Evangelist Zedo

Evangelist Zedo Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Evangelist Zedo, Evangelical church, Shashemene.

ኢየሱስ ያድናል ❤
07/01/2026

ኢየሱስ ያድናል ❤

የአብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ፕሬዝደንቱ ታሰሩ!! ዛሬ በአምልኮ ላይ እያሉ ፖሊስ ቤተ ክርስቲያን ዉስጥ የጦር መሳሪያ ታጥቀዉ በመግባት የቸርቿን ፓስተርና አገልጋዮችን ጉባኤዉን እየመሩ ካሉበ...
02/11/2025

የአብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ፕሬዝደንቱ ታሰሩ!!

ዛሬ በአምልኮ ላይ እያሉ ፖሊስ ቤተ ክርስቲያን ዉስጥ የጦር መሳሪያ ታጥቀዉ በመግባት የቸርቿን ፓስተርና አገልጋዮችን ጉባኤዉን እየመሩ ካሉበት አስወርደዉ ከ20 በላይ ምዕመናን ጋር በሠደፍ እየደበደቡ ወስደዉ አስረዋቸዋል!!

በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ ገነት ቤተ ክርስቲያን ዛሬ ጠዋት አገልጋዮችና ምዕመኑ በአምልኮ ላይ እያሉሉ የቦንጋ ከተማ ፖሊሶች የጦር መሳሪያ ታጥቀዉ ወደ ቸርቿ በመግባት የቤተ ክርስቲያኗን ፓስተርና አገልጋዮችን ጉባኤዉን እየመሩ ካሉበት አስዉርደዉ ከ20 በላይ ምዕመናን ጋር፤ እንዲሁም ከተለያየ የአገሪቱ አካባቢ የሄዱና በአምልኮ ላይ የነበሩ የቦንጋ ዩንቨርስቲ ተማሪዎችን ጨምሮ በያዙት የጦር መሳሪያ ክላሽንኮቭ በሠደፍ ደረታቸዉንና ጀርባቸዉን እየደበደቡና እያዳፊ ወስደዉ እስር ቤት አጉረዋቸዋል።

የቦንጋ ፖሊስ ወስዶ ካሰራቸዉ ከ20 በላይ ምዕመናን መካከል የተወሰኑትን የለቀቀ ሲሆን፤ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ኃላፊ የሆኑትን መጋቢ መለሰ እንዳለን ጨምሮ የቤተ እምነቷን ፓስተርና አገልጋዮች በድምሩ 7 አገልጋዮችን እስር ቤት አስቀርተዋቸዉ ማንም ሰዉ ገብቶ እንዳይጠይቃቸዉ ተደርገዉ በከባድ እንግልትና መከራ ዉስጥ ይገኛሉ። እስካሁን ባለዉ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል በጉዳዩ ላይ ያለዉ ነገር የለም።

በዞኑ በሚገኙ 12 ወረዳዎችና 5 ከተማ አስተዳደሮች
የሚገኙ የወንጌል አማኞችን ጨምሮ በክልሉ የሚገኙ የወንጌል አማኞች ከዞኑ አመራሮች ጀምሮ በከተማዉ አስተዳደር በአማኞች ላይ እየተፈጸመ ያለዉን ከፍተኛ የሆነ ጥቃት የክልሉ መንግሥት እየተመለከተ ዝምታን በመምረጡ በቀጣይ ሠላማዊ ሠልፍ ለማድረግ ጥሪ ቀርቧል። የሠላማዊ ሠልፍ ቀኑና ሠዓቱ መች እንደሆነ መረጃዉ ሲደርሰን የምናሳዉቅ ይሆናል። በአሁኑ ሰዓት በከተማዉ የሚገኙ የወንጌል አማኞች ለምሳ ሳይሄዱ በፖሊስ ጣቢያዉ ዙሪያ መጽሐፍ ቅዱሳቸዉን እንደያዙ ወገኖቻቸዉ እንዲፈቱ እየጠየቁ ይገኛሉ።

አታፍሪምና አትፍሪ፤ አትዋረጂምና አትደንግጪ፤ የሕፃንነትሽንም እፍረት ትረሺዋለሽ፥ የመበለትነትሽንም ስድብ ከእንግዲህ ወዲህ አታስቢም።              ትንቢተ ኢሳይያስ            ...
23/10/2025

አታፍሪምና አትፍሪ፤ አትዋረጂምና አትደንግጪ፤ የሕፃንነትሽንም እፍረት ትረሺዋለሽ፥ የመበለትነትሽንም ስድብ ከእንግዲህ ወዲህ አታስቢም።
ትንቢተ ኢሳይያስ
54፥4

በካፋ ዞን ቦንጋ የወንጌል አማኞች እየተሳደዱ ነዉ!!በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ የቦንጋ ዩኒቨርስቲ ቀጠና ካይኬላ ቀበሌ ያሉ የወንጌል አማኞች በአካባቢዉ በተደራጁ ግ...
20/10/2025

በካፋ ዞን ቦንጋ የወንጌል አማኞች እየተሳደዱ ነዉ!!

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ የቦንጋ ዩኒቨርስቲ ቀጠና ካይኬላ ቀበሌ ያሉ የወንጌል አማኞች በአካባቢዉ በተደራጁ ግለሰቦች "በሰፈራችን ማንም ቸርች አይከፍትም አያመልክም" በማለት ጥቃት እየፈጸሙባቸዉ ይገኛሉ። የክልሉ መንግስት ዝምታን መርጧል!!

➡️ አንድም የተዋህዶ መምህር ከ ዋናዎቹ ጀምሮ በነገረክርስቶስና ገድላት ዙሪያ መወያየት እንደማይፈልጉ ይኼ ወንድም አሳይቶአል! ራሱ ቀጠሮ አስይዞ ከ 13 ሺ ህዝብ በላይ live ላይ እየጠበ...
14/10/2025

➡️ አንድም የተዋህዶ መምህር ከ ዋናዎቹ ጀምሮ በነገረክርስቶስና ገድላት ዙሪያ መወያየት እንደማይፈልጉ ይኼ ወንድም አሳይቶአል! ራሱ ቀጠሮ አስይዞ ከ 13 ሺ ህዝብ በላይ live ላይ እየጠበቀ ድምፁን አጥፍቶ የገባበት አልታወቀም! መምህራኑ ያፈሩበት ገድል ምዕመኑን አይጠቅምም አምልጡ!
ወንጌላዊ ኤርሚ

12/10/2025

መባረክን ትባረካላችሁ

(ወንጌል) =======================የ79 ዓመቱ አባት ልክ እንደሌሎች በባቡር በኒውዮርክ መንደር ታይም አደባባይ ይዞር ነበር። መጽሐፍ ቅዱስን በእጃቸው ይዘዋል። ክርስቶስ ለምን ...
03/10/2025

(ወንጌል)
=======================
የ79 ዓመቱ አባት ልክ እንደሌሎች በባቡር በኒውዮርክ መንደር ታይም አደባባይ ይዞር ነበር። መጽሐፍ ቅዱስን በእጃቸው ይዘዋል።

ክርስቶስ ለምን እንደሞተ የተረዱትን ለሰዎች ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝ፣ መንገድ፣ እውነት እና ሕይወት እንደሆነ በዚያ ላሉት ወንድሞች እውነቱን መንገር ጀመሩ።

የጌታን አዳኝነት እየተናገሩ ሳለ ከአንዲት ሴት ብርቱ ተቃውሞ ገጠማቸው። በንዴት፣ በምሬትና በጥላቻ ተሞልተው የሕያው እግዚአብሔርን ቃል መስማት አትፈልግም ነበር። ሆኖም ሴትየዋ አፉ የማይናገር ወንድ ልጅ ነበራት።

በዚህ መሀል በንዴት ሆና የሄል ጫማውን አውልቃ የእኝህን አባት ጭንቅላት መታቻቸው። በፀጉራቸውም መሀል ደም ወደ ታች በፊታቸውም ፈሰሰ።

በዚህ ውጊያ ውስጥ እያሉ አንድ አስደናቂ ነገር ተሰማ። አንድም ቀን ተናግሮ የማያውቅ ልጅ አፉን ከፍቶ "ውድ እናቴ አትንኪው እርሱ ከእግዚአብሔር የተላከ ሰው ነው" ብሎ አፉን ከፈተ።

ወዲያው የልጅየው እናት ተንበርክካ ማልቀስ ጀመረች። ለምን ታለቅሻለሽ? ለምን ተንበረከክሽ ብለው ጠየቋት? እሷም "ልጄ በጭራሽ አይናገርም, አሁን የታሰረው ምላሱ ተፈትቷል እና ተናገረኝ " አለች "

የጌታችን ወንጌል ያድናል እና ድንቅ ይሰራል።

ወንጌላችን ገና ድል ያደርጋል
የእግዚአብሔር ቃል ገና አለምን ይዞራል 🙏🙏🙏

ተባረኩ መልካም ምሽት

Gospel Tube

  🔥  !በወንጌላውያን አማኞች የዝማሬ አገልግሎት ውስጥ 90ዎቹ ላይ ከተነሱ ወጣት ዘማሪያን አንዱ የናዝሬት አማኑኤል ቤ/ክ ፍሬ የሆነው ዘማሪ ኤፍሬም አለሙ ነው::በብላቴንነት እድሜው አገል...
02/10/2025

🔥

!

በወንጌላውያን አማኞች የዝማሬ አገልግሎት ውስጥ 90ዎቹ ላይ ከተነሱ ወጣት ዘማሪያን አንዱ የናዝሬት አማኑኤል ቤ/ክ ፍሬ የሆነው ዘማሪ ኤፍሬም አለሙ ነው::በብላቴንነት እድሜው አገልግሎት የጀመረው ይሄው ዘማሪ ወንድማችን ኤፍሬም አለሙ "ለየት ያለ መንፈስ ወርዶብኛልና" በማለት ብቅ ካለበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን አራት ያህል ሰንዱቆች ከግሩም ዝማሬዎች ጋር ያበረከተን ሲሆን በጥዑምና ለጆሮ ግቡ በሆኑ ዜማዎቹ ከደመቁ የምት ስልቶቹ ከልዩ የድምፅ ቃናው ጋር በብዙዎች ዘንድ ተፅዕኖ የፈጠረ በጌታም ሞገስ ተወዳጅ የሆነ ዘማሪ ነው::በብዙ የቅርብ ወዳጆቹ ቅንነቱና የዋህነቱ ከቸርነቱ ጋር የሚመሰከርለት የልጅነት እድሜውን በብዙ ውጣ ውረድና ተግዳሮት በድካም በብርታት ገጠር ከተማ ሳይል በአለም አቀፍ መድረኮች ሁሉ ሲያገለግል የቆዬው ተወዳጁ ወንድማችን ዘማሪ ኤፍሬም አለሙ በጌታ ጊዜና ፈቃድ ይሄው "ወንጌል ያሸንፋል!" በተስኘ በአይነቱና በአላማው ልዩ የሆነ ትልቅ የመዝሙር ድግስ መጥቶልናል::የድግሱም አላማ አስቀድሞ አምልኳችን የተገባውን ልዑል እግዚአብሔርን በብዝኃ አንድነት በዝማሬ ማመስገን ሲሆን በመቀጠል እንደ ዝግጅቱ ስያሜ በእለቱና አስቀድሞ ወንጌልን ላላመኑን በማድረስ ነፍሳትን ወደ እግዚአብሔር መንግስት በማምጣት ታላቁ ደስታ በምድርም በሰማይም እንዲሆን ነው::የዚሁ ትልቅ የዝማሬ ድግስ የመጨረሻው አላማ እኛ አማኞች የተቀበልነው ወንጌል ሙሉ እና የከውስጥ ወደ ውጭ ህይወት ለዋጭነቱ ሁለንተናዊ እንደመሆኑ ወጣቱ ትውልድ በጉብዝናው ትጉና ምስጉን የስራ ባህል ያለው በበረከት ፍሬውም የምድርን ፊት የሚሸፍን ለጨለማው አለም ብርሃንና ጨው እንዲሆን ማንቃትና ማነቃቃት ነው::ስለዚህ ጥቅምት 23 እለተ እሑድ ከሰአት በሚሊንዬም አዳራሽ ያላመኑ ወገኖቻችንን በመጋበዝ አይቀርም ሲገቡም በተዘጋጀላችሁ QR Code መመዝገቢያ የቴሌግራም መጠቀሚያ ስማችሁን ብታሰፍሩልን በቀጣይ ለስራና የትምህርት እድል ፈላጊዎች ሰፊ የታሰበ እቅድ እንዳለ እያሳሰብን
#ወንጌል ያሸንፋል
#ዘማሪ ኤፍሬም አለሙ
#ዳሪክ ኢቨንት
እያላችሁ ይህን ልጣፍ በማጋራት ለብዙዎች ተደራሽ እንዲሆን አብሮነታችሁን በአክብሮትና በብዙ ፍቅር እንጠይቃለን::
እግዚያብሔር አምላክ ኢትዮጵያን ይባርክ::

ዳሪክ የመንፈሳዊ ዝግጅት አቀናጅ አገልግሎት!

27/09/2025

ኢየሱስ

27/09/2025

💥
የተሰቀለውን
ትቶ
መስቀሉን ማክበር ከኛ ይራቅ !

26/09/2025

ጌታ ኢየሱስ ይባርካችሁ

Address

Shashemene

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Evangelist Zedo posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share