤት ሆኖ ለመሠራት(ቁ5)
6)እርሱ ለአማኞች የማያፍሩበት ክቡር ድንጋይ ስለሆነ(ቁ6፤7)
7)እርሱ ለማያምኑበት እና ለማይታዘዙት ማሰናከያ ዓለት ስለሆነ(ቁ7፤8)

ማጠቃለያ ሀሳብ
ጴጥሮስ ክርስቶስን ''ሕያው ድንጋይ'' ካለ በኋላ ወዲያው አማኞችን ''ሕያዋን ድንጋዮች'' ይላቸዋል።
ክርስቶስ=ሕያው ድንጋይ
እናንተ ደግሞ=ሕያዋን ድንጋዮች
፦ይህ ማለት አማኝ ብቻውን የተለየ ድንጋይ አይደለም ፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ማህበረሰብ እየገነባ ነውና።
📍ጴጥሮስ የአዲስ ኪዳን የእግዚአብሔር በሙላት መገኛ የሆነው ህንፃ ሳይሆን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ፣
ስለዚህ ፦
▪️የአዲስ ኪዳን ቤተ-መቅደስ ኢየሱስ
▪️የአዲስ ኪዳን መንፈሳዊ መሰዋዕት ኢየሱስ
▪️የአዲስ ኪዳን ሊቀ ካህን ኢየሱስ
▪️መንፈሳዊ ቤት(የእግዚአብሔር በሙላት መገኛ ኢየሱስ ....... አማኞችም ወደዚህ ሕያው ድንጋይ በመቅረብ ሕያዋን ድንጋዮች እንሆናለን ።
ጴጥሮስ እያለ ያለው እንጋራለን ነው።

አማኞች ''ቅዱሳን ካህናት ለመሆን....''
፦ካህን በብሉይ ኪዳን በአምላክና በሕዝቡ መካከል በአገልግሎት የሚቆም ነው ።
ጴጥሮስ ልከሰ እንደዚሁ እናንተም ቅዱሳን ካህናት ለመሆን ተሠሩ ይላል።
ይህ ማለት እግዚአብሔር ያዳነን በመቀመጥ ብቻ እንድንኖር ሳይሆን እንድናገለግልም ነው ።
➢ካህን ካለ መሰዋዕትም አለ።
አማኙ ካህን ነው➩ ስለዚህ መስዋዕት ያቀርባል።
ይህ መሰዋዕት ግን የእንስሳት መሰዋዕት አይደለም ።
አዲስ ኪዳን የሚያሳየን መሰዋዕት ፦
▪️ሕይወታችንን ለእግዚአብሔር መስጠት
▪️ምስጋና
▪️መታዘዝ
▪️ጸሎት እና አምልኮ .......ወዘተ ናቸው
፦ይህ ክቡር ድንጋይ ለምታምኑት ለእናንተ ክብር ፣ ለማያምኑት ደግሞ የማሰነካያ ዓለት ነው።
📍ምን እንማር ?
➢ቤተ ክርስቲያን የድንጋይ ህንፃ ወይም የድስጅት ስብስብ አይደለችም ፣እኛ ሕያዋን ድንጋዮች ነን ።
እርስ በርሳችን በመተሳሰብ ፣ በአንድነት እና በፍቅር ልንገነባ ይገባል ። ምክንያቱም አንዱ ድንጋይ ከሌላው ጋር ሲጣበቅ ብቻ ነውና ቤቱ የሚጸናው ።

ይቀጥላል.........
ፎቶ ከማህደር🙏

Address

Shone

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Shone City Meserete Kirstos Church posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category