ማህበረ ፂዮን ወበ ስንዳፋ Mahiber Tsiyon Web Sendafa

ማህበረ ፂዮን ወበ ስንዳፋ Mahiber Tsiyon Web Sendafa ከልደቱ እስከ አለተ እርገቱ
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 16:13..ንቁ፥ በሃይማኖት ቁሙ፥ ጎልምሱ ጠንክሩ።...

የአእላፋት ዝማሬ መርሐ ግብር በምስል፡-
06/01/2026

የአእላፋት ዝማሬ መርሐ ግብር በምስል፡-

"ነፍሴን ሀገሯን አሳየኋት።"ነፍስ ሄዳ የምትመጣበት-ደብረ ሮሐ***(ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም - ለድሬ ቲዩብ)የዛሬው የቤተ አማኑኤል ማህሌት ያስቀናል። እንኳን በዚህ ሰሞን ዓመቱን በሙሉ ስ...
06/01/2026

"ነፍሴን ሀገሯን አሳየኋት።"
ነፍስ ሄዳ የምትመጣበት-ደብረ ሮሐ
***
(ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም - ለድሬ ቲዩብ)

የዛሬው የቤተ አማኑኤል ማህሌት ያስቀናል። እንኳን በዚህ ሰሞን ዓመቱን በሙሉ ስለ ላሊበላ ቢወራ መች ይጠገባል? የእናቶች ዜማ ጆሮዬ ላይ ቀርቷል ብዬ የምገልፀው አይደለም። ከሰማሁበት ቀን ጀምሮ ደብረ ሮሐን ሳስብ ጆሮዬ ውስጥ የኖረ ድምፅ ነው።
"ነፍሴን ሀገሯን አሳየኋት
ነፍሴን ሀገሯን አሳየኋት
ሀገሬ ስገባ ካላበላሸኋት" እንዲህ የሚሉ ሰዎች ከየስጋቸው ሀገር ወደ ነፍሳቸው ሀገር መጡ። ላሊበላማ የነፍስ ሀገር ነው። ለነፍስ ያለ ላስታ ደርሷል። ሰብአ ሰገል በኮኮብ ተመርተው ስለ መወለዱ እጅ ሊነሱ ጎል ግርግሙ ጋር እንደ ደረሱ ሁሉ ወንጌል የመራቸው የሀገሬ ሰዎች እነሆ መድኃኒት ተወልዶልናል ሲሉ ስለ ልደቱ ብሥራት ላስታ ገቡ።

የሀገሬ ሰው ዛሬ እንደ ንጉሥ አይሹር ነው። በልቡ የምስጋና ወርቅ ይዞ፣ "ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት" ሊል በምድር ወደአለ ሰማዮ ይጓዛል። ያ ላስታ ላሊበላ ነው። እዚያ ስጋ በነፍስ የሰማይ ቤት የምትጎመዥበት። ለዚህም ነው "ነፍሴን ሀገሯን አሳየኋት" የሚሉት።

በነፍስስ ሀገር ለፈጣሪ ክብር ምስጋና ብቻ ነው። የላሊበላ ተጓዦች በዚያ "ነፍሴን ሀገሯን አሳየኋት" የሚሉትም ለዚህ ነው። ሰብአ ሰገል ከምሥራቅ ወደ እርሱ እንደመጡት ሁሉ የሀገሬ ሰው ከየአለበት ለልደት በዓል ወደ ላሊበላ ይመጣል።

ላሊበላ ህይወት ያለው ቅርስ ነው። ያ ህይወት ደግሞ ምድራዊ ብቻ አይደለም። ወገኔ "አይቴ ሀሎ" ብሎ ለዘመናት እርሱ መድኃኒት መወለዱን የምናስብበት የታላቁ ንጉሥ እና ቅዱስ ደጃፍን ፍለጋ ይመጣል። እየዘመረ
"አያወላውልም ይምረናል
አያወላውልም ይምረናል
ያንን ሁሉ መንገድ ስንመጣው አይቶናል" እያለ።

ያ ሁሉ መንገድ እንደምን ያለ ነው ቢሉ የሀገሬ ሰው ከጥንት እስከ ዛሬ ከመስቀል ክብራ እስከ ለብቃ ኢየሱስ ከደብረ ዳሞ እስከ ዲማ ከጎንደር እስከ ሸዋ ከትግራይ ጫፍ እስከ ጎጃም ከኢትዮጵያ የተመጣው። መጥቶ ለምን መጣሁ የሌለበት። ይልቁንም
"ከእንግዲህ አልቀርም ላሊበላ
ከእንግዲህ አልቀርም ላሊበላ
እሱ ያዘዘውን ያለኝን ልበላ....." እያስባለ ዳግም ለመምጣት የሚያስናፍቅ።

ዋዜማ ነው። ልደቱን ለማክበር ሰው ላስታ ገብቷል። አደፋ ደምቃለች። የደብረ ሮሐ የቀድሞ መጠሪያ አንዱ አደፋ ይባላል። እንደ ማር የሚጣፍጥ የምስጋና መስዋዕት የሚቀርብባት ታላቅ ስፍራ። ኢትዮጵያዊያን የኢየሱስ ክርስቶስን መወለድ እንዲህ ያከብራሉ ያስባለች መካነ ቅርስ። ዛሬ ምሽት የሚሆነውን አስቡት....ቤተ ማርያም
በድጋሚ ለምጠቀማቸው ፎቶዎች Lalibela የተባለውን የፌስ ቡክ ገፅ አመሰግናለሁ።

06/01/2026

Address

Sendafa Bake
Sendafa

Telephone

+251946853600

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ማህበረ ፂዮን ወበ ስንዳፋ Mahiber Tsiyon Web Sendafa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share