28/11/2021
ዛሬ ከትላንትም ከነገም ይልቅ ምርጡ ጊዜ ነው። ብዙ ወገብ አጉባጭ ችግሮችን አልፈን በፈጣሪ ድጋፍ ዛሬን ደርሰናል። እንደ ሀገር መናቅ ፣ መካድ ፣ መገፋት ፣ መደፈር ፣ መከፋፈል ሌላም ሌላም ብዙ አይተናል። ይሁንና ይህ ጊዜ ለነቃ የለውጥ ጊዜ ነው ለፈዘዘ የነውጥ ጊዜ ነው። (Change challenges & challenge changes!) አንዳንዴ ለውጥ ያናውጣል _ ነውጥም ይለውጣል! ዋናው ጉዳይ በነውጡም ይሁን በለውጡ አቋቋምህ ምን ይመስላል? ስለራስህ ምን ታስባለህ? ስለሀገርህስ ምን ትላለህ? የሚለው ነው። ለማንኛውም ከመቼውም ጊዜ በላይ አሁን የኢትዮጵያ የከፍታ ጊዜ ነው። አሁን ኢትዮጵያ አድጋለች ፣ ለምልማለች ፣ ከፍ ብላለች ፣ ታላቅ ሆናለች_ እንኳን ደስ ያለን ኢትዮጵያ #አሸንፋለች! ይህን በበለጠ መረዳት እንድትችል ከህዳር 23_30 የሚካሄደውን የተስፋ ኢትዮጵያ የሶሻል ሚድያ ንቅናቄ ተቀላቀል! አብረን ለኢትዮጵያ ከፍታ ፣ አብረን ለራሳችን እድገት በትጋት እንስራ!!
#እንደርሳለን #ኢትዮጵያ #ተስፋ #አላት!!!