21/08/2025
በኤርትራ በእስር ላይ የሚገኙ የቤተ ክርስቲያን መሪዎችን አስመልክቶ ዓለም አቀፋዊ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ።
4 የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት መጋቢዎች እንዲሁም በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በተሐድሶ እንቅስቃሴ ላይ የተሳተፉ ሶስት የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቄሶች ከ20 ዓመታት በላይ በእስር ቤት ውስጥ ለመማቀቅ ተገደዋል።
ምንም እንኳን ቤተ ክርስቲያን በመንግስት እውቅና ካገኙ ጥቂት ተቋማት መካከል አንዷ ብትሆንም እኚህ አገልጋዮች ለእስር የተዳረጉት ከፈረንጆቹ 2003 እስከ 2004 ሲሆን በሀገራችን ዘመን አቆጠጠር ደግሞ በ90ዎቹ ማብቂያ ላይ ነው።
በአስመራ ወንጀል ምርመራ ማቆያ ተይዘው የቆዩት እነዚህ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች በታሰሩበት ከባድ ሁኔታዎች ላይ እንደሆኑ የተገለጸ ሲሆን በዚህ መንገድ ውስጥም ቢሆን ሕጋዊ ውክልናም ካለማግኘታችው በተጨማሪ የቀረበባቸው መደበኛ የሆነ ክስ የለም።
እነዚህ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች የቅርብ ቤተሰቦቻቸው እንዲጠይቋቸው የማይፈቀድላቸው ሲሆን በታሰሩበት ጊዜው አንዳንድ ቤተሰቦቻቸው ሕይወታቸው ያለፈ ሲሆን አንዳንዶች ደግሞ ከሀገሪቱ በስደት ወጥተዋል።
ይህንንም አስመልክቶ የክርስቲያን ተሟጋች ቡድኖች ቮይስ 4 ጀስቲስ የተሰኘ የፍትህ ንቅናቄ በማድረግ ላይ ይገኛሉ። ቡድኖቹም በዓለም አቀፍ ደረጃ ጸሎቶች ፣ ሰላማዊ ሰልፎች እና ዲፕሎማሲያዊ ተጽዕኖዎች እንዲደረጉ ጥሪ በማቅረብ ላይ ናቸው። የንቅናቄው ፕሮግራሞችም በዋሺንግተን፣ ለንደን ፣ ጄኔቫ እና ኮሎምቢያ በመካሄድ ላይ ይገኛሉ።
በክርስቲያን ሶሊዳሪቲ ወርልድ ዋይድ እና በ21ዊበርፎርስ እየተደፈ የሚገኘው ንቅናቄ በኤርትራ ለረዥም ጊዜ የቆየውን የክርስቲያኖች እስር የሚያነሳ ሲሆን ከመንግስት ፈቃድ ባላቸው ቤተ ክርስቲያኖች ጭምር እየደረሰ ያለውን መከራ ለሰዎች ማሳወቅ ላይ እየሰራ ይገኛል።
መረጃውን ከክርስቲያን ዴይሊ ኢንተርናሽናል አገኘነው። ecgbc