22/09/2023
የተሐድሶና የእግዚአብሔር ቤት ቅንዓት የመብላቱ ጉዳይ (ዮሐ 2፡17)
Reformation and the Zeal of God's House
(ወ/ዊ በቀለ ዱባጎ፤ የቁ.1 በሌሣ ቃለሕይወት ቤ/ክ አገልጋይ)
መጽሐፍ ቅዱስን በጥልቀትና በስፋት ያጠኑ ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስን በሦስት ደረጃ ይከፍላሉ፤
Levels of Belief (C.S. Lewis. Our Approach, Convictions, Persuasion and Opinion. Pp 14-21)
1ኛ) ጽኑ እምነት መያዝ ያለበት አቋም |Conviction doctrine
ግትር አቋም መያዝ ያለበት |Dogma or conservative action
ይህም የሕይወት፤ የደህንነት/የድነት፤ የሞትና የሕይወት፤ የመኖርና ያለመኖር፤ የዘላለም ሕይወትን የማጣትና ሽልማትንም የማጣት ጉዳይ ነዉ።
ይህ ብቻ አይደለም የእግዚአብሔር ክብርና ወንድምንም የሚያሰናክል፤ ደግሞም የሥነምግባር ዉድቀትንና ዝቅጠትን የሚያስከትል ጉዳይ ነዉ ይሉታል።
ቤተክርስቲያንን የሚያከፋፍሉ እንዲሁም የሐሰት አስተምህሮዎች፤ ጸሎትንና መጽሐፍ ቅዱስን መቃወም፤ የሥላሴ ትምህርትን መቃወም፣ ዝሙትና የጣኦት አምልኮ ወዘተ ናቸዉ።
2ኛ) ሁለተኛዉ የእምነት ደረጃ ደግሞ የተግባቦት እምነት ነዉ፤ |Persuasion
የመጀመሪያዉን ያህል ጠንካራ አቋም መያዝ የማይፈልጉ፤ ደህንነትን የማያሳጡ፤ ቅድስናን የማያጎድፉ፤ ወይንም ለሥነምግባር ዉድቀት የማያበቁ፤ በመጽሐፍ ቅዱስ እዉነት ላይ የተመሰረቱና መሠረታዊ የአስተምህሮ ልዩነት የማያመጡ ናቸዉ። ተግባብተን መኖር የምንችልበት የእምነት አቋም ነዉ።
3ኛ) ሦስተኛዉ የእምነት አቋም ደግሞ አመለካከት ነዉ። |View or Opinion
ይህንን አቋም ማንም ሰዉ በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ ማሳመን አይችልም፤ ምስጢሩ ለአምላካችን የተባሉ ናቸዉ። (ዘዳ 29፡29)
ስለሆነም ስለማክበር ስናነሳ ከላይ ካየናቸዉ ሦስቱ የመጽሐፍ ቅዱስ እምነት አቋም የትኛዉን ይዘን ነዉ የምንከራከረዉ?
አዲሱ ትዉልድ ባሕላዊ ኃይ ማኖቶችን አመቻምቾ የመሸከም ትከሻ አይኖረዉም። ከጌታ ጋር ሆነን ትግሉ ይቀጥላል!
ባለፈዉ በሚለዉ አጭር ጽሁፌ የሆሳዕና እናት ቃለሕይወት ቤተክርስቲያን የጀመረችዉን ጽፌያለሁ፤ ከእነዚህ መኻል የመስቀል በዓል ጉዳይ ነበር፤ እኛም የበሌሣ ቁ 1 ቃለሕይወት ቤተክርስቲያን በ2014 ዓ/ም መጨረሻ ወደ ኢትዮጵያ ቃለሕይወት ዋና ጽ/ቤት ካቀረብናቸዉ የጥያቄ ሀሳቦች የመስቀል በዓል ጉዳይ ነበር።
በአለማችን አንድ ታዋቂ የሥነመለኮት ምሁር ጄ. ዲ. ዲያግለስ የተባለ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት አዘጋጅ ስለ መስቀልና መሰቀል፤ |Cross -crucification እንዲህ ብሏል፤ የአዲስ ኪዳን ጸሐፊዎች ስለ መስቀል፤ ስለ ክርስቶስ የሚደረግ ጥናት እንጂ ከመሬት በቁፋሮ የተገኘ ታሪካዊ መስቀል አይደለም። ብሏል እናስብበት!
|The new testament writers interest in the cross is neither archeological nor historical but Christological. (J.D. Douglas. New Bible Dictionary. P. 246.)
ከዚህ ቀጥሎ በሚቀርበዉ ፅሑፍ ደግሞ ሰዎች መብሉን እየበሉና መጠጡን እየጠጡ እንዴት አምላካቸዉን እግዚአብሔር እንደሚያመልኩ፤
ወይንም ጣኦታትና አጋንንትን በመጨረሻም ሰይጣንና ዲያቢሎስን እንደሚያመልኩና በመብል እንደሚፈተኑ፤ እንደሚታዘዙ እንዲሁም እንደሚያመነዝሩ፤ ሕያዉና ዘላለማዊ ከሆነዉ ከእግዚአብሔር ቃል በቀጥታ በዝርዝር እንመለከታለን። ተከታተሉ!
ወ/ዊ በቀለ ዱባጎ